4 Jan 2024, 22:45 UTC≈2,050 views3 reactionsread 9 August 2026 ⛸⛸ #የነፍሴ_ደዋሪ ⛸⛸
ምራዊ ሳቃችን፥ ምታስፈነድቀን፤
ህያው ተስፋችን፥ የምትናፍቀን፤
በደሳሳ ጎጆ፥ ሙላተ ማድጋ፤
በነጠፈ ተስፋ፥ ብርቱ ባለጠጋ፤
የሻገተውን፥ ፈጽሞ አለምላሚ፤
የተቆረጠውን፥ እንደአዲስ ገጣሚ፤
ከጥንት ጥንትን መስራች፥
ከዘላለም ዘላለምን ሰሪ፤
የህይወትን ትርጉም፥ የህይወትን ፍቺ፥
ብቻውን ቀማሪ፤
የሰማይ ሰራዊት እና የምድር አራዊት ደዋሪ፤
እውነተኛው ፈገግታችን፤
ሀዘን የለሹ ደስታችን፤
ምራዊ ሳቃችን፥ ምታስፈነድቀን፤
ህያው ተስፋችን፥ የምትናፍቀን፤
መቼ ነው መምጣትህ?
መቼ ነው ምጻትህ?
መችም እንደጥንቱ በረት አትወርድም፤
ዳግም ለእኛው፥ በእኛው አትዋረድም፤
ሰማይ እያወጋህ፥
ምድርም ሸሽጋህ፥
ጠባብ ደረት፤ አጭር ቁምጣ አያመጣህ…
❤3
5 Sept 2023, 20:28 UTC929 views2 reactionsread 9 August 2026 🙏🙏 #ስለበዛ 🙏🙏
መልካሙን
👉 ዕድል እንምረጥ
ከእግሮቹ ስር
👉 እንቀመጥ
ፀጋው ለእኛ
👉 #ስለበዛ
#አንባክን
👉 እዚም እዚያ።
የሚያስፈልገው
ማይወሰድ
👉 #ጥቂት
👉 #አንድ_ነገር
ከአፉ ቃል እየሰሙ
ከኢየሱስ ጋር
👉 #አብሮ_ውሎ
👉 #አብሮ_ማደር።
🧣🧣 @gtmmbetsega 🧣🧣
Let us be together for Grace
🧣🧣 @gtmmbetsega 🧣🧣
❤1🥰1
25 Jun 2023, 05:50 UTC358 views1 reactionsread 9 August 2026 Photo
✅✅ #ባይሆንማ_ኖሮ ✅✅
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ ይህ #ባይሆንማ_ኖሮ እነግራችሁ ነበር፤ የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው። ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋር እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ።
ዮሐንስ 14 (አዲሱ መ.ት) 2-3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
መልካሙ እረኛ ኢየሱስ ፤ ክርስቶስ ና የወይን ግንዱ የሆነው ያልሆነውን አልያም የማያደርገውን የማይናገር እርሱ በአባቴ ቤት ያለውን ብዙ መኖሪያን ለእናንተ ላዘጋጅላችሁ እሄዳለሁ ብሎን ከመሄዱ ቀድሞ ባይሆን ኖሮ ምን አስወራኝ፤ የሚሆን ነውና እመኑኝ። ብሎናል።
ለምን?
