18 Jun 2024, 16:29 UTC317 views7 reactionsread 6 August 2026 አዝናለሁ አልወደቅኩም!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
አንድ ኀሙስ እንደቀረው፣
የብሶት ዜማ የማንጎራጉረው፤
ስለጠፋኝ አይደለም. . .
መንገድ ስለቀረሁ!
ቀናነት ሳይከብድ፣
መኾን ሲቻል መልካም፤
ተንኮል ለመጎንጎን፣
ለደከሙት ድካም. . .
"እሪ!ኩም! ዘመዳ!
"ዘመዳ እሪ!ኩም!"
እኔ ግን. . .
አዝናለሁ! አልወደቅኩም!
.
እበቅላለሁ እያልኩ. . .
በአፍ-ጢሜ ስተከል፤
ማቆጥቆጥ ሲመስለኝ፣
ከሥሬ መነቀል፤
ከአረም ጋራ ኾነ. . .
የእኔ አበቃቀል!
ሆድ ባይብሰኝም. . .
"እሪ!ኩም! ዘመዳ!
ዘመዳ እሪ!ኩም!"
አዝናለሁ! አልወደቅኩም!
.
ግፊያና ግፍተራ የፍቅር መሰለኝ፤
እኔ እንደሁ' ስወድ. . .
ወትሮም ዓይን የለኝ!
ዝቅ ማለት ጎዳኝ፣
መች ዐውቃለሁ ብልጠት?…
👍6❤1
Signed ሀታን አባቴ
31 Jul 2023, 05:25 UTC520 viewsread 6 August 2026 Photo
ለዛሬ ...8
(✍️ሀታን አባቴ)
ውሎአችን እንደአጀማመራችን ነው የሚባል አባባል አለ ፣ ጥሩ ቁርስ የጥሩ ቀን ጅማሮ ነው እንደሚባለው፣ ዳግሞ የምንኖርበት ቀን ለጨመረልን ንጋትን እንድናየው ላደረገን አምላክ ተመስገን ተመስገን🙏
ድንገት እየተራመዳችሁ ጫማችሁ ውስጥ ጠጠር ገብቶባችሁ ያውቃል? ከዛ አረማመዳችሁ እንዴት ሆነ ? ቶሎ አወጣችሁት ወይስ? ቆይ እዛ ጋር ስደርስ ስቀመጥ ምናምን እያላችሁ ያለምቾት ተጓዛችሁ? ይኼን ወደ ህይወታችን እናምጣው በህይወታችን ሳናስበው የገቡ ጠጠሮች አሉ አረማመዳችንን ምቾት የነሱ ቆይ ቆይ እያልን ያሰነበትናቸው፣የሚያስነክሱን ምቾት የሚነሱን፣ ጠጠሩ ሳናስበው ያካበትነው አስተሳሰብ ወይም ልምድ ይሆናል አውጥተን እንጣለው እና መ…
Signed ሀታን አባቴ
14 Jun 2023, 15:00 UTC412 views1 reactionsread 6 August 2026 ለዛሬ ...7
(✍️ ሀታን አባቴ)
ዛሬህ ውድ ስጦታህ ናት
አዲስ ቀን ሲሰጥህ አዲስ ተስፋ አዲስ እድል እየተሰጠህ ነው፣ የተሰጠህን እድል በማይሆን ነገር አታባክነው እያንዳንዱን ደቂቃ አጣጥመህ ኑረው❤፣
የሚገፉህ ሊጥሉህ የሚፈልጉ ባንተ ደስተኛ መሆን የሚያማቸው ፣ ሲያልፍልህ አይናቸው የሚቀላ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፣ በዛው ልክ ያንተን መከፋት ማየት የማይፈልጉ ደስታህ የሚያስደስታቸው ማግኘትህን የሚሹ ስትወድቅ አንተን ለማንሳት እጃቸውን የሚዘረጉልህ መኖራቸውን አትዘንጋ
