22 May 2026, 18:27 UTC274 views2 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112
አልጠፋም ከደጅሽ🥰🥰
ማስተዋል ተስኖኝ ይዞኝ ወጣትነት
ብዙ ብነከርም ብለወስ በሃጢያት
ማንነቴ ቢዝል ቢርቀኝም ሰላም
ሰዉ ሆኖ ተፈጥሮ ሰዉ መሆን ቢያቅተኝም።
ዉስጤ ምን ቢቆሽሽ መልካም ባይወጣኝም
በወዳጅ ብከዳ መኖርን ብጠላም
በፈተና ብዝል እምነት ቢጎለኝም
ሁልጊዜ ባማርር ማመስገን ቢያቅተኝም
ተስፋየ መንምኖ ዉስጤ ቢጨልምም
የያዝኩት ቢበተን ምንም ባይኖረኝም
አለም ብትገፋኝ ብትበረታብኝም
ስጋዬ ቢያይላት ነፍሴ ብትደክምም
አልጠፋም ከደጅሽ እመጣለሁ ሁሌም
በነጋ በጠባ
ልቤ እስክትገቢ ልብሽ እስክገባ
አወን እመጣለሁ ከደጅሽ አልጠፋም
እማምላክ እናቴ
ያላንቺ ማን አለኝ ባዶ አይደል ህይወቴ🥰
✍🏻{@Ye_sh_i}
@AWDEKALAT_2112
@AWDE…
❤2
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
18 May 2026, 19:07 UTC262 views2 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112
✍🏻 የቅዱስ ያሬድ ግጥም !
( ርዕስ - ዝክረ ቅዱስ ያሬድ )
የመላእክት ልጆች ፥ ከቅዱስ ተራራ
በዝሙት ሲወርዱ ፥ ወደ ቃየል ተራ
ስድስተኛው ትውልድ ፥ የአዳም ዘር ውላጅ
ያለ ግብሩ ሲሆን ከክፋት ሲወዳጅ
ውርዝውናን ረስቶ ያለ ጊዜው ሲጃጅ
የዛፉም ቅርኝጫፍ የትውልዱም እትብት
መውረዱን ሲያረዱ ያሬድ ብለው ጠሩት።
መውረዱ ቀጥሎ ፥ ወርዶ ወርዶ ወርዶ
የሰው ልጅ ከጽድቁ ፥ ከከፍታው ነጉዶ
ስሙ ከስማቸው ፥ ከአፋቸው ተላምዶ
ለመሬት ጥሬ ፥ ከአፍ እንዳመለጠ
ዘመን እየጣለ ፥ ቀን እየረገጠ
ቤተ ቀጢን ጓሮ ፥ ለአንድ ብላቴና ለያሬድ ተሰጠ።
@AWDEKALAT_2112
ይህንን ሲሰማ
ያሬድ ምስጢራዊ ነፍሱ ደነገጠ
ለጌታም አደረ መጽሐፍም ገለጠ
ቀለም አልሆን ቢለ…
❤2
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
18 May 2026, 19:01 UTC204 viewsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112File
✞ ምስጋና ጀመረ ✞
ምስጋና ጀመረ ብሎ ሃሌ ሉያ
ማኅሌታይ ያሬድ ዘኢትዮጲያ
ምስጋና ጀመረ ብሎ ሃሌ ሉያ
ይበል ይበል ኧኸ ይበል ሃሌ ሉያ
ጥዑመ ልሳን ያሬድ (፬) ዘኢትዮጲያ
ብሉይን ከሐዲስ ሐዲስን ከብሉይ
አስተባብሮ ቃኘው ያሬድ ማኅሌታይ
ምስጢር ተገልጾለት ከምድር እስከ ሰማይ
አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በመንፈስቅዱስ ኃይል ምስጢር እያስማማ
ምስጋና ጀመረ በጽዮን ከተማ
ለሦስቱ ሥላሴ በሦስት አይነት ዜማ
አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በወርቅ ጸናጽል በብር ከበሮ
ዜማው ሲንቆረቆር በሰው ልጆች ጆሮ
የያሬድ ዝማሬ ያድሳል አእምሮ
አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ተዋህዶ አቅርቢ ለአምላክ ምስጋና
በዕዝራ መሰንቆ በዳዊት በገና
ዜማውን ከ…
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
17 May 2026, 18:11 UTC187 views2 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112
Posted without readable text
👍2