ዳግም ከእርሱ ጋር ሊያኖረን በ…
❤1
24 Jun 2023, 21:00 UTC225 viewsread 9 August 2026 Forwarded from @elgraceministryPhoto
🥇✈️ #አንድ_ቀን_እንደቀረው_ኑር ✈️🥇
"ምድር ላይ እያንዳንዱን ቀን እንደ መጨረሻ ቀንህ አድርገህ ኑር ፤ አንድ ቀን ትክክል ትሆናለህ"
ቲ.ቢ .ጆሽዋ
“ዲያብሎስ #ጥቂት_ዘመን #እንዳለው #አውቆ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።”
— ራእይ 12፥12
ጊዜውን መያዝ መሄዱንም ማቆም ባይቻልም ጊዜውን አልያም ዘመኑን ግን አንድ ቀን እንዳለው ሰው መዋጀት ይቻላል።
አንድ ቀን ዛሬ፤ ዛሬም አሁን፤ አሁን ደግሞ አሁኑኑ ነው።
በቀረው ዘመናችን ቀን ሆነ ሌታችን
ኢየሱስ ይሁን ኑሮና ወጋችን።
@gtmmbetsega @elgraceministry
@Elgracebot @surtsega
@surafeltsegamets
5 May 2023, 20:42 UTC969 views1 reactionsread 9 August 2026 🎚🎙 #በአጭሩ🎙🎚
እየኖሩ መብራት እየዘሩ ማፍራት
በጨውነት መፍካት
በመበስበስ መብዛት
ደከመ ሲሉት እልፎቹን ማበርታት
ስለወንጌል ሲሉ የዕሾህ አክሊል መድፋት
ከእውነት ጋር ወግኖ በዚህ አለም መገፋት
ከዉሃም ከመንፈስ መወለድ
የራስን ባዶ አድርጎ በሰራው መጓደድ
እርሱ ኢየሱስ ነው
እርሱ ክርስቶስ ነው
እርሱ ጌታና አምላክ ነው
ብሎ በልብ አምኖ በአፍ መመስከር
ቆርጦ መከተል እንደወታደር፤
በእግዚአብሔር ፍቅር፤
በድንቅ ስጦታው ከቶ አለማፈር።
ነው ክርስትና
በበጉ ደም ላይ ታትሞ የጸና።
________________________
join and share (ውጥን ሸራዬን)
@gtmmbetsega @gtmmbetsega
@gtmmbetsega @gtmmbetsega
❤1
16 Apr 2023, 03:58 UTC≈2,200 views2 reactionsread 9 August 2026 😭😭#ለምን_ዝም_አለ? 😭😭
ለመታረድ እየሄደ
ለመሸለት እንደሚሔድ ዝም ያለው
መታረዱ ጠፍቶት ሳይሆን
እኔን እና አንተን
እኔን እና አንቺን አስቦ ነው።
ለካ
ፍቅር እንደሱ ነው።
━━━━⊱✿⊰━━━━━
😘😘 @gtmmbetsega 😘😘
😘😘 @gtmmbetsega 😘😘
😘😘 @gtmmbetsega 😘😘
❤2
18 Feb 2023, 05:21 UTC259 views2 reactionsread 9 August 2026 https://t.me/+0VG8PkcT3ZYwMWNk
👍2
18 Jan 2023, 18:13 UTC≈1,620 views1 reactionsread 9 August 2026 Photo
በአለታላቅ ዙፋን ስፍራ እስክታጣ
ተወለደኃል ኢየሱስ በታላቅ ዝቅታ።
ለታመምነው መድህን ለጠፋን መገኛ
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ
ሰው ሆንክ ስለእኛ።
አቤት ትህትና አቤት የዋህነት
ንጉስ ቤት እያለ ማረፍ ከወደበረት
አቤት ትህትና አቤት የዋህነት
በደፈረሰው ዮርዳኖስ መጠመቅ።
ሳትበድል መጠመቅህ
ለዮሐንስ ዝቅ ማለትህ
በእርግብ አምሳል
መንፈስ ቅዱስ ወረዶብህ
አብ ከላይ ልጄ ብሎ ሲመካብህ
ምንም ሳትል ስትሳ
ለሰው ስርዓት ስትገዛ
አቤት የዋህነት አቤት ትህትና
