27 May 2026, 06:10 UTC229 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
ሚኬል አርቴታ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ተባለ
*****
የ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ 2025/26 የውድድር ዘመን የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ተደርጓል።
በዚህም መሰረት የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመባል ተመርጧል።
አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ባለቤት ሲሆን ዘንድሮ አስገራሚ ቁጥሮችን አስመዝግቧል።
ቡድኑ ከ38 የሊጉ ጨዋታዎች በ27ቱ ሲያሸንፍ 25 ጊዜ ደግሞ ከቆሙ ኳሶች ግቦችን ያገኘበት ዓመት ሆኗል።ይህም በሊጉ ታሪክ ቀዳሚው ክለብ አድርጎታል።
አሰልጣኙ 19 ከማዕዘን የተገኙ ግቦችን ጨምሮ አንድም ተጫዋች በቀይ ካርድ ከሜዳ ያልተሰናበተበትና ዓመቱን ሙሉ ፍፁም ቅጣት ምት …
👍2❤1👏1
24 May 2026, 18:41 UTC237 views1 reactionsread 6 August 2026 Photo
አርሰናል ከ22 ዓመት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አነሳ
**
ክለቡ ይህንን ታላቅ ዋንጫ ማሳካት የቻለው ታዋቂው አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ቡድኑን ሳይሸነፍ (Invincibles) ስም ዋንጫ ካነሱበት የ2003/2004 የውድድር ዘመን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
❤1
21 May 2026, 03:01 UTC275 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
አስቶን ቪላ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ
**
የእንግሊዙ ክለብ አስቶን ቪላ የጀርመኑን ክለብ ፍራይበርግን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ የ2025/26 የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል።
በኢስታንቡል በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ዩሪ ቴሌማንስ ፣ ኢሚሊያኖ ቡንዳይ እና ሞርጋን ሮጀርስ ለአስቶን ቪላ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ይህ ድል ለአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ 5ኛ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫቸው ሲሆን፣ ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ በማሸነፍ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ሆነዋል።
አስቶን ቪላም ከ44 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የአውሮፓ መድረክ ዋንጫውን ማሳካት ችሏል።
❤2👍2
19 May 2026, 20:29 UTC248 views2 reactionsread 6 August 2026 Photo
አርሰናል የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሆነ
*****
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት ማንቸስተር ሲቲ ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት አቻ መውጣቱን ተከትሎ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።
በቫሊቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ጁኒየር ክሩፒ በመጀመሪያው አጋማሽ 38ኛ ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር ኧርሊንግ ሃላንድ ሲቲን አቻ ያደገውን ግብ አስቆጥሯል።
ፕሪሚየር ሊጉ ሊጠናቀቅ አንድ ጨዋታ ብቻ የቀረ ሲሆን እስካሁን 82 ነጥቦችን የሰበሰበው አርሰናል 78 ነጥቦች ካሉት ተከታዩ ማንቸስተር ሲቲ ጋር የአምስት ነጥቦች ልዩነት ያለው በመሆኑ ሻምፒዮናነቱን አረጋግጧል።
❤1👍1
18 May 2026, 21:02 UTC254 views1 reactionsread 6 August 2026 Photo
