5 Apr 2026, 13:56 UTC145 views9 reactionsread 8 August 2026 #ምን_ኖሮት_ነው?
:
ጥዑም አይደል ይጎረናል
ልቤ ሲቀኝ እንጉርጉሮ፤
የት አድሎት ዘመም የሚል
ድገምልኝ የሚል ጆሮ።
ዜማው ልዝብ ቃሉ ቀሊል
ሽው ብሎት ሰማው ለሚል
አሉታ እንጂ የሚሂሰው
ፈገግ አይልም የሰማኝ ሰው።
:
መቼት የለው ወይ አላባ
አያንፅም አይገነባ።
አይታጭም አያውቅ እስቲ
በሀ ዘፈን አርቲ ቡርቲ።
:
ስላቅሽን ቀድሞ እያየው
ጠል ላይፈራ የጨቀየው
ስትጥዪኝ እንዳይደድር
እንዳገኘው ጨፌ ምድር
እየጠራኝ ዘጠኝ ሞቱ
አዜምኩልሽ የት አባቱ።
:
ተቀሽሮ ቃል ተኩሎ
ዕዝንሽ ላይ ተኮልኩሎ
ገዢ ድርሰት ተነባቢ
ሲንቆረቆር ሳትሳቢ
ውስጥሽ ሰርፆ ሳይሰማ
በጄ ብለሽ ያዳመጥሺው
ምን ኖሮት ነው የኔ ዜማ?
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@getem
@getem
@getem
@yenee…
❤7👍2
Signed Henock
30 Oct 2023, 05:36 UTC≈1,320 views20 reactionsread 8 August 2026 #ገባኝ
:
:
:
ውበት ግርማሽ እንደ ቀላይ
ቢኬድ ቢታይ አይጨረስም፤
እጅን በአፍ ማስጫን እንጂ
መገለጫ የለሽም ስም።
፡
፡
ዓይቶሽ ዓይኑን ለመለሰው፤
ወቸው ጉድ ነው
ሚተርፈው ሰው።
ጠልቆት ሀሳብ
ዳምኖት ድማም፤
ወይ አይሰማም
ወይ አይለማም።
፡
፡
ሀረግ ስንኝ ለመቋጠር፤
ይደገፋል ጋን በጠጠር፤
ብዬ ባይሽ እኔው ለኔው፤
ልምሻ ዳዳው ፈሊጥ ቅኔው።
፡
፡
ቃል ቃል አጣ
ሆሄም ሞተ፤
አንገት ደፋ ተማረከ
ስነጥበብ ተገመተ።
፡
፡
አፈቀርኩሽ እጅ አልሰጥም
« ሞት አይቀርም » እያባባኝ፤
አንቺን ባጣም ውበት ገባኝ።
አይቆጨኝም!
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita
@yeneeyita
👍11❤4🔥3🥰2
Signed Cyrus
25 Oct 2023, 06:39 UTC≈1,160 views21 reactionsread 8 August 2026 #ያልፋል_አይደል?
:
:
:
እየደለብኩ እየሰባው፤
መሸ ነጋ ወጣው ገባው።
እንደዘበት እንደኑረት፤
ሽቅብ ፍስስ የዕድሜ ጅረት።
ያለ ቁዝም ያለ ስጋት፤
አሁን ምሽት አሁን ንጋት።
ልብ ሳይለኝ ሰቀቀኑ፤
እንደወትሮ ጋመ ቀኑ።
፡
፡
ኖርኩኝ፤
ሄድኩኝ፤
የት እንዳለው ሳላስታውስ፤
እንዲው ንጉድ እንዲው ፍስስ።
፡
፡
መጓዜንም አላበቃው፤
እግር ሲያጥረኝ ድንገት ነቃው።
ልቤ ቢናኝ፤
ዞሬ ስቃኝ፤
ተንደረደርኩ ልደላደል፤
ከቦኝ ኖሯል ለካስ ገደል።
፡
፡
እንዴት ገባው እንዴት ልውጣስ፣
ማን ያድነኝ ምን አውቄ፤
የሚያኖረኝ አንዱ ተስፋ፣
« ያልፋል አይደል ? » ሚል ጥያቄ።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@yeneeyita
