14 Apr 2024, 19:13 UTC≈1,490 views9 reactionsread 6 August 2026 ልደቷ ነዉ ዛሬ
መንግስት ሰራተኛ ምክንያት ለእረፍቱ
የአርሶ አደሩ አራሾች
በረት ሚዉልበት አህያና ከብቱ
ልደቷ ነዉ ዛሬ
ፅድቅን ስለመስራት
አስፓልቱ በድንጋይ ሙሉ ሚዘጋበት
ንፉግ እጁን ለሰዉ የሚዘረጋበት
ልደቷ ነዉ ዛሬ
ኩፍስ መኮፈሱን
ማቅራራቱን ትቶ ባዶነቱን መርሻ
በልደት በምኗ
ዳስ ጥሎ ከደጇ ማደር ስለሚሻ
ይኸዉ ቀን ደረሰዉ ያለ አንዳች ድርድር
አጅቧት እየዋለ አጅቧት የሚያድር
ምክንያት ሆነችለት...
...ለምን... ይሄ ሁሉ ሆነላት አትሉም
ለምን...
ተስፋን ሰጪ አድማስ
ነገ የምታሳይ እንደ ፀሃይ ደምቃ
ዛሬ
የሴትነት ልኳ ልደቷ ነዉ በቃ
🎂🎂🎂🎂🎂🎂
✍️@ታገል ገጣሚው
tiktok.com/@tagelbanti
@afkarish
❤6👍3
Signed ታገል ነኝ ገጣሚዉ✍️
11 Apr 2024, 18:26 UTC≈1,260 views0 reactionsread 6 August 2026 Video
Video, posted without a caption
Signed ታገል ነኝ ገጣሚዉ✍️
21 Mar 2024, 19:38 UTC≈1,360 views5 reactionsread 6 August 2026 ስንት አለ ባገሩ
ተከዳሁ መከዳት ቆሳሰልኩኝ መቁሰል ፣
እያለች ስትነግረኝ ያዝኩና ማብሰልሰል ።
የታመመ ልቧን ፡
አስታምመዉ ብዬ በብልሃት ስገልጠዉ ፣
አስቦ አጥፊነቷ ይሁዳን በለጠዉ ።
ስንት አለ ባገሩ የተጎዳ መስሎ ፣
አቆሰሉኝ የሚል ዕልፍ ልብ አቁስሎ ።
✍️@ታገል ገጣሚው
tiktok.com/@tagelbanti
@afkarish
👍5
Signed ታገል ነኝ ገጣሚዉ✍️
19 Mar 2024, 18:01 UTC≈1,230 views2 reactionsread 6 August 2026 ልቤን አስገቢዉ
ባገር ሰፈሩ ሰዉ የማልፈራ
ጉረኛ ነበርኩ የወንዶች አዉራ
እንዳልፎከረ እንዳላቅራራ
ደንዳናዉ ልቤ ባንቺ ተገራ
እናልሽ እቴ
መላ እንደጠፋዉ እይንሽን ይዘሽ
የለሁበትም እያልሽ ከምትሽሽ
ደገፍ አድርጊኝ ልደገፍና
ያጎነበስኩት በክንድሽ ልቅና
፨፨፨፨፨
አንቺ ነሽና
በልቤ ሃገር ከእንስታቱ
ምትመላለሽ በየሰዓቱ
አንቺ ነሽና
ወንዱን እንደ ሴት ጉድ ያደረግሽዉ
በፍቅርሽ ወጥመድ ግዞት የጣልሽዉ
ለአንቺ ነዉና
ለእኔነቴ አዛዥ ለመዉደዴ አድባር
የገበርኩልሽ ልብ እንደገባር
///// ለአንቺ ነዉና //////
እንዳዉ በናትሽ
በእምዬ ማርያም ስለ ቁልቢዉ
ደጅ የጠናዉን ልቤ አስገቢዉ
.....ልግባ......
✍️@ታገል ገጣሚው
tiktok.com/@t…
❤1👍1
Signed ታገል ነኝ ገጣሚዉ✍️
19 Mar 2024, 17:36 UTC994 views1 reactionsread 6 August 2026 ተመልሻለሁ ቤተሰቦች በፅናት ስለጠበቃችሁኝ እያመሰገንኩ ፣ የተለመደዉን የፍቅር ግጥሞች የምለጥፍላችሁ ይሆናል ፣ እናንተም በምፀፋላችሁ ግጥሞች ያላችሁን አስተያየት ጀባ በሉኝ ፣እናንተም የምትፈልጉትን ሀሳብ አጋሩኝ በግጥም የማቀርብላችሁ ይሆናል እወዳችኋለሁ ❤🥰🙏
👍1
Signed ታገል ነኝ ገጣሚዉ✍️
Live stream finished (24 seconds)
Live stream started
17 Nov 2023, 15:40 UTC≈1,590 views13 reactionsread 6 August 2026 Photo
ተይዤልሻለሁ
ቱ
እኔ አልመለስም ፡
ተፍቼ እንደዉሻ ትፋቴን አልስም ።
ተዉኩህ ፣
አፈቀርኩህ እንጂ መች እኔ ወለድኩህ ።
እናት መሆን በቃኝ እዘኝ ለጀርባዬ ፣
እስከምን ነዉ ምዘልቅ አንተን አባብዬ ።
ቱ
ትፋብኝ ብመለስ ፡
የባይተዋር ኑሮን በል እስቲ ልመደዉ ፣
''ደህና ሁን' እያለች ወዴት ነዉ ምትሄደዉ ?
