19 Aug 2026, 10:40 UTC52 views2 reactionsread 19 August 2026 +++ "የምወደው ልጄ ይህ ነው" +++
ጌታችን ከሐዋርያቱ መካከል "የምሥጢር ሐዋርያ” የተባሉትን ያዕቆብና ጴጥሮስ፣ ዮሐንስንም ወደ ቅዱሱ የታቦር ተራራ ብቻቸውን ይዟቸው ወጣ። ከተራራውም ጫፍ ሲደርሱ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የመምህራቸው ፊት እንደ ፀሐይ ሲያበራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሲሆን ተመለከቱ። እነሆም ከቀደሙት ጻድቃን ታላላቆቹ ሙሴና ኤልያስ በታቦር ተገኝተው ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።
እነዚህ የብሉይ ኪዳን ነቢያት የትንቢታቸው ፍጻሜ ከሆነው ክርስቶስ ጋር ምን ተነጋገሩ? መቼም በጊዜው ከጌታ ጋር ውለው ያድሩ እንደ ነበሩት ተማሪዎቹ ሐዋርያት "አትሙትብን" አይሉትም። በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ሱባኤ የያዙለትና ደጅ የጠኑት የድኅነት ተስፋ እናዳ…
❤1🔥1
18 Aug 2026, 17:48 UTC337 views9 reactionsread 19 August 2026 + ከታቦር ተራራ አትቅር +
"አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ። "
ማር 9: 3
/ሽራፊ ሃሳቦች ከደብረ ታቦር ንባብ/
የወንጌላውያን ትሕትና ይደንቃል ፣ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ስለ ደብረ ታቦር ሲጽፉ ዮሐንስ አልጻፈም። ዮሐንስ ተመርጦ የተገኘበትን ታሪክ "ተመርጬ" ብሎ አልጻፈም። የቀሩት ወንጌላውያን ደግሞ "እኛ የሌለንበትን ነገር አንጽፍም" አላሉም። አንድ ወንጌል እየሰበኩ የሚፎካከሩ ፣ የአንድ ቤት ጣሪያ እየሠሩ ቆርቆሮ የሚሻሙ የእኛ ዘመን አገልጋዮች አልነበሩምና እነርሱ ያልተመረጡበትን ታሪክ ለመናገር ተሯሯጡ። እኛን የማያካትት ክብር ፣ እኛን የማይጨምር ድግስ ጉዳይ ሲነሣ ለማይጥመን ፣ እኛ የሌለንበትን ፎቶ እንኳን…
❤9
17 Aug 2026, 05:53 UTC559 viewsread 19 August 2026 ስድብ ኃጢአት ባይሆን ኖሮ መሰደብ የሚገባው ዲያቢሎስ ነው:: ፍጥረት ሁሉ ስድብ ቢያዋጣ ለዲያቢሎስ የሚመጥን አይሆንም:: የክፋት ምንጭ ለሆነ ለእርሱ ሁሉም ክፉ ቃል መገለጫው ነው::
ይሁንና ቅዱስ ሚካኤል ይህንን ክፉ ጠላት ደፍሮ አልሰደበውም:: "እግዚአሔር ይገሥጽህ!" አለው:: (ይሁ 1:9)
እንደ ሚካኤል ንጹሕ በእኛ ዘን ማን አለ? እንደ ዲያቢሎስስ ክፉ በእኛ ዘንድ ማን አለ?
መልእክቱ ግልጽ ነው:: አንሆንም እንጂ እንደ ሚካኤል ንጹሕ ብንሆን እንኳን እንደ ሰይጣን የከፋን ሰው እንኳን መሳደብ አንችልም::
የመላእክት አለቃ ሚካኤል ከሥልጣኑ የወረደውን የቀድሞውን የመላእክት አለቃ ዲያቢሎስን አንድም ክፉ ቃል አልተናገረውም:: አንዱ ከሥልጣኑ ወድቆ ሌ…
