8 Aug 2026, 06:28 UTC23 views1 reactionsread 8 August 2026 Photo
አልክድም መሆኔን ድኩም
ስሉል ነኝ አልጠነከርኩም
ከንብርክክ ተማፅኖዬ ጋር
ከደጅህ አልተነጠልኩም።
°
ተመልከት ከድቶ ሲተፋኝ
ያያዝኩት ምርኩዝ ሲጠፋኝ
ዘመመ ቅፅሬ ተናደ
በወረት ክንዴ ታጨደ።
°
እንግዲህስ ቀኜ ካራቀኝ
የዋጥኩት መድህን ካነቀኝ
ለብሼ ልብሴ ካረዘኝ
በቁሜ ሰው ከገነዘኝ
ይቅርብኝ መሸነጋገል
አንተው ነህ የምታጸድቀኝ።
°
አላዝን አልንገዳገድ
ከንግዲህ ማንስ ቢረታኝ፣
ምን ቀረኝ ብዬ ዝላለሁ
ሃይልህ ነው የሚያበረታኝ።
°
@Zemari_Abel_Mekbeb
@Zemari_Abel_Mekbeb
@Zemari_Abel_Mekbeb
👍1
Signed 23/03/2017 Vs 2020 Patience ✝️🇪🇹
8 Aug 2026, 06:26 UTC22 viewsread 8 August 2026 Forwarded from @EOTC21_mediaPhoto
"ሰላም ለኪ ማርያም፣ ጸጋ የተመላሽ፣ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ በሴቶች ሁሉ መካከል ብፅዕት ነሽ፣ የማኅፀንሽም ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ብፁዕ ነው።"
@Eyob_Yimenu
@Eyob_Yimenu
Signed Kiyu
7 Aug 2026, 16:51 UTC36 views6 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @EOTC21_mediaPhoto
በመንግስትህ ስትመጣ ቢያንስ ፈልጓል ብለህ መቃተቴን ቆጥረህ ከጎንህ አቁመኝ !
ምንም ባልጥር ፣ ምንም ተግባር ባይኖረኝ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ ጌታዬ፤ ካንተ በላይ ሌላ እንዳልፈለኩ ታውቃለህ።
ያንተ ባለመሆኔ እኮ ከፍቶኝ ያውቃል ፣ አዎ በድዬሃለው እኮ ግን ደስ እያለኝ አይደለም ፣ እረስቼሃለው በብዙ ትቼሃለሁ ግን አውቄ አይደለም ተታልዬ ነው !
ቢያንስ አንዴ እንኳን እንደ ሰው አሳዝነኸኝ ታውቃለህ፤ የሆነ ቀን ላንተ እኮ ተሰብሬ አልቅሼ አውቃለሁ።
ቢያንስ መፈለጌን አይተህ እባክህ ማረኝ !
ፈልጉ ታገኙኛላችሁ ብለሃልና በመፈለጌ ተገኝልኝ !
