29 Jan 2026, 13:45 UTC573 views2 reactionsread 9 August 2026 #ኤሳውነት/ የኤሳውን መንገድ መከተል
“ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው”
ኤሳውን እንደምሳሌ ከጸጋ የጎደለ ሰው ማንነት ያሳእናል።ይህም ስለጊዜያዊ ደስታ እና እርካታ መንፈሳዊ ርስቱን እና ከጌታ ጋር ያለውን ህብረት የለወጠን ሰው ይወክላል። ብኩርና ዋጋ ያለውን መንፈሳዊ ውርስ ወይም ርስት ይወክላል።
👉የእግዚአብሄርን ነገር እንደ ተራ ወይም እንደማይጠቅም መቁጠር፣ ለመንፈሳዊ ነገር ፍላጎት ያጣ ህይወት
👉የመንፈስ ፍሬ እና መንፈሳዊ ስነምግባር ልምምድ የጎደለው ህይወት
👉ውስጣዊ የእምነት መገለጫዎች ማለትም ጽድቅ፣ ሰላም እና ሃሴት የጎደለው ህይወት መኖር
👉በፍቅር፣ በመልካም ስራ እና በመንፈሳዊ እድገት ፍሬ አልባ ህይወት
👉ለጸሎት …
🔥2
28 Jan 2026, 08:42 UTC≈1,070 views2 reactionsread 9 August 2026 የእምነት ምንጮች
(ሰማያዊ እና ምድራዊ እውቀት)
ምንባብ፡ 1 ቆሮ 2፡10
ስለ ህይወታችን መረጃ የምንቀበልባቸው 2 የእውቀት ምንጮች አሉ፡ ሰምያዊ እውቀት እና ምድራዊ እውቀት ይባላሉ።
የሰማያዊ እውቀት እን አየምድራዊ እውቀት ንጽጽር፡
የሰማያዊ እውቀት ምንጩ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን የምድራዊ እውቀት ምንጩ ማየት፣ መማር እና መስራት ወይም መለማመድ ነው።
መንፈስ ቅዱስ ሰማያዊ እውቀትን ለልባችን በቃሉ በጸሎት እና ከእርሱ ጋ ባለን ህብረት ውስጥ ይገልጥልናል።
1ኛ ቆሮንቶስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ነገር ግን፦ ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንደተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።¹⁰ መንፈስም የእግዚአብ…
👍2
27 Jan 2026, 08:33 UTC869 viewsread 9 August 2026 📍አብ የጸጋ ምንጭ ነው፣ ወልድ ደግሞ የጸጋ መገለጥ ነው ፣ መንፈስ ቅዱስ የጸጋ አከፋፋይ እና በህይወታችን አስጀማሪ ነው።ያለ መንፈስ ቅዱስ ጸጋን መለማመድ ሆነ መጠቀም አንችልም።
27 Jan 2026, 08:20 UTC113 views1 reactionsread 9 August 2026 #እድገት
"እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።"
1ጢሞ 4:7
መንፈሳዊ እድገት የሚመጣው #በልምምድ ነው።
#'discipline'
📌መንፈሳዊ እድገታችን የሚመሠረተው ቃሉን ለማጥናት እና ለፀሎት ያለን ልምምድ ላይ ነው።
👍1
26 Jan 2026, 06:12 UTC≈1,160 views3 reactionsread 9 August 2026 📍
#GDD(Grace Deficiency Disease)
ይህ ከመንፈሳዊ በሽታዎች አነዱ ሲሆን
📌ምልክቶችም :የቅድስና ችግር ሴሰኝነት ለአለም መመቸት ስጋ ስጋ መሽተትይገኙበታል።ይህ በሽታ በመጨረሻ አማኙ ከሀጥያት ቀንበር በታች እንዲወድቅ ያደርገዋል።
📌ይህ በሽታ ተላላፊ እና በህብረት ውጥ ሊዛመት የሚችል ስለሆነ ምልክቶች ሲታይብዎ በአፋጣኝ ወደ ፀጋው ዙፋን ቀርበው ምህረትን እና ፀጋን እንዲለምኑ እናበረታታዎታለን።
ዕብራውያን 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥
¹⁶ ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለ…
👍3
26 Jan 2026, 06:06 UTC200 views1 reactionsread 9 August 2026 እድገት 3
"ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ።"
#የጌታ ስራ : መንፈሳዊ ልምምድ(ፀሎት፣ መፅሀፍ ቅዱስ ጥናት፣ ምስክርነት፣ ፅሞና፣ ህብረት፣ አምልኮ፣ አገልግሎት...
👉በየእለቱ የምናደርገው የጌታ ስራ በየእለቱ ህይወታችንን ይገነባል።
👍1
23 Jan 2026, 12:22 UTC462 views1 reactionsread 9 August 2026 #እድገት 2
"ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፥ ከሁሉ በሚያንስም የሚያምፅ በብዙ ደግሞ ዓመፀኛ ነው።"
ሉቃ 16:10
👉ትናንሽ ያልካቸው እርምጃዎች የትልቁ መግቢያ በሮች ናቸው።
👉እያንዳንዱ የመሠላሉ መወጣጫ በሰሪው እጅ ተመጥኖ ታስቦበት የተሰራ ነውና ንቀህ አትተወው።
learn how to pray effectively for 5 minute.
🔥1
22 Jan 2026, 08:13 UTC378 views3 reactionsread 9 August 2026 #እድገት 1
"ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።"
እብ 5:12
👉እድገት በራሱ የሚመጣ ሳይሆን የኛን የማያቋርጥ ትጋት የሚፈልግ ነው።
👉መንፈሳዊ እድገት የየእለት ርምጃ ውጤት ነው።
👍2🔥1
10 Jan 2026, 18:41 UTC587 views1 reactionsread 9 August 2026 "ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥"
ፊልጵ 3:13
ትላንትህ ነገህን አይወስንም።
#እንደ ጳውሎስ
ይህን አንድ ነገር አድርግ፦ዛሬ ወስነህ ነገህን ጀምር!!!
🔥1
9 Jan 2026, 19:06 UTC538 views1 reactionsread 9 August 2026 "አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።"
ገላ 3:28
መጠሪያህ አይገልፅህም
labels dont define you.
የተሰጠህን ስያሜ በስጋ የተሸከምከውን ማንነት ተውና እግዚአብሔር በክርስቶስ የሰጠህን ማንነት እንዲገልጥልህ ጠይቀው።
እኛ ከዘር ከፆታ ከስራ ሁኔታ ላለፈ ማንነት ተሰቶናል።
we are beyond the measures and the labels of this world!!!
👍1
8 Jan 2026, 20:10 UTC435 views1 reactionsread 9 August 2026 "እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ #ተፈጠርን።"
ኤፌ 2:10
በክርስቶስ ለልዩ አላማ ለ2ኛ ጊዜ #ተፈጥረሀል።
በክርስቶስ ሁሉ ነገርህ ተቀይሯል።
አስቀድሞ የታሰበልህን ኑር!!!
👍1
7 Jan 2026, 18:40 UTC552 views1 reactionsread 9 August 2026 " እነሆ፥ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ"
ኢሳ 49:16
እግዚአብሔር የማያይህ እና የተወህ ሲመስልህ ይህን አስታውስ።
you are #engraved in his palms!!!
በመዳፉ ቀርፆሀል።
🔥1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @ben_canaan. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.