@yeneeyita
@yeneeyita
❤15👍6
Signed Cyrus
5 Oct 2023, 13:54 UTC≈1,080 views22 reactionsread 8 August 2026 #ምኗ_ነው?
:
:
:
ምኗን ነው ግን የወደድከው
አልፎ አልፎ ይለኛል ሰው፤
እንዲ ብሎ ሚጠይቀኝ
የሆነ ብቃት እንዳነሰው፤
መጠይቁ ያሳብቃል፤
የልቡ ዓይን ያልበራለት
ወትሮስ ፍቅርን እንዴት ያውቃል።
:
:
ብዙ ማዕረግ ብዙ ገድል
የቀለም ቀንድ ጥልቅ ሀሳቡ፤
እስካልበራ እውር ልቡ፤
ፍቅር ወርሶ እስካልቋጨው፤
ሰው አይሆንም የምድር ጨው።
:
:
ሆነሽልኝ ዝርግፍ ጌጤ፣ ወርቀዘቦ፣ ተክህኖ፤
አዋቂው ሰው ለጋ ሆኖ፤
እንዲያ ብሎ ሲጠይቀኝ
ያደርገኛል ደርሶ ብግን፤
የሚጠላው ምኗ ነው ግን?
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
(@yeneeyita)
@yeneeyita
@yeneeyita
@yeneeyita
❤15👍4🥰3
Signed Cyrus
17 Sept 2023, 11:24 UTC≈1,230 views17 reactionsread 8 August 2026 #ተነድፈሽ_ክበሪ
:
:
እኔ አልነደፍም የሚለው ፉከራ፤
በገዛ አንደበትሽ በኩራት ሲወራ፤
ካንዴም አስር ጊዜ ደርሶ ሰምቻለው፤
ትክክል ነው ብሎም የሚያጎበጉብ ሰው በቅርብ አይቻለው።
:
:
እውነት ነው ወይ ብዬም በዙሪያሽ ያሉትን ዞሬ ሳጤናቸው፤
መላከፍ ነው እንጂ መንደፍ የማይችሉ ተራ ዝንቦች ናቸው።
:
:
አፍኜው ነው እንጂ ድሮም ያንቺ ነገር ያንገበግበኛል፤
ከንቱ ፉጨት ከቦሽ መኩራትሽ ገርሞኛል።
:
:
ከ ዐጀቦችሽ አንፃር መደምደምሽን ሳይ አናገረኝ እንጂ የሆዴ መከፋት፤
ባንቺ አልተጀመረም አደባባይ ቆሞ በጀሌ ተከቦ አጉል ጉራ መንፋት።
:
:
እውነት እውነት ስልሽ ያለመነደፍሽን ሚስጥሩን ላወቀው፤
ልክ እንደኔ ሁሉ ሆድ ቢብሰው እንጂ ቅንጣትም አይደንቀው።
:…
👍11❤2👏2🔥1🙊1
Signed Cyrus
8 Aug 2023, 04:35 UTC≈1,280 views15 reactionsread 8 August 2026 #አልገባሽም
:
:
:
ስንለያይ ጊዜ
የየብቻው ጉዞ ገና ሲጠነሰስ፤
አብረን የገራነው የጋራችን ፈረስ፤
ትዝታን ሸክፎ ቤትሽ እንደመጣ፤
ከዛም ከደጃፍሽ አራግፎ እንደወጣ፤
የኋሊት ጎትቶ ሆዴን ሊያላውሰው፤
በሰመመን ስትሄጅ ነግሮኛል ያየሽ ሰው።
:
:
ስንለያይ ጊዜ
ህይወት በኛ ስትከር፤
እንዲው እንደ ዘበት ፍቅራችን ሲሰበር፤
የሀዘን ድንኳን ጥለሽ፤
እንዴት ሆነ ብለሽ፤
እንባሽን ስትዘሪ፤
ደግሞም ከራስሽ ጋር ስትከራከሪ፤
ባላይ እንኳን ባይኔ፤
ያየሽ አርድቶኛል ሁሉን ክንዋኔ።
:
:
ስንለያይ ጊዜ
ያቆራኘን ገመድ እንደተበጠሰ፤
የትካዜው ሾተል ስለቱን አስሎ ካንቺ እንደደረሰ፤
ከዚያም አልፎ ተርፎ እንዶነብሽ እዳ፤
ሁሉን ሰምቻለው ያንቺን ሳሎን ጓዳ።
:
:
ስንለያይ …
👍8❤6👏1
Signed Cyrus
2 Aug 2023, 08:55 UTC≈1,200 views9 reactionsread 8 August 2026 #ታምር
:
:
:
ቅንነቷ ጩኸታም ነው
ይዳረሳል ለመንደሩ፤
ፈሊጥ ቅኔ መደርደሩ፤
ለቀባሪው እንደማርዳት፤
ጆሮው ዳባ ያልለበሰ
ሁሉም ሰው ነው የሚወዳት።
፡
፡
መልኳ ደሞ ዝም ያለ ነው
እርግት ጭጭ የረበባት፤
በአርምሞ ላነበባት፤
ውበት እፍስ ስክነት ልቅም፤
አራት ነጥብ ገጿ አያውቅም።
፡
፡
ምትሰማ ዝግ ብላ፤
ምጥን ያለች የምትጎላ፤
ሳትናወዝ የምታምር፤
እኔ ግርም እሷ ታምር።
እወድሻለሁ!