❤6
Signed Kiyu
7 Aug 2026, 12:09 UTC49 views5 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @EOTC21_mediaPhoto
" ከመናገርህ በፊት ÷ የምትናገረዉ ቃል ከዝምታህ የተሻለ መሆኑን መርምር ።''
- ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ -
@EOTC21_media
@EOTC21_media
❤3👏2
Signed Kiyu
6 Aug 2026, 09:53 UTC71 views3 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @EOTC21_mediaPhoto
መጣችልን እኮ ፍልሰታ ደረሰች
እንኳን ደሳላችሁ እሰይ የምስራች❤️🥰
ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን 🙏
@Eyob_Yimenu
@Eyob_Yimenu
❤3
Signed Kiyu
4 Aug 2026, 08:25 UTC97 views9 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @EOTC21_media
አንድ ሴት እግዚአብሔርን ፈራሁ ካለች ክብሯን ጠብቃ ለስጋ ወደሙ መብቃት አለባት ። ስለዚህ እህቴ ሆይ አንድ ወንድ እንጂ ሁሉ የሚያገባሽ አይምሰልሽ ።
በማስተዋል የምታደርጊውን ከማታደርጊው ፣ ፈጣሪ የሚፈቅድልሽን ከማይፈቅድልሽ በመመርመር ለዪ ።
ለሁሉም ጊዜ አለው ትዕግስት ይኑርሽ ፡፡ ሰው አለባበስን እና ውበትን ያያል ። እግዚአብሔር ግን ልብ እና ኩላሊትን ይመረምራል ፡፡
የጥበብ ሁሉ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነውና እግዚአብሔርን በመፍራት ኑሪ ።
@Official_Dn_henok_haile
@Official_Dn_henok_haile
👍4🥰4❤1
Signed Kiyu
1 Aug 2026, 06:04 UTC131 views2 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @BookMerejaFile
መርቆሬዎስ
መርቆሬዎስ ሰማዕት ገባሬ ተአምር ወኃይል
ምርሐኒ ለወልድከ ፍና ፅድቅ ወሣህል [፪]
አዝ
የወንጌልን ቃል የፈፀምክ
በመንፈስ ቅዱስ የታተምክ
የአብ ወዳጅ ፒሉፓዴር
ሰማእቱ ልብስህ ሰንፔር
መኑ መኑ ዘይትማሰለከ መኑ
እንበለ ጊዮርጊስ ሰማዕት ዘአዳም ስሩ
አዝ
ምሉዓ ጥበብ ወሞገስ
ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ
በምግባር የኖርክ በእምነት
ዓለም የናቅክ ለእውነት
መኑ መኑ ዘይትማሰለከ መኑ
እንበለ ጊዮርጊስ ሰማዕት ዘአዳም ስሩ
አዝ
ዕጉሠ ሕማም ወምንዳቤ
እናመስግንህ በይባቤ
ገድልን የፈጸምክ በክብር
መርቆሬዎስ ገባሬ ተአምር
መኑ መኑ ዘይትማሰለከ መኑ
እንበለ ጊዮርጊስ ሰማዕት ዘአዳም ስሩ
አዝ
ልቡሰ ዓቢይ ግርማ
ዝናህ በዓለም ተሰማ
ዳኬዎስ ንጉስ አፈረ
…
❤2
Signed Kiyu
31 Jul 2026, 06:11 UTC118 views2 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @BookMerejaFile
ቁጥርህ ከመላእክት
ቁጥርህ ከመላእክት ተስተካክሏል
ከኪሩቤል መሐል ገብተህ አጥነሃል
ተክለሃይማኖት በጸሎትህ
ብዙ ድውያን ፈውሰሃል
አዝ
ባሕር ሳያሰጥመን ደርሶልን
አለፍን በደረቅ ከፍሎልን
ኢትዮጵያዊው ሙሴ ተክለሃይማኖት
የሚሳነው የለም በሃይማኖት
አዝ
ጸሎቱ ምህላው ቅዳሴው
ገብቷል ከቤታችን መዓዛው
ጸጋ በረከትህ በዝቶልናል
በአማላጅነትህ ተምረናል
አዝ
ድካም በሌለበት በምስጋና
አምላኩን ያከብራል በትህትና
ስለ እኛም ዝም አይልም ይማጸናል
የአባታችን አምላክ ይሰማናል
አዝ
ዘመናችን ሲረክስ መንገዳችን
ፈጥኖ ደረሰልን አባታችን
ተክለሃይማኖት እርዳን ልጆችህን
አታርቀው ከእኛ ኪዳንህን
መዝሙር
🎙ዘማሪት ጸዳለ ጎበዜ🎤
❖═@OrthodoxTewahedo…
❤2
Signed Kiyu