አዲስ ቀን ውስጥ ሁሉም አዲስ ነው፣ አዲስ እድል 😍ትላንት የደከምክበትን ውጤት የምታይበት ይበልጥ እንድትሰራ የሚያነሳሳህ አዲስ እድል😍
አዲስ ቀን ሲሰጥህ ትላንት የሰራኸውን ስህተት እንድታ…
👍1
Signed ሀታን አባቴ
31 May 2023, 08:38 UTC390 viewsread 6 August 2026 ለዛሬ .....6
(✍️ሀታን አባቴ)
አንዳንዴ የሆነ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ እንገባለን፣ እያየን አናይም ፣ እየሰማን አንሰማም፣ እየኖርን ያለነው የተመቸን ይመስለን እና አዲስ ነገር አንፈልግም፣ ያለንበትን ምቾት ለማስጠበቅ ወይ ከተኛንበት ላለመንቃት ጭልጥ ያለ ሰመመን ውስጥ እገባለን ፣ የሆነ ቀን ላይ ከተኛንበት የሚያነቃን የሆነ ደወል ይደወላል ፣ የረሳነውን የሚያስታውስ፣ ያሳዘናቸውን ልቦች እንድንጠግን እድል የሚሰጠን ደወል፣ በቂ ጊዜ ሰጥተናቸው የማናቃቸውን ነገሮች ጊዜ እንድንሰጣቸው የሚያደርጉን ደውሎች አሉ፣
በህይወትህ ሁሉም የሚመጣው ለምክንያት ነው ፣ እየሆነ ያለው ሁሉ፣ እየተሰማን ያለው ድምፅ እኛን ለማንቃት ነውና ነቃ እንበል ።
ልብህን ለ…
Signed ሀታን አባቴ
3 May 2023, 05:03 UTC353 viewsread 6 August 2026 ለዛሬ....5
✍️(#ሀታን- አባቴ)
ፍቅር እና ጥላቻ
ፍቅር እና ጥላቻ ይምታታብኛል ልበል የሆነ ጊዜ እርር ብለን የወደድናቸው ከለታት ባንዱ ቀን እንጠላቸዋለን፤ ያለነሱ መኖር መሞት የሆነብንን ሰዎች ካየናቸው የምንሞት እስኪመስለን እንጠላቸዋለን ይኼ ጥላቻ ከፍቅር ነው እንዴ የሚመጣው ነው ፍቅር ከመጥላት ነው የሚመጣው🤔 በህይወታችን የሆኑ ሰዎች አሉ በህይወታቹ ሲገቡም ሲወጡም አይታወቃቹም፣
ለራሳችን የሰጠነው ቦታ ትልቅ ከሆነ በኛ ቀን ውስጥ በሚያልፉ ሰዎች ህይወታችን አይመዘንም መኖራቸው ያልጠቀመን ሰዎች መሄዳቸው ሊጎዳን አይችልም ፣ ሊያስተምረን እንጂ❤
ዛሬ ከተቸረን እፁብ ድንቅ ስጦታ በላጩ ነው ስንኖር ጭማሪ ልንሆን እንዳይሆን እኛ በመኖራችን በራሳችን…
Signed ሀታን አባቴ
22 Sept 2022, 13:31 UTC528 viewsread 6 August 2026 ✍️#ሀታን አባቴ
በግጥም እንደ መምጠቅ
በቃላት እንደመራቀቅ
እንደ አዋቂ አዕምሮ
እንደ ሰነፍ እሮሮ
ስለ አንተ ለመፃፍ
ሀሳብ ግር የሚለኝ
የሚያጥረኝ ሚረዝመኝ
ስላንተ ልፅፍ ስል
ሚታክተኝ ሚያደክመኝ
.
.
.
.
