30 Nov 2023, 13:00 UTC555 views5 reactionsread 9 August 2026 ሁሉም ሲያያት ለአልጋ የሚመኛት ሴት መሆን ስልችት ብሎኛል። ከስሜት ጡዘት በኃላ ጀርባ የሚሰጣት ሴት መሆኔ ደግሞ ስብርብር አድርጎኛል።
ደግሜ ደጋግሜ ራሴን ቀጥቼዋለው! ምርር ... ትክት ብሎኝ 'ሁለተኛ...' እርም ብዬ ምዬ ተገዝቼ ተመልሼበታለው፤ ተመላልሼበታለው!
ራሴን ታዝቤዋለው! ሰው እንዴት? ደግሞ ደጋግሞ ባቆሰለው ነገር ዳግም ለመቁሰል ይሄዳል?
የድሮዋ እኔን አጥቻታለው። ህሊናዬንም በመጠጥ ካላራስኩ የሚንቀሳቀስ ስጋ የለኝም። ለነገሩ የሚሰክር ነፍስ ሲኖረኝ አይደል!
መፈለግን እ'ኮ እፈልጋለሁ! መወደድን ከዛም ሲያልፍ መከበርን! አዝኜ ሳለቅስ የመጀመሪያዋን ማበሻ መሐረብ የሚሰጠኝን፣ የደስታዬ ልክ የለሽ ሳቅ የሚያስፈግገውን ፣ አቅም አ…
👍5
Signed Yabsira Tesfaye
30 Nov 2023, 12:59 UTC442 views1 reactionsread 9 August 2026 ትላንትን መድገም እንዴት ያሰለቻል ነገን ደ'ሞ በተስፋ መኖር!
ኡፍፍፍፍ............
እሱ ምንሽ ነው? ብለው ቢጠይቁኝ መልሴ ሊሆን የሚችለው ዛሬ'ዬ የሚል ነው። አንተ እየኖርኩት ያለሁት ዛሬ ነህ። ትላንቴም ነገዬም እንድትሆን አልፈልግም።
ከትላንቴ ማህደር ሳገላብጥ የማገኘው ትዝታ ብቻ ነው። ያውም መጥፍ ትዝታ! ዘወር ብለው ቢያዩት የማይመለሱበት ትፋት! ታዲያ ምን ብዬ ነው ትላንቴ የማደርግህ?
በነገዬ አልተማመንም። ምን ይዞብኝ እንደሚመጣ አላውቅም። ምን አልባት ሊሰጠኝም ሊነሳኝም ይችላል ግን አላምነውም።
ስለዚህ አንተ ዛሬዬ ብቻ ሁንልኝ! ከእንቅልፌ ስነቃ እንደማያት ፀሐይ ፣ ሲመሽብኝ ደግሞ እንደምትተካው ጨረቃ አሁኔ ሁንልኝ እና ልኑርህ!
…
👍1
Signed Yabsira Tesfaye
27 Nov 2023, 19:07 UTC380 views1 reactionsread 9 August 2026 ይፈራል! ኸረ እንደሚስቴ አስቢና ባሰብሽበት ልዋል ይለኛል.... እንደ እናቱ እያሰብኩ ተቸግሮ እኮ ነው!
