28 Aug 2026, 18:56 UTC≈1,440 views10 reactionsread 29 August 2026 Photo
የሩሲያ ጥቃት 90% የዩክሬንን የምግብ አቅርቦት መጉዳቱ ተገለጸ።
በዋና ከተማዋ ብቻ የሚገኙ 14 የምግብ ማከማቻዎች በሞስኮ ጥቃት ሙሉ በሙሉ መድመዋል ተብሏል።
የኪቭ ቀጠና ወታደራዊ አዛዥ ቲሙር ቲካችንኮ አብዛኞቹ ጥቃቶች የተፈፀሙት በካሚካዝ ድሮን ነው ብለዋል።
የምግብ አቅርቦቱ ኢላማ የተደረገው ከማከማቻ ወደ ማከፋፈያ ሊጓጓዝ የነበረ መሆኑን ተናግረዋል።
ከምርት ወደ መጋዘን መግባት ቢችልም ወደ ህዝብ መከፋፈል ግን አልቻለም ብለዋል ቲካችንኮ። #telegraph
@EyobTikuye @ThiqahEth
😢5❤3🕊2
28 Aug 2026, 18:52 UTC≈1,470 views16 reactionsread 29 August 2026 Photo
የሶርያ ፕሬዚዳንት ሙሐመድ አልሻራ የኩርድ "አማፂ ቡድን" መሪን አማካሪያቸው አድርገው ሾሟቸው።
ፕሬዚዳንቱ ማዙልም አብዲን የፕሬዚዳንታዊ ጉዳዮች አማካሪ አድርገው መሾማቸውን አስታውቀዋል። አብዲ የኩርድ መር ዲሞክራሲያዊ ሀይል (SDF) መሪ በመሆን ማዕከላዊ መንግስትን ሲዋጉ ቆይተዋል።
ቡድኑ ከአልሻራ መንግሥት ጋር ባደረገው ድርድር ትጥቅ ለመፍታት በመወሰኑ ነው ስልጣን የተጋራው። የሶርያ ትምህርት ሚኒስቴር ከሁለት ወር በፊት የኩርድ ቋንቋ በትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ስርዓት እንዲካተት መወሰኑ ይታወቃል። #france24
@EyobTikuye @ThiqahEth
👍9👏4🕊3
28 Aug 2026, 18:46 UTC≈1,460 views15 reactionsread 29 August 2026 Photo
በኔፓል በተከሰተው አስደንጋጭ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 579 ሲደርስ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደብዛቸው ጠፋ።
የኔፓል የአደጋ ጊዜ ኤጀንሲ እንደገለጸው ከጠፉት ሰዎች መካከል ቢያንስ 517ቱ የውጭ ዜጎች ናቸው።
ከኔፓል ጋር በምትዋሰነው የቻይናዋ ራስ ገዝ አስተዳደር ቲቤትም በአደጋው አምስት ሰዎች ሲሞቱ፣ ከ550 የሚልቁት መጥፋታቸውን የቻይና የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ሁኔታዎች በፍጥነት የሚለዋወጡ በመሆኑ የተለያዩ ባለሥልጣናት የሚገልጹት ቁጥር የተለያየ ቢሆንም የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው።
አደጋው ከተከሰተ ከሁለት ቀናት በኋላም የነፍስ አድን ጥረቱ እንደቀጠለ ነው። የጠፉ ሰዎችን በተመለከተ የሚወጡ መረጃዎችን ወዳጅ ዘመዶቻቸው በጭንቀት እየጠበ…
😭6❤5😢3😱1
27 Aug 2026, 20:23 UTC≈2,110 views9 reactionsread 29 August 2026 Photo
በአልጄሪያ በተቀሰቀሰ ሰደድ እሳት ቢያንስ የ12 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በሰሜናዊ አልጄሪያ በተከሰተው ከባድ የሰደድ እሳት 54 ሰዎች መጎዳታቸውም ተገልጿል፡፡ የሰሜን አፍሪካ ሀገራት በተለይም ቱንዚያ እና አልጄሪያ በሰደድ እሳቱ ተጋላጭ መሆናቸው ተመላክቷል።
ሰደድ እሳቱን ለማጥፋት 70 የሚደርሱ ባለሙያዎች መሰማራታቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል። ሰደድ እሳቱ የተከሰተው በአካባቢው ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ችግር ነው። #bbc
@EyobTikuye @ThiqahEth
💔5❤2😢1🙏1
27 Aug 2026, 20:22 UTC≈2,090 views7 reactionsread 29 August 2026 Photo
ከፍተኛ የሩሲያ ወታደራዊ አመራር በቦምብ ጥቃት ተገደሉ።
