10 Jul 2022, 19:06 UTC335 viewsread 10 August 2026 12 Fucking Rules for Success
1. Do the fucking work. Don't be lazy.
2. Stop fucking waiting. It's time.
3. Rely on yourself. The Universe doesn't give a fuck.
4. Be fucking practical. Success is not a theory.
5. Be productive early. Don't fuck around all day.
6. Don't be a fucking baby. Life's hard. Get on with it.
7. Don't hang out with fuckwits.
8. Don't fucking waste energy on shit you can't control
9. St…
Signed Habtamu
27 Feb 2022, 21:06 UTC295 viewsread 10 August 2026 One day it just clicks... you realize what's important and what isn't.
You learn to care less about what other people think of you and more about what you think of yourself. You realize how far you've come and you remember when you thought things were such a mess that you would never recover. And you SMILE. You smile because you are truly proud of yourself and the person you've fought to become.
https://t.me/ethios…
Signed Habtamu
24 Nov 2021, 18:42 UTC298 viewsread 10 August 2026 ብሩህ እሳቤ ለብሩህ ነገ!
https://t.me/burhan9
Signed Habtamu
18 May 2021, 20:19 UTC311 viewsread 10 August 2026 😱😱😱ቅን-ቅን😱😱😱
አባቴ ሲመክረኝ ልጄ ቅን ሁን አለኝ
እማም ተደርባ እንደዚያው አለችኝ
የኔም የነሱ መች ላሳፍራቸው
የሁለቱም ምክር እንዳይቀርባቸው
አዋሃድኩኝና ቅን-ቅን ሆንኩላቸው ።
@ethiosankofa
Signed Habtamu
18 May 2021, 20:19 UTC339 viewsread 10 August 2026 ❤️❤️ጥርጣሬና ፍቅር❤️❤️
አትወደኝም ብሎ ልቤ ጠረጠረ
ልቤ ሲጠረጥር ፍቅሬ ተጓደለ
ፍቅሬ ሲጎልበት የሷም ልብ ሻከረ
የሻከረ ልቧም እኔን አላምን አለ
በሂደት በጊዜ ቀስ ቀስ እያለ
እንደጠረጠርኩት ያው ፍቅሯም ጎደለ
ያ ከንቱ የኔም ልብ እንዲህ ሲል ፎከረ
ቀድሞ አውቄዋለሁ ያልኩት እውነት ሆነ
ገና ከጅምሩ ልቧ እንደሻከረ
እያለ ፎከረ እያለ ሸለለ
አሱ ያልገባው እውነት ከሱ የተሰወረ
ቀድሞ ጥፋተኛ እሱ እንደነበረ
የሱን ተከትሎ የሷ እንደቀጠለ፡፡
@ethiosankofa
@ethiosankofa
@ethiosankofa
Signed Habtamu
18 May 2021, 20:19 UTC395 viewsread 10 August 2026 ፈጣሪ ለምድር ብርሃንን ሲፈጥር
ጨረቃን ለምሽት ፀሃይን ለቀን
የሰውን መገረም በአንክሮ አስተውሎ
ከዚህም የሚበልጥ ተአምር መኖሩን ለማሳየት ብሎ
ያው አንቺን ፈጠረሽ ከሁሉም አግንኖ
ውበትሽ ድንቅ ነው ምን ይወጣለታል
ያላንዳች ተቃውሞ ሁሉንም አስማምቷል
የሚያበራው አይንሽ ተዓምር ታድሏል
ከላይ ላይ ተሻግሮ ውስጥ ይመረምራል
ፀሃይዋ ባትወጣ ጨረቃም ለምኔ
ሁሉን የሚያሳየኝ አይንሽ ይኑር ለኔ
በረዶ መሳዩ ድርድሩ ጥርስሽ
እንዲሁም ያፈዛል እንኳንስ ስቀሽ
ቀጥ ብሎ የቆመው ሰልካካ አፍንጫሽ
ዟ ብሎ የተኛው ለስላሳው ፀጉርሽ
እንዴት ቢወድሽ ነው እንዲህ ያሷበሽ
የወንዱስ ምንም ነው ሴቱን አፈዘዝሽ
ተዓምሩን ሊያሳይ ጉድ ሊያስብልብሽ
በዚህ ቁንጅና ላይ ፀባይም ሰጥቶሽ
የኔ…
Signed Habtamu
15 May 2021, 20:10 UTC330 viewsread 10 August 2026 ✍ ደስታ ትፈልጋላችሁ
✏️ ብዙ ሰዎች ደስተኛ መሆን እንፈልጋለን ግን አልቻልንም ሲሉ ይሰማሉ!! ደስታ ለጥቂቶች ብቻ የሚገለጥ ሚስጥር አይደለም፡፡ እንግዲህ ደስተኛ መሆን አቃተን አልቻልንም የምትሉ የተወሰኑ ደስተኛ የሚያረጓችሁ ነገሮች ልንገራችሁ እነዚህን በትክክል ከተገበራችሁ ደስተኛ ትሆናላችሁ!!!
