14 May 2026, 16:18 UTC≈5,790 views3 reactionsread 8 August 2026 Photo
የገንዘብ ሽልማት የሚያስገኝ የሥነ ጽሑፍ ውድድር ጥሪ
ዘውግ፦ አጭር ልቦለድ
(ከ900 ቃላት ያልበለጠ፣ ለኅትመት ያልዋለ ዐዲስ ጽሑፍ)
ጽሑፍ የመላኪያ ቀናት - ከግንቦት 3 - 10 / 2018 ዓ.ም
አሸናፊዎች የሚታወቁበት ቀን - August 29
ጽሑፍ የመላኪያ ኤሜል - [email protected]
ይህ ውድድር የዐዲስ ቅኝት ቴሌቪዥን አንደኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲኾን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች ከTASLAW የገንዘብ ሽልማት ይበረከትላቸዋል።
❤3
Signed ኒያስ
Channel photo updated
2 Mar 2026, 12:00 UTC466 views4 reactionsread 8 August 2026 Photo
እንኳን ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 🇪🇹
አድዋ ማለት የጥቁር ሕዝብ የነፃነት ጮራ ብቻ አይደለም፤ አድዋ ማለት የማይቻል የሚመስልን ተራራ በአንድነት የመናድ፣ የቆሰለ ልብን በፍቅር የመጠገን እና በቃላት የማይገለጽ የጽናት ተምሳሌት ነው።
ያኔ አባቶቻችንና እናቶቻችን በአንድነት ቆመው ታሪክን እንደቀየሩት ሁሉ፣ ዛሬም እኛ በመካከላችን ያለውን ልዩነት በፍቅር ድል አድርገን፣ የታረቀ ልብና የታደሰ ተስፋ ይዘን እንድንጓዝ የአድዋ መንፈስ ብርታት ይሁነን።
ፍቅር ከሁሉ ይበልጣል፤ አንድነትም ድል ያደርጋል!
መልካም በዓል!
❤2🔥2
Signed Kalariya
29 Apr 2025, 09:27 UTC≈1,120 views16 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @alememayaPhoto
ይች አይጥ አሳም ውስጥ በሚገኝ ATM ማሽን ውስጥ ድንገት ገብታ ያላሰበችው ሲሳይ ገጠማት።
አይጧ'ም ኤትኤሙ ውስጥ ያለውን 17,600 ዶላር ቅርጥፍጥፍ አድርጋ በላችው።
አስገራሚው ነገር ብሩን ከበላች በኋላ የገባችበት የገመድ ቀዳዳ ሊያስወጣት ባለመቻሉ ኤቲኤሙ ውስጥ ሙታ ተገኘች።
🕹join & share
@alememaya
@alememaya
😁12😭4
Signed ኒያስ
29 Apr 2025, 08:23 UTC924 views15 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @alememayaPhoto
ፖሊስ እኒህን እናት አምስት እንቁላል ስትሰርቅ እጅ ከፈንጅ ያዛት።ለምን እንደሰረቀች ሲጠይቃት "ለልጄ ማበላት አጥቸ ነው" በማለት ነበር የመለሰችለት።
ፖሊሱ ይህን ሲሰማ አላሰራትም ይልቁንም ወደ ሱፐር ማርኬት በመሄድ የሚያስፈልጋትን ያህል የቤት አስቤዛ ገዝቶ ሰጣት🥰
🕹join & share
@alememaya
@alememaya
🥰13❤2
Signed ኒያስ
29 Apr 2025, 07:15 UTC832 views8 reactionsread 8 August 2026 Photo
በመተኛት ብቻ ገንዘብ እንደሚገኝ ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ?
