11 Aug 2026, 15:15 UTC497 views1 reactionsread 12 August 2026 Photo
ጨዋታ ፖድካስት
****
በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ የራሳቸውን አሻራ ካሳረፉ ግለሰቦች አንዷ ናት።
በአሁኑ ሰዓት የላይቤሪያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆነችው ኢንስትራክተር ሰላም ዘርዓይ የጨዋታ ፖድካስት እንግዳችን ናት።
ነገ ረቡዕ ከረፋድ 4:00 - 5:00 ሰዓት በኢቲቪ መዝናኛ እና በዶትስትሪም አማራጮች ይጠብቁን።
https://t.me/EBCSPORTchannel
#ጨዋታ_ፖድካስት #ebcsport
🥰1
11 Aug 2026, 13:54 UTC600 views2 reactionsread 12 August 2026 Photo
"ለአዲሱ የውድድር ዓመት በሚገባ ተዘጋጅቻለሁ" — ፍሎሪያን ቪርትዝ
**************
የሊቨርፑሉ ጀርመናዊ ተጫዋች ፍሎሪያን ቪርትዝ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጋር በሚገባ መላመዱንና ለሁለተኛው የውድድር ዘመን በከፍተኛ ተነሳሽነት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
ባለፈው የውድድር ዓመት በ116 ሚሊዮን ፓውንድ ከባየር ሌቨርኩሰን ሊቨርፑልን የተቀላቀለው የ23 ዓመቱ አማካይ፣ በመጀመሪያው ዓመት ቆይታው 7 ግቦችን በማስቆጠርና 10 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ተስፋ ሰጪ የሚባል ጊዜን አሳልፏል።
ቪርትዝ የጀርመን እና የእንግሊዝ ሊጎች የጨዋታ ስልት የተለያየ ቢሆንም፣ አሁን ግን የሊጉን ጠንካራ ፉክክር በሚገባ ስለተረዳ ለተሻለ ውጤት ዝግጁ መሆኑን ተ…
🔥2
11 Aug 2026, 12:04 UTC649 views1 reactionsread 12 August 2026 Photo
ቼልሲ የአርጀንቲናዊውን ተጫዋች ዋጋ ይፋ አደረገ
********************
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የኤንዞ ፈርናንዴዝ የመሸጫ ዋጋ 120 ሚሊዮን ፓውንድ መሆኑን አስታውቋል።
ኤሊየት አንደርሰንን ክብረወሰን በሆነ 116 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ ያስፈረሙት እንዲሁም ከአዩብ ቡኣዲ ጋር በግል ጥቅማጥቅም ዙሪያ ከስምምነት የደረሱት ማንቸስተር ሲቲዎች የተጫዋቹ ዋነኛ ፈላጊ ናቸው።
ኤንዞ በጥር ወር 2023 ነበር ከቤኔፊካ በ106 ሚሊዮን ፓውንድ በሆነ ዋጋ ከቤኒፊካ ቼልሲን የተቀላቀለው።
https://t.me/EBCSPORTchannel
#EPL #PremierLeague #Chelsea #Enzo #sports #football #EBC
❤1
11 Aug 2026, 10:33 UTC655 views2 reactionsread 12 August 2026 Photo
ፒኤስጂ ጃፓናዊውን ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተስማማ
***************
የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ፒኤስጂ ዚዮን ሱዙኪን ከፓርማ በ35 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም ተስማምቷል።
ተጫዋቹ በፈረንሳዩ ክለብ የአምስት ዓመት ውል የሚፈርም ይሆናል።
ሱዙኪ በ23ኛው ዓለም ዋንጫ ላይ የጃፓን ብሔራዊ ቡድንን ወክሎ ድንቅ ብቃቱን ማሳየቱ ይታወሳል።
በተለይም ሉዊስ ኤንሪኬ ግብ ጠባቂው በእግሩ የመጫወት ላቅ ያለ ብቃት ስላለው፤ እርሱን ወደ ክለባቸው ለማምጣት ፍላጎት አሳድረው ቆይተዋል።
በእዮብ ተሰማ
https://t.me/EBCSPORTchannel
#PSG #parissaintgermain #sports #football #EBC
❤2
11 Aug 2026, 09:42 UTC652 views4 reactionsread 12 August 2026 Photo
ሀሪ ኬን የወርቅ ጫማ ሽልማት አሸነፈ
****
የባየር ሙኒክ እና የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ሃሪ ኬን የ2025/26 የውድድር ዘመን የአውሮፓ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ነው የወርቅ ጫማ ሽልማት አሸንፏል።