1⃣ 'ኛ' ማመስገን እኔ በህይወቴ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ግን ሁሉም ስለተሟላልኝ ወይም ሁሉንም ስላገኘሁ አይደለም!!የምፈልጋቸው ግን ያላገኘዋቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ ግን ደስተኛ እንዳልሆን አልከለከሉኝም፡፡ ምክንያቱም ከሌለኝ ነገር ይልቅ ያለኝን ስለምመለከት፡፡ አንተም በሌለህ ነገር ያለህ ነገር ይበልጣልና አያቶቻችን ከነገ ዶሮ የዛሬ እንቁላል ይበልጣል…
Signed Habtamu
15 May 2021, 20:08 UTC249 viewsread 10 August 2026 🗞አካልየ ና ገብርየ ማን ናቸው?!🗞
ይዋጓል እንደገብርየ፣
ይማሯል እንደ አካልየ፣
ሸዋ ከተስፋ ገብረስላሴ እስከ እስከ ህሩይ ወልደስላሴ፣ከከበደሚካኤል ሚካኤል እስከ ዳኛቸው ወርቁ እና
ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ በጥበብ ማህደርነቱም ደምቆ ይታያል፡፡
መምህር አካለወልድ ሰርፀወልድ!!!
.በ 1824 ሸዋ ተጉለት ተወለዱ፡፡ አቡጊዳን በአካባቢያቸው፣ቡሉያት ና ሀዲሳት ከጎንደር ሊቃውንት ተምረዋል ፡፡አካለወልድ ፈላስፋ ናቸው፡፡ንግግር አዋቂም ናቸው፡፡
በጎንደር በ 19 ኛው ክፍለዘመን የሚከበሩ መምህርም ነበሩ፡፡
ካሳ ሃይሉ ከቋራ ጀምረው ደብረታቦር ጎጃምን በእጃቸው እስከ 1847 ዓም አስገቡ፡፡በወቅቱ ቴወድሮስን ጎንደሮች እና ጎጃሞች አልወደዷቸውም፡፡
…
Signed Habtamu
8 Apr 2021, 20:46 UTC229 viewsread 10 August 2026 እንደምነሽ?
========
እንደምነው ዓይንሽ ጥቁር እና ነጩ
እንደጊዜው መንግስት ሕዝብ አበጣባጩ.
እንደምነው ጡትሽ እንደጦር የቆመው
እንደጊዜው ምርጫ የተጭበረበረው.
እንደምነው ጭንሽ የሚወዛወዘው
እንደ ህዝብ ንብረት የሚበዘበዘው።
እባክሽ ንገሪኝ ወገብሽ እንዴት ነው?
እንደ ጋዜጠኛ ሲታሰር የኖረው። .
እኔ እንዳለሁ አለሁ እቴ ምን ጎሎብኝ
የማይመጣ ባቡር ቆሜ እየጠበኩኝ
ኔትወርክ ለሌለው ስልክ ካርድ እየገበርኩኝ
ለማይመጣ ውሃ ቧንቧ እየተከልኩኝ
ለማይበራ መብራት ደሞዝ እየላኩኝ
ለሎተሪው ቤቴ እያጠራቀምኩኝ አለሁ እንደተውሽኝ ። .
እየውልሽ እቴ የዘንድሮ ኑሮ ሆነልሽ አስፈሪ
ድንገት ተገጣጥመው ግንቦት ስላሴና የሆነ አሸባሪ
"መብራት የለም" ያለው እየተፈረጀ…
Signed Habtamu
12 Jan 2021, 17:41 UTC293 viewsread 10 August 2026 Sorrow prepares you for
Joy. 🦋
It violently sweeps everything out of your house,
So that new joy can find space to enter.
It shakes the yellow leaves from the bough of your heart,
So that fresh, green leaves can grow in their place.
It pulls up the rotten roots,
So that new roots hidden beneath
have room to grow.
Whatever sorrow shakes from your heart, far better things will take their place.
#thought
Signed Habtamu
31 Oct 2020, 20:07 UTC323 viewsread 10 August 2026 ዕይታ(view)
" አቧራ የጠገበን ምንጣፍ በዱላ የምትመታው አቧራውን ለማራገፍ እንጂ ምንጣፉን ለመጉዳት አይደለም ። የሰውን ድክመት የምትነግረውም ስህተቱን እንዲያርም እንጂ ሰውዬም በስራው ተስፋ እንዲቆርጥ አይደለም ። "
/ ቀደምት የአገራችን አበው ፍልስፍና /
Signed Habtamu
30 Oct 2020, 22:00 UTC319 viewsread 10 August 2026 ጥቂት ነው ምኞቴ
እኔ በሕይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ከድፍና ከግፍ
የጠዳ
በረንዳ
እዛ ላይ መቆየት
ከሚደምን ዛፍ ላይ፥
ቅጠል ሲዘንብ ማየት፤
እኔ በሕይወቴ
ጢኖ ነው ምኞቴ
ለከርስ ጤፍ እንጀራ
ለነፍስ ባልንጀራ
ድክመቴን ስናዘዝ ተግቶ ሚያዳምጠኝ
በደሌን መዝኖ ቀኖና ማይሰጠኝ፤
እኔ በሕይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ሊሞላ የቃጣው፥
ደርበብ ያለ ኑሮ
በስዊዝ ቤተ ንዋይ፥
ሶስት መቶ ሺ ዩሮ
ደሞ ከተቻለ፥
ቆንጆ ሚስት ወይዘሮ
እግዜርና ሰይጣን፥
ተጋግዘው የሳሏት
ቢቻል ትንሽ ቪላ፥
አስር ክፍሎች ያሏት፤
ግና ምኞቴ ሆይ
እንዲያው ለመሆኑ
ጥቂት ብሎ ነገር፤
ስንት ነው መጠኑ።
➮ ከበእውቀቱ ስዩም
━━━━━━✦✗✦━━━━…
Signed Habtamu
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @yesatedarechewata. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.