4 Aug 2026, 15:38 UTC96 views13 reactionsread 8 August 2026 Photo
እግዚአብሔር በስራ ላይ ነው።
እግዚአብሔር አዳምና ሄዋንን ፈጠረ፣ ሁለት ነበሩ፣ "ብዙ ተባዙ ምድርን ሙሏት።" ሲል የበረከትን ቃል አስቀመጠ። ከዛ ከመብዛት ማንም አላቆማቸውም። አቤል ቃየልን ሲገል፣ ያበቃ ይመስል ነበር፣ የባቢሎን ግንብ ሲገነባ፣ እግዚአብሔር በውሃ ምድር ሲመታ ያበቃ ይመስል ነበር፣ ግን አያበቃም አንዴ እግዚአብሔር "ተባረኩ" ብሏልና እንበዛለን።
በእናንተ ላይ እግዚአብሔር ያስቀመጠው የበረከት ቃል ከመሆን ማንም አያግደውም። ሳይሳካላችሁ፣ የተመኛችሁትን ሳታገኙ፣ ከምትሄዱበት ሳትደርሱ፣ የልባችሁን መሻት ሳታገኙ ምንም አትሆኑም። እግዚአብሔር ስለናንተ በስራ ላይ ነው።
በዚህ ሁሉ መከራ እግዚአብሔር ልጆቹን ያኖራል። ምግብ ይወደዳል እግዚአብ…
❤10👏2🔥1
3 Aug 2026, 16:06 UTC123 views12 reactionsread 8 August 2026 Photo
እኔ ግን በእግዚአብሔር
ፍቅርን የሚገድል ጥላቻን የሚተክል ምነው በዛ?? ምነው ዳንኪራው ከቅዳሴው በለጠ?
ምነው ጥላቻ ከፍቅር በለጠ? ምነው ክፉ ዜና ጮኸ?
ምነው ሰይጣን የሚወደውን ወደድን? ምነው የሰይጣን ፍሬ በየአደባባዩ ታየ። ጥላቻ የማን ነው? ግድያ የማን ነው? ድሃን ማፈናቀል የማን ነው? ህፃን ማሰቃየትና ማስራብ የማን ነው? ጦርነት የማን ነው??
ፀልየን የቆመው ጦርነት ምነው ጀመረ? እናቶች ምህላ ገብተው ያስቆሙትን ጦርነት፣ ፀሎት የማያውቁ ለምን ጀመሩት? የአንተን ሰላም ለጦርነት ተጠቀምንበት። ገዳይ እያረፈ ይጀምራል።
አንተ ሰላም ስትሰጠን እኛ ለጦርነት አደረግነው።
ስለዝናብ ፀልይን ሰጠኸን፣ ዝናብ ስትሰጠን እንረሳሃለን፣ አንተ ያበቀለው…
❤7🔥2🥰2👍1
29 Jul 2026, 15:33 UTC254 views11 reactionsread 8 August 2026 Photo
ቃለ እግዚአብሔር።
ብዙዎችን በየትኛውም ጥበብ ልትለውጧቸው አትችሉም። ልጆቻችሁን የትኛውንም ሃብት መድባችሁ በአለም የታወቀ ዩኒቨርሲቲ ብታስተምሯቸው መለወጥ አይችሉም። መፅሀፍ ቅዱስ ሁለንተናን ይለውጣል።
መፅሀፍ ቅዱስ ፈልጎ ያገኛችኋል። ለመፅሀፍ ቅዱስ ፍቅር የነበራት፣ ከቦርሳዋ መፅሀፍ ቅዱስ ጠፍቶ የማያውቅ በብዛት ቅዱሱን መፅሀፍ ስታነብ የምትታይ አንዲት ሴት፣ መፅሀፍ ቅዱሱን እንዴት እንደምታነብና እንደምትወድ ስትጠየቅ። "እኔኮ መፅሀፍ ቅዱስ አላነብም እሱ ያነበኛል፣ እኔ መፅሀፍ ቅዱስን አላፈቅርም፣ ቃሉን ሳነብ መፈቀሬን እረዳልሁ እንጂ" ስትል መልሳ ነበር።
እውነት ነው፣ መፅሀፍ ቅዱስ እርሱ እራሱ መስታወት ነው። እራሳችንን ያሳየናል፣ እንደመታጠቢያ…
❤9🔥2
27 Jul 2026, 14:46 UTC195 views14 reactionsread 8 August 2026 Photo
