1 Sept 2026, 09:11 UTC393 views13 reactionsread 1 September 2026 መቼስ መፅሐፍ መጻፍ እና ማሳተም ፅንስ ከመገላገል ያነሰ ደስታ አይኖረውም። ወንድማችን ፊሊሞን ነጋ(@ownkin)ጌታ ረድቶት የመጀመሪያ መፅሐፉን ሊያሳትም ነው ። በመፅሐፉም ላይ ደቀመዝሙርነት ፣ የመስቀል ማዕከልነት ፣ ለወንጌል ያለ መቃጠል እንዲሁም በርካታ ጠቃሚ ሀሳቦች በቆንጆ አማርኛ ተሞሽረው ቀርበዋል ። ፀሀፊው ለመፅሀፍ ቅዱስ ጥግት ያለ ፤ ጤናማ ስንመለኮትን የሚያራምድ ፤ ለቤተክርስቲያን ሸክም ያለው ፤ ተልዕኮ እና ደቀመዛሙርነት ጩኸቱ የሆነ ፤ በክርስቶስ መስቀል የተብሰከሰከ መልካም ምስክርነት ያለው አገልጋይ ነው ። በፀሎትም ሆነ በቻላችሁት ነገር ከአጠገቡ እንድትቆሙ እንዲሁም ለገቢያ በሚወጣበት ጊዜ መፅሐፋን በመግዛት እንድታተርፉ የአክብሮት ጥሪ…
🔥12🥰1
1 Sept 2026, 08:51 UTC53 views7 reactionsread 1 September 2026 Forwarded from @cgfsdPhoto
''አብሰክስከን'' የሥነ-መለኮትን ጥልቀት ከእረኛዊ ልብ እና ርህራሄ ጋር አዋህዶ የያዘ፣ የወጣቱን ትውልድ መንፈሳዊ ጥማትና የቤተክርስቲያንን ወቅታዊ ጥሪ በትክክል የተረዳ ድንቅ ጥራዝ ነው። ወንድማችን ፊልሞን ነጋ ክርስቶስንና የመስቀሉን እውነት በማዕከልነት አቁሞ፣ ትውልዱ ከላይ ላይ መንፈሳዊነት ወጥቶ በጌታ ፊት እንዲብሰከሰክ ያቀረበው ጥሪ እጅግ ወቅታዊ ነው። እያንዳንዱ አማኝ፣ አገልጋይና የነገዋ ቤተክርስቲያን ተስፋ የሆነ ወጣት ሊያነበው የሚገባ ወቅታዊ የመንፈስ ቅዱስ ጥሪ ነው!"
እስራኤል ቴዎድሮስ
(የቃሉ አስተማሪ )
❤7
4 Aug 2026, 08:12 UTC195 views11 reactionsread 1 September 2026 Forwarded from @ahav3
ወንጌል የእግዝሀብሔር የምህረት ደብዳቤ ነው✨
❤11
31 Jul 2026, 09:38 UTC272 views12 reactionsread 1 September 2026 ያለ መንፈስ ቅዱስ ዳግም መወለድ የለም ፣
ያለ መንፈስ ቅዱስ ወደ እግዚአብሔር መመለስ የለም ፣ ያለ መንፈስቅዱስ ክርስቶስንና ሥራውን ማወቅ የለም ፤ ያለ መንፈስ ቅዱስ ለሁሉ ነገር መካከለኛ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ትኩረት ማድረግ አንችልም ። መንፈስ ቅዱስም ከመጣበት ዓላማ ውጪ ስንጮኽለት ደስ አይሰኝም ። ክርስቶስን ከመጣበት ዓላማ ውጪ ስንፈልገው ደስ እንደማይሰኝ ሁሉ ።
- ተገኝ ሙሉጌታ -
❤10👏2
27 Jul 2026, 19:57 UTC312 views5 reactionsread 1 September 2026 https://youtu.be/7wLPhLG0JQE?si=0zExX_JwzaRwE0aF
❤5
21 May 2026, 17:25 UTC635 views30 reactionsread 1 September 2026 አቤቱ እንደ ማርታ ለምትውተረተር ነፍሳችን ከብዙ መሮጥ ይልቅ እንደ ማርያም እግርህ ስር መቀመጥ መልካም ዕድል እንደሆነ አስተምራት ፤ ከመውተርተር ለማታርፍ ነፍሳችን እግራችን ሰብረህ በትከሻህ መንጣለልና ጠረንህን ለምዶ መቀረትን በረከት አርገህ ስጣት 🙏
❤25🙏5
20 May 2026, 16:23 UTC454 views6 reactionsread 1 September 2026 File
File, posted without a caption
❤5🔥1
7 May 2026, 12:03 UTC567 views15 reactionsread 1 September 2026 በል ንገረኝ ለምን ሸጠህ ያ ይሁዳ
እንዴት ችሎ መምህሩን አንተን ከዳ
ባበላከው ባስተማርከው ከጠዋቱ
መሸጥ ሆነ መጨረሻው በምሽቱ
😭7❤5🥰3
7 May 2026, 06:15 UTC576 views11 reactionsread 1 September 2026 ክፍል 3 ፦ የሙሴ ወንበር
ማቴዎስ ወንጌል 23:2-3
² “የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል።