ዓለም ላይ ከፍተኛ ገንዘብ የሚገኝባቸው 7 አስደናቂ ስራዎች😄
1) ለህክምና ምርምር የሚያገለግሉ መርዞችን ከእባብ ማውጣት በወር 670 ሺህ ብር ያስገኛል።በዚህ መንገድ ታልቦ የሚሰራው መዳኒት የብዙ ሰዎችን ህይወት ታድጓል።
2) ፍራሽ አምራች ድርጅቶች የፍራሻቸውን ምቾት እንዲነግሯቸው በእንቅልፍ የተካኑ ሰዎችን ይቀጥራሉ።በተጨማሪም አዳዲስ ሆቴሎች ሲከፈቱ የአልጋውን ምቾትና ውበት ተኝተው እንዲነግሯቸው የሚቀጥሯቸው ሰዎች በሳምንት እስከ 200 ሺህ ብር ይከፈላቸዋል።
3) ዶዶራንት ወይም ሽቶ አምራች ድርጅቶች ጠረን የሚያሸት ሰው ይቀጥራሉ።የዚህ ሰው ሀላፊነት የሰው ብብት ላይ የተነፋው ዶድራንት ጠረ…
😨5👍3
Signed ኒያስ
27 Apr 2025, 09:04 UTC644 views8 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @alemmayapicturesPhoto
ወሰን የለሽ ጓደኝነት
በጎርጎሮሳውያን አቆጣጥር 2004 ላይ በህንድ ውቅያኖስ ኃይለኛ የሱናሚ ማዕበል ተነሳ።በዚህ ምክንያት ኦወን የተባለው ህጻን ጉማሬ ከቤተሰቦቹ የመነጠል እጣ ገጠመው።ሱናሚው የኬኒያ የባህር ዳርቻ ላይ አደረሰው።
የአካባቢው ሰዎችም ጉማሬውን አንስተው ወደ ሃለር የዱር እንስሳት መጠለያ ፖርክ አስገቡት።ፖርኩ ውስጥ ከገባ በኋላ ነበር 130 ዓመት የሞላት ምዚ የተባለች ኤሊ ያገኘው።
ከኤሊዋ ጋር ጓደኝነት መሰረቱ።እሷ በምትሄድበት ሁሉ ተከትሏት ይጓዛል።በእናት እጦት የሚሰቃየው ህጻኑ ጉማሬ ኤሊዋን እንደ ሁለተኛ እናቱ ነበር የሚያያት።ከዛን ጊዜ ጀምሮ ማይነጣጠሉ ጓደኛሞች ሆኑ።
ምግብ አብረው ይበላሉ ፤ ያርፋሉ ፤ የትም ሲጓዙ አብረው ነው …
🥰7👍1
Signed ኒያስ
23 Apr 2025, 08:55 UTC762 views6 reactionsread 8 August 2026 Photo
ጠየቀቺኝ ፍቅሬ...
“ይሄ ዝርግ ሰማይ ፥ ሽቅብ የምናየው
ከእኔ ተፈጥሮ ጋ ምንድን ነው 'ሚለየው ?”
(እኔም ስመልስ እንዲህ እላለሁ...)
ልዩነትማ...
ልዩነት አለው !
የሳቅሽ እንደሆን
ሰማይ መኖሩን እዘነጋለሁ ።
Nizar Qabbani.
ትርጉም - Hab
🥰6
Signed ኒያስ
12 Apr 2025, 16:43 UTC819 views13 reactionsread 8 August 2026 ትንሽ ቦታ 🥰
---
በዚህ ዓመት፣
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ትንሽ ቦታ መጠለያ
ትንሽ ብቻ መሠደጃ።
ምናለበት፣
ለምን አልባት ብንተውለት?
ፍፁም መሆን ስለማንችል
ትንሽ ባዶ እንዋዋል፣በልባችን ደግ በኩል።
ለአንጎላችን መላወሻ
ትንሽ ቦታ እንተውለት
''ምናልባት'' የምንልበት !!