30 Jul 2026, 06:02 UTC102 views3 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @Abel_mekebebFile
የልቤን ሁሉ
የልቤን ሁሉ የውስጤን ሁሉ
የመረከመረከው በማዕበሉ
የቀና መንገድ ያሳየኸኝ
እምላኬ ሁሌ ተናገረኝ
አዝ
መቀመጤን መነሳቴን
መች ታያለህ አንተ ፊቴን
የልቤ ነህ የውስጥ አይኔ
ምከተልህ በዘመኔ
አዝ
ምድረ በዳው ደስ ይለዋል
እግዚአብሔር ይሰራዋል
ባዶ ብሆን ባንተ ፊት
ሰጥኸኛል ሰገነት
አዝ
በእግዚአብሔር ልቤ ጸና
ደግ አድራጊ ቸር ነውና
አንስቶኛል ካፈር ትቢያ
ልበልለት ሃሌ ሉያ
ዘማሪ ዲያቆን ቤኛ ግርማ
https://t.me/Abel_mekebeb
https://t.me/Abel_mekebeb
https://t.me/Abel_mekebeb
👍3
Signed Kiyu
30 Jul 2026, 05:43 UTC99 views2 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @EOTC21_mediaPhoto
ብርታትም ጉብዝናም ከእግዚአብሔር ነው
ክብርም ሞገስም ከእግዚአብሔር ነው
ጥበብና አስተዋይነትም ከእግዚአብሔር ነው
የሰው መውደድም መደነቅም ከእግዚአብሔር ነው
ከእኛ የሆነ አንዳች ነገር የለም
ስለሆነውም
ስላልሆነውም
ስለሚሆነውም
እግዚአብሔር ይመስገን
@Official_Dn_henok_haile
@Official_Dn_henok_haile
👍2
Signed Kiyu
30 Jul 2026, 05:43 UTC99 views1 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @EOTC21_mediaPhoto
እንኳን ወደ 𝟒-𝟑-𝟑 𝐎𝐍𝐋𝐈𝐍𝐄 𝐖𝐎𝐑𝐊 ቻናል በደህና መጡ! 💸
ያለ ምንም Investment ኢንተርኔታችሁን, ስልካችሁን እና ላፕቶፓችሁን ተጠቅማችሁ በOnline ገንዘብ የምትሰሩባቸዉ! የተረጋገጡ እና ደህንነታቸዉ የተጠበቁ የተለያዩ ስራዎችን በሰፊዉ ለናተ የምናደርስበት ቻናል ነዉ። ስለዚህ ወደ ቻናላችን እየገባችሁ ያላችሁ ሰዎች በሙሉ አሁኑኑ 𝐉𝐎𝐈𝐍 የሚለዉን በመጫን የቤተሰባችን አካል ይሁኑ ገቢዮትን እጥፍ ድርብ ያድርጉ!
Stay tuned and get ready 🔥
ለተለያዩ Online ስራዎች ያለ ግብር ቤታችሁ ቁጭ ብላችሁ ለመስራት በዚህ Link ግቡ👇👇👇
SHARE//@Online_Work_433_Team
SHARE//@Online_Work_433_Team
S…
👍1
Signed Kiyu
29 Jul 2026, 05:17 UTC122 views2 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @Abel_mekebebFile
ቸርነትህ ነው
ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከዛሬ
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከዛሬ
ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ/2/
አዝ
መክሊቴን ቀብሬ ባሳዝንህ
መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ
በታላቅ ይቅርታ እንዳትረሳኝ
በፍቅር ጎብኝተህ ከሞት አውጣኝ
ከቤትህ እርቄ መች ጠገብኩኝ
በረሐብ በእርዛት ተቸገርኩኝ
አምናለሁ አምላኬ እንድትምረኝ
ለይቅርታ መጣሁ ተቀበለኝ በለኝ
አዝ
አንዳች እንደሌለኝ አውቀዋለሁ
ባንተ ቸርነት ግን እመካለሁ
የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል
ይቅርታ ለባርያህ ይደርሰኛል
በመቅደስህ ቆሜ ለመዘመር
ስራህን ለትውልድ ለመመስከር
እኔ ማነኝ ብዬ አስባለሁ
አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ
አዝ
በሰው እጅ መመካት አቁሚያለሁ
እረዳቴ አንተ ነህ አውቄያለሁ
አንተ ከጠበከ…
❤2
Signed Kiyu
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Zemari_Abel_Mekbeb. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.