መኖሪያችን
ክፉ በሆነ መንገድ በየምሽት ክለቡ የሙዚቃ ስራ እሰራ ነበር፣ የምኖረውም በዚህ ሙያ ነው፣ በዚሁ ሙያዬ ስራዎችን ለማቅረብ ከባንዶች ጋር አሜሪካ ገባን፣ ህይወቴን የምቀይርበት እድል አገፕሁ።
አሜሪካ ገብተን ሆቴል እንደያዝን በመጀመሪያው ቀን እንቅልፍ አጣው፣ "መሞቻህ ነው" የሚል ድምፅ ሰማሁ፣ ሳልተኛ ነጋ።
በፍጥነት ወደ ፕሮሞተሩ አቀናሁ፣ ከዚህ በኋላ ከሙዚቃ ቡድኑ መውጣቴን ነገርኩት፣ በጣም ተገረመ "ምን እያልክ ነው፣ አንተን የሚተካ ሰው የለም፣ ይሄን ስራ ጨርሰህ ታቆማለህ" አለኝ። "በጭራሽ" አልኩት። በጣም ተገርሞ አየኝ "ይሄን እድል አታበላሽ" ታምሜ መሰለው። "በደህናህ አይመስለኝም፣ ምን ትበላለህ፣ በምን ትኖራለህ?" አለኝ። እግዚአብ…
🔥12🙏2
24 Jul 2026, 15:32 UTC221 views15 reactionsread 8 August 2026 Photo
ክርስቶስ ሆይ
ክርስቶስ ሆይ ካንተ በላይ ውብ ቃል የለም፣ ባንተ ቃል ውብ የሆኑት ሰማይ ምድር ተፈጥረዋል። ቃልህ አንዴ ፈጥሮ አልተወንም፣ በየእለቱ ይሰራናል። "ይሁን" እያለ ውበትን የፈጠረ ቃልህ እንዴት ውብ ነው።
በሰው ልብ ብዙ ነገር አለ፣ አንተ የመከርከው ቃል ብቻ ይፀናል። ክርስቶስ ሆይ ምክርህ እንዴት ውብ ነው። አንተ ስትናገር "አልሰማም" የሚል አንዳች የለም። ክርስቶስ ሆይ ተናገር እኛም እንሰማሃለን።
ክርስቶስ ሆይ ኦ ድምፅህ፣ የሚያጓራውን አውሎ ነፍስ ይገስፃል። መስማት ያልቻለውን ጆሮ ይከፍታል፣ መናገር ያልቻለውን ምላስ ያናግራል።
ቃልህን የሚቋቋም የለም፣ ዳጎን ቢሆን ይሰበራል፣ ኢያሪኮ ቢሆን ይፈርሳል።
ክርስቶስ ሆይ ድምፅህ እንዴት ው…
❤13🔥2
22 Jul 2026, 16:59 UTC226 views18 reactionsread 8 August 2026 Photo
ሃሌሉያ "አለም ዋንጫ"
ባሳለፍነው የአለም ዋንጫ ታዋቂው ጀስቲን ቢበር በፍፃሜው ቀን ሙዚቃ ከሚያቀርቡ ዳንኪረኞች አንዱ ነበር። ብዙዎቹ በብዙ ሙዚቀኞች፣ በብዙ ዳንሰኞች፣ በብዙ ብልጭልጭ ዳንኪራቸውን አቅርበዋል።
ጀስቲን ቢበር ተራው ሲደርስ አንዲት አኩስቲክ ጊታር ይዞ፣ ያለ አጃቢ "Everything Hallelujah" የተሰኘ ዘፈን አቀረበ።
ያቀረበው ዘፈን በመጨረሻ አልበሙ ያወጣው ቢሆንም ሀሳቡ ግን ክፉ አይደለም፣ "በደስታ ስንደንስ ፀሀይ አየችን፣ አዲስ ቀን መጣ ሃሌሉያ፣ በውሃ እደሰታለሁ ሃሌሉያ፣ ሁሉ ደስ ይላል፣ ወደ መስክ ስወጣ፣ ውበትን ሳይ ሃሌሉያ።"
"ዝናብ ከሰማይ ሲዘንብ፣ የሚነፍሰውን አየር ስተነፍስ፣ በዚህ ሁሉ ስዘምር ሃሌሉያ፣ በደስታ …
🙏11🔥4❤3
21 Jul 2026, 16:23 UTC222 views16 reactionsread 8 August 2026 Photo
ሲሰሙት ደስ የሚል!!!!