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
@yeneeyita
@yeneeyita
@yeneeyita
@yeneeyita
🔥5❤3👍1
Signed Cyrus
30 Jul 2023, 05:41 UTC≈1,160 views10 reactionsread 8 August 2026 #በዋልክበት_ፍሰስ
:
:
:
እውነትን ሰንቄ ብታትር ብለፋ፤
ሲበሉ እንጂ ማየው የምጎርሰው ጠፋ፤
መልካም የዋልኩለት ዞሮ በኔው ከፋ።
:
:
ድጡን አለፍኩ ስል ማጡ ተከተለ፤
ስንዴ እየተመኘው እንክርዳድ በቀለ።
የ ህሊናዬ ሰላም የክንዴም መፈርጠም፤
ከገዛ ጠላቴ ከሆዴ አልበለጠም።
:
:
ያ ቀናው ጎዳናም ትክክሉ መንገድ፤
አመላላሽ ሆኗል ሀረግ እና ዘመድ።
ትዝብት ዓይኔን ገልጦት ዞሬ ብመረምር፤
ያንዱ ቤቱ ሰማይ ያንዱ ቤቱ ምድር።
:
:
የባለሳምንቱ ወጥመዱ እንዲሰበር፤
ሀቅ አንግቡ እያልኩኝ ስለፈልፍ ነበር።
ለካስ እንዲ ኖሯል ...
ሆድ ሰላም እንዲያድር ልቦናህን መተው፤
በዋሉበት መፍሰስ በዋሉበት ሞልተው።
#ሄኖክ_ብርሃኑ (@yeneeyita)
(@yeneeyit…
😢5👍4👏1
Signed Cyrus
23 Jul 2023, 04:48 UTC≈1,170 views13 reactionsread 8 August 2026 #?
፡
፡
አንቺን ሳስብ፤
ሀሳብ ስስብ፤
ይገርመኛል ስናፍቅሽ፤
ቆይ ግን እስኪ ልጠይቅሽ።
:
:
በመልካም ነው ግን በደ'ና?
ልክ እንደ ሞት የታጣልሽ
ዳግም ዕድል እንደገና።
በቸር ነው ወይ ግን በጥሩ?
መልክ ግብርሽ ምስለኔ አጥቶ
አንዴ ብቻ መፈጠሩ።
በጤና ነው ግን በበጎ?
አንቺነትሽ ያልተገኘው
ካንቺ ውጪ ተፈልጎ?
እንጃ!
:
:
እወድሻለሁ !