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
10 May 2026, 08:53 UTC221 views1 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112
ባንቺ በኩል ልዳን🥺
እየውልሽ እመአምላክ ወላዲቷ
ከልቤ ለይ ሃዘን አለ ብዙ እንባ
የማዋየው የምነግረው ዘመድ የለም ካጠገቤ
ተለመኚኝ እመቤቴ
......... 🥺
..............🥺
..................... 🥺
ፊቱን ነሳኝ ወዳጅ ያልኩት
በሩን ዘጋ ገና ከሩቅ ዘመድ ብዬ የቀረብኩት
መግቢያ ሁሉ ጨላለመ በኔ ሂወት
ተለመኚኝ እመ ምረት❤️🩹
ንገሪው ለልጅሽ አንቺን ይሰማሻል
ከፊቱ አልቆምም የኔ ሃጥያት በዝቶል
ባንቺ አይጨክንም ምረት ይሰጠኛል
ባንቺ በኩል ልዳን የኔ ሃጥያት በዝቶል
❤️🩹❤️🩹❤️🩹
@AWDEKALAT_2112
❤1
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
9 May 2026, 18:41 UTC208 viewsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112
ማርያም
እሙ ለፀሀይ ፅድቅ
የፍጥረት መመኪያ የነቢያት ትንቢት
ምስራቀ ምስራቃት
ቤዛዊተ አለም ርግብየ ሰናይት
ሀገረ እግዚአብሔር
የዳዊት መሰንቆ አክሊለ ንፁሀን
የያዕቆብ መንሰላል
የጌድዮን ፀምር ናዛዚተ ንዙሀን
የአሚናዳብ ሠረገላ
አቁራሪተ መዓት ሰዓሊተ ምህረት
የሀዋርያት ሞገስ
ተቅዋሞ ዘወርቅ ዕፀ ህይወት ልዕልት
የህዝቅኤል አዳራሽ
የአቤል ይውህና እግዝእትነ ማርያም
የኢያሱ ምስክር
ሀመልማላዊ ወርቅ ብፅህት የአዳም ሰላም
የሰለሞን ቀለበት
ምልዕተ ውዳሴ የሀዋርያት ሞገስ
የሙሴ ፅላቱ
የደስታ መገኛ የሲና ዕፀ ጳጦስ
የሴም ዕድል ፈንታው
…
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
8 May 2026, 19:57 UTC188 views2 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112File
🔴 "ለልደትሽ ምስጋና ይገባል "ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ | ግጥም : መምህር ብሩክ ባይለየኝ
@AWDEKALAT_2112
❤2
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
7 May 2026, 19:57 UTC202 views1 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112
✞መከራ ጽና✞
በመከራ ጽና በፈተናም ጽና
ለጊዜው ነው እንጂ ሁሉም ያልፋልና
እዮብ ተጨነቀ በጣም ተማረረ
ከመከራው ብዛት ትዕግስትን ተማረ
ልጅ የሌለው ሆነ አጣ ንብረቱን
በመከራ ጸና አልካደም አምላኩን
አዝ= = = = =
መፈተን መልካም ነው ያነጥራል እንደ ወርቅ
በመጨረሻው ቀን በክብር እንድንደምቅ
አንዱን ሳትሻገር ሌላው ቢተካብህ
በሕይወትህ ዘመን መከራ ቢያጠቃህ
አዝ= = = = =
ከአምላክህ ተስማማ እራስህን አዋርድ
በቃሉም ተመራ እንደ ፈቃዱም ሂድ
ዋጋ ከአምላክህ ዘንድ በሰማይ አለና
በርታ ክርስቲያን ሆይ በመከራ ጽና
መዝሙር
አዲስ ለማ
"በጊዜውም አለጊዜውም ጽና።"
…
👍1
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
6 May 2026, 19:04 UTC180 viewsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112
የልደታ ለማርያም ግጥም !!