በዚህ ምድር ኢየሱስን እያወቁ አለመደነቅን የመሰለ መበደል የለም።
ኢየሱስ በመቅደስ እለት እለት ሲያስተምር ሁሉም በደስታ ይሰሙት ነበር፣ በዚህ ቅናት ያደረባረባቸው ሊገድሉት ይፈልጉ ፈለጉ፣ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ተንጠልጥለውበት ነበርና አልቻሉም። በእውነት ህዝቡ ሁሉ ተንጠልጥለውበት ነበር የሚለውን ሳነብ ልቤ ሀሴት ያደርጋል። በወጉ ሰላም ለማለት ፍላጎት ባጡ አገልጋዮች መሃል ስንገኝ ክርስቶስ ላይ ግን ይንጠለጠሉበት ነበር። ሉቃስ 19:47
ኢየሱስ ህዝቡን በምሳሌ ያስተምት ነበር፣ ፈሪሳውያንና የሄሮድስ ወገኖች ግን ተበሳጭተው ሊይዙት ፈለጉ፣ ህዝቡ በደስታ ግን ይሰሙት ስለነበር ማድረግ አልቻሉም።
ስለ ኢየሱስ መስማት ሀሴት ነው…
❤12🔥4
19 Jul 2026, 15:27 UTC353 views19 reactionsread 8 August 2026 Photo
የስጋ ድካም
ስጋ ደካማ ነው። የቱንም ያህል ብትንከባከቡት ስጋ ደካማ ነው፣ ለፀጉራችሁ በጊዜው ይሸብታል፣ ለፊታችሁ "ክሬም፣ ሰን ስክሪን" ብትጠቀሙም፣ በጊዜው መጨማደዱ አይቀርም። ዘመን ሲጨምር የቱንም ያህል እራሳችሁን ብትንከባከቡትም ታረጃላችሁ።
ለጤና ተስማሚ ምግብ ብትመገቡም፣ ስጋ ከማርጀት አይመለስም፣ ብዙ ዘመን የመገባችሁት ሰውነት ጥቂት ቀን ምግብ ሲያጣ ፊታችሁ ይጠቁራል፣ አስር አመት ያለማቋረጥ በሰአቱ የመገባችሁት ሰውነት አስር ሰአት አይታገሳችሁም፣ ብዙ አመት በልቻለው ዛሬን ልታገስ አይላችሁም፣ ስጋ ውለታ ቢስ ኑው።
ህፃናት ልጆቻችሁን ቀኑን ሙሉ፣ ብዙ ብታበሏቸው ወፍራምና ሞኝ ይሆናሉ፣ ጎበዞች እንዲሆኑ ብላችሁ የተመጣጠነ ምግብ ያበላችኋቸው …
❤18🙏1
17 Jul 2026, 15:42 UTC610 views17 reactionsread 8 August 2026 Photo
በዚህ ቃል ተፅናኑ።
ደካሞች እንደደከሙ አይቀሩም፣ ሀዘንተኞች እንዳዘኑ አይቀሩም፣ ፊታቸው በሃዘን ለጠቆረ እግዚአብሔር ተስፋ አለው፣ ያዘኑ ፈገግ የሚሉበት ቀን ይመጣል።
ወደ እልፍኛቸው ገብተው ያለቀሱ፣ በሰው ፊት ግን በፈገግታ የዋሉ እግዚአብሔር አይቷቸዋል፣ ሀዘናቸውን ወደ ደስታ፣ ድካማቸውን ወደ ብርታት ይቀይራልና በዚህ ቃል ተፅናኑ።
ግራ ለተጋቡ፣ እውነተኛ መፅናኛ እግዚአብሔር ነውና በዚህ ቃል ተፅናኑ። አሮጌው ያልፋል ሁሉን አዲስ ያደርጋልና በዚህ ቃል ተፅናኑ፣ የሰለጠነባችሁን ይሰብርላችኋልና በዚህ ቃል ተፅናኑ።
