6 Aug 2026, 11:13 UTC8 viewsread 6 August 2026 ❣ጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/
🌺ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ ተሰደደ፤ ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡
🌺ጾመ ፍልሰታ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እመቤታችን በዚህ ዓለም ፷፬ ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ጌታችን የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ጥር ፳፩ ቀን ፵፱ ዓመተ ምሕርት አረፈች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው…
Signed A ̤D ̤A ̤M ̤ ̤z ̤ ̤G ̤r ̤e ̤a ̤t ̤
28 Jul 2026, 19:36 UTC27 views1 reactionsread 6 August 2026 "ሰላም ማለት በዙሪያህ ምንም ዓይነት ጫጫታ ወይም ችግር አለመኖር አይደለም። ሰላም ማለት በመከራና በማዕበል መሀል ሆኖ እንኳን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለህን ኅብረት በመጠበቅ በልብ ውስጥ የሚገኝ የሰማይ ዕረፍት ነው። ሰላምን በውጭው ዓለም የምትፈልገው ከሆነ ከቶ አታገኘውም፤ ምክንያቱም ሰላም የሚገኘው በጸጥታና በትሕትና በተሞላ የውስጥ ቤት(ልብ) ውስጥ ነውና።"
ምንጭ፦ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ "በሰላምና በጸሎት ሕይወት ላይ የተሰጠ ትምህርት"
@yaminadabseregela
👍1
Signed A ̤D ̤A ̤M ̤ ̤z ̤ ̤G ̤r ̤e ̤a ̤t ̤
28 Jul 2026, 19:36 UTC26 viewsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed A ̤D ̤A ̤M ̤ ̤z ̤ ̤G ̤r ̤e ̤a ̤t ̤
24 Jul 2026, 15:39 UTC33 views4 reactionsread 6 August 2026 ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች👏 እንደምን ቆያችሁ🙏
❤3🥰1
Signed ᰌ'ღ ꌉέǁ̬ ▄︻̷ ┻ ═━一🚶♂️
27 Jun 2026, 22:52 UTC65 viewsread 6 August 2026 የ አ ሚ ና ዳ ብ : ሠ ረ ገ ላ
አባ ሕርያቆስ እመቤታችንን የአሚናዳብ ሠረገላ አንቺ ነሽ በማለት አመስግኗታል ።
መተርጉማኑ ደግሞ እመቤታችን በአሚናደብ ሠረገላ የተመሰለችበትን ምሥጢራዊ ምክንያት ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ ፦
የአሚናደብ ሠረገላ ልዝብና ፈጣን ምቹ ነበረች እመቤታችንም ለነፍስ ለሥጋ የምትመች በንጽሕና በቅድስና የለዘበች ለምሕረት የፈጠነች አፍጣኒተ ረድኤት ሰአሊተ ምሕረት ምዕራገ ጸሎት ናትና ነው።
« አንቀጸ : ሰላማዊት : ድንግል : ሆይ : ያንቺ : ሰላም ከሁላችን : ጋር : ይሁን : የጌታችን : እናት : እናታችን ማርያም : ሆይ : ለምኚልን : ከደጅ : እንዳንቆም : አማልጂን » !!!
