10 Jan 2023, 08:07 UTC920 viewsread 9 August 2026 " አይ ዘመን"
( ግዮናይ ነኝ)!፧
ብረት በገለባ ወገቡ ሲሰበር:
ሰነፍ እያቅራራ ጀግና ሰው ሲቀበር:
ምነው ይሄን ታ'ምር ባላየነው ነበር።
ቅል ድንጋይን ሰብሮ በታየበት ዘመን:
ግድየለም እስከዚያው እንኑር በጎመን።
.................................................
ጊዜ የጣለውን ጊዜ እሰከሚያነሳው:
ጅብ እየገነነ ይሞታል አንበሳው።
እስከተፈቀደ እንደዚህ ቢኖርም:
ሁሉም ወደ ቦታው መመለሱ አይቀርም።
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
@yfonkowa
Signed 𝖐𝖊 𝖑𝖊𝖚𝖑 ለማ҉ ር҉ ያ҉ ም҉
17 Aug 2022, 13:22 UTC≈1,130 viewsread 9 August 2026 አላውቅም 😂
መሳቅ ግን ምንድነው እኔ አላውቅም ስቄ
መረዳት አቃተኝ ጠይቄ ጠይቄ
አልቅሼም አላውቅም ምንድነው ማልቀስ
አንገት አቀርቅሮ ከአይን እንባ ማፍሰስ
አፍቅሬም አላውቅም አይገባኝም ጥቅሙ
በፍቅር የመክነፍ በፍቅር የመስጠሙ
በልቼም አላውቅም ጠጥቼም ለብሼም
አመስግኜ አላውቅም ረግሜም ወቅሼም
ኖሬም እኮ አላውቅም ምንድነው መኖር😜
ይህን ግጥምስ መች ፃፍኩኝ ጨብጬ ብዕር 😜
✍✍✍✍✍ በ Birukti
@yfonkowa
@Tirsite_mikael
Signed Burikti Yefonkowa
17 Aug 2022, 13:20 UTC951 viewsread 9 August 2026 የሌት ማሕሌት
(በእውቀቱ ስዩም)
ትንሽ ቆየት ብሎ ፥ ኮረንቲው ይጠፋል
እሱን ተከትሎ፥ደምኖ ያካፋል
ከናፍቆትሽ በቀር፥ ሁሉ ነገር ያልፋል ::
አሁን መብራት ጠፋ ፥ ተረኛ ነን አይደል
ቁና ይዠ ቀረብሁ፥ ጨለማ ሲታደል ፤
እያገላበጠ ብቻነት አመሰኝ፥
“ ዝናቡ እየጣለ ጋራ ጋራውን
ጎርፍ ያመጣሽ ‘ንደሁ ልጠብቅ ጎርፉን “
የሚል እንጉርጉሮ፥ በድንገት ታወሰኝ ::
ግን ይሄ ትውስታ
አራራይ ትዝታ
ለቆሰለው ልቤ፥ መዳኒት አልሆነም
ያባቶቼ ዘፈን፤ ለኔ አልተዘፈነም፤
ማዶ ዝናብ ዘንቧል፤
ዶፉን ተከናንቧል-
-እንጦጦ-ዲልዲላ
በገፈጅ ይመስል ፥ቀበናም ቢሞላ
ምንም አያመጣም፤ ከ’ድፍ ውሀ ሌላ
እሳት ነው ፍጥረትሽ፥ ከውሃ ጋ አትኖሪም
አንቺ መብረቅ እንጂ፥ ጎርፍ አትሳፈሪ…
Signed Burikti Yefonkowa
9 Aug 2022, 20:09 UTC884 viewsread 9 August 2026 ያንድ ምሽት ናፍቆት
ዛሬ ታምራለች ጨረቃ
ፊትሽን ፊቷ ላይ ፣ እንደ ጭንብል አጥልቃ
እንሆ እኔም ቆሚያለሁ
የዛፉን መልክ መልኬ አድርጌ
በሩቅ ማየት ተፈቅዶልኝ
መንካቱን ግን ተነፍጌ
[ በእውቀቱ ስዩም ]
@yfonkowa
@Tirsite_mikael
Signed Burikti Yefonkowa
24 Jul 2022, 17:44 UTC958 viewsread 9 August 2026 እኔ ሆይ ተይ በቃሽ