ነገርስ🤔
Signed ሀታን አባቴ
22 Sept 2022, 05:11 UTC471 viewsread 6 August 2026 ለዛሬ 2
#ሀታን አባቴ✍️
ከጨለማ ይልቅ ንጋት ለውጣችን ሰላም ይሰጣል እንደዚሁም ከህይወታችን ጨለማው ክፍል ሳይሆን ብርሀናማው ይበልጥ ተስፋ ይበልጥ ሀሴት ይበልጥ ደስታን ይሰጠናል ይህን ስል ለአንዳንዶቻችን የህይወት ስህተቶቻችንን እንደጨለማ ጊዜ ልንቆጥረው እንችላለን ለአንዳንዶቻችን ደግሞ ባለማወቅ ወይ በአላዋቂነት ያሳለፍናቸው ጊዜ ወይ ሌላም ሌላም ብቻ ጨለማ የምንለው የህይወት ገፅ ይኖረናል ።
ቀናችንን የሚያበላሹት ወይ የሚያሳምሩት ሌሎች ናቸው በመልካም ንግግር እና ተግባራቸው ቀናችንን ብሩህ ሲያደርጉት በእኩይ ተግባር እና ንግግራቸው ቀናችንን ያጨልሙታል በየትኛውም ሁኔታ የኛን ቀን ሌላ ሰው እንዲኖረው አንፍቀድ እንዲያናድዱን እንዲያበሳጩን ቀናችን…
Signed ሀታን አባቴ
21 Sept 2022, 05:07 UTC435 viewsread 6 August 2026 ለዛሬ 1
#ሀታን አባቴ ✍️
ቀናችንን ውብ ለማድረግ በጎ አስተሳሰብን ወደኛ እናምጣ በአዎንታዊ ነገር እንጀምረው እኔ እችላለው ፣እኔ ልዩ ነኝ፣ እኔ ቆንጆ ነኝ፣ እኔ ታታሪ ነኝ ፣ እኔ ጠንካራ ነኝ የሚሉ አስተሳሰቦችን እናዳብር መልካምነት ዋጋ የለውም ይባላል ግን አለው መልካምነት ዋጋው የህሊና እረፍት የነፍስ ሀሴት የህይወት ስንቅ ነው። ለዛሬ ትንሽን ምፅዋት በመስጠት መልካምነትን እንጋራ ❤
ካሳለፍነው ትላንትም ሆነ ካላየናት ነገ በእጃችን የተሰጠች ዛሬያችን አሁናችን በላጭ ናትና ዛሬን እንኑረው
ሰናይ ዛሬ❤
Signed ሀታን አባቴ
16 Sept 2022, 05:04 UTC459 viewsread 6 August 2026 ተኝቶ አለመነሳት አለና ንጋትን እንድናይ ላደረገን ተመስገን🙏 አልሀምዱሊላህ
ልክ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ቀናችንን እናየዋለን ዛሬ በግራዬ ነው መሰል የተነሳሁት ወይ በቀኝ ጎኔ ነው የተነሳሁት እንደምንለው ማለት ነው ቀናችን የሚያምረው ወይ በጥሩ ቁርሳችን ወይ በጥሩ ዱዐችን አልያ ከቤት ለስራ ተጣድፈን ስንወጣ ረዥሙ የታክሲ ሰልፍ አበሳጭቶን ቢሮ ስንደርስ የአለቃችን ግልምጫ ቀናችንን ያጨልምብናል ግን ግን ሲመስለኝ ቀናችንን የማሳመር የማብራት እድሉ እኛው እጅ ላይ ነው ቀናችንን በአሪፍ ነገር እንጀምረው
ሰናይ ቀን 😁
ካልተሰጠን ነገም ሆነ ካሳለፍናት ትናንት ዛሬያችን ባላጭ ናትና ዛሬን እንኑረው❤
Signed ሀታን አባቴ
19 Aug 2021, 08:15 UTC970 viewsread 6 August 2026 ምልጃ ከፈጣሪ🙏
✍️ሀታን አባቴ
ያልተረገዘ ቀን ያላማጡት ውልደት
ያልታከኩት እከክ ያልቆረጡት እትብት
እኔ ምልህ ፈጣሪ.....
