3 Dec 2024, 16:22 UTC≈12,800 views6 reactionsread 14 August 2026 Photo
* ህይወት እንደምታስቧት ቀላል አይደለችም፤ ህይወት አስቸጋሪ እና ውስብስብ ነች፤ በህይወት ውስጥ የባለፈው ጊዜ እና የወደፊቱ ሁሉም ጊዜ የሚገናኙበት ነች፤
ያ....የነበረው ነገር እንደምንም እስካሁንም ድረስ አለ፤ እንዴትስ ሊጠፋ ይችላል? ሁሉም እዚያ የነበረው ነገር እስካሁንም ድረስ እዚያ ነው! በዚች ቅፅበት መላው የያለፈው ጊዜ፣ የሰብዓዊው ፍጡር የያለፈው ጊዜ ብቻ ሳይሆን መላው ዩኒቨርስ ይጠቁማል፤
እናታችሁ፤ አባታችሁ፤ አያቶቻችሁ፤ ቅማቶቻችሁ፤ አዳም እና ሄዋን ሁሉም በውስጣችሁ ይገለፃሉ፤ አንድ የሆነ ነገራችሁ በአዳም ውስጥ ነበር፤ በሄዋን ውስጥ ነበር፤ እናም እነርሱ በጠቅላላው በውስጣችሁ አሉ፤
🔥3❤1👍1🥰1
Signed 🎭ⓤⓝⓗⓄⓁⓎ 🗽ⒶⓃⒼⒺⓁ🎭
23 Nov 2024, 03:26 UTC≈1,610 views3 reactionsread 14 August 2026 Photo
* በአእምሯችሁ ውስጥ የምትኖሩ ከሆነ በሀሳቦቻችሁ እና በነፀብራቆቻችሁ ውስጥ ነው የምትኖሩት፤ የሀሳቦቻችሁ ድርብርቦሽ ከእውነታ ይደብቋችኋል፤ እናም እውነታን ከእናንተ ይሸሽጉባችኋል፤
አእምሮን መጣል ማለት ቅዠትን መጣል ማለት ነው፤ ዋናውን አእምሮን መጣል ማለት ዋናውን የቁም ቅዠት መሠረት መጣል ማለት ነው፤
አንዴ አዕምሮ እዛ ከሌለ በድንገትም ያ...እዚያ የሆነው ነገር ይገለጣል፤ እናም እግዚአብሔር እንጅ ስለ እግዚአብሔር ያለ ሀሳብ አይደለም፤
🤔3
Signed 🎭ⓤⓝⓗⓄⓁⓎ 🗽ⒶⓃⒼⒺⓁ🎭
14 Nov 2024, 10:55 UTC530 views2 reactionsread 14 August 2026 ‹‹ወንድ ማለት በሴት የተገራ ለማዳ እንሰሳ ነው!››
በሴት መደነቅ የጀመርሁት ስለሄዋን በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ የሰፈረውን ካነበብኩ በኋላ እንደበር ትዝ ይለኛል። እስከዛሬም ስለእሷ ባሰብኩ ቁጥር እንደአዲስ መደነቅ የሚፈጥሩብኝ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አንዳንዶቹን ላስፍርና እግረ መንገድ ስለአምሳያዎቿ በኦስካር ዋይልድ የተመሰከረውን አመጣለሁ:: (ኦስካር ዋይልድ ማነው የሚል አንባቢ ጥበብ ቅፅ ፪ ላይ ታሪኩ ሰፍሮለታል። በተለይ ስለሴት የነገረን ብዙ ነው።)
በመጀመሪያ ስለሔዋን የሚደንቀኝ ነገር ‹‹ድፍረቷ›› ነው። ወንድ ደፋር ለሚመስላቸው ሁሉ የሄዋንን ልጅ ሴትን ባታውቋት ነው በሉልኝ። እስቲ አስቡት ዕባብ ወደ ሄዋን መጥቶ ስለበለሱ ፍሬ ሲያናግራት እርጋታዋ…
👍1🤔1