የ33 ዓመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ለክለቡ ባየር ሙኒክ እና ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በሁሉም ውድድሮች በድምሩ 73 ግቦችን አስቆጥሯል።
ሀሪ ኬን በ2026 የዓለም ዋንጫ ለሀገሩ እንግሊዝ 6 ግቦችን በማስቆጠር ብሔራዊ ቡድኑ 3ኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
በጀርመን ቡንደስሊጋም 36 ግቦችን በማስቆጠር የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው።
ኬን ባየርን ሙኒክን በተቀላቀለበት ዓመትም በተመሳሳይ 36 ግቦችን በማስቆጠር ሽልማ…
❤2🔥2
11 Aug 2026, 08:35 UTC675 views2 reactionsread 12 August 2026 Photo
"ጂያኒ ኢንፋንቲኖን ከኃላፊነታቸው ማንሳት ትልቅ ስህተት ነው" — ዶናልድ ትራምፕ
********************
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፊፋው ፕሬዝዳንት ጃኒ ኢንፋንቲኖ ከስልጣን ከተነሱ "ትልቅ ስህተት" እንደሚሆን ተናግረዋል።
ትራምፕ ኢንፋንቲኖን "ድንቅ መሪ" ሲሉ የገለጿቸው ሲሆን፣ በእርሳቸው አመራር የ2026 ዓለም ዋንጫ ከመቼውም ጊዜ በላይ እጅግ ስኬታማና በአራት እጥፍ ትርፋማ ሆኗል ብለዋል።
ኢንፋንቲኖ ከኃላፊነታቸው ከለቀቁ ፊፋ ዳግመኛ እንደ አሁኑ ስኬታማና ትርፋማ ሊሆን እንደማይችልም አስጠንቅቀዋል።
ምንም እንኳ ኢንፋንቲኖ ከአህጉራዊ ማኅበራት ተቃውሞ ቢገጥማቸውም፣ ትራምፕ ግን ለፕሬዝዳንቱ ያላቸውን ጠንካራ ድጋፍ በማህበራ…
❤1🤬1
11 Aug 2026, 07:37 UTC711 views2 reactionsread 12 August 2026 Photo
ሚኪ ቫን ደ ቬን በቶተንሃም የሚያቆየውን አዲስ ውል ተፈራረመ
**************
ሚኪ ቫን ደ ቬን ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ጋር ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ለመቆየት ተፈራርሟል።
የቶተንሃሙ ዋና አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ስለ ዝውውሩ አስተያየት ሲሰጡ፣ ቫን ደ ቬን በአውሮፓ ካሉ ምርጥ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቾች አንዱ መሆኑንና ለቡድኑ ስኬት አስፈላጊ የሆነው ብቃትና ስነ-ልቦና እንዳለው ገልጸዋል።
አሰልጣኙ አክለውም፣ ተጫዋቹ ውሉን ማደሱ ክለቡ ለወደፊት ለሚገነባው ጠንካራ ቡድን ትልቅ መነቃቃት የሚፈጥርና ተጫዋቹ በክለቡ ራዕይ ላይ ያለውን እምነት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።
https://t.me/EBCSPORTchannel
#EPL #Premie…
👍1🔥1
10 Aug 2026, 16:42 UTC870 viewsread 12 August 2026 Photo
አሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌ ለ39 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ
***
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው መስከረም ወር ለሚያደርጋቸው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ 10 የመጀመርያ ሁለት ጨዋታዎች ዝግጅት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለ39 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።
ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል ከ20 ዓመት በታች ናሽናል ካምፕ ላይ የሚገኙ 6 ተጫዋቾች ተካተዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዓርብ ነሐሴ 8 ከ8፡00 ጀምሮ በጁፒተር ሆቴል በመሰባሰብ ዝግጅት እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል።
https://t.me/EBCSPORTchannel
#EthiopianBroadcastingCorporation
