9 May 2026, 06:08 UTC≈33,700 views587 reactionsread 22 September 2026 “ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ!” (ቅዱስ ያሬድ)
ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በአድባረ ሊባኖስ ግንቦት አንድ ቀን ወለዷት፡፡ በዚያን ጊዜ ጠላታቸውን ለመሸሽ በስደት ላይ ስለነበሩ ምግብ አልያዙም፤ ስንቃቸውም ‹‹ንፍሮና ጥራጥሬ›› ነበር፡፡ በዚህም የእመቤታችን ማርያምን የልደት በዓል በሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ የነቢያቱ ትንቢት የተፈፀመበት፣ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጆች ሁሉ (ለሕያዋን ሁሉ) ታላቅ የደስታ ቀን ነው፡፡
በንጽህናዋ እና በቅድስናዋ ተደንቀው ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም ያመሰግኗታል፡…
❤363👍94👏57🎉41🥰15😱7🔥5🤩5
8 May 2026, 21:11 UTC≈30,100 views137 reactionsread 22 September 2026 Photo
#ግንቦት_ልደታ_ለማርያም
ግንቦት ልደታ ለምን ይከበራል?
ግንቦት ልደታ (ግንቦት 1) የሚከበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት ለማሰብ ነው። በዓሉ የሰው ልጅ የመዳን ተስፋ መጀመሪያ የሆነችው ማርያም ከአባቷ ከኢያቄም እና ከእናቷ ከሐና በአድባረ ሊባኖስ የተወለደችበትን ዕለት የሚያከብር ታላቅ በዓል ነው።
የበዓሉ ዋና ዋና ምክንያቶች፦
የድንግል ማርያም ልደት፦
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በግንቦት 1 ቀን መወለዷን ለማሰብ።
የትንቢት መፈጸምያ፦
በብሉይ ኪዳን የነበሩ ነቢያት ስለ መሲሁ መምጣት የተነበዩት ትንቢት መፈጸሚያ የሆነችው የጌታ እናት የተወለደችበት ቀን በመሆኑ።
…
❤94🥰21🙏12👍7🕊3
12 Apr 2026, 06:16 UTC≈34,300 views431 reactionsread 22 September 2026 Photo
† እንኳን ለጌታችን እና መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሳኤ በሰላም አደረሰን †
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሠላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሠላም፡፡”
መልካም በዓል !
@Eotc_Books_By_Pdf
@Eotc_Books_By_Pdf
❤258🙏154❤🔥12👍6🤩1
8 Apr 2026, 04:33 UTC≈35,500 views344 reactionsread 22 September 2026 Photo
#ህማማት
በህማማት ሳምንት (Holy Week) የየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ እና ቅዱስ ሳምንት ነው ፤ የኢየሱስ ክርስቶስ መከራ፣ ሞት እና ትንሣኤ ይዘከራል። በዚህ ሳምንት የሚደረጉ ነገሮች እነዚህ ናቸው፦
1. ጾም (ጾመ ህማማት)
ከሌሎች ጾሞች የበለጠ ጠንካራ ነው
ምግብ እስከ ማታ ይቆያል (አንዳንድ ሰዎች ሙሉ ቀን ይጾማሉ)
ስጋ እና የእንስሳ ምርቶች ፈጽሞ ይከለከላሉ ።
2. ጸሎት እና ስግደት
ቤተክርስቲያን ብዙ ጊዜ መገኘት
ረጅም ጸሎቶች እና ስግደት (መስገድ)
መጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ።
3. የቀናት ልዩ ትርጓሜ
ሰኞ ፣ ማክሰኞ ፣ ረቡዕ : የተለመዱ ጸሎቶች እና ጾም ይከናወናል።
ሐሙስ (ጸሎተ ሐሙስ): የመጨረሻ እራት ዝ…
❤299🙏22👏12🥰8👍2🎉1
28 Mar 2026, 01:02 UTC≈36,300 views338 reactionsread 22 September 2026 የዐቢይ ጾም ሳምንታት
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስሙ ጐልቶ ከሚነሳባቸው ጉዳዮች አንዱ በዐቢይ ጾም ውስጥ ለሚገኙ ሳምንታት የየራሳቸው መጠሪያ በመስጠቱ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ለሳምንታቱ ስያሜዎችን ሲሰጥ ጌታችን የሠራቸውን የቸርነት ሥራዎችን፣ ያስተማራቸው ትምህርቶችን፣ ተጠቅሟል፡፡
በአጠቃላይ በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚገኙ ሳምንታት ስያሜያቸው . . .
1/ ዘወረደ
2/ ቅድስት
3/ ምኩራብ
4/ መፃጉ
5/ ደብረ ዘይት
6/ ገብር ኄር
7/ ኒቆዲሞስ
8/ ሆሣዕና
@Eotc_Books_By_Pdf
@Eotc_Books_By_Pdf
❤271👍31🙏25🥰6👏5
14 Feb 2026, 04:04 UTC≈50,700 views321 reactionsread 22 September 2026 Photo
#ቅድስት_ሥላሴ
"ሥላሴን " " ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር ምንድን ነው ?
አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ፤ ሥላሴም ይህንን
ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም ።
አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር
አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር # ቅድስት ተብለው ይጠራሉ ።
አንድም ሴት አዛኝ ናት ፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት
ሁሉ ያዝናሉ ፥ ይራራሉ ፥ ምህረት ይሰጣሉ ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ።
ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ "
በማለት ያመሰጥራ…
❤228🙏48🥰19👏7🤩7😇6⚡3👍3
6 Feb 2026, 19:45 UTC≈44,400 views241 reactionsread 22 September 2026 #ጸሎተ_ሃይማኖት (የሃይማኖት ጸሎት)
ነአምን በ፩ዱ፡ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኲሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ።
ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።
መቅድም
ሀ. ስሙ
1. ጸሎተ ሃይማኖት
2. የኒቅያ የሃይማኖት መግለጫ (ውሳኔ ሃይማኖት፤ አንቀጸ ሃይማኖት) Nicene Creed
3. የኒቅያ ቁስጥንጥንያ ውሳኔ ሃይማኖት Nicene-Constantinopolitan Creed
ለ. ለምን አስፈለገ?
1. « መለኮታዊውንና ሐዋርያዊውን እምነት ጠቅልሎ ያስቀመጠ ስለሆነ።» ቅዱስ አትናቴዎስ
2. ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ግልጥ…
❤212👏18🎉7👍4
4 Feb 2026, 17:58 UTC≈33,900 views244 reactionsread 22 September 2026 Photo
#ፀሎት
ፀሎት ማለት ምን ማለት ነው?
#ጸሎት ማለት ፦ጸለየ፣ለመነ፣ ጠየቀ አማለደ፣ ማለደ ካለው የግዕዝ ቃል የወጣ ቃል ነው፡፡ ጸሎት ማለት ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እግዚአብሔርን ማመስገን መለመን፣ መጠየቅ፣ መማለድ፣ መማፀን ነው፡፡ “ጸሎት ብሂል ተናግሮ ምስለ እግዚአብሔር፡፡” አባታችን አዳምም ከመላእክት ተምሮ በየሰዓቱ ይጸልይ ያመሰግን ነበር፡፡ ዲያብሎስ በእባብ አድሮ ወደ አዳም በመጣ ጊዜ ጸሎት እያደረገ ስለነበር ዲያብሎስን ድል ነሥቶታል ሔዋንን ግን ሥራ ፈትታ እግሯን ዘርግታ ስለአገኛት ድል ነስቷታል፡፡
ጸሎት ሰማእታት ከነደደ እሳት፣ ከተሳለ ስለት፣ ከአላውያን መኳንንት፣ ከአሕዛብ ነገሥታት ከዲያብሎስ ተንኮል እና…
🙏156❤75👏13
2 Feb 2026, 18:46 UTC≈33,900 views106 reactionsread 22 September 2026 #በእንተ_ፆም
ጾም ‹‹ጾመ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ትርጕሙም መተው፣ መጠበቅ፣ መከልከል ማለት ነው፡፡ ጾም ከምግብ መከልከል ብቻ ሳይኾን ከክፉ ተግባር ዅሉ መቆጠብ ጭምር ነው፡፡ ሠለስቱ ምዕትም፡- ‹‹ጾምሰ ተከልኦተ ብእሲ እመብልዕ በጊዜ ዕውቅ በውስተ ሕግ፤ ጾምስ በታወቀው ሰዓት፣ በታወቀው ዕለት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው›› በማለት የጾምን ትርጕም ያስረዳሉ /ፍትሐ ነገሥት፣ አንቀጽ ፲፭/፡፡
ጾም በብሉይ ኪዳንም ኾነ በሐዲስ ኪዳን የታወቀ፣ በነቢያት የነበረ፣ በክርስቶስ የጸና፣ በሐዋርያት የተሰበከ እና የተረጋገጠ መንፈሳዊ ሕግ፤ ፈጣሪን መለመኛ መንፈሳዊ መሣሪያ ነው፡፡
ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይኾን ልዑል እግዚአብሔር የመሠረተው፣…
❤70🙏16👏8🥰8🤩3👍1
1 Feb 2026, 17:26 UTC≈34,200 views226 reactionsread 22 September 2026 #ጾመ_ሰብአ_ነነዌ
‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው (ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪)፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የሆነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶ ነበር (ዮናስ ፬፥፲፩)፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ዮናስ የስሙ ትርጓሜ ‹ርግብ› የሆነ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይን ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲ…
❤199👏9🥰9👍3🙏3🔥2🤩1
✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚 pinned a photo
29 Jan 2026, 06:38 UTC≈35,200 views119 reactionsread 22 September 2026 #ጥር_21_የእመቤታችን_በዓለ_ዕረፍት !
” አስተርእዮ ማርያም “
አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።
ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈ…
❤70🙏27🥰11👏5🤩4👍2
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Eotc_Books_By_Pdf. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.