23 Aug 2026, 07:55 UTC111 views2 reactionsread 23 August 2026 🌿† ስንክሳር ነሐሴ 17 †🌿
እንኳን ለሰማዕታት ቅዱስ እንጣዎስ እና ቅዱስ ያዕቆብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
❣† ቅዱስ እንጣዎስ አሞራዊ †❣
ይሕ ቅዱስ በቀደመ ሕይወቱ ክርስቲያኖችን የሚጠላ አስቸጋሪ አረማዊ ነበር:: ሃገሩ #ሶርያ( #ደማስቆ) ሲሆን ግብሩ ጣዖት ማምለክና መስረቅ ነበር:: በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በምዕመናን ላይም ግፍን ፈጽሟል:: በሥጋዊ ጉልበቱ ኃይለኛ ስለ ነበር የተፈራ ነው::
ሁልጊዜ በጠዋት ወደ #ቤተ_ክርስቲያን ይሔዳል:: የሚሔደው ግን ንዋያተ ቅድሳትን ለመዝረፍ: አንድም ካህናትን ለመደብደብ ነበር:: የሚገርመው ግን የወቅቱ …
👏2
21 Aug 2026, 19:00 UTC227 views3 reactionsread 23 August 2026 ሥርዓተ ማኅሌት ዘነሐሴ ፲፮ በዓለ ኪዳነምህረት
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
#መልክአ_ሥላሴ፦
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
#ዚቅ፦
ወታስተሥርዩ…
👏3
21 Aug 2026, 18:11 UTC213 viewsread 23 August 2026 Photo
📖 መማር እንሻለን - የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ ዘመቻ
ማኅበራዊ ቀውሶች የብዙ ሕፃናትን የትምህርት ጉዞ አግድመውታል። የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት እነዚህን ሕፃናት ለመደገፍ ሰፊ የንቅናቄ ዘመቻ ጀምሯል።
🔹 ዓላማ፦ ሕፃናቱ በትምህርት መሣሪያ እጥረት ሳይስተጓጎሉ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ።
🔹 መዋጮ፦ የአንድ ተማሪ ዓመታዊ ቁሳቁስ ወጪ 3,300 ብር ቢሆንም፣ ማንኛውም ሰው የቻለውን ያህል (አንድ ደብተርም ቢሆን) ማበርከት ይችላል።
🏦 የባንክ መረጃዎች፦
CBE: 1000309803648
Ahadu: 0025393810901
Abyssinia: 23375458
Wegagen: 083731610101
📍 የመቀበያ ቦታ፦ አምስት…
21 Aug 2026, 17:50 UTC157 viewsread 23 August 2026 Forwarded from @igziyabhernFile
ድንግል ትንሳኤሽን
ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ
ለእኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምህረት /2/
ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው
የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
ትንሳኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን አይተናል
ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል /2/
አዝ___
ልናየው ወደድን የቶማስን ክብር
ለምን ተስወረን የትንሳኤሽ ምስጢር
በራችንን ዘግተን በፀሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል
ሞትማ በሞት ተሽንፏል
ባንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል/2/
አ…
21 Aug 2026, 17:21 UTC131 viewsread 23 August 2026 Photo
🌿🌿🌿☘ ሻደይ ☘🌿🌿🌿
ክፍል-፩-
አሸንዳ - ሃይማኖታዊ ወይስ ባህላዊ?
የእመቤታችን የዕርገትዋ በዓል ሲመጣ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የሚታይ አንድ ሃይማኖታዊ ክንዋኔ አለ:: እሱም
✍ አሸንዳ!! በአክሱምና አካባቢዋ
✍ዓይንዋሪ ”፣ በምስራቃዊ ትግራይ
✍ “ ማሪያ ”፣ በመቐለና አካቢቡዋ
✍ በሰቆጣ፣ ላስታ ላሊበላና በራያ ቆቦ ደግሞ " ሻደይ " ይባላል።
❣ይህ ሃይማኖታዊ የሴቶች በዓል ከነሐሴ 16 ጀምሮ እንደየ አካባቢው እስከ 2 ሳምንትም እስከ አዲስ ዓመትም ሊደርስ የሚችል መንፈሳዊ በዓል ነው::
❣ ነገር ግን ለብዙ ዘመናት ከባሕል ጋር ተዳቅሎ፣ መንፈሳዊነቱ ተረስቶ በመቆየቱ፣ አንዳንዶችም ባሕላዊ በዓል ነው ለማለት ደርሶ ሲቃጣቸው እናያለን።
📌በአሸን…
21 Aug 2026, 17:21 UTC151 viewsread 23 August 2026 ሻደይና አሸንዳ በሃይማኖታዊ እይታ
ክፍል-፪
፪:- የአሸንዳ በዓልም "የሴቶች የነፃነት ቀን" ነው። በዓሉ የሴቶች በዓል እንደሆነ ሲነገር በተጨማሪም የሴቶች ብቻ ሳይሆን የደናግል_ሴቶች በዓል ነው::
ይሄም የእመቤታችንን ድንግልና የሚያስታውስ ሲሆን አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው እንዳለው «የወጣቶች የደናግልና የመነኮሳት መመክያ ናት» እንዳለው የድንግልናቸውን ዋጋ የምታሰጣቸው ናትና ደናግል ያመሰግኗታል ይዘምሩላታል::
፫:- የአለባበስ ሥርዓቶቹ :- ሴቶቹ ለበዓሉ መስቀል ያለበት አዲስ ቀሚስ በአንገት የሚደረግ የብር/ብረት መስቀልና በተለይም ደግሞ በወገባቸው
የሚታጠቁት የአሸንዳ ቅጠል ነው::
የመስቀል ሐብልና በመስቀል ያጌጠው
ቀሚስ ክርስቶስን የሚሰብኩበትና በ…
21 Aug 2026, 17:20 UTC102 viewsread 23 August 2026 መሞቷንም ሆነ ማረጓን
የነገረችን EOTC ናት።
የኢየሱስን እናት አሟሟት መጽሐፍ ቅዱስ አልነገረንም ፤ ግን መሞቷን ሁሉም ያምናል።
ዐርጋለች ሲባል ግን ማመን የከበደን ለምንድነው ?
