7 Aug 2026, 18:22 UTC558 views5 reactionsread 8 August 2026 መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ ወልደሽልናልና ከዳዊት ሥር የተገኘሽ ባሕርይ አንቺ ነሽ /ሉቃ.፩፡፴፪/፡፡ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ ከአብ ባሕርይ ዘእም ባሕርይ አካል ዘእም አካል የተወለደ፣ ተቀዳሚ ተከታይ (ታላቅም ታናሽም) የሌለው አካላዊ ቃል ባሕርዩን በሥጋ ሠወረ፡፡ ከአንቺም አርአያ ገብርን ነሣ /ፊል.፪፡፯/፡፡
ከእናንተ መካከል፡- “አካላዊ ቃል አርአያ ገብርን ነሥቶ (የባሪያን መልክ ይዞ) በሰውም ምሳሌ ኾኖ ራሱን ባዶ አደረገ ሲል ምን ማለት ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- ራሱን ባዶ አደረገ ሲል የእኛን ባሕርይ ገንዘብ ባደረገ ጊዜ ባሕርየ መለኮቱ ተለውጧል ማለት አይደለም፡፡ ባሕርየ መለኮቱን ትቶ …
❤3🔥2
Signed Tekel - ቴቄል 👑
7 Aug 2026, 13:06 UTC710 views10 reactionsread 8 August 2026 ለወንዶች የሚከፈል ዕዳ በሴቶች ላይ ነበረ፤ ያለ እናት ሔዋን ተገኝታ ነበርና፡፡ ስለዚህም የሔዋንን ብድራት ለአዳም ትከፍለው ዘንድ ድንግል ያለ ዘርዐ ብእሲ (ያለ ወንድ ዘር) ክርስቶስን ወለደችው፡፡ አዳም ያለ እናት ሔዋንን ስላስገኘ እንዳይመካ ድንግል ያለ አባት ክርስቶስን ወለደችው፡፡ ድንቅ በሚኾን አንድነት ይህ አንድ የፍጥረት እኩልነት ይታወቅ ዘንድ” (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
ቀድሞ ወንዶች ሴቶችን በእናንተ ምክንያት ከገነት ወጣን እያሉ ርስት አያካፍሏቸውም ነበር፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “ብእሲ ወብእሲት አሐደ እሙንቱ በክርስቶስ - ወንድም ሴትም የለም፤ ኹላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” ብሎ እስኪያስተምር ድረስ /ገላ.፫..3፡..28፳፰/ …
❤8🔥2
Signed "ተዋሕዶ"
7 Aug 2026, 06:57 UTC≈1,250 views7 reactionsread 8 August 2026 የማኅፀኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን ኹሉ አድኗልና፡፡ ከእኛ መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አጠፋልን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ኹሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና” እንዲል /ቈላ.1፡19-20/ በመካከል ኾኖ በመስቀሉ አስታረቀን፡፡ ልዩ በኾነ ትንሣኤውም ሰውን ዳግመኛ ወደ ገነት መለሰው፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ልዩ በኾነ ትንሣኤ ሲል ምን ማለቱ ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- ከእነ አልዓዛር ትንሣኤ የተለየ መኾኑን ለማሳየት ነው፡፡ ምክንያቱም፡-
1ኛ) እነ አልዓዛር አስነሺ ይሻሉ፤ እርሱ ግን “ላኖራት ሥልጣን አለኝ፤ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ” ብሎ…
❤4🥰3
Signed Tekel - ቴቄል 👑
6 Aug 2026, 20:00 UTC619 views10 reactionsread 8 August 2026 1ኛ ዮሐንስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን።
⁴ አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።
👉 በአንድነት ኑሩ እግዚአብሔር የሚወደውንም ሥራ ብቻ ሥሩ።
❤7🔥3
Signed Tekel - ቴቄል 👑
6 Aug 2026, 06:27 UTC≈1,060 views12 reactionsread 8 August 2026 ዮሐንስ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ ኢየሱስም መለሰ አለውም፦ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል...
.
.
²⁴ የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም...
“ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፥ ና።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 16፥22
የአባታችን የጌታችን የአምላካችን ቃል የማያልፍ ቃል ነው ።
👉“ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።”
— ዮሐንስ 6፥54
👉“በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ።”
— 1ኛ ዮሐንስ 2፥9
ከዚህ እርቆ ጌታ ጌታ ማለቱ ከንቱ ድካም ነው ..እባካችሁ ወደ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ እንቅረብ የምርም ጌታን እንውደደው…
❤8🔥4
Signed Tekel - ቴቄል 👑
5 Aug 2026, 06:07 UTC139 views13 reactionsread 8 August 2026 “የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።”
ሮሜ 12፥2
ሠናይ ዕለት 🌿
👉 በአንድነት ኑሩ እግዚአብሔር የሚወደውንም ሥራ ብቻ ሥሩ።
❤7🔥6
Signed Tekel - ቴቄል 👑
4 Aug 2026, 18:23 UTC≈1,450 views15 reactionsread 8 August 2026 "ገበሬ ዘርን በእጁ ብቻ ይዞ ካልዘራው መኸር እንደማያገኝ፣ ክርስቲያንም የጌታን ቃሉን ሰምቶ በሥራ ካልገለጠው በሕይወትም ከአልኖረው የሕይወት ፍሬ አያፈራም። ክርስትና የተግባር እንጅ የቃል ብቻ አይደለም ።
(ኦርቶዶክሳዊ ወጣት)
“በእርሱ (በጌታ ) እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል።”
— 1ኛ ዮሐንስ 2፥6
“ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።”
— ያዕቆብ 1፥22
👉 በአንድነት ኑሩ እግዚአብሔር የሚወደውንም ሥራ ብቻ ሥሩ።
❤13🔥2
Signed Tekel - ቴቄል 👑
4 Aug 2026, 06:14 UTC185 views12 reactionsread 8 August 2026 “በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤”
—
ሮሜ 12፥12
🥰8❤3👍1
Signed "ተዋሕዶ"
3 Aug 2026, 18:48 UTC≈1,480 views13 reactionsread 8 August 2026 ስለ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የማይናገሩ /መናገርን የሚፈሩ የሚያፍሩ/ ሰዎች ለእኔ የመቃብር ድንጋዮች እና የሞቱ ጠጠሮች ናቸው
( ቅዱስ አግናጥዮስ)
ማቴዎስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤
³³ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።
“በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።”
— ማርቆስ 8፥38
ክርስቲያኖች በጌታችን ስም ልናፍርበት አይገባም በስራ ቦታም በሁሉም ቦታ የአባታችንን የአምላካች…
❤12🔥1
Signed Tekel - ቴቄል 👑
3 Aug 2026, 07:31 UTC205 views8 reactionsread 8 August 2026 መድኃኔዓለም ክርስቶስ ዘእምቅድመ ዓለም ነበርከ
አግብርቲከ ዘተሞቅሑ ተሞቂሐከ ፈታሕከ
ወበሞትከ ሙታነ አንሣእከ
ከዓለም በፊት የነበርክ መድኃኔዓለም ሆይ
የታሠሩ አገልጋዮችህን ታሥረህ አስፈታሐቸው
ሙታንንንም በሞትህ አነሣሀቸው
(መልክአ መድኃኔዓለም)
እንኳን አደረሳችሁ 🙌
❤5🔥3
Signed Tekel - ቴቄል 👑
2 Aug 2026, 18:31 UTC≈1,860 views9 reactionsread 8 August 2026 መብል መጠጥ የሆነ ሙሽራ! (መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ)
''በሠርጉ ጊዜ ሥጋውን የሚሠዋና ፈጽሞ መብል የሚሆን ሙሽራ ያየ ማነው?የእግዚአብሔር ልጅ ዓለም ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ከእርሱ በቀር ሌላ ያደረገው የሌለ አዲስ ሥርዓት ሠራ፥ በሠርጉ ጊዜ በሐዋርያት ፊት ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ማዕድ አድርጎ ሠራ። ከእርሱ ይበሉ ዘንድ፥ ያመኑበት ይድኑበት ዘንድ። በሠርጉ ጊዜ መብል መጠጥ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የሰጠን አምላካችን ብሩክ ነው፥ለኃጢአት ማስተሰርያ ሊሆን ለዘለዓለም እንድንበት ዘንድ። ለእርሱ ምስጋና ይግባው ለዘለዓለሙ አሜን።''
(ሥርዓተ ቅዳሴ)
ዮሐንስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵³ ስለዚህ ኢየ…
❤7🔥2
Signed Tekel - ቴቄል 👑
2 Aug 2026, 08:37 UTC≈2,230 views9 reactionsread 8 August 2026 ይሁዳ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤
¹⁸ እነርሱ፦ በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና።
¹⁹ እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው።
²⁰ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
²¹ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
👉 በአንድነት ኑሩ እግዚአብሔር የሚወደውንም ሥራ ብቻ ሥሩ።
❤6🔥2🥰1
Signed Tekel - ቴቄል 👑
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Tekeltube1. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.