በልቶ ያልጠገበ፣ ተቀብቶ ያልወዛ ያህል ይሰማኛል። 'ትክ' ብዬ ሳየው የከሳ ይመስለኛል። ለነገሩ ዐይኔ ነው ያከሳው ዐይን ዐይኑን እያየሁት። የገረጣም የጠቆረም መልክ በአንድ ጊዜ ሰው እንዴት ያያል? እሱ ላይ ግን ይታየኛል።
እንስፍስፍ አንጀቴ ከአጋር ለወላጅ ይቀርባል። አድራጎቴ የእናት ነው። እንደሚስት እኮ ማሰብ እፈልጋለው። ግን እንዲህ አስብ እንዲህ በል አእምሮ አይባል።
... አለ አይደል ሲያመሽ ቀሙት፣ መቱት፣ ደበደቡት፣ ገደሉት ከሚል ጭንቀት ወጥቼ ያመሸው እያመነዘረ ነው ብል እኮ ደስ ይለኛል።
አዎ እሱም ብቻ ሳይሆን እኔም እፈራለሁ! …
👍1
Signed Yabsira Tesfaye
10 Nov 2023, 19:04 UTC336 views1 reactionsread 9 August 2026 🛑 ፃማ 🛑
ክፍል አስራ ሶስት
ትዝታ ከቤት እንደወጣች ብሌን በእፎይታ ሶፋው ላይ ተወረወረች። እዮብ ቢሆን እንደዚች አይነቷን አይደለም ለጓደኝነት ለአይንም ቢሆን ይጠየፋት ነበር ስትል አሰበች። መልካቸው ብቻ ነው ለካ የሚመሳሰለው አለች በልቧ። ምንም ስለአልአዛር የግል ህይወት አያገባኝም! ግን ምን ሲሆን ከእንደዚች አይነቷ ጋር ሆነ? ብሌን ከቅሬታዋ በላይ የሚሰማት ብስጭት መንስኤውን አለማወቋ አሳሰባት። ምን አልባት አልአዛርን እንደ እዮብ ቆጥራው ይሆናል። ወይም የወንድሙ ውለታ ስለሱ እንድትጨነቅ አስገድዷትም ይሆናል። ብቻ ተበሳጭታለች። ማታ አልአዛር እስኪመጣ መታገስ አቃታት።
እንደምንም መሸና አልአዛር ቤት መጣ። እራት ካቀረበች በኃላ "ትዝታ የምትባል …
👍1
Signed Yabsira Tesfaye
9 Nov 2023, 19:04 UTC245 views1 reactionsread 9 August 2026 🛑 ፃማ 🛑
ክፍል አሰራ ሁለት
ስሙ ማን ይባላል? አለች። እጮኛዬ ነው ብላ የምትዋሸውን ሰው ስም እንኳን አለማወቋ እያስገረማት። ናትናኤል ይባላል። አለ አልአዛር ስሙን ስላልነገራት እያፈረ። ፈጠን ብሎ ከብፌው ላይ የተቀመጠውን የወጣት ፎቶ እያመለከተ ያ ነው አላት። ብሌን እጮኛዋ ነው የተባለው ሰው ፎቶ ላይ አፈጠጠች። ስንት አዲስ ነገሮችን በህይወቷ እንደምታይ አሰላሰለች። አዲስ ስም! አዲስ ኑሮ እንዲሁም እጮኛ ተፈጥሮላታል። ጊዜ የሚያመጣውን ከማየት ውጪ ሌላ አማራጭ ስለሌላት ሁሉንም በሽንፈት ተቀበለችው።
እዚህ ቤት ከመጣች ዛሬ አምስተኛ ቀኗ ነው። አልአዛር የሚወጣው ጠዋት የሚገባው ደግሞ ለአይን ያዝ ሲያደርግ ስለሆነ በዛ ቤት ውስጥ የወረራትን ብቸኝነት…
👍1
Signed Aryam Tesfaye
9 Nov 2023, 17:10 UTC199 views1 reactionsread 9 August 2026 🛑 ፃማ 🛑
ክፍል አስራ አንድ
በእሷ የመጣ ማንንም ቢሆን አይምሩም። ብቸኛ ልጃቸው ናትና። እንደ ዐይናቸው ብሌን ይሳሱላታል። ታዲያ በዚህ አይነት አስተዳደግ ያደገችው ትዝታ ፈልጋ ልታገኘው ያልቻለችው አንድ ነገር አልአዛርን ብቻ ቢሆን ምን ያስገርማል? ለእሷ የተመኘችሁን ማጣት ትልቅ ሽንፈት ነው። ሽንፈትን ደግሞ በፀጋ የሚቀበል ጭንቅላት የላትም። በፍፁም ላጣው አልችልም ብላ ለራሷ ደምድማለች።