እኔ ሆይ ተይ በቃ እራስሽን አትደልይ
ገብቶሽ እንዳልገባው እውነቱን አትደልይ
ለማይዘልቅ መውደድ ለማይከርም ፍቅር
በግዜሽ በእድሜሽ መቀለዱ ይቅር
እርቀሽ ተቀመጭ ከወረት አብሮነት
ያለፈው በቃ አልፏል ኑሪ አሁን የእውነት
እኔ ሆይ እሺ በይ
የቆምሽበት ቦታ አይመጥንም ላንቺ
እውነቱን ተቀበይ ትችያለሽ በርቺ
ሼን
#እናት
@Yfonkowa
@tirsite_mikael
Signed Burikti Yefonkowa
21 Jul 2022, 17:15 UTC854 viewsread 9 August 2026 ያመጣል መንገድ፣ ይወስዳል መንገድ
መንገድ ዓይኑ ይፍሰስ አይባልም ደርሶ
የወሰደውን ሰው ያመጣል መልሶ
#ኢንት
@yfonkowa
@Tirsite_mikael
Signed Burikti Yefonkowa
20 Jul 2022, 12:07 UTC783 viewsread 9 August 2026 Forwarded from @Mahder_Kasahun
.
.
አ ን ዳ ን ዴ መኖር ግራ ይገባናል.. ለምን እንደምንኖር. ለማን እንደምንኖር. እንዴት እንደምንኖር ሳይቀር ይጠፋብናል.. ግን ደሞ ገብቶንም ይሁን ሳይገባን መርጠንም ይሁን ተመርጠን መኖር ይቀጥላል.. "በቃቹ!" እስኪለን መኖር ይቀጥላል............
🦋 #ዮቶራዊት🦋🦋..
Signed Burikti Yefonkowa
19 Jul 2022, 20:17 UTC762 viewsread 9 August 2026 ........ቃልሽ ቀን ነበረው........
------- --------
ከጎጆው አጠገብ በረንዳው ላይ ቆሞ
ስለሷ እያሰበ ደጋግሞ ደጋግሞ
የጻፈውን ግጥም እያነበበችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው 😢😢
.
.
‘’ቃልሽ ቀን ነበረው…
ቃልሽ ቅን ነበረው…
ቃልሽ ቀን ገደለው…’’
የሚለውን መግብያ ዘጠኝ ጊዜ አንብባ
ቃሏንና ቀኗን አንድ ላይ አስባ
መአልትና ሌቱን አንድ ላይ ሰብስባ
.
.
የገደለችውን ቀን ልክ እንዳወቀችው
የናፈቀው ፊቷን በእንባዋ አጠበችው❤️❤️
‘’ህይወት ውጣ ውረድ የትሙ ብዙ ነው
ቀን የገደልሽውም አውቀሽ ሳታውቂ ነው
.
.
.
በፀሀይቱና በጨረቃ መሀል
በሰዓታት እጣ በቀን ማታ ክፍል
ከአንደኛው ትንፋሼ ቀ…
Signed Burikti Yefonkowa
18 Jul 2022, 11:26 UTC717 viewsread 9 August 2026 .........ሲነጋ❤️❤️❤️
ስለምንወዳቸው ፤ስለምናከብራቸው ፤ቦታ ስለምንሰጣቸው፤ ስለዋሉልን ፤ ስለተረዳናቸው ... ፦
የምንሰጣቸውን ክብር ፤ መውደድ፤ የበዛ ትህትና፤ ገብቶን እንዳልገባን የምንሆነውን፤ የምንለግሰውን ..... ።
ሞኛ ሞኝ ሆነን ከመሰላቸው ፤
ለራሳችን ካለን ትንሽ ክብር የመነጨ ሲመስላቸው ፤ ሲያሳንሱን ... ።
ግርግር ሳንፈጥር ፤ ሳንጨረጨር ፤ ሳናብራራ ሳይጠይቁን የሰጠናቸውን ሳንጠይቅ መንጠቅ ነው ያለብን !!