አርሰናል በዋንጫ ግስጋሴው ወሳኝ ድል አስመዘገበ
******
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 37ኛ ሳምንት ጨዋታ በርንሌይን የገጠሙት መድፈኞቹ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት በማሸነፍ ሦስት ነጥብ ማሳካት ችለዋል።
ብቸኛዋን ግብ ካይ ሃቨርትዝ በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥሯል።
ድሉን ተከትሎ አርሰናል ነጥቡን ወደ 82 ማሳደግ የቻለ ሲሆን፣ በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 5 ከፍ አድርጓል።
#EthiopianBroadcastingCorporation #EPL #Arsenal #Soccer
❤1
18 May 2026, 10:06 UTC174 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
አርሰናል ከ በርንሌይ -የመድፈኞቹን የዋንጫ መዳረሻ የሚጠቁመው ወሳኝ ጨዋታ
******
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ37ኛ ሳምንት ጨዋታ ዋንጫውን ከ22 ዓመታት በኋላ ወደ ኤምሬትስ ለማምጣት የተቃረበው አርሰናል በርንሌይን ያስተናግዳል።
ምሽት 4ሰዓት በኤምሬትስ ስታዲየም በሚጀምረው ጨዋታ መድፈኞቹ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፉ ለዋንጫው በእጅጉ የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
አርሰናል በሊጉ ከበርንሌይ ጋር ካደረጋቸው 19 ጨዋታዎች መካከል የተሸነፈው 1 ጨዋታ ብቻ ሲሆን 14ቱን ማሸነፍ ችሏል።
በጊዜያዊ አሰልጣኝ ማይክል ጃክሰን የሚመሩት በርንሌዎች አስቀድሞ ወደ ታችኛው ሊግ መውረዳቸው የሚታወስ ሲሆን ፣ ባለፈው ሳምንት ከአስቶን ቪላ ጋር 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት መለያየታቸ…
👍2❤1🔥1
16 May 2026, 16:14 UTC184 viewsread 6 August 2026 Photo
ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ
*****
በዌምብሊ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ቼልሲን 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት በመርታት የ2025/26 የውድድር ዓመት የኤፍኤ ካፕ ባለቤት ሆኗል።
በስፔናዊ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ፣ በጨዋታው ላይ የታየውን ስልታዊ የበላይነት ወደ ድል በመቀየር በክለቡ ታሪክ ሌላ የክብር ምዕራፍ አስመዝግቧል።
ምንም እንኳ የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋንጫውን ለማሸነፍ እስከመጨረሻው ደቂቃ ድረስ ብርቱ ፉክክር ቢያደርግም፣ በ72ኛው ደቂቃ ላይ አንትዋን ሴሜንዮ ያስቆጠራት አስደናቂ ብቸኛ ግብ የሰማያዊዎቹን የዋንጫ ተስፋ አክሽፋለች።
ይህ ወሳኝ ድል ማንችስተር ሲቲ በውድድ…
10 May 2026, 17:52 UTC333 views1 reactionsread 6 August 2026 Photo
አርሰናል ዌስትሀም ዩናይትድን በማሸነፍ ይበልጥ ወደ ዋንጫው የቀረበበትን ውጤት አስመዘገበ
*****,
በ36ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በለንደን ደርቢ አርሰናል ዌስትሀም ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በለንደን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሌአንድሮ ትሮሳርድ የማሸነፊያዋን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።
ከወሳኙ ጨዋታ ወሳኝ ሦስት ነጥብ ያገኘው አርሰናል የሊጉን መሪነት አጠናክሮ ሲቀጥል ነጥቡን 79 አድርሷል።
መድፈኞቹ ከ22 ዓመት በኋላ የሊጉ ሻምፒዮን ለመሆን የሚቀሯቸውን ሁለት ጨዋታዎች ብቻ ማሸነፍ ይጠበቅባቸውል።
👍1
9 May 2026, 16:02 UTC239 viewsread 6 August 2026 Forwarded from @EBCNEWSNOW
እናት! ቃላት የማይገልጿት...
************
ዓለም ብዙ ቋንቋዎች አሏት፤ ነገር ግን በሁሉም ቋንቋዎች ውስጥ ትርጉሙ የማይለወጥና ድምፀቱ የማይቀየር አንድ ጣፋጭ ቃል አለ... 'እናት!'