Signed 🎭ⓤⓝⓗⓄⓁⓎ 🗽ⒶⓃⒼⒺⓁ🎭
9 Nov 2024, 14:12 UTC≈1,380 views8 reactionsread 14 August 2026 Photo
* ቡራኬ እውነተኛው ደስታ ነው፤ እናንተ ደስታ ብላችሁ የምትጠሩት የተደበቀውን መከራ ነው፤ እናንተ ደስታ ብላችሁ የምትጠሩት ተዝናኖትን ነው፤ ይህ ደግሞ ጊዚያዊ ነው፤ ይህ እውነት መሆን አይችልም፤
እውነት አንድ ብቃት ሊኖራት ግድ ነው፤ እናም ብቃቷ ዘላለማዊ መሆኗ ነው፤ አንድ የሆነ ነገር እውነት ከሆነ ያ ነገር ዘላለማዊ ይሆናል፤ ትክክል ካልሆነ ደግሞ ጊዜያዊ ይሆናል፤
እውነተኛው ደስታ ከች የሚለው አእምሮ ሙሉ በሙሉ መከወኑን በሚያቆምበት ጊዜ ብቻ ነው፤ ደስታ ከውጭ አይመጣም፤ ደስታ ከራሳችሁ ፍጥረት ነው የሚፈልቀው፤ ሞልቶም ይፈስባችኋል፤
በብርሀን የተሞላችሁም ትሆናላችሁ፤ የፍስሀ ፏፏቴንም ትሆናላችሁ፤
❤5👍3
Signed 🎭ⓤⓝⓗⓄⓁⓎ 🗽ⒶⓃⒼⒺⓁ🎭
30 Oct 2024, 00:36 UTC≈1,970 views2 reactionsread 14 August 2026 Photo
* ቡድሀዎች(የነቁት) ለመኖር የተለየ ትርጉም አላቸው፣ ትርጉማቸው ንቃትን የያዘ ነው፤ እየተነፈሳችሁ ስለሆነ እየኖራችሁ እንደሆነ አይናገሩም፤ ደማችሁ እየተዘዋወረ ስለሆነ እየኖራችሁ እንደሆነ አይናገሩም፤
እነሱ የሚናገሩት በህይወት የምትኖሩት የነቃችሁ ከሆናችሁ እነደሆነ ነው፤ ስለሆነም ከነቃው ሰው በስተቀር ማንም የእውነት እየኖረ አይደለም፤
እናንተ የምትራመዱ የምታወሩ ነገሮችን በማድረግ የተሞላችሁ ሬሳዎች ብቻ ናችሁ፤
🤔2
Signed BŁÌÑĐ ŠØŰŁ
27 Oct 2024, 13:29 UTC≈2,090 views2 reactionsread 14 August 2026 Photo
* በጣም አስፈላጊ የሆነ አንድ ነገር...ይህንን ነገር በልባችሁ ውስጥ በጥልቁ እንዲሰጥም አድርጉት፤ እውነት ንድፈ ሀሳብ በጭራሽ አትሆንም፤ እውነት ፈፅሞ መላምት አትሆንም፤ እውነት ሁሌም ልምድ ነች፤
በዚህም ምክንያት የተነሳ የእኔ እውነት የእናንተ መሆን አይችልም፤ እውነቴ አምላጭ ባልሆነ ሁኔታ የእኔ እውነት ነው፤ እውነቴ የእኔ እውነት እንደሆነ ይቀራል፤ የእናንተ ሊሆን አይችልም፤ ልንጋራው አንችልም፤ እውነት የማይካፈሏት፤ ተላልፎታዊ ያልሆነች፤ ተግባቦታዊ ያልሆነች፤ አይገለፄ ነች፤
እውነትን እንደተቀዳጀኋት ልገልፅላችሁ እችላለሁ ዳሩ ግን እውነት ምን እንደሆነች መናገር አልችልም፤
🔥2
Signed 🎭ⓤⓝⓗⓄⓁⓎ 🗽ⒶⓃⒼⒺⓁ🎭
24 Oct 2024, 14:20 UTC≈1,440 views2 reactionsread 14 August 2026 Photo