አልቆ መላቅ አስተምረሃልና።
እኛን ትወክል ዘንዳ ሁሉን የሆንህ
ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ የተፈተንህ
መካከለኛችን የአብ ፍጹም ደስታ
ጽድቃችን የሆንህ ንጉስ የለበስንህ ጌታ
እስከ ሞት ታዘህ እኛን…
❤1
Signed ሱራፌል ወርቁ ጸጋ
7 Jan 2023, 19:36 UTC263 views0 reactionsread 9 August 2026 🤔 #ኧረ_ከግርግም_እንውጣ 🤔
" በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው። "
ሉቃ 2 ፥ 6-7
✅ በእርግጥ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት በግርግም ተጠቅልሎ ተቀምጧል ይሁን እንጂ በግርግም አልያም በበረት ውስጥ አልተወለደም።
አልተጠቀሰም ተብሎ መታለፍ ሲችል ያልተጻፈ ለምን እንዘባርቃለን? በተጨማሪም ማብራርያ ቢደገፍም እንኳን በረት እንዳልሆነ ግን በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
✅ ሰባሰገሉ (የሩቅ ምስራቅ ጠቢባን) ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸውን መስዋት (ከርቤ፣ ወር…
Signed ሱራፌል ወርቁ ጸጋ
23 Dec 2022, 18:14 UTC333 views1 reactionsread 9 August 2026 #ለገዳዩ_ሟች #ረቡኒ
የራስ ቅል ከምለው ቀራንዮ ጎልጎታ
ራሴን ፈትቼ አንተን የሰቀልኩህ ዕለታ
ከአንተ የተካለልኩበት ድንበሬ ፈረሰ
የተበተበኝ መጋረጃዬ ላይሽር ተቀደደ።
ተጠማሁ ስትለኝ ለጥምህ ማብረጃ
ሆምጣጤ ለህመምህ የሰጠሁህ ዕለታ
ቤተ-መቅደስ ያልኩት ግንብ እየፈረሰ
ለአንተ ማደሪያነት ልቤ ተቀደሰ።
በጥፊ ስመታህ በተመታህልኝ
እጅህን ለችንካር በዘረጋህልኝ
ጎንህን በጦር በተወጋህልኝ ''''''''' "አፍታ"
ነውር አልባ ደምህን ያፈሰስኩት ዕለታ
ትግስት ፍቅርህን በሚገልጥ ዝምታ
የማትሞተው ስትሞት በድኩም ስትረታ
ዘላለም ላይሻር ታሪኬ ተፃፈ
ከሞት ፍርሃት ቀን…
❤1
Signed ሱራፌል ወርቁ ጸጋ
12 Dec 2022, 05:48 UTC≈2,610 views1 reactionsread 9 August 2026 ━━━━⊱ #አንድ_ርዕሴ ⊰━━━━━
ትናንት
አንተን ብዬ ጽፌአለሁኝ ግጥም
መሸ ነጋ ብዬ
ዛሬ
ርዕስ አልለውጥም
አንተው ነህ ግጥሜ
አንተው ነህ ዜማዬ
አንተን ነው የምቀኘው
የማልጨርስህን ልቀኝ ምጀምረው።
አንተው ነህ ያው አንተ ሁሉንም ያበጀ
ዘላለምን አሸምግሎ በዘላለም ያላረጀ።
የፍጥረታት ሁሉ ዘዋሪ
ጅማሬ የሌለው ጀማሪ
አንተው ነህ ያው አንተ
ከእቅፍህ የወጣው ልጅህ የተረከህ
ለዘመንህ ቁጥር አልባ
አመታቶችህ የማያልቁ
ታላቅ የለሽ አንድ ትልቁ።
አላየሁም ፊትህ ቀርቦ
ልጅህን ብሎ ያልጸደቀ
ተማምኖብህ ተመርኩዞህ
በአጥፊው ወጥመድ የወደቀ።
━━━━⊱✿⊰━━━━━
👉👉 @gtmmbetsega 👈👈
👉👉 @…
👍1
Signed ሱራፌል ወርቁ ጸጋ
Channel photo updated
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @gtmmbetsega. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.