Signed A ̤D ̤A ̤M ̤ ̤z ̤ ̤G ̤r ̤e ̤a ̤t ̤
27 Jun 2026, 22:52 UTC60 viewsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed A ̤D ̤A ̤M ̤ ̤z ̤ ̤G ̤r ̤e ̤a ̤t ̤
19 Jun 2026, 13:50 UTC58 views1 reactionsread 6 August 2026 Photo
🥺አለኝ ትዝታ ከቤት🥺 ❤️🩹ከልጁነቴ
ስትሳሳልኝ እያየው ❤️🩹 🌟ፀንቷል ጉልበቴ ☺️
🤲ልዘምር እንጂ ላመስግን🤲🌹ተላቁን ጌታ
አንተን🌹 💝የሰጠኝ ጠባቂ 💝 🌕በቀን በማታ🌚
የኔ ሩሩህ መላክ ቅዱስ ሚካኤል🥰
❤1
Signed A ̤D ̤A ̤M ̤ ̤z ̤ ̤G ̤r ̤e ̤a ̤t ̤
19 Jun 2026, 08:26 UTC61 viewsread 6 August 2026 የቀን : እረኛ : የሌሊት : ጠባቂ : ቅዱስ : ሚካኤል
#ሰኔ_12_ቀን ቅዱስ ሚካኤል ቅድስት አፎሚያን ከዲያብሎስ መንጋጋ ያስጣለበት እንዲሁም የባሕራንን የሞቱን ጦማር ቀዶ ሠርግ ያደረገበትን እለት ነው።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ልጆቿን ሰብስባ በዓልን ሰርታ በታላቅ ድምቀት ከዓመት ዓመት ታከብረዋለች።
መጋቤ ብሉይ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በተአምራቱ ዘወትር እንደሚጠብቀን ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ እንዲህ እያለ ይመሰክራል ፦
« የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የቀን እረኛ የሌሊት ጠባቂ ክንፎቹ የእሳት የሆነ ዘወትር የሚጠብቀን ቅዱስ ሚካኤል የእውነት የድንኳን ከተማ ነው። » በማለት ተናግሯል።
በዚህ መሠረት ድንኳን ከቀን ሐሩር ከሌሊት ቁር …
Signed A ̤D ̤A ̤M ̤ ̤z ̤ ̤G ̤r ̤e ̤a ̤t ̤
19 Jun 2026, 08:26 UTC37 viewsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed A ̤D ̤A ̤M ̤ ̤z ̤ ̤G ̤r ̤e ̤a ̤t ̤
18 Jun 2026, 20:20 UTC38 viewsread 6 August 2026 ''ኦ ሚካኤል ኦ ሚካኤል ኦ መተንብል፣
ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል፣
ዘእምርኡሳን ርኡስ ወዘእምልዑላን ልዑል፣
ጊዜ ጸዋዕኩከ ቅረበኒ በምሕረት ወሣህል፡፡
''ትርጉም'''
#አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ እኮን። የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ እኮን። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ።
( መልክአ ሚካኤል)
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
❤❤❤❤❤❤❤❤❤
Signed A ̤D ̤A ̤M ̤ ̤z ̤ ̤G ̤r ̤e ̤a ̤t ̤
20 May 2026, 04:16 UTC80 views1 reactionsread 6 August 2026 Photo
#ግንቦት_12
የመምህር ወመገስጽ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የእረፍቱ ቀን፣ የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አጽም እና የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የቃልኪዳን ዓመታዊ ክብረ በዓል ነወ።
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ…
😁1
Signed ᰌ'ღ ꌉέǁ̬ ▄︻̷ ┻ ═━一 █▬█ █ ▀█▀
19 May 2026, 20:36 UTC53 viewsread 6 August 2026 ሙሴ ጸሊም በግብፅ በረሃዎች ውስጥ የሚኖር እጅግ አስፈሪ የሽፍቶች አለቃ ነበር። ቁመቱ ግዙፍ፣ ጉልበቱ ብርቱ፣ ልቡም በነፍስ ግድያና በዝርፊያ የደነደነ ሰው ነበር። ማንም ሰው ስሙን ሲሰማ ይንቀጠቀጣል። አንድ ቀን ግን መንግሥት ሊይዘው ሲፈልግ፣ ሸሽቶ "አስቄጥስ" ወደሚባል የገዳም አባቶች ቦታ ገባ።
በዚያም መነኮሳቱ ሲጸልዩ፣ በሰላምና በፍቅር ሲኖሩ አየ። የእነዚያ ድሆች መነኮሳት ጸጥታና ደስታ የዚህን ጨካኝ ሽፍታ ልብ ነካው። በኃጢአቱ ተጸጽቶ አለቀሰ፤ መነኩሴም ሆነ። ነገር ግን የድሮው የክፋት አጋንንት በቀላሉ አልለቀቁትም፤ በዝሙት፣ በቁጣና ወደ ቀድሞ ሕይወቱ እንዲመለስ በብዙ ፈተና ተሰቃየ። ሙሴ ግን ጾሙን አጠበቀ፣ ሌሊቱን ሙሉ ሳይተኛ በመቆም ይጸልይ …
Signed A ̤D ̤A ̤M ̤ ̤z ̤ ̤G ̤r ̤e ̤a ̤t ̤
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @yaminadabseregela. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.