ስማቸው ያልተገለፀውና የሩሲያ ኤሮስፔስ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ወታደራዊ ባለስልጣን በሴይንት ፒተርስበርግ ከተማ ነው ጥቃት የተፈፀመባቸው።
የሌተናል ኮሎኔልነት ማዕረግ እንዳላቸው የተገለፁት እኒህ አመራር ከባለቤታቸው ጋር በግል መኪናቸው እየሄዱ በነበረበት ወቅት ነው የተገደሉት።
ባለቤታቸው ከባድ የመቁሰል አደጋ እንደገጠማቸውና ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ ተገልጿል። ስለደረሰው ጥቃትና የወንጀለኛ አያያዝ ላይ ከፖሊስ የተሰጠ ማብራሪያ የለም። #militarnyi
@EyobTikuye @ThiqahEth
❤5💔2
27 Aug 2026, 20:18 UTC≈2,040 views10 reactionsread 29 August 2026 Photo
በኔፓል የሟቾቹ ቁጥር 300 ደረሰ። ቢያንስ 1500 መጥፋታቸው የኔፓል አደጋ አስተዳደር አስታውቋል። የጎርፍ አደጋው ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ተከስቷል።
@EyobTikuye @ThiqahEth
😢8😡2
25 Aug 2026, 20:04 UTC≈2,780 views24 reactionsread 29 August 2026 Photo
"ኢራን አንደኛውን ልጄን ኢላማ አድርጋብኛለች" ኔታንያሁ
ኔታንያሁ "ኢራን ልጆቼን ልትገድልብኝ ሞክራለች" አሉ። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኔጃሚን ኔታንያሁ "የማይታመን ነገር ተፈጥሯል፣ ከሁለቱ ልጆቼ አንዱ በኢራን ኢላማ ተደርጓል" ሲሉ ተናግረዋል። የት እና መቼ እንደሆነ ግን ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም። #chanel14
@EyobTikuye @ThiqahEth
❤9😡7👏6🥰1😢1
25 Aug 2026, 20:00 UTC≈2,800 views17 reactionsread 29 August 2026 Photo
"ኦንታሪዎ ሀይቅን ወደ አሜሪካ ሀይቅ እንቀይረዋለን" ትራምፕ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካናዳን ወንዝ በአሜሪካ ስም ለመቀየር ማሰባቸውን ተናገሩ።
ትራምፕ "ከካናዳ ጋር ከዚህ በኋላ ብዙ የንግድ ግንኙነት ይኖረናል ብየ አላስብም" ብለዋል።
"ዩናይትድ ስቴትስ የሀይቁን ስም ለመቀየር እያጤነችበት ነው" ብለዋል። "ኦንታሪዎ ሀይቅን ወደ አሜሪካ ሀይቅ እንቀይረዋለን" በማለት ዝተዋል።
"ካናዳ ስምምነት ለመድረስ ከሚያስቸግሩ ሀገራት መካከል አንዷ ናት" ሲሉ ተችተዋል። "እነሱ ያለ እኛ መኖር አይችሉም፣ ይሄንን በተግባር እያየን ነው" በማለት ያልተለመደ አስተያየት ሰጥተዋል።
ትራምፕ ካናዳን የአሜሪካ 51ኛ ግዛት አደርጋለሁ ማለታቸው የሚታወስ ሲሆ…
👎9❤5👍1🕊1😱1
25 Aug 2026, 19:55 UTC≈2,520 views2 reactionsread 29 August 2026 Photo
በሄይቲ 47 ሰዎች በታጣቂዎች ሲገዱ፣ 22 በደረሰባቸው ጥቃት ቆስለው ሆስፒታል ገቡ።
ጥቃቱ የተፈፀመው በዋና ከተማዋ ፖርቶ ፕሪንስ መሆኑን በሀገሪቱ የተሰማራው የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል አስታውቋል።
የሄይቲ የሰብዓዊ መብት ቡድን በበኩሉ በፀጥታ ችግሩ ምክንያት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት እንዳልቻለ ጠቁሞ፣
የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ገልጿል።
በኪንሳፍ ግዛት በተፈፀመ ጥቃት በሁለት ወር ውስጥ 260 ሰዎች መሞታቸውን፣ 200 ቤቶች መውደማቸውን እና ከ3000 በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን ተመድ አመላክቷል። #times
@EyobTikuye @ThiqahEth
😡1😭1
