1 Aug 2026, 11:01 UTC351 views3 reactionsread 7 August 2026 🌧 ከፈተና (በላእ) ጀርባ ያለው ብሩህ ተስፋ...
«ያማረችና የተረጋጋች ሕይወት፣ ሰላሟን ከሚያደፈርስ አንዳች መከራ (ፈተና) መቼም ቢሆን አትጠራም።
አንድ አማኝ (ሙእሚን) በዚህ መከራ የሚፈተነው እንዲሁ በከንቱ አይደለም፤ ይልቁንም ከኃጢአቱ ጠርቶ እንዲነፃ፣ እንዲሁም ሳያውቀው የተዘፈቀባቸውን ጸጋዎች አስተውሎ ከዝንጉነት እንዲነቃ ነው።
በዚህም ፈተና አማካኝነት፦
✨ አቋሙ ይበልጥ ይጠነክራል
✨ ነፍሱ ልዕልናን ትጎናጸፋለች
✨ የአኺራ ደረጃው ከፍ ይላል
✨ ስህተቱ ይታለፍለታል አሊያም ወንጀሉ ሙሉ በሙሉ ይሰረዝለታል።»
🌿@lafto_qirat
❤3
Signed طالب العلم
31 Jul 2026, 18:08 UTC200 viewsread 7 August 2026 ✨ ነፍስን መተሳሰብ ...
📜 ማሊክ ኢብኑ ዲናር (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
«አላህ ያን ባሪያ ይዘንለት ነፍሱን፦ "የእንዲህ አይነት ጥፋት ባለቤት አይደለሽምን? የእንዲህ አይነቱንስ የሰራሽ አንቺ አይደለሽምን?" በማለት ለወቀሳት ከዚያም ልጓም አጥልቆ ለገራት በመቀጠልም ታላቁን የአላህ መጽሐፍ አጥብቃ እንድትይዝ አድርጎ (ቁርኣኑ) መሪ ለሆነላት።»
📚 (ኢዕቲላል አል-ቁሉብ፣ 28)
🌿@lafto_qirat
Signed طالب العلم
31 Jul 2026, 05:13 UTC330 views2 reactionsread 7 August 2026 ✨ ሙስሊም ወንድሜ ሆይ! ይህንን ሐዲሥ በተግባር ለማዋል እንትጋ!
📜 አውስ ኢብኑ አውስ (ረዲየላሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት፤ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ይላሉ፦
«የጁሙዓ ቀን ገላውን በደንብ የታጠበ፣ በጊዜ ወደ መስጂድ የሄደ፣ ሳይሳፈር በእግሩ የተጓዘ፣ ከኢማሙ ተጠግቶ የተቀመጠ፣ እንዲሁም በፀጥታ ያዳመጠና ከማይረባ ተግባር የተቆጠበ ሰው፤ በሚያራምደው እያንዳንዱ እርምጃ የአንድ አመት የፆም እና የሌሊት ሶላት (ቂያም) ምንዳ ይጻፍለታል።»
📚 (አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚ እና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል)
📌 የጁሙዓ ሱናዎች ዝርዝር፦
✅ ትጥበት ማድረግ
✅ በጊዜ መገኘት
✅ በእግር መጓዝ
✅ ከኢማሙ መጠጋት
✅ በፀጥታ ማዳመጥ (አለመዘናጋት)
🌿@l…
❤2
Signed طالب العلم
30 Jul 2026, 11:46 UTC187 views2 reactionsread 7 August 2026 ከተውሒድ ጤናማነት ጋር የሚስተካከል ምንም ነገር የለም!
📜 ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
«ወደ አላህ ከተውሒድ የበለጠ የተወደደ ምንም ነገር የለም ወደ እርሱም ከሽርክ የበለጠ የተጠላም ምንም ነገር የለም።
ተውሒድ ትክክል ሆኖ ወንጀል መብዛቱ ተውሒድ ተበላሽቶ ወንጀል ከማነሱ የተሻለ ነው።»
📚 (አል-ኢስቲቃማህ፣ ገጽ 364)
🌿@lafto_qirat
👍2
Signed طالب العلم
28 Jul 2026, 19:23 UTC249 views3 reactionsread 7 August 2026 ⚠️ ወላሂ ይህ አባባል እጅግ የሚያስፈራ ነው! ⚠️
«حقوق العباد لا تسقط بطول قيام، ولا حسن صيام، ولا بألف ختمة قرآن..»
