1 Sept 2026, 11:02 UTC998 views3 reactionsread 3 September 2026 ቋሚ ኮሚቴው በተቋማት ግንባታ ረገድ ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን ገለጸ
-------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 26፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባለፉት 5 ዓመታት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማጠናከር ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ገምግሟል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እጸገነት መንግስቱ በሰጡት አስተያየት ቋሚ ኮሚቴው ባለፉት 5 አመታት ጥራታቸውንና አገራዊ ፋይዳቸውን የጠበቁ አዋጆችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የመመርመርና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ የማቅረብ ተግባራትን በብቃት ሲወጣ ቆይቷል ብለዋል።
በሂደቱም ለአገራዊ ሪፎርም፣ …
❤2👍1
31 Aug 2026, 13:41 UTC≈1,200 views4 reactionsread 3 September 2026 "ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ለቀጣዩ ጉዞ ታላቅ አርአያ ናቸው" — የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ
------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 25፣ 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፤ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ውስጥ ባለፉት አምስት ዓመታት የነበሩት አባላት አገራዊ ኃላፊነታቸውን በከፍተኛ የስራ ትጋት በመወጣት በርካታ አበረታች ሥራዎችን አከናውነው ማለፋቸውን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ ገልጸዋል።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በየዘርፉ ያከናወኗቸው ዘመናዊና የተቀናጁ ተግባራት የኮሚቴውን አቅም ከማሳደጋቸውም በላይ፣ ለቀጣይ የፓርላማ የሥራ …
❤4
31 Aug 2026, 10:07 UTC≈1,160 views4 reactionsread 3 September 2026 የህፃናት ማቆያዎች ለተቋማት ውጤታማነት የላቀ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሆነ ተገለጸ
--------------------
(ዜና ፓርላማ)ነሐሴ 25 ፣ 2018 ዓ.ም፤ በመንግስት ተቋማት የሚከፈቱ የህፃናት ማቆያዎች እናቶች ያለ ስጋት በስራ ገበታቸው ላይ ሙሉ ትኩረት እንዲሰጡ ከማስቻላቸውም ባለፈ ለተቋማት ውጤታማነት የላቀ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጭቴ ፍላቴ እንደገለጹት የህፃናት ማቆያ ቦታዎች የሰራተኛ መረጋጋትን ለመፍጠርና የተቋማትን ውጤታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፆ እያበረከቱ ነው፡፡
በመንግስት ተቋማት የህጻናት ማቆያ ቦታዎ…
❤3👍1
28 Aug 2026, 14:18 UTC≈1,680 views5 reactionsread 3 September 2026 ቋሚ ኮሚቴው ባለፉት አምስት ዓመታት የፋይናንስ ሕጋዊነትና የክዋኔ ኦዲቶች ህጎችን መሠረት አድርገው መተግበራቸውን ክትትልና ቁጥጥር ሲያደርግ መቆየቱን ገለፀ
--------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 22 ፣ 2018 ዓ.ም፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባለፉት አምስት ዓመታት የፋይናንስ ሕጋዊነት እና የክዋኔ ኦዲት ህጎችን መሠረት አድርገው መተግበራቸውን ክትትልና ቁጥጥር ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።
ቋሚ ኮሚቴው ይህን የገለፀው የአምስት ዓመታት ዓበይት ተግባራት አፈፃፀምን በተመለከተ ከቴሌቪዥን ጣቢያችን ጋር ባደረገው ቆይታ ነው።
የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮ…
❤5
27 Aug 2026, 12:03 UTC≈1,860 views5 reactionsread 3 September 2026 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት እየሰጠ ያለው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ተጠናከሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ
-------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 21፣ 2018 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት እየሰጠ ያለው ፈጣን፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት ተጠናከሮ መቀጠል እንዳለበት የሪፎርም ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መለሰ መና ገልጸዋል፡፡
ሰብሳቢው ይህን ያሳሰቡት፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና እና የቀጣይ ዓመት እቅድ ዝግጅት በተገመገመበት ወቅት ነው፡፡
የምክር ቤት ጽህፈት ቤት አግልግሎት እየተሻሻለ የመጣ መሆኑን የተከበሩ አቶ መለሰ መና ጠቁመው፤ የምክር ቤቱ በሕገ…
👍3❤2
26 Aug 2026, 05:38 UTC≈1,910 views7 reactionsread 3 September 2026 የንግድና ቱሪዝም ዘርፎች ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸው አስተዋፅዖ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ
--------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 20 ፣ 2018 ዓ.ም.፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች ባለፉት አምስት ዓመታት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት አስመልክቶ ከኢቲቪ ፓርላማ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የንግድና ቱሪዝም ዘርፎች ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸው አስተዋፅዖ እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል።
የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አሻ ያህያ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በንግድ፣ ቱሪዝምና ኢንቨስትመንት ዘርፎች አዳዲስ ለውጦችና እድገቶች መመዝገባቸውን አንስተዋል።
ሀገሪቱ ያላትን ሰፊ …
❤5👏2
24 Aug 2026, 13:42 UTC≈1,890 views5 reactionsread 3 September 2026 በሀገራችንና በመላው ዓለም ለምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤
እንኳን ለ1ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ ልደት (መውሊድ) በዓል አደረሣችሁ! አደረሠን!
