13 Oct 2021, 07:52 UTC416 viewsread 9 August 2026 Photo
በፈረንጆቹ 1536 በዛሬው ቀን #ዊሊያም_ቴንድል “መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም ሰው አንብቦ ሊረዳው በሚችል ቋንቋ ይተርጎም” በማለቱና ለዚያም እውነት በመትጋቱ በእንጨት ላይ ተጠርቆ ተቃጠለ!!
የመጨረሻ ጸሎቱ "እግዚአብሔር ሆይ:- የእንግሊዝን ንጉስ ዓይኖች ክፈት" የሚል ነበር::
ዛሬ ሁሉም ሰው መጽሐፍ ቅዱስ በገዛ ቋንቋው ያነባል:: የዘመናችን መሰረታዊው ችግር መጽሐፍ ቅዱስን በቋንቋችን ያለማግኘት ሳይሆን በቋንቋችን የተገኘውን መጽሐፍ እንደምኞታችን ፈቃድ እንዳሻን መተርጎም ነው!!
ዛሬ ዛሬ ለመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛ ትርጏሜ የሚጋደሉና ለዚያ እውነት የሚሞቱ ቴንድሎች ያሹናል!!
"እግዚአብሔር ሆይ የቃሉን ሰባኪዎች እና አንባቢዎች ዓይኖች ለዚህ እውነት ክፈት…
Signed ιllιlı.ıl ιllιlı.ıl @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ lıιllιlı. lıιllιlı.
29 Sept 2021, 08:41 UTC351 viewsread 9 August 2026 ✍ በቃ እንዲያውም አትዘምር
********************
ወዳጄ ሆይ መዝሙር ስትዘምር.......
✍ ክርስቶስን እንጂ ብሶትህን አትዘምር....የክርስቶስን ድል እንጂ ያንተን መከራ ግጥምና ዜማ አትስራለት.....በክርስቶስ ያገኘኸውን ደስታ ዘምር እንጂ በአለም ሳለህ ያለብህን የተሸነፈ መከራ አትቀኝ.....የክርስቶስን ማንነት የመስቀሉን ስራ እውነት ዘምር እንጂ ችግር እየቆጠርክ ስሜትህን አትዘምር.....ኢየሱስን አይተህ ዘምር እንጂ ጓዳህን አይተህ አትዘምር.......ኢየሱስን አይተህ ዘምር እንጂ ያንተንና የጎረቤትህን ኑሮ አወዳድረህ አትዘምር.....የምትጽፈው ዝማሬ መልዕክቱ ኢየሱስ ካልሆነ ስለ ኢየሱስ እስክትጽፍ ድረስ እንዲያውም በቃ አትዘምር!!
✍ …
Signed ιllιlı.ıl ιllιlı.ıl @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ lıιllιlı. lıιllιlı.
6 Sept 2021, 19:01 UTC255 viewsread 9 August 2026 https://youtu.be/ZrmU1ayRz9A
This is the link 👆👆👆👆
U can watch full worship #Endegena nafekegn
Join us at 👇👇👇
@yesemaymaed
Signed ιllιlı.ıl ιllιlı.ıl @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ lıιllιlı. lıιllιlı.
4 Sept 2021, 19:06 UTC252 viewsread 9 August 2026 Video
Live#worship with Hebron Samuel
እንደገና አንተን አልኩኝ እንደገና እንደገና ናፈከኝ እንደገና
@yesemaymaed 👈
@yesemaymaed 👈
Signed ιllιlı.ıl ιllιlı.ıl @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ lıιllιlı. lıιllιlı.
26 Aug 2021, 05:41 UTC270 viewsread 9 August 2026 ✍ የወደድከኝ ጊዜ
*********
ሰማይ የለም ነበር ፣ ገና አልተዘረጋም
ቀን አልተቆጠረም ፣ አልመሸም አልነጋም
ጨረቃ የለችም ፣ በምሽት ላይ ደምቃ
ጸሐይም አታውቅም ፣ ወጥታና ጠልቃ
የወደድከኝ ጊዜ.......
የብሱ ተገላልጦ ፣ ምድር አልተባለም
ውኃ በአንድ ስፍራ ፣ አልተሰበሰበም
ምድር መሽከርከሯን ፣ ገና አልጀመረችም
የሜዳን ቡቃያ ፣ አላበቀለችም
የወደድከኝ ጊዜ.......
ወፎች በሰማይ ላይ ፣ መብረር አልጀመሩም
አራዊቱ ሁሉ ፣ በስም አልተጠሩም
ምድርን ሊያጠጡ ፣ ወንዞች አልፈሰሱም
አሦች በባሕር ውስጥ ፣ አልተንቀሳቀሱም
የመረጥከኝ ጊዜ.......
