19 Aug 2026, 05:53 UTC129 views3 reactionsread 19 August 2026 Forwarded from @dnhenok_haile
+ ከታቦር ተራራ አትቅር +
"አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ። "
ማር 9: 3
/ሽራፊ ሃሳቦች ከደብረ ታቦር ንባብ/
የወንጌላውያን ትሕትና ይደንቃል ፣ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ስለ ደብረ ታቦር ሲጽፉ ዮሐንስ አልጻፈም። ዮሐንስ ተመርጦ የተገኘበትን ታሪክ "ተመርጬ" ብሎ አልጻፈም። የቀሩት ወንጌላውያን ደግሞ "እኛ የሌለንበትን ነገር አንጽፍም" አላሉም። አንድ ወንጌል እየሰበኩ የሚፎካከሩ ፣ የአንድ ቤት ጣሪያ እየሠሩ ቆርቆሮ የሚሻሙ የእኛ ዘመን አገልጋዮች አልነበሩምና እነርሱ ያልተመረጡበትን ታሪክ ለመናገር ተሯሯጡ። እኛን የማያካትት ክብር ፣ እኛን የማይጨምር ድግስ ጉዳይ ሲነሣ ለማይጥመን ፣ እኛ የሌለንበትን ፎቶ እንኳን…
🙏2❤1
19 Aug 2026, 03:39 UTC175 views5 reactionsread 19 August 2026 #ቃለ_ወንጌል
13/12/2016
ሉቃ ፱÷፳፪-፴፰
ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ። ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤ በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።
ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ። ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን፦ “አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ፡” አለው…
❤5
18 Aug 2026, 17:14 UTC216 views3 reactionsread 19 August 2026 Forwarded from @EOTCmahlet
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ስርአተ ማህሌት ዘበዓለ ደብረ ታቦር
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ሥርዓተ ነግሥ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
መልክአ ሥላሴ፦
ሥላሴክሙ ሥላሴ ይረስየኒ መካነ፤ድኅረ ተዋሓድኩሰ ዘሥላሴሁ ብርሃነ፤ዮርዳኖስክሙ ዝየ እስመ ኵለንታየ ኮነ፤ኢየኀሥሥ እምዮርዳኖስ ሰማዕተክሙ ምእመነ፤ወኢይትሜነዮ ለታቦር እ…
❤3
18 Aug 2026, 17:13 UTC189 viewsread 19 August 2026 File
File, posted without a caption
18 Aug 2026, 16:36 UTC206 viewsread 19 August 2026 በዓለ ደብረ ታቦር
ከጌታችን ዓበይት በዓላት አንዱ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የምናከብረው የደብረ ታቦር በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን የገለጠበት በመሆኑ በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ (ማቴ .፲፯፡፩፣ ማር.፱፡፩፣ሉቃ.፱፡፳፰)፡፡
ደብረ ታቦር፡- ‹‹ደብረ ታቦር›› ደብር እና ታቦር ከሚባሉ ከሁለት ቃላት የተገኘ ሲሆን ‹‹ደብር›› ማለት ተራራ ማለት ነው፤ ‹‹ታቦር›› ደግሞ በናዝሬት አካባቢ በሰማርያ አውራጃ በገሊላ የሚገኝ የረጅም ተራራ ስም ነው፡፡ የደብረ ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል ፲ ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ጠለል በላይ ፭፻፸፪ ሜትር …
18 Aug 2026, 16:36 UTC215 views5 reactionsread 19 August 2026 በተጨማሪም ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ሹመት፣ ሽልማትና ክብር ፈላጊዎች ነበሩ፡፡ ከዚህ ምድራዊ ሐሳብ እንዲታደሱ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለድኅነተ ዓለም የመጣው በሞቱ ድኅነት የሚሆነን አምላክ “ልሰቀል ነው” ባለ ጊዜ “አይሁንብህ” ብሎት ስለነበር እንዲህ ያለው ሐሳብ የጠላት እንጂ የሰው ልጆች ሊሆን አይችልም ከሞቱ በቀር ድኅነት ሊያስገኝልን የሚችል የለምና፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግን መምኅሬ ከሞተ ክብሬ ምንድን ነው? የሚለውን በማሰብ “አይሁንብህ” አለ፡፡ በሌላም ጊዜ እንደዚሁ “ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንግዲያስ ምን እናገኝ ይሆን?” በማለት በጠየቁት ጊዜ ጌታችን ግን ዋጋችሁ ሰማያዊ ክብራችሁ ዘላለማዊ ነው ሲል እስከ ፍጹማን መዓርግ /ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ/…
❤5
18 Aug 2026, 10:36 UTC315 views1 reactionsread 19 August 2026 በዓለ ደብረታቦር
➛ ደብረታቦር ምንድነው?
➛ በደብረታቦር ቡሄ የተባለው ለምንድነው ?
➛ በበዓለ ደብረታቦር ለምን ሙልሙል ይጋገራል?