-----------------------
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነብዩ መሐመድ የልደት በዓልን በማስመልከት ለሕዝበ ሙስሊሙ እንኳን አደረሣችሁ ሲል የመልካም ምኞት መልዕክት ያስተላልፋል።
ነብዩ መሐመድ ህይወታቸውን በሙሉ ለሰው ልጆች ምሳሌ ሆነው ያለፉ ነብይ እንደመሆናቸው መጠን ሕዝበ ሙስሊሙ ከነብዩ መሐመድ ህይወት በመማርና የእሳቸውን የእምነት አስተምህሮ በመከተልና ተምሳሌት በማድረግ ለሰው ልጆች ፍቅርና ሠላም እንዲኖር ሊተጉ ይገባል፡፡
ታላቁ ነብዩ መሀመድ በነበራቸው የላቀ ስብዕና …
❤4👍1
24 Aug 2026, 09:04 UTC≈2,070 views2 reactionsread 3 September 2026 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ5 ዓመታት የአገልግሎት ዘመን በቁልፍ የፋይናንስ ተቋማት ላይ የክትትልና ቁጥጥር ስራ ሲያከናውን መቆየቱ ተገለፀ
--------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 18 ፣ 2018 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በ6ኛው ምክር ቤት የ5 ዓመታት የስራ ዘመን የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት በላቀ ደረጃ ለማከናወን የሚያስችለውን አደረጃጀት ዘርግቶ በቁልፍ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ እንደገለጹት፣ የትኛውም ተቋም በጽኑ የህግ መሰረት …
❤2
22 Aug 2026, 13:02 UTC≈2,060 views7 reactionsread 3 September 2026 "ተመካካሪዎች በአብዛኛዎቹ አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል" ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረ ሥላሴ
--------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 16፣ 2018 ዓ.ም፤ በኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ የተሳተፉ ተመካካሪዎች፣ ለሀገራችን ችግሮች መፍትሔ ይሆናሉ ያሏቸውን ምክረ ሐሳቦች አጠናቅረው ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ማስረከባቸውን የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ወይዘሮ ሂሩት ገብረ ሥላሴ አስታወቁ።
ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፣ በምክክር ሂደቱ ተሳታፊዎች በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በቀላሉ መግባባት የቻሉ ሲሆን፣ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ደግሞ ሰፊ ጊዜ ወስደው ጠንከር ያሉ ውይ…
❤7
22 Aug 2026, 12:10 UTC≈1,960 views5 reactionsread 3 September 2026 "ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን" የተከበሩ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
---------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 16፣ 2018 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም፣ አንድነት እና አብሮነት በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም ያለመው ታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አፈ-ጉባኤው በመልዕክታቸው፣ ይህ ጉባዔ ለነገዋ ጠንካራ ኢትዮጵያ መሠረት የተጣለበት እና የሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጋራ የተቀረጸበት ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።
የዚህ የምክክር ሂደት ዋና ዓላማ …
❤5
22 Aug 2026, 11:42 UTC≈1,780 views4 reactionsread 3 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤4
21 Aug 2026, 14:29 UTC≈2,280 views2 reactionsread 3 September 2026 ቋሚ ኮሚቴው በአስፈጻሚ ተቋማት ላይ ያካሄዳቸው የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች በሳይንሳዊ ጥናት የተደገፉ መሆናቸውን ገለጸ
-----------------------
(ዜና ፓርላማ) ነሐሴ 15፣ 2018 ዓ.ም፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባለፉት አምስት ዓመታት በከተሞች የሚስተዋሉ የመሬት፣ የቤትና የትራንስፖርት ችግሮችን በሳይንሳዊ ምርምር አስደግፎ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ ገልጿል።
የቋሚ ኮሚቴው አባል የተከበሩ ገነት ከተማ ከኢቲቪ-ፓርላማ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ቋሚ ኮሚቴው አሰራሩን ከተለመዱ ሪፖርቶች እንዲወጡ በማድረግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከፐብሊክ ሰርቪስ …
❤1👍1
Showing the 12 most recent of 42 posts we hold for @ParlamaNews. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.