© Adhanom Mitiku✍
@Yfonkowa
@saktawa
Signed Burikti Yefonkowa
16 Jul 2022, 07:42 UTC723 viewsread 9 August 2026 Photo
በዚህች ቀን ነበር በምጥ የተጨነቅሽው
በዚህች ቀን ነበር ማርያም ትማርሽ የተባልሽው
በዚህች ቀን ነበር ከማንም በፊት ያየሽኝ
በዚህች ቀን ነበር እኔ ለአንቺ አንቺ ለኔ የተሰጠሽኝ
በዚህች ቀን ነበር እማ አምጠሽ የወለድሽኝ
አመሰግናለሁ እናቴ😘😘
HBD to me😍😍
@yfonkowa
@saktawa
Signed Burikti Yefonkowa
9 Jul 2022, 18:50 UTC698 viewsread 9 August 2026 እቴዋ መነኩሲት
___
እኔ ምንም አልልም
አላወራምም..
ዝምም አልልም..
ቀን እጂ (እቴዋ ) ሰው ሰውን አይጥልም!
ባወራም ባወራም ማውራትም አልችል፣
ዝም ብዬ በምስር
ዝም ብል ዝም ብል፣
ባዶ ትንፍሽ ብቻ በባዶ መዋለል
ተልሚድ ሁኖ መዋል፣
ባዶ ጨረቃ ፈርቶ በባዶ መገልገል፣
ባዶ ጥላ ይዞ በጨለማ ማታ በጥላ መጠለል፣
ሲመሳጠር ጊዜ ከሰው ሲወዳጅ፣
ይሆናል ገመድ ይከዳል ከደጅ፣
እቴዋ ገዳሜ ቀበጢት ዋልፈሰስ፣
እቴዋ መነኩሲት ሂያጅ መጪ በፈረስ፣
ምነው ልጓሙ በወዝሽ ዳዊትሽ አደፈስ..
ገብስ አጣ ወይ እግርሽ ፥ከደጅሽ የሚያደርስ፣
...ኧረ ያንቺስ መሞልከስ...
_
ግዕዝ ሙላት
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት
@yfonkowa
@yfonkowa
@yf…
Signed 𝖐𝖊 𝖑𝖊𝖚𝖑 ለማ҉ ር҉ ያ҉ ም҉
6 Jul 2022, 17:26 UTC664 viewsread 9 August 2026 Photo
(ል) ብ_ ስ ል
____
የለበሺው ገበር ነፅቶ መስታወቱ፣
ይሄው ተዋደድኩኝ እኔም ከጥቁረቱ፣
ክረምት መጣ ብዬ ስንቴ ተጨንቄ፣
ሁሉም እንዳምናው
ደርቆ እንደሚቀር እኔ ምን አውቄ፣
አይጠበቅ ነገር ሚስማሩ ጌታ ነው፣
መዶሻ ራስ መቶት ክፍት ጥርስ ነቀለው፣
ብዬ ስተርብሽ አልገባሽም ስል
ከጅረቴ ሼራ ጥቁር ሚዛን ስስል፣
መቼ ክረምት ገብቶሽ
ደመና ሲባዝል
ውሃን እንደሚያዝል፣
ብስል ነገር ለካ በጣምም ሲበስል፣
ሞኙ እንደቁራኛ ተሳስሮ ከስርስር፣
አይገባም ሰላምታ ሲዳር ከልብ ጥል፣
ስደግስ ልሞሸር ከነምናምንቴው፣
ለአንቺ በሰልኩ ላልሽው፣
አይታይሽ ለካ
ዳሱን እንደጣልኩ ወጡን ሳስበስለው፥
እኔ እጂ የተሞኜው፥
ሙሽራ ሆንኩ ስ…
Signed 𝖐𝖊 𝖑𝖊𝖚𝖑 ለማ҉ ር҉ ያ҉ ም҉
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @yfonkowa. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.