➛ ለምን ጅራፍ ይጮሃል?
➛ ለምን ችቦ ይበራል?...👇👇👇
ማታ 12:00 ይጠብቁ
🙏1
18 Aug 2026, 03:41 UTC481 views7 reactionsread 19 August 2026 #ቃለ_ወንጌል
12/12/2017
ማቴ 22:1-23
ጌታችን ኢየሱስ ዳግመኛ መልሶ በምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህም አለ፦ “መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች። ለሰርጉም የታደሙትን ይጠሩአቸው ዘንድ አገልጋዮቹን ላከ፤ ሊመጡም አልወደዱም። ዳግመኛም ሌሎችን አገልጋዮች እንዲህ ብሎ ላከ፤ የታደሙትን እንዲህ በሉአቸው፦ እነሆ ድግሴን አዘጋጅቻለሁ፤ ኮርማዎቼና የሰቡ ከብቶቼ ታርደዋል፥ ሁሉም ተዘጋጅቶአል። ወደ ሰርጉ ኑ።
እነርሱ ግን ቸል ብለው ሄዱ፤ ወደ እርሻው የሄደ አለ፤ ወደ ንግዱም የሄደ አለ። የቀሩትም አገልጋዮቹን ይዘው ሰደቡአቸው፤ ገደሉአቸውም፤ ንጉሡም ተቈጣ፤ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮ…
❤6🔥1
17 Aug 2026, 17:39 UTC311 viewsread 19 August 2026 File
File, posted without a caption
17 Aug 2026, 17:39 UTC326 views4 reactionsread 19 August 2026 Forwarded from @dnhenok_haile
ስድብ ኃጢአት ባይሆን ኖሮ መሰደብ የሚገባው ዲያቢሎስ ነው:: ፍጥረት ሁሉ ስድብ ቢያዋጣ ለዲያቢሎስ የሚመጥን አይሆንም:: የክፋት ምንጭ ለሆነ ለእርሱ ሁሉም ክፉ ቃል መገለጫው ነው::
ይሁንና ቅዱስ ሚካኤል ይህንን ክፉ ጠላት ደፍሮ አልሰደበውም:: "እግዚአሔር ይገሥጽህ!" አለው:: (ይሁ 1:9)
እንደ ሚካኤል ንጹሕ በእኛ ዘን ማን አለ? እንደ ዲያቢሎስስ ክፉ በእኛ ዘንድ ማን አለ?
መልእክቱ ግልጽ ነው:: አንሆንም እንጂ እንደ ሚካኤል ንጹሕ ብንሆን እንኳን እንደ ሰይጣን የከፋን ሰው እንኳን መሳደብ አንችልም::
የመላእክት አለቃ ሚካኤል ከሥልጣኑ የወረደውን የቀድሞውን የመላእክት አለቃ ዲያቢሎስን አንድም ክፉ ቃል አልተናገረውም:: አንዱ ከሥልጣኑ ወድቆ ሌ…
❤4
17 Aug 2026, 03:32 UTC541 views3 reactionsread 19 August 2026 #ቃለ_ወንጌል
11/12/2016
ሉቃስ 6:20-24
እርሱም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዓይኑን አነሣ፥ እንዲህም አላቸው፦ “እናንተ ድሆች ብፁዓን ናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ነውና። እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና።
ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና።
#መልእክታት
1 ቆሮንጦስ 5:11-ፍጻሜ
1 ዮሐንስ 2:14-20
ሐዋ.ሥራ 12:18-ፍጻሜ
ምስባክ
…
❤3
16 Aug 2026, 17:32 UTC354 views6 reactionsread 19 August 2026 Forwarded from @dnhenok_haile
እችላለሁ ካልህ ትችላለህ!?
ክርስቲያን "ሁሉን እችላለሁ" ይላል ወይ? አዎ ይላል:: ግን ከፊቱ የሚቀር ሐረግ አለ::
"ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ" (ፊል. 4:13)
በራስ መተማመንም እግዚአብሔርን ከለላ በማድረግ ብቻ ነው:: "በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን በራስህም ማስተዋል አትደገፍ" ምሳ. 3:5
ስለዚህ በእግዚአብሔር መታመን በራስ ከመታመን በላይ ነው:: Confidence ከሚለው ይልቅ Godfidence የሚል አዲስ ቃል ሳይገልጸው አይቀርም::
የተፈጥሮ ጸጋህን እወቅ በሚል በጎ መነሻ የተጀመረው "ነኝ ካልኩ ነኝ" የሚለው መፈክር አሁን ላይ ምድርን እየበጠበጠ ይገኛል:: ሰዎች "ውብ ነኝ ጎበዝ ነኝ ፤ ደፋር ነኝ" ብለው ራሳቸው…
❤4🙏2
Showing the 12 most recent of 16 posts we hold for @Eotc_spritual_books. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.