በቅርቡ በመካከላቸው ግጭት ስለተፈጠረ ለጥቂት ቀናት ታግሳ ከእሱ ላለመገናኘት ወስናለችና ወደ ቤቱ ዝር አላለችም። ወደ ሱቁም ቢሆን አልሄደችም። ዐይኑን ካየች ሶስት ቀናት ቢያልፋትም ቢያንስ አንድ ሳምንት በትዕግስት ለማሳለፍ ራሷን አጠነከረች።
አልአዛር የትዝታ መጥ…
👍1
Signed Aryam Tesfaye
5 Nov 2023, 16:56 UTC193 views2 reactionsread 9 August 2026 ያቀፍኩትን ጣዕረ ሞት ለመላቀቅ ሰከንዶች አልፈጀብኝም። ምንም የስንብት ቃል ሳላወጣ እየተጣደፍኩ ከፊት ለፊቴ ያገኘሁት ታክሲ ውስጥ ዘው አልኹ።
ታክሲው የት እንደሚሄድ የጠየኹት ከጋቢናው ቀጥሎ ካለው መቀመጫ ላይ ሶስተኛ ተደራቢ ሆኜ ከተቀመትኹ በኅላ ነው።
ከጎኔ የተቀመጠችሁን ሽቅርቅር ወጣት "ታክሲው የት ነው የሚሄደው?" አልኳት። ዝም! ምንም ሳትመልስልኝ ከፍ ዝቅ አርጋ አይታኝ በእጇ ወደያዘችው ተንቀሳቃሽ ስልክ አቀረቀረች።
ራሴን ተመለከትኹ... ምን አልባት ጣዕረሞት መስያት ይሆን? ቀፈፈኝ የሆነ የማይገባ ስሜት ተሰማኝ።
ረዳቱ ሂሳብ ሲሰበስብ የታክሲውን መዳረሻ አወቅኹት። ተመስገን! አልተሳሳትኹም።
ወዲያው ግን እነዛ ስሜቶች አካል ለብሰው አያቸው…
👍2
Signed Yabsira Tesfaye
5 Nov 2023, 16:55 UTC173 views1 reactionsread 9 August 2026 🛑 ፃማ 🛑
ክፍል አስር
በግድ ከውሀው ወጣችና ወደ መስታወቱ አመራች። መስታወቱ ጎን ካለው ኮመዲኖ ላይ መቀሱ ተቀምጧል። አላመነታችም ብድግ አድርጋ ፀጉሯን ከጆሮዋ ትንሽ ዝቅ አድርጋ ቆረጠችው። ስትወጣ አልአዛር ተደነቀ። ከፊል እሷነቷ ፀጉሯ ሲቆረጥ ተቀይሯል። መአዛ አሸናፊ የሚለውን መታወቂያ ከጠረጴዛው ላይ አንስታ አየችው። ፎቶ የሚለጠፍበት ቦታ ባዶ ነው። ይሄ ማለት ደሞ ፎቶ መነሳት አለባት። አዲስ በገባችበት ኑሮ ውስጥ ያላት አስተዋጽኦ ምን እንደ ሆነ ተቀምጣ ማሰላሰል ጀመረች። ማንነቱን ከማታውቀው እንግዳ ሰው ጋር ተረጋግታ መቀመጧ ገርሟታል።
አልአዛር የተጠቀለለ ጋዜጣ ያለበትን ፌስታል ወደ ፊቷ ወረወረና ልብስሽን መቀየር አለብሽ። ከዛም ይዘሻቸው የመ…
👍1
Signed Yabsira Tesfaye
5 Nov 2023, 15:35 UTC166 views2 reactionsread 9 August 2026 🛑 ፃማ 🛑
ክፍል ዘጠኝ
ደብዳቤውን አንብባ እንደጨረሰች ራሷን ጉልበቶቿ መሀል ወሸቀቻቸው። ለምን ይሄን ሁሉ መስዋዕትነት? ለምን ይህን ያህል ለአንዲት ሴት ራስን አሳልፎ መስጠት? በምላሹ ታፍቅረው አታፍቅረው ሳያውቅ ለምን ራሱን ለእሷ ሰጠ? በህይወት ቢኖርና ይህንን ጥያቄዋን ቢመልስላት በወደደች ነበር ግን እዮብ አይመለስ አሸልቧል።
ተሳሳትክ እዮብ ብትነግረኝ ይሻል ነበር። ከጭንቅላቴ የማይሻር ጠባሳ ተውክብኝ! መቼም ከፊቴ የተዘረረውን ያንተን አካል መዘንጋት አልችልም ፣ከአእምሮዬ ሊጠፋ አይችልም። እዮብ ስህተት ሰርተኻል አዎ በጣም ተሳስተሃል! እጇ ላከ የነበረውን ወረቀት ጨመደደችው። ምን ልታስብ እንደሚገባት ማወቅ አልቻለችም። ብቻ ልትከፍለው የማትችለው …
👍1👏1
