5 May 2026, 06:17 UTC95 viewsread 7 August 2026 +++ ምስካዬ ኅዙናን - ለተበደሉትና ላዘኑት ማረጋጊያ ማጽናኛ ማለት ነው +++
ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ በመገኘት : የሀገራችንን በጣልያን መወረር አቤቱታ ቢያሰሙም : ምንም ተስፋ ሰጪ ምላሽ በማጣታቸው በመንግስታቱ ማኅበር ላይ ተስፋ በመቁረጥ ፊታቸውን ወደ አባቶቻቸው አምላክ በማዞር በጾምና በጸሎት ለመማጸን በማሰብ እንዲሁም የሃይማኖት ችግር እንዳያገኘን የሚያድጉ ልጆቻችን የሃይማኖታቸውን መሠረት እንዳይለቁ በማለት በብፁዕ እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ ፈቃድ ቀደም ሲል በአፄ ምኒሊክ ወደ ኢየሩሳሌም ዴር ሱልጣን ገዳም ተልኮ አገልግሎት እየሰጠ የነበረውን ታቦተ መድኀኒዓለምን ከኢየሩሳለም ወደ እንግሊዝ እን…
Signed Haile Desalegn
5 May 2026, 06:17 UTC95 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Haile Desalegn
20 Jan 2025, 10:13 UTC416 viewsread 7 August 2026 አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ”?
ክብር ይግባውና አምላካችን ይህንን የተናገረው
እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም፡፡ ‹‹አንቺ ሴት››
ሴት የሚል ቃል የፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ
አክብሮ ሲጠራት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ
ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ
ሲል ተናግሮ ነበር ‹‹ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት
ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና
ሴት ትባል›› (ዘፍ ፪÷፳፫) በመሆኑም ጌታ አንቺ
ሴት ማለቱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ
መንሣቱን ለማጠየቅ ነው፡፡ ‹‹ከአንቺ ጋር ምን
አለኝ?›› ጌታም እንዲህ ሲል ውኃውን ወይን
አድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ
ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው፡፡ መልካም ቀና ዘገሊላ በዓል
Signed Haile Desalegn
12 Jan 2025, 07:03 UTC271 viewsread 7 August 2026 የፊታችን እሁድ የሚከበረው
ዓመታዊ ንግሥ በዓል•••
✧ #የአዲስ_አበባ_ደብረ_ነጐድጓድ_ቅዱስ_ዮሐንስና #መካነ_ጐልጎታ_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን።
✧ ጠባቂዬ የዮሐንስ ወንጌላዊ ታቦት በደቡብ ጎንደር ስላለ እርሱ ሳይመጣ እኔ አልነግሥም፡፡ /ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ/
✧ ንግሥት ዘውዲቱ የነገሠችው በምትወደውና ታቦተ ሕጉ አብሯት በማይለየው በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ እለት የካቲት 4 ቀን 1909ዓ.ም. ነው፡፡
✧ ደብረ ነጐድጓድ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያንም አሁን ባለበት ቦታ ላይ የተመሠረተው ጥቅምት 4ና ጥቅምት 25 ቀን 1914 ዓ.ም. ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያኑ አሁን ባለበት ቦታ የተከሉት ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ /1909-1922ዓ.ም./ ሲሆኑ የተመ…
Signed Haile Desalegn
12 Jan 2025, 07:03 UTC415 viewsread 7 August 2026 በኋላ ግን የቤተክህነቱ ባለሥልጣናት ታቦቱን ከአስገባን ዘንድ ንግሥትን ጠርተን ማሳየት ግዴታችን ነው፤ ከአዩት ደግሞ በቤቱ አነስተኛነት መቆጣታቸው አይቀርምና ከዚህ ከፍ ያለ ቤት ብንፈልግ ይሻለናል በማለት በፀበሉ ቦታ ላይ በዘመኑ የተሻለ ነው ተብሎ የሚገመተውን የነጋድራስ ሠርፀ ወልድ ፎቅ ቤትን በማስለቀቅ ጥቅምት 4 ቀን 1914 ዓ.ም. ግርማዊት ንግሥተ ነግሥታት ዘውዲቱ በተገኙበት ለ፪ኛ ጊዜ ታቦተ ቅዱስ ዮሐንስ ከመጀመሪያ የሳር ክዳን ጎጆ ቤት ወደ ሁለተኛው ፎቅ ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡
የመጀመሪያው ሕንፃ ክብ ቤ/ን (ዛሬ የእመቤታችን ቤ/ን ያለበት) የመሠረት ድንጋይ በፊታውራሪ አባ ይሬ ቦታ ላይ በ1924 ተጣለ፤ ከ2ት ዓመታት በኋላም በ1926 ሕንፃ ቤ…
Signed Haile Desalegn
27 Dec 2024, 14:41 UTC224 viewsread 7 August 2026 #መልክአ_ቅዱስ_ገብርኤል
የአሸናፊና የኃይል መልአክ #ገብርኤል_ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ከፍጹም ጥፋት እድን ዘንድ ክንፍህን ጋርድልኝ።