³ ስለዚህ የሚነግሯችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ጠብቁትም፤ ነገር ግን እንደሚናገሩት አያደርጉምና ተግባራቸውን አትከተሉ።
፨ በክርስትና ህይወት እንዲሁም በክርስትያናዊ አገልግሎት ውስጥ የኖሩትን መስበክ በመቀጠልም የሰበኩትን መኖር ጥያቄ ውስጥ በማይገባ መልኩ አስፈላጊ ነው ። አገልግሎት ከህይወት ተፋቶ መቆም የማይችል በህይወት ሲታይ እየደመቀ እና እያበራ የሚቀጥል ጉዞ ነው ። ይህ እውነት ሆኖ ሳለ አገልጋይ በህይወት የሚደክምበት ፤ ያወራውን ሳይኖር ፤ ያልኖረውን ሲሰብክ ሊናይ እና ልናስተውል እንችላለን ።
፨ በኢየሱስ ክርስቶስ …
❤9🔥1🤝1
5 May 2026, 06:03 UTC418 views9 reactionsread 1 September 2026 ክፍል 2 ፦ ለኔም ነው
ኤፌሶን 5:25-27
²⁵ ባሎች ሆይ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳትና ራሱንም ስለ እርሷ አሳልፎ እንደ ሰጠ፣ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤
²⁶ በቃሉ አማካይነት በውሃ ዐጥቦ በማንጻት እንድትቀደስ፣
²⁷ እንዲሁም ጕድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም አንዳች እንከን ሳይገኝባት ቅድስትና ነውር አልባ የሆነች ክብርት ቤተ ክርስቲያን አድርጎ ለራሱ ሊያቀርባት ነው።
፨ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ጌታችን ክርስቶስ ኢየሱስ ቤተክርስቲያንን የፊት መጨማደድ ፣ ጉድፍ ፣ እንከን ሳይገኝባት ቅድስት እና ነውር አልባ እንድትሆን አካሉን የሚያንፅበት እንዲሁም የሚመግብበት እና የሚቀድስበት አንዱ መንገድ ነው ። ይህን ካልን ዘ…
❤🔥7❤1🫡1
4 May 2026, 14:47 UTC313 views10 reactionsread 1 September 2026 ክፍል 1 ፦ ልበ-ቤርያ
የሐዋርያት ሥራ 17:11
የቤርያ ሰዎች ከተሰሎንቄ ሰዎች ይልቅ አስተዋዮች ስለ ነበሩ፣ “ነገሩ እንደዚህ ይሆንን?” እያሉ መጻሕፍትን በየዕለቱ በመመርመር ቃሉን በታላቅ ጕጕት ተቀብለዋል።
፨ ከምስባክ ለምንሰማው ለእያንዳንዱ ትምህርት ሁሉ እንዲሁ አሜን ማለት እና ሳይመረምሩ መቀበል መፅሐፍ ቅዱሳችን ያላስቀመጠልን ኢ - መፅሃፍቅዱሳዊ ሀሳብ ነው ። መፅሐፍቅዱሳችን የሚናገር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናነር እንዳለ ሁሉ የሚስማም እንደ እግዚአብሔር ቃል ከሆነ ይስማ ብንል መፅሐፍቅዱሳዊ ጨዋነትን ያልለቀቀ ፍቱን ሀሳብ ነው ። ስለዚህ እንደ ቤርያ ሠዋች አስተዋይ በመሆን ነገሩ እንዲዚህ ይሆንን እያሉ መጻሕፍትን በመመርመር ከፈሪሳውያን…
❤9💯1
4 May 2026, 14:34 UTC311 views5 reactionsread 1 September 2026 የእግዚአብሔር ቃልን እንዴት እንስማ?
በክርስቶስ ኢየሱስ በማመናችን ካገኘናቸው በረከቶች መካከል የጌታ የኢየሱስ ቤተክርስቲያን ተጠቃሽ ናት ። ታዲያ በቤተክርስቲያን ውስጥ የተለያዩ ለህብረቱ መታነፅ የሚናከወኑ እልፍ መርሃግብሮች አሉ ። ግንባር ቀደም ሆኖም የሚጠቀሰው የቃለ እግዚአብሔር አግልግሎት ነው ። አብዛኛውን ጊዜ የምንማረው እንዴት ቃለ እግዚአብሔርን እንደምንሰብክ ነው እንጂ እንዴት ቃለ እግዚአብሔርን እንስማ የሚል አይደለም ።
፨ ሆኖም ግን የእግዚአብሔር ቃል አሰባበካችን ብቻ ሳይሆን አሰማማችንንም ልናስተካክለት የተገባ ነው ። ስለዚህም የእግዚአብሔርን ቃል ከምስባክ በምንሠማበት ጊዜ ልንስማ የሚገባበትን አግባብ በተወሰኑ ነጥቦች አስቀምጠን…
❤5
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @Bibliophagos. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.