እኛ ካለንበት ምድር ካልካት አለም
አንድም የተቃና የዘመም የለም
እኮ ካለንበት ከንቱ ካልካት አለም
ሙሉ ሳቅም የለም
ሙሉ ለቅሶም የለም
ጎዶሎውን ሊሞላ የሞላን ነው ማጉደል
እንዲህ ነው አሳሩ ይህኛው እንዲሞላ ያኛውን መበደል
ከሌለው ላይ ቀምቶ ያለውን ማካበት
ከሚጎርሰው ነጥቆ ለራስ ኑሮ ማበጃጀት
እና እንደነገርኩክ ያለንባት ምድር
ስቃይ የእለት ጉርሷ ዋይታ ነው ዜማዋ
አዕላፋት ወጥተው ቀሩ ባዶ ሆኗል ጉያዋ
እናልህ ፈጣሪ
እኛ ካለንበት ከንቱ ካልካት ምድር
ጥላቻ ወሮናል አትታይም ፍቅር
መዐት ነው የካበን
ባክህ ተለመነን
ከከበበን መዐት…
Signed ዊልዳን ያህያ
10 Aug 2021, 04:56 UTC816 viewsread 6 August 2026 ሰላም ውዶች ተኝቶ አለመነሳት አለና ንጋትን እንድናይ ላደረገን ተመስገን 🙏
✍️(#ሀታን-አባቴ)
ህይወትን ልክ የቅብብሎሽ ዱላ አድርገህ አስብ፣
በህይወትህ ተደሰት ያለችህ ጊዜ ዱላውን ጨብጠህ ከኋላኛው ለሚመጣው የምታስረክብበት ብቻ ያለችው ክፍተት ናት ያንተ መጎተት የኋላኛውንም የሚመጣውንም ይጎዳል ፣ የኋላኛው ትላንት ዱላውን ላንተ ሰጥቶካል የሚመጣው ነገ እየጠበቀክ ነው 😍 ነቃ በል፣ ተንቀሳቀስ ዛሬ ትላንት አይደለም፣ ትላንትም ዛሬን አይሆንም ፣ ካላወካት ነገም ሆነ ካለፍካት ትላንት አሁንክ በላጭ ናትና ተደሰት፣ ለሚያስከፋክ ለሚያስጨንቅህ ነገር ሁላ ቦታ አትስጥ ነገ እጁን ዘርግቶ የያዝከውን ዱላ እስክታቀብለው እየጠበቀህ ነውና ፍጠን የተደሰትክበት…
Signed ዊልዳን ያህያ
24 Mar 2021, 05:51 UTC≈1,690 viewsread 6 August 2026 ከተዘበራረቀው ገፄ 1
አንዳንዴ ግን ደግሞ ሁሌ እንዲህ አስባለው 😯
"ሕይወት ልክ እንደ መፅሃፍ ናት" ማን ነበር ያለው ብቻ ማንም ይበል ማን እኔ ተቀብዬዋለው ስንቶቻችን"ህይወት ልክ እንደ መፅሀፍ ናት " የሚለውን ሰምነተናል ፣ ሰምተንስ አምነናል? ፣ ማመን ብቻቸውን አይደልም የምናሳልፈው እያንዳንዷ ቀን እያንዳንዷ ድርጊት በዛ መፅሀፍ ላይ የተፃፈ ወይም የምንፅፈው ቢሆንስ ብለን አስበን እናውቃለን፣ እኔን ከጠየቃችሁኝ አዎ ነው መልሴ ግን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ገፆቹን አዘበራርቄዋለው...
የተዘበራረቀው ገፅ....
@yetezeberareku
Signed ሀታን አባቴ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @yetezeberareku. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.