1 Sept 2026, 14:16 UTC≈1,970 views116 reactionsread 3 September 2026 ስለ ወንድሜ አብዱረሒም አህመድ...
ወንድሜ አብዱረሒም አህመድን በግል ቅርበት ያወቅኩት፣ የ"ድምፃችን ይሰማ" ንቅናቄ በጎመራበትና የሙስሊሙ ትግል ጫፍ በደረሰበት በዚያ ፈታኝ ወቅት ነበር። ጊዜው በመንግሥት በኩል ከፍተኛ አፈና የነበረበት ሲሆን፣ በግሌ የማውቃቸው በርካታ ጓደኞቼ በወቅቱ በነበረው እንቅስቃሴ ምክንያት ማረሚያ ቤት ወርደው ስለነበር፣ በሚዲያ ቀርቦ መናገር ከፍተኛ ስጋት ነበረው። በወቅቱ ደግሞ ቢቢኤን ሬዲዮ የትግሉ አንደበት ሆኖ በስፋት ይደመጥ ነበር።
በዚህ ጭንቀት ውስጥ ሆኜ ነበር አብዱረሒም ለአንድ ቃለ-መጠይቅ ያናገረኝ። ስጋቴን ሲረዳ፣ ማንነቴ እንዳይታወቅ ድምፄን ቀይሮ ሊያቀርበኝ ቃል ገባ። በቃሉ መሠረት ኢንተርቪው አደረግን፤ ቃለ-መጠ…
❤79👍30🥰7
1 Sept 2026, 14:16 UTC≈1,910 views15 reactionsread 3 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👍15
25 Aug 2026, 13:51 UTC≈4,030 views100 reactionsread 3 September 2026 በ20ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በሚሽነሪዎች ዓለም ከተፈጠሩት እጅግ አወዛጋቢና የረቀቁ ስትራቴጂዎች አንዱ "የውስጥ እንቅስቃሴ" (The Insider Movement - IM) የተሰኘው ስልት ነው። የዚህ ስልት ዋነኛ ፍልስፍና "አንድ ሙስሊም ክርስቲያን ለመሆን ዲናዊ የነበረውን አኗኗሩን፣ ማህበረሰቡንና ሃይማኖታዊ መለያውን መተው የለበትም" የሚል ነው።
ከዚህ ቀደም ሰዎች እምነታቸውን ሲቀይሩ ስማቸውን ለአብነት ከ'መሀመድ' ወደ 'ጳውሎስ' ይቀይራሉ፣ ከመስጊድ ወጥተው ወደ ቤተክርስቲያን ይሄዳሉ። ይህ ግን በማህበረሰቡ ዘንድ መነጠልንና ከፍተኛ ተቃውሞን ስለፈጠረባቸው፣ አዲሱ ስልት ሰውዬው ራሱን "ሙስሊም" ብሎ እየጠራ፣ ነገር ግን በውስጡ የክርስትናን ዶክትሪ…
👍75❤18😱4😢3
25 Aug 2026, 13:50 UTC≈3,360 views10 reactionsread 3 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
👍8❤2
24 Aug 2026, 17:28 UTC≈3,880 views117 reactionsread 3 September 2026 በቅርቡ የምክክር ኮሚሽኑ በሀገራችን የዘመን አቆጣጠር ላይ ሲውል የነበረውን እና ሃይማኖታዊ አንድምታ ያለውን "ዓ.ም." (ዓመተ ምህረት) በመተው፣ ሁሉንም አቃፊና ገለልተኛ እንደሚሆን በተስማሙበት "ዓ.ል." (ዓመተ ልደት) ወይም "እ.ኢ.አ." (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) እንሸጋገር የሚል ሀሳብ አቅርቧል። ይህን ተከትሎ ግን በአንዳንድ የኦርቶዶክስ እምነት አክቲቪስቶች ዘንድ ሰማይ ምድሩን የሚያቀልጥ ጩኸት እየሰማን ነው። አንዳንዶችም "ለምን የኛን ተውት ትላላችሁ? ሂጅራስ ለምን ሆነ?" እያሉ እያማረሩ ነው።
እዚህ ላይ ግን በግልጽ መነጋገር ያለብን እጅግ አስገራሚ ደብል ስታንደርድ አለ። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ሙስሊሙ የራሱ የሆነ የ"ሂጅራ" ዘመን አቆጣጠር …
👍90❤25😱2
24 Aug 2026, 17:27 UTC≈3,440 views4 reactionsread 3 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤4