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@yeneeyita
@yeneeyita
@yeneeyita
❤5👏4🥰4
Signed Cyrus
13 Jul 2023, 06:47 UTC≈1,270 views15 reactionsread 8 August 2026 #ቸገረኝ
:
:
:
ፉንጋ ሴት አፍቅሬ ቢሆን የነበረው፤
ጥላኝ መኮብለሏ ልቤን ባልሰበረው።
፡
፡
ፉንጋ ሴትስ ሞልቷል፤
ጎራዳ ሴት ሞልቷል፤
ክብረት ለምድሪቱ እንባ ሳግ አያንቀኝ፤
ተለያየን ብዬ ምን ሊያነፋርቀኝ።
አሰፍራኝ አሳር የሄደች እንደሆን ለግዜው ብከፋም፤
በልቤ ምትገባ እራሷን ምትመስል ፉንጋ ሴት አትጠፋም።
፡
፡
መልከቀናም ብትሆን የተጣባቺኝ ሴት ልቤ ፍቅሯን ሽቶ፤
ጥላኝ ጠፋች ብዬ ማቅ አለብስም ከቶ።
፡
፡
መልከቀናም ሞልቷል፤
ቆንጆ ሴትም ሞልቷል፤
ትሂድ ብቻ እንጂ ወላድ ሴት በድባብ፤
ተለያየን ብዬ አይዘልቀኝም ሀሳብ።
ልቧ ቢሸፍትም ፍቅሬን ከማጥ ከታ፤
ይዋል ይደር እንጂ...
ቆንጆ ሴት አትጠፋም ልቤን ምታርፍበት ያቺን ሴት ተክታ።
፡
፡
ምስ አ…
👍7🤔7😢1
Signed Cyrus
19 Jun 2023, 05:17 UTC≈1,240 views9 reactionsread 8 August 2026 #አለማማር_ማማር
:
:
ገጣሚው በግጥሙ ገና ከምርጊቱ
ውበትን ያደንቃል፣
ወረቀት ብዕሩም የቆንጆን ሴት ፀዳል
እልፍ ያንፀባርቃል።
:
:
አንደኛው ገጣሚ፦
:
:
ዐይኖችሽን አይተው ኮከቦች አፈሩ፣
ድንቄም ብርሃን ሆንን ብለው ተናገሩ።
ፀሀይዋም ጠለቀች ባለችበት ቦታ፣
አንቺን ብታይ ጊዜ ተደናግራ ፈርታ።
እውነት እልሻለው ምዬ በዚ ሰማይ፣
ጨረቃም ሻማ ናት ካንቺ አንፃር ስትታይ።
እያለ ይገጥማል እያለ ይፅፋል፣
ቃላትን አዝንቦ ውበትን ያጎርፋል፣
ሰማይ ጠቀስ ግጥሙን በቀለም ይነድፋል።
:
:
ሌላኛው ገጣሚም፦
:
:
ገና ከሩቅ ሳይሽ ይድናል ህመሜ፣
ብሞትም አይቆጨኝ ከንፈርሽን ስሜ።
ባለንጋ ጣቶችሽ የዳበስሺኝ እንደው፣
እንደ እቶን እሳት ነው ውስጠቴ ሚነደው።
ዳሌሽ…
👍6👏2😱1
Signed Cyrus
17 Jun 2023, 04:15 UTC≈1,080 views19 reactionsread 8 August 2026 #ወይናደጋ
:
:
እኔ ቆላ እኔ ደጋ
የሚሞቀኝ የሚበርደኝ፤
ስትቀርበኝ የምቦርቅ
ስትርቀኝ የሚነደኝ፤
ግልፅ ፊቴ ይነበባል
እንቆቅልሽ መች አውቅና፤
ባብሮነቷ ጮቤ ምረግጥ
ከሰው ሳያት የምቀና፤
ሆድ መቋጠር አልችልበት
የልቤን ቃል የምናገር፤
ስታኮርፈኝ የምሻክር
ጥርሷን ስትገልጥ የምሆን ገር።
:
:
እሷ እንደሆን ለዘብተኛ
ስቃ አትስቅ አትጨነቅ፤
ከፋም ደላት ፊቷ ደረቅ፤
ውጭም አልጋ ቤትም አልጋ፤
ለብ ያለች ሴት ወይናደጋ፤
ትውደድ ትጥላኝ ልወቅ በምን፤
ፀሀይ ናት ስል ደግሞ ድምን።
#ሄኖክ_ብርሃኑ
@yeneeyita
@yeneeyita
@yeneeyita
🥰10👍4❤3👏1🔥1
Signed Cyrus
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @yeneeyita. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.