ወይስ የእሷ ማረግ የክርስትናውን ክብር ይቀንሰዋል ?
. ተነሥታለች ስንል አልዓዛርን ከሞት ባስነሳው በልጇ ኃይልና ሥልጣን ነው።
. ዐርጋለች ስንልም ኤልያስን ባሳረገው በእግዚአብሔር ኃይልና ሥልጣን መሆኑን አንዘነጋም።
ነገር ግን ለሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ይጠቀስልኝ ማለት የጌታ ኃይልና ሥልጣን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብቻ ቀርቷል በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈው ውጭ ጌታ ሥራን አልሠራም ኃይሉም ቆሟል ወደሚል ክህደት ይወስዳል።
መቼም መነሣትና ማረግ አምላክን ከመውለድ ቢያንስ…
21 Aug 2026, 17:19 UTC159 views2 reactionsread 23 August 2026 🔔 ስንክሳር ነሐሴ 16 🔔
🌻 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ 🌻
❖ ነሐሴ ፲፮ ❖
❤️እንኩዋን ለእመቤታችን
ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ የትንሳኤና የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
🌻 ዕርገተ_ድንግል_ማርያም 🌻
👉 ይሕች ዕለት እጅጉን ታላቅና ክብርት ናት:: ምክንያቱም የድንግል ማርያም ሥጋዋ ተነስቶ ዐርጐባታልና:: ድንግል እመቤታችን ተነሳች: ዐረገች ስንል እንደ እንግዳ ደርሶ: እንደ ውሃ ፈሶ: ወይም በአጋጣሚ የተደረገ አይደለም::
ጥንቱን በአምላክ ልቡና ታስቦ: ሁዋላም ትንቢት
ተነግሮለት ነው::
¤ታሪኩ: ነገሩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላ…
👏2
20 Aug 2026, 15:43 UTC216 views4 reactionsread 23 August 2026 🌿✞ ስንክሳር ነሐሴ 15 ✞🌿
እንኳን ለንጹሐት እናቶቻችን ቅድስት እንባ መሪና እና ቅድስት ክርስጢና ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✞✞✞
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
✞✞✞ ቅድስት እንባ መሪና ✞✞✞
✞ ቤተ ክርስቲያን "እንቁዎቼ" ከምትላቸው ሴት ጻድቃን አንዷ ቅድስት እንባ መሪና ናት:: ጣዕመ ዜናዋ: ሙሉ ሕይወቷ: አስገራሚም: አስተማሪም ነው:: ቅድስቷ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ተወልዳ ያደገች ክርስቲያን ናት:: ወላጆቿ ከእርሷ በቀር ሌላ ልጅ የሌላቸው ሲሆን በአኗኗራቸውም ደግና ቅን ነበሩ::
ቅድስት እንባ መሪና ትክክለኛ ስሟ "መሪና" ነው:: ምክንያቱም "እንባ መሪና" የወንድ…
👏4
20 Aug 2026, 07:42 UTC209 viewsread 23 August 2026 Forwarded from @yaregalabegaz
‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል›› (መዝ. ፹፰፥፲፪)
በትንቢት ‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስም ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነቢዩ ዳዊት እንደተናገረው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ (መዝ. ፹፰፥፲፪)
በዚህችም ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፡፡
ስለ እርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ፡፡ ሰዎች ሁሉ እ…
19 Aug 2026, 16:06 UTC248 views1 reactionsread 23 August 2026 🙏 ስንክሳር ነሐሴ 14 🙏
✞እንኳን ለጌታችን ቅዱስ ዕፀ መስቀል ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
❣✞ ቅዱስ ዕፀ መስቀል ✞❣
✞ የዕፀዋት ሁሉ ንጉሣቸው የሚሆን ቅዱስ ዕፀ መስቀል ለእኛም ኃይላችን: ቤዛችን: መዳኛችን: የድል ምልክታችን ነው:: መስቀል በደመ ክርስቶስ ተቀድሷልና አንክሮ: ስግደት ክብርና ምስጋና በጸጋ ይገባዋል::
ቅዱስ መስቀለ ክርስቶስ ላለፉት ሁለት ሺ ዓመታት ብዙ ተአምራትን ሠርቷል:: ከእነዚህ መካከልም አንዱን በዚህ ዕለት እናዘክራለን::
ታሪኩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በ400 ዓ/ም አካባቢ በግብፅ አባ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ሳለ: ቅዱስ…
🙏1
19 Aug 2026, 07:36 UTC312 views3 reactionsread 23 August 2026 #ደብረ_ታቦር
ከጌታችን ዓበይት በዓላት አንዱ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የምናከብረው የደብረ ታቦር በዓል ነው፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን የገለጠበት በመሆኑ በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ (ማቴ .፲፯፡፩፣ ማር.፱፡፩፣ሉቃ.፱፡፳፰)፡፡
ደብረ ታቦር፡- ‹‹ደብረ ታቦር›› ደብር እና ታቦር ከሚባሉ ከሁለት ቃላት የተገኘ ሲሆን ‹የደብረ ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል ፲ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡
በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ክቡር ዳዊት በመዝሙሩ “ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል” በማለት…
🙏3
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @Sinksar. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.