16 Aug 2026, 06:52 UTC585 views1 reactionsread 19 August 2026 እችላለሁ ካልህ ትችላለህ!?
ክርስቲያን "ሁሉን እችላለሁ" ይላል ወይ? አዎ ይላል:: ግን ከፊቱ የሚቀር ሐረግ አለ::
"ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ" (ፊል. 4:13)
በራስ መተማመንም እግዚአብሔርን ከለላ በማድረግ ብቻ ነው:: "በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን በራስህም ማስተዋል አትደገፍ" ምሳ. 3:5
ስለዚህ በእግዚአብሔር መታመን በራስ ከመታመን በላይ ነው:: Confidence ከሚለው ይልቅ Godfidence የሚል አዲስ ቃል ሳይገልጸው አይቀርም::
የተፈጥሮ ጸጋህን እወቅ በሚል በጎ መነሻ የተጀመረው "ነኝ ካልኩ ነኝ" የሚለው መፈክር አሁን ላይ ምድርን እየበጠበጠ ይገኛል:: ሰዎች "ውብ ነኝ ጎበዝ ነኝ ፤ ደፋር ነኝ" ብለው ራሳቸው…
❤1
15 Aug 2026, 04:50 UTC599 views4 reactionsread 19 August 2026 + ለምን ትቀናለህ? +
በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ፡፡ ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉበት፡፡ በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ፡፡ አልተሳካም፡፡ በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡
አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ…
❤3🥰1
14 Aug 2026, 11:51 UTC235 views2 reactionsread 19 August 2026 እግዚአብሔር ዓሣን ሲፈጥር "ሕይወት ያላቸውን አስገኝ" ብሎ ባሕርን ተናገረው
እግዚአብሔር ዛፎችን ሲፈጥር ደግሞ ዛፍ እንድታበቅል መሬትን ተናገራት
ሰውን ሲፈጥር ግን የተናገረው ለራሱ ነበር
እግዚአብሔርም አለ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር"
ልብ አድርጉ :-
ዓሣ ከባሕር ከወጣ ወዲያውኑ ይሞታል
ዛፍም ከምድር ላይ ከተነቀለም ይሞታል
ሰውም ከእግዚአብሔር ከተለየ ይሞታል:: ባሕር ለዓሣ መሬት ለዛፍ ተፈጥሮአዊ መጠለያቸው እንደሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮአዊ መጠጊያችንም እግዚአብሔር ነው:: የተፈጠርነው ከእርሱ ጋር ልንኖር ነው:: ሕይወት ያለን ከእርሱ ጋር ነውና መኖር የምንችለው በእርሱ ብቻ ነው::
ይህንንም እናስታውስ
ዓሣ ያለ ባሕ…
🥰2
14 Aug 2026, 04:49 UTC187 views4 reactionsread 19 August 2026 “ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዲህ አለ:-
በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕት እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ ... የተራ ቀለማት
መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም፡፡
የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ስለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡
እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር? እነሆ የድንግል…
❤4
5 Aug 2026, 15:54 UTC348 views5 reactionsread 19 August 2026 + ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +
ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"
ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::
ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)
ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁ…
❤5
Channel photo updated
3 Aug 2026, 07:18 UTC908 viewsread 19 August 2026 (ከፕሮቴስታንትነት ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሕማማትን መጽሐፍ አንብቦ የተመለሰው ወንድም )
መጽሐፈ #ሕማማት እና የእኔ ገጠመኝ
#የሕማማት መጽሐፍ ከአንባብያን ከቀረበች ሶሰተኛም የዓብይ ጾምን ይዛለች። መጽሐፉ ጸሐፊ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እኔ የምኖርበት አካባቢ የሕማማት መጽሐፍት እንዳሉና የታተመውን መጽሐፍ እኔ ከምኖርበት ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ እንዳደርስ ነግሮኝ ስለነበር ከዛሬ ሰባት ቀን በፊት በነግህ ተነስቼ በግዮን ባስ መጽሐፍቱን ይዤ ወደ አዲስ አበባ አቀናሁ።
ዲያቆን ሄኖክ መጽሐፍቱን እንዳስረክበው በስልክ ካገናኘን ሰው ጋር ተገናኝተን መጽሐፍቱን አስረክቤ ዕለቱን ወደ ሻሸመኔ መመለስ ስለነበረብኝ ከዚህ ቀደም ባነበውም ለመንገድ እንዲሆነኝ ብዬ…
30 Jul 2026, 06:04 UTC324 views3 reactionsread 19 August 2026 በከበረች ጸሎቱ ይቅር ይበለንና ራሱን በትሕትና "ከጌቶች ልጆች የሚወድቀውን ፍርፋሪ የሚለምን ውሻ" ብሎ የሚጠራው ሶርያዊው ኮከብ ቅዱስ ኤፍሬም በየድርሰቶቹ መካከል እንዲህ እንዲህ አለ:-
"ጌታችን ከሣምራዊትዋ ሴት ጋር በተነጋገረ ጊዜ በንግግራቸው መጀመሪያ ማንነቱን አልገለጠላትም። መጀመሪያ ያየችው ውኃ የጠማውን ሰው ነበር ፣ ከዚያ አይሁዳዊ ፣ ከዚያ መምህር (ረቢ) ፣ ቀጥሎ ነቢይ ከሁሉም መጨረሻ መሲህ መሆኑን አየች።
ውኃ የተጠማውን ሰው በንግግር ልትረታ ስትሞክር በአይሁዳዊ ላይ ያላትን ጥላቻ አሳየች። ከመምህሩ ጋርም ተከራከረች ፣ ከነቢዩ እግር ስር ተንበረከከች ፣ መሲሁንም ወደደችው"
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (ስለ ሣምራዊቷ ሴት ዮሐ 4:1)
★ ★ ★
…
🙏2❤1
29 Jul 2026, 20:23 UTC270 viewsread 19 August 2026 File
File, posted without a caption
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @dnhenok_haile. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.