Signed Yabsira Tesfaye
1 Nov 2023, 18:18 UTC181 views2 reactionsread 9 August 2026 🛑 ፃማ 🛑
ክፍል ስምንት
እዮብ የእሺታም ሆነ የእንቢታ መልሶቿ እንደሚጎዱት አስቧል። እንቢ ስትለው ልቡ በማይጠገን ሁኔታ ይሰበራል። ይህ ደግሞ ህብረቱ እሱን በጥብቅ በሚፈልግበት ሰአት የማይሆን ነገር ነው። እሺ ብትለው ደግሞ ፍቅሩን የሚያጣጥምበት ጊዜ የለሁም። በቅርቡ እንደሚሞት አውቋል። እሷም ብትሆን ከሞተ በኃላ በሀዘን እንድትሰቃይ አልፈለገም። እራሱን አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተተ የጥቃቱ ጊዜ ደረሰ። ያ ከሀዲ ዳዊት ባያጋልጣቸው ኖሮ ምናልባትም ዛሬ በህይወት ሊኖር ይችል ነበር። ሁሉም ነገር ግን በእዮብ ሞት መዝገቡን ዘጋ።
ብሌን ሌሊቱን ሙሉ በቅዥት ስትንፈራገጥ ነው ያደረችው። እዮብ ተመቶ ሲወድቅ ፣ ያ ከሀዲ ዳዊት እላይዋ ላይ ሲከመር እንዲሁም ሌሎች…
👍2
Signed Yabsira Tesfaye
1 Nov 2023, 17:05 UTC168 views3 reactionsread 9 August 2026 🛑 ፃማ 🛑
ክፍል ሰባት
እጁን ዘርግቶ የተራቆተ እግሯን ሸፈነላት። ምን ነካኝ? አለ ራሱን ቆጣ ብሎ። የተገተረበትን ቦታ ለቆ ወደ መኝታ ቤቱ አመራና አልጋው ላይ ተወረወረ። ጎጃምን ለቆ ሲወጣ የሚያስታውሰው ነገር የለም። በዛን ጊዜ በጣም ልጅ ነበረ። ነገሮች ተረስተውታል። አንድ የማይረሳው ነገር ግን አለ። ታናሽ ወንድሙ እዮብ። በሁለት አመት ውስጥ አከታትላ የወለደቻቸው እናታቸው የ አራት ወንዶችና የሁለት ሴቶች ልጆች እናት ናት። የእድሜ ልዩነታቸው ብዙም ስላይደለ እዮብና አልአዛር መንታ ይመስላሉ።
አባታቸው በእናታቸው ላይ የሚያደርሰውን ግፍ ማየት የሚችልበት ጥንካሬ ስላጣ አንድ ቀን ወንድሙ እዮብን ብቻ ተሰናብቶ ጎጃምን ለቀቀ። ለቀቀ የሚለው ቃል አል…
👍3
Signed Yabsira Tesfaye
7 Oct 2023, 16:57 UTC234 views2 reactionsread 9 August 2026 🛑 ፃማ 🛑
ክፍል ስድስት
ባሰበችው ቁጥርም ይሄ ንግግሩ ይገርማት ነበር። አሁን ግን ነገሮች እየተገለጡላት መጡ። "አፍቅሮኝ ነበር ማለት ነው" እራሷን ጠየቀች። ለዚህ ነው ወደ ንቅናቄው መግባቴን የተቃወመው? የመጨረሻውን ስብሰባ እንዳትካፈል ያላደረገው ጥረት እንዳልነበር ትዝ አላት። በተኩሱ መሀል መጥቶ ጎትቶ ሲወስዳት ዐይኑ ላይ ይነበብ የነበረው ፍቅር ከየት እንደመጣ በዛን ጊዜ ለማወቅ ተቸግራ ነበር። ግን ለምን አልነገረኝም? እኮ ለምን? ልቧ በሀዘን ደምቷል።
ታክሲው ካዛንቺስ ደርሶ ሲቆም ወረደች። የተባለው አድራሻ ጋ ለመድረስ ብዙ ሰአት አልወሰደባትም። አልአዛር ከተባለው ሰው የጥያቄዎቿን መልስ እንደምታገኝ ስለገመተች አድራሻው ላይ የሰፈረው…
👍2
Signed Aryam Tesfaye
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @yabsiratesfaye. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.