አለም ላይ ያላንቺ ፡
ሰዉ መሆን እንዳልችል ለብቻ በልተሽኝ ፣
ፈዉሴ ሆይ በእስራት ወዴት ነዉ ምትሸሽኝ ።
እንደቀሳዉስቱ ፡
እግዚያር ይፍታህ ብለሽ እስራቴን ፍቺ ፣
የተያዝኩት እኔ ምን አለብሽ አንቺ ።
ደህና አድርጊኝ እንጂ ፡
ቅበጠጥ ወደ ነዳሽ ፡
በሄድሽበት ሁሉ እከተልሻለሁ ፣
ይልቅ ነይ ትፊብኝ ተይዤልሻለሁ ።
✨✨✨✨✨✨
✍️ታገል በንቲ
👍11❤1👏1
Signed ታገል ነኝ ገጣሚዉ✍️
17 Nov 2023, 15:36 UTC≈1,300 viewsread 6 August 2026 Photo
ዉዴ ሆይ ፡ እዉነትን የሚሸሽ እንጂ የሚጋፈጠዉ ያለ አይምሰልሽ ፡ እንደ ዓለት የከበደን ነገር ፡ ማን ሊማረክለት ይችላል ?......ሊሸከመዉ የታደለ ጫንቃ ኢምንት ነዉ ። ሁሉም ቀላሉን ይመርጣል (ዉሸትን ) .....እዉነት ደግሞ ፡ በሰዎች አለመመረጡ በሽሽግ አያስቀረዉም ፡ ይልቁንም ጎልቶ ለመታየት ገሃዱን ይመርጣል ።
✨✨✨✨✨✨✨✨
❤❤❤❤❤❤❤❤
✍️ታገል ገጣሚው
tiktok.com/@tagelbanti
@afkarish
Signed ታገል ነኝ ገጣሚዉ✍️
17 Nov 2023, 15:27 UTC≈1,220 views3 reactionsread 6 August 2026 .....✍️አንዳንድ ሰዎች ይንቁኛል ፣ ለምን ናቁኝ ብዬ አጉል ፀብ ዉስጥ አልገባም፣ ነገር ግን ሁለት ነገሮችን እመለከታለሁ፣ አንድም ...የናቀኝ ሰዉ ከኔ የባሰ መንገድ ላይ ካለ ፣ እኔን መናቁ ትክክል እንደሆነ አስባለሁ ምክንያቱም ሰዉ የሚንቀዉ የቀናበትንና መድረስ ያልቻለዉን ቦታ ሌላ ሰዉ ሲደርስ ሲመለከት ነዉ ። ሁለተኛዉ ደሞ የናቀኝ ሰዉ ከኔ የተሻለ ከሆነ ፣ ትክክል እንደሆነ አስባለሁ፣ ምክንያቱም እሱ የደረሰበት መድረስ ያልቻልኩ ብኩን ስለሆንኩ በወኔዬ መላሸቅ መናደዱና እኔን መናቁ ያለ ነገር ነዉ፣ እናም ....እራሴን በቻልኩት ሀቅም እሱ ከደረሰበት ቦታ በተሻለ ለመድረስ እጥራለሁ እንጂ አልወቅሰዉም ፣ እንዲያ ነዉ ነገሩ ።
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
✍️ታገል…
👍3
Signed ታገል ነኝ ገጣሚዉ✍️
1 Nov 2023, 16:32 UTC≈1,320 views3 reactionsread 6 August 2026 አደራ
እታባ አብሯአደጌ ፡
የኔ ተንሰፍሳፊ መፅናኛ ታዛዬ ፣
ሞት ጥርሱን አግጥጦ ፡
ሊዉጠኝ ቢመጣ ማምለጫ ቤዛዬ ፣
አሜኬላ ፈርተሽ ፡
ፈራ ተባ ማትይ ቆሳስለሽ ለመድማት፣
ቀና ብዬ ሰዉ ፊት ፡
አምሮብኝ እንድታይ ለረሃቤ ነሽ ሌማት ።
ለደስታዬ ተግተሽ ፡
ያንቺን ሁሉ ለኔ ስትቸሪኝ እያየሁ ፣
ምን እንደ ጎደለው ፡
ሙላቴ ሳላጣሽ ጎደለኝ እላለሁ ።
ሰዉ አልቸገረኝም ፡
የዓለም ፈተናን አልፍበት መበርቻ ፣
ሁሉ ፊቱን ያዙር ፡
እንዳትጨክኚብኝ አደራ አንቺ ብቻ ።
✨✨✨✨✨✨
✍️ታገል በንቲ
👍3
Signed ታገል ነኝ ገጣሚዉ✍️
9 Oct 2023, 19:09 UTC≈1,410 views9 reactionsread 6 August 2026 Video
Video, posted without a caption
👍8🥰1
Signed ታገል ነኝ ገጣሚዉ✍️
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @afkarish. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.