( ርዕስ - ለደስታችን ዜና ለልደትሽ ብሥራት )
#ለደስታችን_ዜና_ለልደትሽ_ብሥራት
#ምን_ስጦታ_እናምጣ_ለፈጣሪ_እናት፤
በመኑ ድንግል ሆይ በማን እንመስልሽ
ቃላት ቢረቃቸው አበው ወዳጆችሽ
በአርምሞ ሆነው እንዳመሰገኑ የልጅሽን ስራ
ከትውልዱ የሆንን በልደትሽ ደስታ እኛም ስንጠራ።
ዝም እንበል እንጂ ክብርሽ ቢረቅብን
ላንቺ ያልነው ሁሉ ስጦታ ቀሎብን
እንውደድሽ እንጂ እናድንቅሽ እንጂ በዕንባችን ዘለላ
ለልደት ስጦታ አንቺን የሚመጥን ምንም የለን ሌላ ።
#ለደስታችን_ዜና_ለልደትሽ_ብሥራት
#ምን_ሻማ_እናብራልሽ_የብርሃን_እናት፤
ጨረቃችን ማርያም ተስፋችን እኮነሽ
በጨለማ ሳለን ጸሐይን የወለድሽ፤
የጸሐይ ማደርያው በእውነት ጸሐይ ነ…
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
5 May 2026, 17:24 UTC174 viewsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112
የኔ መድሀኒያለም❤️
ስለኔ ሲል ሞቶ፣
ስጋውን ቆራርሶ በደሙ የዋጀኝ
ልጄ ብሎ ጠርቶ፣
የረከስኩት እኔን ክብር ያቀዳጀኝ
ምንም የሚመጥን፣
ባይኖረኝ አንድ ቃል ለክብሩ ሚበቃ
ክበር ተመስገን ልበል፣
ደጅህንም ልጥረግ ሌላ የለኝም በቃ
ተይዤ በመዳፍህ፣
ስንት ጭንቅ መከራን ባንተ ተሻገርኩኝ
በእቅፍህ ገብቼ፣
ከአለም ግሳንግሷ ከወጥመዷ ዳንኩኝ
ጊዚያዊ ነው ሁሉም፣
በሰከንድ ሚጠፋ የአለም ፍቅሯ
በዙ ለመንጠቅ ነው፣
ጥቂት አቀብላ በህይወት ማኖሯ
ጊዜ ማይቀይረው፣
የዘላለም መውደድ ያንተ ብቻ አባ
ታጥቦ ጭቃዋ እኔ፣
መጥቻለውና ይቅር በለኝ ልግባ
ልታደስ በቃልህ፣
ልክበር በቁርባ…
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
4 May 2026, 17:47 UTC165 viewsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112
ምልጃሽ ይመልሰው
ምንኛ ንፉግ ነው ፣ስለክብርሽ መስገድ ፅድቁ ያላረገ፣
ምልጃሽን በመካድ፣ የኢየሱስን ምልጃ በአለም የሰበከ።
ምን ፀጋ መነፈግ ፣ወንጌል ተከደነ በአእይንተ ልቡ፣
የጌታውን ስብከት ፣አጣሞ በማርቀቅ አይኖቹ ተራቡ።
ባይገባው ምስጢሩ፣የቀዳማዊ ቃል ከስጋ መዋሀድ ፣
የሰባቱ መንጦላይት፣ከፍጥረታት አክሊል ማህፀን መጋረድ፣
እግሮቹ ይከዱታል፣ለመለኮት ሀገር ከእግሯ ጫፍ ለመስገድ ።
መታደል አይደል ወይ ፣ክብርሽ ተገልጦለት ሶልያና ማለት ፣
በዕስመ ዝማሬ ተመስጦ መቀኘት ፣ውዳሴን ማሰማት ።
እንዴት አንደበቱ ፣ቃል አጣ ለፃድቂቱ እርግብ፣
በስጋ በነፍስም ፣ተለቀደሰችው የአምላክ በጎ ሀሳብ ።
የሰው ልጅን መና፣በሆዷ አስተናግዳ ለከበረች መሶብ ፣
በዳዊት …
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
3 May 2026, 18:21 UTC154 views1 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @awdekalat_2112File
♡ ይናፍቃል ልቤ ♡
ይናፍቃል ልቤ በብዙ(2)
ሊታዘዝህ ሊገዛልህ ሊያገለግልህ(2)
ኃጢአትም እንደ ሕልም ውስጤን ሲገዛኝ
በፍቅርህ ስታየኝ አነባለሁኝ
በውስጤ ይፈሳል ፍቅርህ እንደዘይት
እንዴት ልርሳው ቸርነትክን ከተለወጥኩበት
...........
ለፍርድ አትቸኩልም በልጆችህ ላይ ልቦናዬን ማርከኸዋል ከምንም በላይ
የእኔ አይደለምና የምድር ሰውነቴ
ላገልግልህ ባሪያህ ሆኜ ቸር ነህ መድኃኒቴ
...........
አመፅን ለመስራት ስፈጥን ከመንገድ ከአጠገቤ አይሃለሁ እብደቴን ስታግድ እንደምን ወደድከኝ ምን እከፍልሃለሁ
ከሰው ምንም የማትወስድ
መሆንክን አውቃለሁ
...........
እንግዳ ነህ ለእኔ አዲስ ነህ ለቤቴ
ትልቁ ዘመዴ ለብቸኝነቴ
ዳር ሆነህ አታየኝ ሐዘ…
❤1
Signed 𝖒𝖊𝖐𝖉𝖊𝖘𖣔ꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋꠋ✞︎ᬼ⃝:
Showing the 12 most recent of 19 posts we hold for @OrthodoxPhotographs. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.