ልክ እንደ አምና - በዚህ ዓመት ።
ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ
ብንታሰር ይቅር ማያ
ይቅር ብለን መታሰሪያ
ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ
ጥግ ድረስ የለም ስራ፣ጥግ ድረስ የለም ፋታ።
በልባችን ደግ በኩል፣እንፈልግ ባዶ ቦታ፣
የጳጉሜ አይነት ትንሽ ቦታ
ለዘመን መለወጫ።
©ነብይ መኮንን
📖ስውር ስፌት ቁ.2
❤11👍2
Signed ኒያስ
5 Apr 2025, 06:21 UTC793 views6 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @netsaalemePhoto
💥💥💥ተስፋ💥💥💥
ተስፋ እንደ ፍቅር ምንም እንኳን ሶስት ቃል ብቻ ቢሆንም ረቂቅ ነገር ነው።
ተስፋ የኔልሰን ማንዴላ የ ሀያ ሰባት አመት አበርቺ ጎደኛቸው ነው ባይሆን ኑሮማ ያንን መከራ በምን ይጋፈጡት ነበር።
ተስፋ ከነገ ፀሀይ ተውሰን የዛሬ ጨለማን የምንገፍበት ብርሀን ነው።
በድሮ ዘመን ዝሆን ማደን የሚፈልጉ ሰዎች ዝሆኑ የሚደገፍበትን ዛፍ ከስር ከስሩ ይቦረብሩታል ትንሽ ሲቀረው ትተወት ይሄዳሉ።ያዝሆን ሀገር ሰላም ብሎ ዛፍን ሲደገፍ ዛፉ ተገንድሶ ይዞት ይወድቃል።ያመነው የከዳው ዝሆን መነሳት አይችልም ። ሞቱን ከመጠበቅ ውጪ!!!
ተስፋ ማድረግ ባይከፋ ተስፋ ያደረግንበትን ነገር ጠንቅቀን እንወቀው የዝሆኑ እጣፈንታ እንዳይደርሰን።
"" የሰው ልጅ…
👍6
Signed ኒያስ
21 Mar 2025, 06:39 UTC860 views11 reactionsread 8 August 2026 "ምን ያህል እንደምወድሽ ያሳየሁሽ አይመስለኝም" አልኳት።
"አይቼዋለሁ! መውደድህ በማክበር ተጠቅልሎ... ከማክበር በላይ መውደድ የት አለ? ፊትህ እኮ ብዙ የሚናገር ሰው ነህ..."
"የሚገርምሽ ቁስልሽን ስትነግሪኝ፤ ፈገግ እያልሽ ቀለል አድርገሽ ነበር ግን ...ስንቴ መሰለሽ ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ? ስንቴ መሰለሽ ያልነገርሺኝን ሁሉ በምናቤ እየጨመርኩ ብቻዬን የቃተትኩት?"
"...ታዉቂያለሽ? የኔ ሸክም ላይ ሸክምሽ ሲጨመር አልችለው ይሆናል ብዬ ነው የሸሸሁት...እንጂ ካንቺ ጋ መኖር ሕይወትን እንዳትሰለች ያደረጋታል።"
ትንሽ ፈገግ ብላ..."እውነቱን ልንገርህ...?" አለችኝ። ንገሪኝ አልኳት።
"እውነተኛውን ሸክሜን በቶሎ ባላሳየው ያገባኝ ይሆን እን…
👍8❤1👏1🥰1
Signed ኒያስ
15 Mar 2025, 04:32 UTC≈1,180 views17 reactionsread 8 August 2026 Photo
የአሜሪካው የስነ ህዋ ምርምር ተቋም (NASA) አስትሮኖመር ወደ ህዋ በሚልክበት ሰዓት አንድ ያልጠበቀው ችግር አጋጠመው።ተመራማሪዎቹ ህዋ ላይ ሁነው ዳታዎችን በወረቀት ለመመዝገብ ሲሞክሩ ስክርቢቷቸው አይጽፍም።ምክንያቱም የቦታው ግራቪቲ ዜሮ ስለሆነ የስክርቢቶ ቀለም ሊወርድ አይችልም።
ተመራማሪዎቹ ይህ ችግር ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ ሌት ተቀን በዜሮ ግራቪቲ የሚሰራ ስክርቢቶ ለመስራት ምርምር ማድረግ ጀመሩ።ለስራው ማስኬጃ 12 ሚሊየን ዶላር ተመደበ።በመጨረሻም ከአስር ዓመት ምርምር በኋላ ሐሳባቸው እውን ሁኖ መስራት ቻሉ።
አስገራሚው ነገር በጠፈር ሳይንስ ዘርፍ የአሜሪካ ተፎካካሪ የሆነችው ራሽያ'ም ይህ ችግር ግጥሟት ነበር።ሁኖም ምንም አይነት ከባድ ምርምር …
👍14👏2❤1
Signed ኒያስ
Showing the 12 most recent of 16 posts we hold for @wegochi. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.