"የሰዎች ሀቅ በረጅም የለሊት ሶላት፣ ባማረ ፆም፣ ወይም ቁርኣንን ሺህ ጊዜ በማክተም አይሰረዝም..."
«حقوق العباد لا تسقط إلا بعفو أصحابها.»
"የሰዎች ሀቅ ሊሰረዝ የሚችለው ባለሀቆቹ (የበደልናቸው ሰዎች) አፉ ሲሉን (ይቅር ሲሉን) ብቻ ነው።"
«"وعند الله تجتمع الخصوم"»
"አላህ ፊትም ተከራካሪዎች (ባለሀቅ እና ባለዕዳዎች) ይሰበሰባሉ!
💡 አጭር ማስታወሻ፡
በአላህ ሀቅ ላይ ያጠፋነውን (ለምሳሌ ሶላት ማሳለፍ፣ ፆም መተው) አላህ አዛኝ ስለሆነ በተውበት ሊ…
❤2👍1
Signed طالب العلم
28 Jul 2026, 11:02 UTC252 views5 reactionsread 7 August 2026 ከማህበራዊ ሚዲያ እብደትና ሱስ ስታገግም... በርካቶች ቀድመውህ የራቀ ጉዞ እንደተጓዙ ታያለህ።
አንደኛው ቁርዓን ሲሃፍዝ፣ ሌላው መሠረታዊ የእስልምና እውቀቶችንና ልዩ ልዩ ጥበቦችን ሲቀስም አንተ ግን ስልክህ ላይ እንደተደፋህ ጊዜህ በከንቱ ያልፋል፤ ዕድሜህ ሲነጉድ እንኳ አይሰማህም። በአንተና በመቃብርህ መካከል ግን የቀረችው አንዲት እርምጃ ብቻ ልትሆን ትችላለች!
🌿@lafto_qirat
💯3❤1🔥1
Signed طالب العلم
27 Jul 2026, 19:40 UTC246 views1 reactionsread 7 August 2026 🔘በመታገስና በመስገድ
ጭንቀትን አስወግድ!
▪️ የችግሮች ሁሉ መፍትሄ -በአላህ ፈቃድ- ትዕግስትና ሰላት ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፥
( وَٱسۡتَعِینُوا۟ بِٱلصَّبۡرِ وَٱلصَّلَوٰةِۚ )
سُورَةُ البَقَرَةِ: ٤٥ >
(በመታገስና ሰላት በመስገድ የአላህን እርዳታ ፈልጉ) አልበቀረህ: 45
▪️ የአላህ እርዳታ ሁሌም ከትክክለኛ አማኞች ቅርብ ነው። የትክክለኛ አማኝ አንዱ መገለጫ ደግሞ ሰላት ነው።
▪️ ነቢዩ ሙሐመድም ﷺ ችግር ሲገጥማቸውና የሆነ ነገር ሲያሳስባቸው ፈጥነው ሰላት ይሰግዱ ነበር (አቡ ዳውድ: 1319)
▪️ بالصبر والصلاة تتيسر الحياة.
በትዕግስትና በሰላት ሕይወት ይቀላል።
ያለ…
👍1
Signed طالب العلم
26 Jul 2026, 17:33 UTC241 views2 reactionsread 7 August 2026 🔥 በጓደኞችህ ብዛት አትደሰት... 🔥
አንድ ጥበበኛ እንዲህ አለ፡
«الإِخْوَانُ بِمَنْزِلَةِ النَّارِ، قَلِيلُهَا مَتَاعٌ، وَكَثِيرُهَا بَوَارٌ، فَلا تُسَرَّنَّ بِكَثْرَةِ الإِخْوَانِ إِذَا لَمْ يَكُونُوا أَخْيَارًا»
"ጓደኞች ልክ እንደ እሳት ናቸው ጥቂቱ ይጠቅማል (ያሞቃል) ብዙው ግን ያጠፋል (ያቃጥላል)። ስለዚህ ደጎችና መልካሞች እስካልሆኑ ድረስ በጓደኞችህ ብዛት ደስ አይበልህ።"
💡 መልእክት፡
በህይወታችን ውስጥ ዋናው ቁምነገር የጓደኞቻችን ብዛት ሳይሆን ጥራትና መልካምነት ነው።
📚 ምንጭ፡
ኢማም ኢብኑ አብዱልበር (ረሂመሁላህ)
(በህጀቱል መጃሊስ - 1/722)