10 Aug 2026, 14:02 UTC902 views1 reactionsread 12 August 2026 Photo
ግብ አስቆጥሮ ደስታውን ሲገልጽ ጉዳት የገጠመው ተጫዋች እና የተሰረዘው ግብ
***
በብራዚል ከፍተኛ ሊግ የኮሪቲባው ተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ጃሲ ማራንሃኦ ከቻፔኮይንሴ ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ በጭንቅላቱ ግብ ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን ለመግለጽ ሲሞክር ያልተጠበቀ ጉዳት አስተናግዷል።
የ29 ዓመቱ ተከላካይ ወደ ደጋፊዎቹ በመሮጥ የማስታወቂያ ሰሌዳውን ዘሎ ሲያልፍ፣ በሌላኛው በኩል ወደ ተጫዋቾች መልበሻ ክፍል በሚወስደው ጥልቅ መተላለፊያ ጉድጓድ ውስጥ ተዘቅዝቆ ወድቋል።
በዚህ ድንገተኛ አደጋ በቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፣ ከእረፍት መልስም በጉዳቱ ምክንያት ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል።
ተጫዋቹ ስለ ሁኔታው ሲናገር "ግቡን ካስቆጠርኩ በኋላ ደስታዬን…
❤1
10 Aug 2026, 12:07 UTC883 views2 reactionsread 12 August 2026 Photo
አርሰናል ቡድኑን ለማጠናከር በዝውውር መስኮቱ የሚያደርገውን ጥረት ይቀጥላል - ሚኬል አርቴታ
**
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸውን ይበልጥ ጠንካራ ለማድረግ አሁንም አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም "እየጣሩ" መሆኑን ገለጸዋል።
ይህን አስተያየት የተሰጡት ክለቡ በጥብቅ ይፈልገው የነበረው ብራዚላዊ ኮከብ ቪኒሲየስ ጁኒየር በሪያል ማድሪድ ለመቆየት አዲስ ውል መፈረሙን ተከትሎ ነው። አርሰናል በቅርቡ ብሩኖ ጊማሬሽን በ75 ሚሊዮን ፓውንድ ከኒውካስል ቢያስፈርምም፣ ቡድኑ በቅድመ ውድድር ጨዋታዎች ላይ በተከታታይ የተጓዘበትን የውጤት ማጣት ለመቀልበስ አሁንም ተጨማሪ ጥራት ያላቸው ተጫዋቾች እንደሚያስፈልጉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።
በተለይም ክለቡ በግ…
❤1🔥1
8 Aug 2026, 16:59 UTC488 views6 reactionsread 9 August 2026 Photo
በወዳጅነት ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ፒኤስጂ አቻ ተለያየ
****
በቅድመ ውድድር ዘመን የወዳጅነት ጨዋታ የአውሮፓ ሻምፒዮኑን ፒኤስጂ የገጠመው ማንቸስተር ዩናይትድ 1 አቻ ተለያይቷል።
ጨዋታው በተጀመረ በ2ኛው ደቂቃ ሴኔጋላዊው ኢብራሂም ምባዬ ፓሪስ ሴንት ዠርሜንን ቀዳሚ ቢያደርግም፤ 32ኛው ደቂቃ ላይ ካሜሩናዊው ብሪያን እምቡሞ ያስቆጠራት ግብ ዩናይትድን አቻ አድርጋ ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።
https://t.me/EBCSPORTchannel
#manchesterunited #PSG #preseason #FriendlyMatch #football #sports #EBC
❤6
8 Aug 2026, 15:57 UTC603 views6 reactionsread 9 August 2026 Photo
''ለአርሰናል የቻልኩትን ለማበርከት ቃል እገባለሁ'' - ብሩኖ ጊማሬሽ
****
በዛሬው ዕለት አርሰናልን በይፋ የተቀላቀለው ብሩኖ ጊማሬሽ "መድፈኞቹን በመቀላቀሌ በጣም ደስተኛ ነኝ" ብሏል።
''ቃል እገበለሁ ፣ የእኔን ምርጡን ነገር እሰጣችኋለሁ፣ የእናንተው ተፎካካሪ ነኝና መቼም እጅ አልሰጥም" ሲል ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።
በርካታ የሚታወሱ ነገሮችን አብረን እንደምንሰራ ተስፋ አደርጋለሁ ሲልም ብራዚላዊዉ ተጫዋች ተናግሯል።
የአርሰናል የልብ ምት ይሆናል ተበሎ የሚጠበቀዉ ጊማሬሽ የተከላካይ አማካይ፣የመሀል አማካይ እና የሳጥን ዉስጥ ተጫዋች በመሆኑ አበርክቶቱ የጎላ ይሆናል ተበሎ ታምኖበታል።
ተጫዋቹ የ39 ቁጥር ማሊያን በመልበስ በአዲሱ የውድድር ዓ…
🔥5😁1
Showing the 12 most recent of 34 posts we hold for @EBCSPORTchannel. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.