#ወደ_ድንግል የተላክ #ገብርኤል_ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የደስታ ምስራች ተናጋሪ ገብርኤል ሆይ፤ ሰላም ላንተ ይሁን። ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የደስታ አብሳሪ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። የአካላዊ ቃልን የመጸነስ ብሥራት በማኀፀነ ማርያም ላሳደርክ ሰላም ላንተ ይሁን።
በመለአከ ሞት ከመውደቅ የምትታደግ #ገብርኤል_ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አማላጅነትህን በመታመን ተስፋ እናደርጋለንና በመዓልትም በሌሊትም አንተ ጠብቀን አሜን።
Signed Haile Desalegn
12 Dec 2024, 02:45 UTC255 viewsread 7 August 2026 እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከተመረጡ የተመረጠች፣ ከተለዩ የተለየች፣ ከተከበሩ የተከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእናቷ ከቅድስት ሐናና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ከተወለደችበት ዕለት ግንቦት ፩ ቀን ጀምሮ በወላጆቿ ቤት ለሦስት ዓመት ከኖረች በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ታኅሣሥ ፫ ቀን ‹‹በዓታ ለማርያም›› በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡:
ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ‹‹ልጄ ሆይ ስሚ እይ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ ክርስቶስ ውበትሽን /ንጽሐ ባ…
Signed Haile Desalegn
21 Nov 2024, 01:06 UTC281 viewsread 7 August 2026 ✝✞✝ እንኩዋን ለሊቀ መላእክት "ቅዱስ ሚካኤል" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝
✝✞✝ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ✝✞✝
=>ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::
+ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::
+በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ…
Signed Haile Desalegn
18 May 2024, 16:49 UTC396 viewsread 7 August 2026 Video
Video, posted without a caption
Signed Haile Desalegn
9 May 2024, 07:29 UTC415 viewsread 7 August 2026 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
"አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ኾይ!
የብርሃን እናት ነሽና አንቺን ብቻሽን በክብር በምስጋና እናገንሻለን።
የተባረክሽ አንቺ ከመላእክት ትበልጪያለሽ ከደቂቀ አዳምም ትበልጪያለሽ ከአሳቦች ኹሉ ትበልጪያለሽ ገናንነትሽን መናገር የሚቻለው ማን ነው? አንቺን የሚመስል የለምና።
ማርያም ኾይ መላእክት ያገኑሻል ሱራፌልም ያመሰግኑሻል።
በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ አድሮ የሚኖር ጌታ መጥቶ በማኅፀንሽ አድሯልና። ሰውን የሚወድ ወደ እርሱ አቀረበን ክብር ምስጋና ያለው እርሱ የኛን ሞት ተቀብሎ የእርሱን ሕይወት ለኛ ሰጠን ። ቅድስት ኾይ ለምኝልን።…"
🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲
Signed Haile Desalegn
5 May 2024, 15:42 UTC371 viewsread 7 August 2026 ‹‹ከመስቀሉ ወደ ሲኦል በመውረዱ አዳነን፤ በአባታቸው በአዳም በደል በሲኦል ተግዘው የነበሩ ጻድቃንን ፈታ፤ ከሙታን ተለይቶ አስቀድሞ በተነሣ በእውነተኛ ትንሣኤውም አስነሣን፡፡ የንስሐንም በር ከፈተልን፤›› (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ ሃይ. አበ. ፴፮፥፴)፡፡ መልካም የትንሣኤ በዓል
Signed Haile Desalegn
2 Mar 2024, 08:46 UTC501 viewsread 7 August 2026 የዐድዋ ድል በጸሎት ተጀምሮ በጸሎት የተጠናቀቀ ነው !
____
ኢትዮጵያ ሥጋችን ቤተ ክርስቲያን ነፍሳችን ናት፤ ነፍስ እና ሥጋ ደግሞ አንድ ነው፡፡ አገር ያለሃይማኖት፣ ሃይማኖት ያለአገር የለም፤ ኢትዮጵያን ያህል አገር ማጣት እግዚአብሔርን ከሚያህል ጌታ መለየት ሞት ነው፡፡ ሃይማኖትን እና ነጻነትን ማጣት ሽንፈት ነው፤ ስለ አገር፣ ሃይማኖት እና ነጻነት መሞት ደግሞ ክብር ነው፡፡”
“በቀደሙት የጦርነት ታሪኮች ከፍተኛ ጥቃት የደረሰባት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ለሚፈራረቅባት መከራ አንዱ ምንጭ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቀጥተኛ ቅኝ አገዛዝን በመቃወም ሀገራዊ ሉዓላዊነትን እና ነጻነትን ከማረጋገጥ አልፋ ኢትዮጵያዊነት የጥቁሮች ኩራት እና …
Signed Haile Desalegn
Showing the 12 most recent of 19 posts we hold for @yemaryammekenet. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.