25 Aug 2026, 19:53 UTC≈2,500 views5 reactionsread 29 August 2026 Photo
ከ300 በላይ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ለመንግስት እጅ ሰጡ ተባለ።
የናሽናል ሳልቬሽን ፍሮንት (NSF) አማጺ ቡድን ተፋላሚ የነበሩ ታጣቂዎች የትጥቅ ትግል አቁመው ሰላማዊ የትግል አማርጭን በመከተለው ወደ ዋና ከተማዋ ጁባ ገብተዋል ተብሏል፡፡
የታጣቂዎቹ እጅመስጠት የደቡብ ሱዳንን ሰላም እና መረጋጋት ያጠናክራል ተብሎ ተስፋ ተደርጓል።
የአማጺ ቡድኑ መሪ ብርጋዴር ጄነራል ሄላሪ ኢድሰን ያካኒ ጁባ በሚገኘው ብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት ተገኝተው በሰጡት መግለጫ ቡድናቸው ከመንግስትጋር በድርድር ልዩነቶችን ለመፍታት መወሰኑን እና ሙሉ በሙሉ የተጥቅ ትግል ለማቆም መስማማቱን አስታውቀዋል፡፡
የደቡብ ሱዳን ህዝብ በጦርነት መሰቃየት የለበትም ያሉት ያካኒ ሌሎች አ…
❤3🙏2
25 Aug 2026, 19:48 UTC≈2,350 views15 reactionsread 29 August 2026 Photo
"የማህበራዊ ሚዲያ መጪውን ትውልድ በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዳው ነው" - ኒውዝላንድ
ኒውዝላንድ በህጻናት የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምላይ ገደብ ልትጥል መሆኑ ተገለጸ፡፡
የኒውዝላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ሉክሶን እድሜያቸው ከ16 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች የማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል እቅድ ማቅረባቸው ተገልጿል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያ መጪውን ትውልድ በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዳው ነው ብለዋል፡፡
በ2025 በሀገሪቱ በተደረገው ጥናት መሰረት፣ አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት የኒውዝላንድ ህፃናት በቀን ለአምስት ሰዓት በማህበራዊ ሚዲያ ጊዚያቸውን ያጠፋሉ።#morningstar
@EyobTikuye @ThiqahEth
👏9❤5😢1
24 Aug 2026, 10:37 UTC≈2,900 views14 reactionsread 29 August 2026 Photo
#ፑንትላንድ
"ስምንት በጥቃቱ የተቃጠሉ አስከሬኖች አይቻለሁ" - የዓይን እማኝ
በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ ታግቶ የቆመ ነዳጅ ጫኝ #መርከብን ዒላማ ያደረገ #የድሮን ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መግደሉን የፑንትላንድ ባለሥልጣናት ተናገሩ።
ጥቃቱ የተፈጸመው በሶማሊያ ኑጋል ክልል፣ ጎዶብጂራን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ መሆኑን ተናግረዋል።
መርከቧ ኤምቪ ሉቱፍ (MV Lutuf) የምትባል ሲሆን ከቀናት በፊት በባሕር ላይ ወንበዴዎች ታግታ ወደ አካባቢው ማምራቷን ደግሞ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የካሜሮንን ሰንደቅ ዓላማ የምታውለበልበው ይህች መርከብ መዳረሻዋ ቱርክ ነበር።
መርከቧ ከዚህ ቀደም ጋርማል የሚባል አካባቢ ቆማ የነበረ ሲሆን በአካባቢው በተፈጸመ የድሮን ጥቃት አራት ሰዎ…
❤11😭2👍1
Showing the 12 most recent of 75 posts we hold for @thiqahEth. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.