እኔ እንኳን ራሴ ፣ ገና አልተፈጠርኩም
አንተን አላወ'ኩም ፣ አንተን አልመረጥኩም
ያለነቀፌታ ፣ …
Signed ιllιlı.ıl ιllιlı.ıl @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ lıιllιlı. lıιllιlı.
19 Aug 2021, 19:14 UTC299 viewsread 9 August 2026 ✍ እሠይ!!
************
ፍቅርህን ላወራ ፣ ባንተ መወደዴን
ገና አንተ 'ኮ ብየ ፣ ስከፍት አንደበቴን
ቃላት አቅም አ'ተው ፣ ይልፈሰፈሳሉ
ቃል ለሆንከው ላንተ ፣ ቃል የለም እያሉ
ሽርጉድ ይላሉ ፣ በብዕሬ ጫፍ ላይ
አቦ እሠይ እላለሁ ፣ እኔም ይህንን ሳይ
እሠይ እሠይ እሠይ ፣ እሠይ ለቃል መስነፍ
እሠይ እሠይ እሠይ ፣ ለፍቅርህ መግዘፍ
እሠይ ለመውደድህ
እሠይ ለም'ረትህ
እሠይ ለስጦታህ
እሠይ ለችሎታህ
እሠይ በፍቅርህ ፣ እሠይ ስላዳንከኝ
እሠይ አሳርፈህ ፣ እሠይ ስላስባልከኝ
እያልኩ እጽፋለሁ ፣ ወረቀቴ ይርሳል
የብዕሬ ቀለም ፣ በእምባ ይለወሳል
የልቤን ደስታ ፣ ብዕሬ ይገልጣል
አንተን ካላገኙ ፣ እሠይ ኬት ይመጣል
አሁንም ደሞ እሠይ
ደሞ እንደገና እ…
Signed ιllιlı.ıl ιllιlı.ıl @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ lıιllιlı. lıιllιlı.
15 Aug 2021, 20:11 UTC182 viewsread 9 August 2026 ✍️አንተን የበላ
*************
የአባት መና ፣ ሕያው እንጀራ
ዳግም ላታስርብ ፣ የምትበላ
የሕይወት መጠጥ ፣ የዘልአለም
አንተን ጠጥቶ ፣ መጠማት የለም
ሁሉ አንተ ነህ ፣ በሁሉም አንተ
ስለሞትክለት ፣ ላንተ የሞተ
ሳይጥር ሳይለፋ ፣ ላቡን ሳይዘራ
እንዴት ይራበው ፣ አንተን በላና
ያ ስጋ እንጀራህ ፣ የተቆረሰው
ለኔ ነው ብሎ ፣ ያመነብህ ሰው
ልሙት ቢል እንኳን ፣ አይሆንለትም
አንተን የበላ ፣ ሞት የለበትም
Join us at 👇👇
@yesemaymaed 👈🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
@yesemaymaed 👈🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺
Signed ιllιlı.ıl ιllιlı.ıl @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ lıιllιlı. lıιllιlı.
15 Aug 2021, 19:59 UTC176 viewsread 9 August 2026 File
🎬 Title : ሳንዃዃ
👤 Artist : ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ)
⏰ Length : 05:36 Min
💾 Size : 8.0 Mb
🆕 New : New Album
🎹 Genre : Praise & Worship
💽 Album : እዩልኝ
🎵 Format : Audio Mp4
🔊 Language : Amharic
💿 Quality : HD
® Publisher : Enzemer Tube
📱📲 Share ♻️ Join ♻️ Share
📽 Subscribe Our YouTube Channel : https://www.youtube.com/c/EnzemerTube
📥 Channel: @Enzemer_Tube
@Enzemer_Tube
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
Signed ιllιlı.ıl ιllιlı.ıl @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ lıιllιlı. lıιllιlı.
20 Apr 2021, 15:58 UTC321 viewsread 9 August 2026 ✍ ስለ ማን ልግጠም
********************
በህልውናህ በልዕልናህ
አላምንም ብሎ ፣ ስንቱ ሰድቦሀል
የቁጣ ፈሳሽ ፣ ሳታፈስበት
ቤቱን ሳትቀጣ ፣ ስንቱን ምረሀል
ማንም ተነስቶ ፣ ያሻውን ሲልህ
ውረድ ወይ ፍረድ ፣ ብሎ ሲናገር
እግዚአብሔር የለም ፣ ብሎ እየካደ
ሰነፍ ለሰነፍ ፣ ባንተ ሲማከር
በቁጣ ፈንታ ፣ ምህረት አዝንበህ
ከነቆሻሻው ፣ አቀፍከው ሳምከው
ለኃጢአተኛው ፣ ጻድቁን ሰዋህ
ልጅህን አርደህ ፣ ሰነፉን ማርከው
በቸርነትህ ፣ ንስሀ ገብቶ
በጨለመበት ፣ ብርሃን ሁነኸው
ዳግም ለኃጢአት ፣ ሕያው እንዳይሆን
ምኞቱን ነቅለህ ፣ …
Signed @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ
27 Jan 2021, 08:43 UTC310 viewsread 9 August 2026 ✍ መዳኔ እርግጥ ነው
********************
ኢየሱስ የመስቀል ሞት ሲሞት.......