* ባዶነት ከመከራ ይልቅ ሰዎችን ያስፈራቸዋል፤ ውስጣዊ ማዕዘን ግን ባዶነት ነው፤ ከመከራ ይልቅ ሰዎችን የሚያስፈራቸው ባዶነት ነው፤ ምነም መሆን የሚፈልግ ሰው የለም፤ ውስጣዊ ተፈጥሮአችን ደግሞ ባዶነት ነው፤ ስለዚህ ልንቀበለው አንችልም፤
መፈለጋችንን እንቀጥላለን፤ ሰው ለመሆን የምንዳርገውን መከራም እንቀጥላለን፤ ደስታን ማግኘት ካልቻልን ደግሞ ቢያንስ ስቃይን ልናገኝ እንችላለን፤
ደስታን ማግኘት ባንችል ከመከራ ጋር መጣበቅ እንችላለን፤ አንድ መፅናኛ ግን አለ፤ የምንደግፈው አንድ ነገር አለን፤ ባዶ እጃችንን አይደለንም፤
❤2
Signed 🎭ⓤⓝⓗⓄⓁⓎ 🗽ⒶⓃⒼⒺⓁ🎭
24 Oct 2024, 13:23 UTC≈1,240 views5 reactionsread 14 August 2026 Photo
* ህይወት ከየትም ወደ የትም የሚደረግ ጉዞ ነው፤ የሚያስገኘውም ነገር አይኖርም፤ ማንም ሰው ከህይወት ያገኘው ነገር የለም፤ ሰዎች ይሮጣሉ፤ ፍጥነታቸውንም ይጨምራሉ፤ የትም ግን አይደርሱም፤
ጠንክረው ይሰራሉ፤ ይለፋሉ፤ ከዚያ ስራ የሚገኝ ነገር ግን የለም፤ ምንም ነገር አይፈጠርም፤
ከአንተም በፊት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ኖረዋል፤ የት ደረሱ? ወደ አፈር ተቀላቀሉ፤ ከአፈር ወደ አፈር ይፍጠንም ይዘግይም ወደ ተመሳሳይ አፈር መቀላቀላችን አይቀርም፤
ስንቶቻችን ሁሉ ወደ አፈር ተቀላቅለን እንጠፋለን፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ስልጣኔዎች ተነስጠው ጠፍተዋል፤ ያለምንም አሻራ....
👍3❤1👏1
Signed BŁÌÑĐ ŠØŰŁ
20 Oct 2024, 19:21 UTC≈1,480 views8 reactionsread 14 August 2026 Photo
* በርካታ ቅዱሳን በርግጥም የአእምሮ ህሙማን ናቸው፤ መሳቅ አይችሉም፤ አንተ ደግሞ የማትስቅ ከሆነ እንዴት ማልቀስ ትችላለህ? እንዴትስ ማንባት ትችላለህ? ሁለቱም በጣም አስቸጋሪ ነገሮች ናቸው፤
ሣቅና ጩኸት ደግሞ የማይቻሉ ሲሆኑ ልብህ ሙሉ በሙሉ ዝግ ይሆናል፤ ምንም ስሜቶች አይኖሩህም፤ በጭንቅላትህ ብቻ መኖር ትጀምራለህ፤ አጠቃላይ እውነታህም ሀሳብን ብቻ የሚይዝ ነው፤
ሐሳብ ደረቅ ነው፤ ሳቅ መፍጠር አይችልም፤ ዕምባ ማምጣት አይችልም፤ ዕምባ ሊያመጣ አይችልም፤ ዕምባና ሳቅ ሊመጡ የሚችሉት ከልብ ነው፤ ንፁህነት ደግሞ ከአዕምሮ ሳይሆን ከልብ ነው፤ ግራ መጋባትም ከአእምሮ ነው፤
🖕4👎2💯2
Signed BŁÌÑĐ ŠØŰŁ
12 Oct 2024, 17:27 UTC≈1,280 views7 reactionsread 14 August 2026 Photo
* የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ስትሆኑ ግለሰብነታችሁ ይጠፋና ጥንድ ትሆናላችሁ፤ የአንድ ነገር ሁለት ገፅታ ትሆናላችሁ፤ ጥንድ ማለት ከፍቅረኛችሁ ጋር አንድ አካል መሆን ማለት ነው፤
ሀዘንም ሆነ ደስታቸውን በጋራ ይቀበሉታል፤ አንዳቸው የሌላቸው አካል ክፋይ በመሆን የጋራ የሆነን አንድ ህይወት ይኖራሉ፤ የናንተ ግማሽ አካል የሌላኛው ህይወት ውስጥ ይገባል፤
የጋራ ህይወታችሁ በሁለታችሁ ልብሶች የተሞላ አንድ ሻንጣን ይመስላል፤ የጥንድ አብሮነት ሙሉ በሙሉ ይሸፍናችሁና ማንነታችሁን ትዘነጉታላችሁ፤ ሁሉ ነገራችሁ በጓደኞቻችሁ ቀለም ይሸፈናል፤ ነገሮ በሙሉ የሚገለፁት በጋራ ቀለማችሁ ይሆናል፤
👍7
Signed 🎭ⓤⓝⓗⓄⓁⓎ 🗽ⒶⓃⒼⒺⓁ🎭
6 Oct 2024, 14:04 UTC≈1,730 views1 reactionsread 14 August 2026 Photo
* በህይወት ታላቁ ያልተለመደው (ከመደበኛው ነገሮች ውጭ የሆነው) ነገር ተራው (የተለመደው) ነው፣
ሁሉም ሰው ያልተለመደ መሆን ይፈልጋል፤ ይህም የተለመደ ነው፤ ነገር ግን ተራ መሆን እና ተራ በመሆንም ዘና ማለት መቻል ይህ ታላቅ ያልተለመደ ነገር ነው፤
አንድ ያለምንም ማጉረምረም እና መነጫነጭ ተራ መሆኑን በደስታ የተቀበለ ሰው ያለውን ደስታ ማንም ሰው ሊያጠፋው አይችልም፤
አንድም ሰው ታላቅ ደስታውን ሊሰርቀው ወይም ሊወስድበት አይችልም፤ በመሆኑም የትም ቦታ ሆናችሁ ደስተኛ ትሆናላችሁ፤
👍1
Signed 🎭ⓤⓝⓗⓄⓁⓎ 🗽ⒶⓃⒼⒺⓁ🎭
3 Oct 2024, 15:47 UTC≈1,500 views5 reactionsread 14 August 2026 Photo
* የምንመጣው እና የምንሄደው እኛ ነን፤ ህይወት እንዳለች ትኖራለች፤ የሚያልፈው ጊዜ ሳይሆን እኛ ነን፤ እኛ እንደምናልፍ ከማየት ይልቅ፤ ሰአት የሚባል ትልቅ ግኝት ፈጥረናል፤
ይህ የተሳሳተ ነው፤ አስቡት እስኪ! በዚች ምድር ላይ ምንም ሰው ባይኖር የሚያልፍ ጊዜ ይኖራል? ሁሉም ነገሮች ይኖራሉ፤
ውቅያኖስ ወደ ባህር ዳርቻ ይፈሳል፤ ሞገዱም ከድንጋዮች ጋር ይጋጫል፤ ፀሀይ ትወጣለች፤ በርግጥ ፀሀይ ወጥታም ይሁን ገብታ አታውቅም፣
ጠዋት ወይም ማታ የሚባል ነገር አይኖርም፤ ጊዜ አእምሮ የፈጠረው ነው፤ በመሰረቱ ጊዜ ሊኖር የሚችለው በትናንት እና በነገ እንጅ የአሁኗ ቅፅበት የጊዜ አካል አይደለችም፤
ልክ አሁን እዚህ እንዳላችሁ ጊዜ የሚ…
❤5
Signed 🎭ⓤⓝⓗⓄⓁⓎ 🗽ⒶⓃⒼⒺⓁ🎭
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @UNVOICESCREAM. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.