21 Aug 2026, 18:42 UTC≈4,740 views138 reactionsread 3 September 2026 እፎይ የተሰኘው የካራ እምነት ተከታይ በሰሒሕ ሙስሊም ላይ የሰፈረውን ይህንን ሐዲስ አንስቶ ያቀረበው ትችት፣ የአላህን መሐሪነትና የሰውን ተፈጥሮ በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነው። ሐዲሱ እኮ ሰዎችን ለኃጢአት የሚያነሳሳ ሳይሆን፣ በተቃራኒው ተስፋ መቁረጥን የሚያክም ታላቅ ነብያዊ መድኃኒት ነው። የሰው ልጅ እንደ መላእክት ኃጢአት የማይሠራ ፍጹም ፍጡር ሆኖ አልተፈጠረም፤ ስህተት ሰርቶ መመለስ የሚችል ነጻ ፍቃድ የተሰጠው ፍጡር ነው። አላህ እጅግ መሐሪ በመሆኑ፣ ይህ መለኮታዊ ባሕሪው ይቅርታ ጠያቂዎችን በምህረት የሚመለከትበት ማንነቱ ነው። ሰዎች ፈጽሞ የማይሳሳቱ ቢሆኑ ኖሮ፣ የመላእክትን ባህሪ ይላበሱ ነበር እንጂ የሰው ልጅ የመፈጠሩ ዓላማ በተግባር ባልታየ ነበር…
❤91👍41🔥3🤩3
21 Aug 2026, 18:41 UTC≈4,260 views0 reactionsread 3 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
17 Aug 2026, 10:47 UTC≈6,410 views71 reactionsread 3 September 2026 አላህ የፍጥረታትን መጨረሻ አስቀድሞ ያውቃል። ይህ መለኮታዊ ዕውቀቱ ፍጹም መሆኑን ያሳያል። ነገር ግን "አስቀድሞ አወቀ" ማለት "አስገድዶ አሠራ" ማለት አይደለም። ለምሳሌ፣ አንድ ብቁ መምህር የትኛው ተማሪው እንደሚያልፍና የትኛው በስንፍናው ምክንያት እንደሚወድቅ አስቀድሞ ሊያውቅ ይችላል፤ ወረቀት ላይም ሊጽፈው ይችላል። ተማሪው ሲወድቅ ግን የወደቀው መምህሩ አስቀድሞ ስላወቀና ስለጻፈው ሳይሆን፣ የራሱ ምርጫና ስንፍና ስላመጣበት ነው። አላህም ሰዎች በነጻ ምርጫቸው ምን እንደሚሠሩ አስቀድሞ ያውቃል፤ አዋቂነቱ ግን የሰዎችን ነጻ ምርጫ አይነጥቅም።
አስተያየት ሰጪው ያነሳው ጥያቄ አዲስ አይደለም፤ ከ1400 ዓመታት በፊት ታላላቆቹ ሰሐባዎች ልክ እንደዚሁ ነብዩን…
👍46❤19👏3🤷3
17 Aug 2026, 10:46 UTC≈4,380 views8 reactionsread 3 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤6👍2
15 Aug 2026, 10:35 UTC≈5,380 views85 reactionsread 3 September 2026 ክርስቲያን ወገኖች "ጅን"ን በተመለከተ ባለው የእስልምና አስተምህሮት ዙሪያ የሚሳለቁት፣ ቃሉን ከራሳቸው የ"ጋኔን" (እርኩስ መንፈስ) ትርጓሜ ጋር በማምታታት ነው። በክርስትና አስተምህሮ ጋኔን ማለት ወደ ንስሐ የማይመለስና የወደቀ እርኩስ መንፈስ ነው። "ታዲያ ከእርኩስ መንፈስ ጋር እንዴት ወንድማማችነት ይፈጠራል?" ብለው መገረማቸው የዚሁ የተሳሳተ መነጽር ውጤት ነው።
እውነታው ግን እጅግ የተለየ ነው። በእስልምና ጅን ማለት ልክ እንደ ሰው ልጅ ነጻ ፍቃድ የተሰጠው፣ የሚያስብ እና የራሱ ምርጫ ያለው ፍጡር ነው። በመሆኑም ከነሱ ውስጥ አላህን የሚያመልኩ ደጋጎች እንዳሉ ሁሉ፣ የሚያምፁ እርኩሳንም (ሰይጣናት) አሉ። እስልምና በእምነት "ወንድሞቻችን" የሚለው…
👍63❤22
15 Aug 2026, 10:34 UTC≈3,920 views2 reactionsread 3 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤2
Showing the 12 most recent of 37 posts we hold for @Yahyanuhe. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.