…
❤2
Signed طالب العلم
26 Jul 2026, 10:21 UTC300 views2 reactionsread 7 August 2026 ⚖️ «በአላህ ዘንድ ተከራካሪዎች ይገናኛሉ...»
ይህ ልብን የሚያናውጥ፣ እንዲሁም ጊዜው ሳያልፍ የሰዎችን መብት እንድንመልስና ከበደል እንድንፀዳ የሚያስጠነቅቅ ታላቅ ማስታወሻ ነው!
በቂያማ ቀን የሰው ልጅ የሚሸከመው ከባዱ ጭነት በእርሱና በፈጣሪው መካከል ያለ ወንጀል ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም፦
⚠️ ያልከፈለው የሰው መብት ወይም
⚠️ የሰውን ልብ ሰብሮ ይቅርታ ያልጠየቀበት አንዲት ቃል ልትሆን ትችላለች!
አላህ ሆይ! በቂያማ ቀን የሰዎች መብትና ዕዳ በላያችን ላይ ሳይኖር፣ በንፁህ ማንነት ከሚያገኙህ ባሮችህ አድርገን!
🌿@lafto_qirat
💔2
Signed طالب العلم
24 Jul 2026, 13:54 UTC563 views1 reactionsread 7 August 2026 «አንዳንድ ዑለማዎች እንዲህ ብለዋል፦ አንድ ሰው ኻቲማው(የሂወቱ መጨረሻ) እንዲበላሽ ከሚያደርጉ ታላላቅ ምክንያቶች አራት ናቸው፦
1.ለሰላት ግድየለሽነት ማሳየት።
2.የሚያሰክር መጠጥ (ኸምር) መጠጣት።
3.ወላጆችን መበደልና አለመታዘዝ።
4.ሙስሊሞችን አዛ ማድረግ።»
— አስ-ሱዩጢ رحمه الله
🌿@lafto_qirat
❤1
Signed طالب العلم
24 Jul 2026, 09:26 UTC367 views1 reactionsread 7 August 2026 ከአላህ በስተቀር ሁሉም ምትክ አለው!
የሰው ልጅ ላጣቸው ነገሮች ሁሉ ይብዛም ይነስ ምትክ ( አማራጭ ) ሊያገኝ ይችላል፤ አላህን ያጣ ( ከርሱ የራቀ፣ እሱን ያስቆጣ ) ሰው ግን ምንም ዓይነት ምትክና አማራጭ መቼም ማግኘት አይችልም።
ስለዚህ መቼም ቢሆን፣ ለማንም ለምንም ብለህ አላህን እንዳታጣ ተጠንቀቅ!
ዛዱል መዓድ
🌿@lafto_qirat
❤1
Signed طالب العلم
23 Jul 2026, 19:52 UTC342 views2 reactionsread 7 August 2026 ✨ የተዘጉ በሮችን የሚከፍተው ቁልፍ...
አንዳንዴ የሰው ልጅ ሁሉንም የመፍትሔ በሮች አንኳኩቶ ምንም አይነት ለውጥ ላያገኝ ይችላል። ነገር ግን በቁርኣን ውስጥ ከተጠቀሱት መፍትሔን ከሚያመጡና መለኮታዊ የአላህን ራህመት ከሚያስገኙ ታላላቅ ምክንያቶች መካከል አንዱንና ዋነኛውን ይዘነጋል
እርሱም፡- በብዛት አላህን ምህረት መጠየቅ (ኢስቲግፋር ማብዛት) ነው!
ኢስቲግፋር (ሁሌም "አስተግፊሩላህ" ማለት) የጭንቀት መውጫና የችግሮች ሁሉ መፍቻ ነው! 🤍
🌿@lafto_qirat
❤2
Signed طالب العلم
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @lafto_qirat. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.