እናት ማለት ተራ ቃል አይደለም። መዝገበ ቃላት ሊፈቱት የማይችሉት ረቂቅ ትርጉም ነው፤ እናት የሕይወት መጀመሪያ፣ የፍቅር ምንጭ እና የጽናት ተምሳሌት ናት፡፡
ራስን በመርሳት ለሌላ ሰው መኖር የሚችል ማን አለ? የገዛ ህመምን ደብቆ የልጅን ሳቅ መምረጥ፣ የራስን ረሃብ ችላ ብሎ ለልጅ ማብላት... እነዚህ የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮች በሙሉ ለእናቶች ተችለዋል፡፡
እናት ማለት በጨለማ ውስጥ ብርሃን የምትሆን፣ በድካም ውስጥ ብርታት የምትሰጥ፣ እንዲሁም ዓለም ፊቷን በምታዞ…
9 May 2026, 03:54 UTC243 views1 reactionsread 6 August 2026 Photo
ማንችስተር ሲቲ ከ ብሬንትፎርድ፣ ሊቨርፑል ከ ቼልሲ
*****
በ36ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ሲቲ ብሬንትፎርድን ያስተናግዳል። ከኤቨርተን ጋር ነጥብ መጋራቱን ተከትሎ የሊጉን ዋንጫ የማንሳት ዕድሉ ሙሉ በሙሉ ከእጁ የወጣው ማንችስተር ሲቲ፣ አሁንም ያለውን ጥቂት ዕድል ለመጠቀም እና በአርሰናል ላይ ጫና ለማሳደር ወደ ሜዳ ይገባል።
ሆኖም ዘንድሮ ጠንካራ የውድድር ጊዜ ያሳለፈው ብሬንትፎርድ፣ የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎን ለማግኘት እየታገለ በመሆኑ ጨዋታው ለሲቲ እጅግ ፈታኝ እንደሚሆን ይጠበቃል። በተለይ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶን ቪላ በዩሮፓ ሊግ እና በኮንፈረንስ ሊግ ለፍጻሜ መድረሳቸውን ተከትሎ፣ በቀጣይ ዓ…
👍1
7 May 2026, 17:23 UTC187 views1 reactionsread 6 August 2026 Forwarded from @EBCNEWSNOWPhoto
የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከለባቸው ቦታዎች የትኞቹ እንደሆኑ ያውቃሉ?
********************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የምርጫ ቅስቀሳ ሥነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 33/2018 አንቀጽ 11 መሰረት የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከለባቸው ቦታዎች እና ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፦
1) በሚከተሉት ቦታዎች የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግም ሆነ የምርጫ ቅስቀሳ ጥሪ ማድረጊያ ቁሳቁሶችን መለጠፍ፣ ማስቀመጥ ወይም በማንኛውም መንገድ ማስራጨት የተከለከለ ነው።
ሀ) ቤተ ክርስትያኖች፤
ለ) መስጊዶች፣
ሐ) ወታደራዊ ካምፖች እና ፖሊስ ጣቢያዎች፤
መ) በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ፅ/ቤቶች አካባቢ
ሠ) የመማር ማስተማር ሂደት ተግባር እየተከናወነ በሚገኝበት ወቅት በት…
👍1
6 May 2026, 05:10 UTC167 views1 reactionsread 6 August 2026 Forwarded from @EBCSPORTchannelPhoto
አርሰናል ከ20 ዓመት በኋላ በሻምፒዮንስሊግ ለፍጻሜ ደረሰ
****
አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽፍጻሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል አትሌቲኮ ማድሪድን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሷል፡፡ በኤምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ቡካዮ ሳካየማሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሯል፡፡
በመጀመሪያው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታበስፔን አንድ አቻ ተለያይቶ የተመለሰው አርሰናል በድምር ውጤት 2 ለ 1 በማሸነፍ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
በዚህ ዓመት በሻምፒዮንስ ሊግአንድም ጨዋታ ያልተሸነፈው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በአውሮፓ ትልቁ የክለቦች ውድድር ከ20 ዓመት በኋላ የደረሰበትም ምሽት ሆኗል፡፡
አርሰናል በቡዳፔስት በሚደረገውየፍጻሜ ጨዋታ ከባየር ሙኒክ እና ፒኤስጂ አሸናፊ የሚገና…
👍1
Showing the 12 most recent of 12 posts we hold for @Ethiopian_Radio. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.