✍ ሀጥያቴን አስወግዷል? አዎ አስወግዷል!!
✍ ደዌዬን ተቀብሏል? አዎ ተቀብሏል
✍ ህመሜን ተሸክሟል? አዎ ተሸክሟል!!
✍ ስለመተላለፌ ቆስሏል? አዎ ቆስሏል!!
✍ ስለበደሌ ደቅቋል? አዎ ደቅቋል!!
✍ ቅጣቴን ተቀጥቷል? አዎ ተቀጥቷል!!
✍ አብ ቁጣው በርዷል? አዎ በርዷል!!
✍ በኢየሱስ ስራ እረክቷል? አዎ እረክቷል!!
✍ እኔን ላይቆጣ ምሏል? አዎ ምሏል!!
✍ በዘላለም ቸርነት ምሮኛል? አዎ ምሮኛል!!
✍ መስቀል ላይ ያልተከፈለ ዕዳ የለም? አዎ የለም!!
እና እኔ 'ምልህ...........
ነጻ ነህ እያለኝ ፣ ከፍሎ የጨረሰው
ምን አርበደበደኝ ፣ እዳ እንዳ…
Signed @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ
21 Jan 2021, 05:32 UTC260 viewsread 9 August 2026 ትንቢተ ኢሳይያስ 2:5
እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ ኑ፤ በእግዚአብሔር ብርሃን እንመላለስ።
እየተከሰተ ስላለው ነገር መረጃን አውቆ መገኘት ጥሩ እና አስፈላጊ ነው። ሆኖም፣ የዜናው መለዋወጥ ወይም አስደንጋጭነት ህይወታችንን እንዲመራልን መፍቀድ የለብንም። የተቤዠን፣ የወደደን አባት አለን። እኛ በጌታ ዘንድ የታወቅን ነን እና እኛም እናውቀዋለን፡፡ ተስፋውን፣ ሰላሙን ቀምሰናል፤ ይህን መርሳት አይገባንም። አዕምሮአችንን በእርሱ እውቀት እና ሰላም እንሙላ። መረጃን እንቀበል፣ ነገር ግን ደግሞ የእኛን መሠረት፣ ቤዛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን መሠረታችንን እንዳንረሳ ወይም እንዳናረክስ ማረጋገጥ አለብን። ፍርሃት፣ ድንጋጤ ወይም እርግጠኛ አለመሆን እንዲገሽ አትፍቀጂ። …
Signed @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ
16 Jan 2021, 17:29 UTC222 viewsread 9 August 2026 ነህምያ 4:2
የፍርስራሽ ክምር የሆነውን ድንጋይ ነፍስ ሊዘሩበት ይችላሉን?
ከአድካሚ የስራ ቀን በኋላ ወደ ጊዜያዊ ማረፊያዬ እየሔድኩ ሳለሁ በውስጤ ብዙ ሃሳብ ይመላለስ ነበር። ተስፋ የላቸውም ብዬ የምቆጥራቸው ነገሮች ሲበዙ ከፈረሰው ነገር ባሻገር ማየት አቃተኝና ጥልቅ የሆነ ሃዘን ዉስጥ ገባሁ። ተስፋዬም እያሽቆለቆለ ሲሄድ ድምፅ አልባ በሆነ መቃተት ወደ እግዚአብሔር ተማፀንኩ።
ወዲያውኑም አንድ ቃል ወደ ውስጤ መጣ። ነህምያ እና ሕዝቡ ኢየሩሳሌምን እንደገና መስራት እንደጀመሩ እነ ሳናባላጥ በሰሙ ጊዜ እንዲህ ብለዉ ተሳለቁባቸው “እነዚህ ደካማ አይሁድ ምን እያደረጉ ነው? ቅጥራቸውን መልሰው ሊሰሩ ነውን? መስዋዕት ሊያቀርቡ ነውን? በአንዲት ጀንበር ሠርተው …
Signed @ᒍᝪᔑᗴᑭᕼ.Ꭲ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @yesemaymaed. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.