ስራ ትርፍ ያላስገኘላችሁ፣ በትምህርት መሻገር ያቃታችሁ፣ ሰው ከቁም ነገር የማይጥፋችሁ፣ በምድር ሚዛን ጎደላችሁ፣ ጓደኛ የሌላችሁ፣ ቤተሰ…
❤13🔥3🙏1
14 Jul 2026, 15:22 UTC313 views17 reactionsread 8 August 2026 Photo
የእግዚአብሔር በአላት።
የእስራኤል ህዝብ ከግብፅ ባርነት እንደወጣ በየመንገዱ በአል ያደርግ ነበር፣ ድንኳን የመትከል በአል፣ ድንኳን የማንሳት በአል፣ የሞሎት የኮከቦች በአል፣ የወርቅ ጥጃ በአል፣ የሞአብና ምድያም መስዋእት በአል፣ የመናፍስት መጠየቅ በአል፣ ለአማልክት መስዋእት ማቅረብ በአል፣ የልጆች መስዋእት ለሞሎክ በአል... እጅግ ብዙ በአላትን ከአህዛብ ተቀብለው ሲያከብሩ ይውሉ ነበር።
እግዚአብሔር ለእርስቱ የመረጠው ህዝብ ያገኘውን ሁሉ የሚያከብር ሆነ፣ የሌሎች አማልክትን በአል ያክበራሉ።
በኛ ዘመን ብዙ የአህዛብ በአል ሳይታወቀን እየወረሰን ነው፣ ገና ትምህርት ለሚጀምሩ ህፃናት በየቤቱ በአል ይደረጋል፣ በተባበሩት መንግስታት አማካይነት ብዙ የስላ…
❤13🔥3🙏1
11 Jul 2026, 16:14 UTC292 views17 reactionsread 8 August 2026 Photo
የኔ ምስክርነት። ፪
(እግዚአብሔር አይቷል።)
የሥነ ልቦና ጉዳት እውነት መሆኑን የምመሰክር ነኝ፣ ሁሉ ቢችል በተግባር ባይችል በዘዴ የስነ ልቦና ጥቃት አድራሽ ነው። ያለፈው ህይወቴ ልክ እንዳሁኑ ሁኖ ይሰማኛል።
ጌታ እንዲህ ያደረገ ይመስለኛል። ሁል ጊዜ ፊቴ የተገተረውን ትልቅ ቋጥኝ "ግፋው" የሚለኝ ልክ እንዳለኝ ያን ቋጥኝ ስገፋ ብውልም ቋጥኙ ንቅንቅ የማይል።
ጌታ ያደረገው ፊቴ የተገተረውን ቋጥኝ ማንሳት አይደለም፣ እሱ ያደረገው፣ እኔን ማጠንከር ነው፣ አሁን እኔ ጠንካራ ነኝ፣ ፊቴ በተነጠፉት ብዙ ችግሮች መሃል ጌታ ብርቱ አድርጎኛል፣ በዘመኔ የሚገዳደሩኝን ሁሉ ክርስቶስ አይቷልና ብርቱ ያደርገኛል።
ሰዎች ድሮ ባሳለፍኩት ችግር ዛሬም እንደ ድሮ እን…
❤15🔥1🥰1
10 Jul 2026, 15:40 UTC317 views14 reactionsread 8 August 2026 Photo
በርጤሜዎስ እና የሰፈራችን ለማኝ።
እንዲህ ያለ ነገር በየሰፈራችሁ ሰምታችሁ ይሆናል፣ እኛ ከመወለዳችን በፊት በልመና የሚተዳደሩ፣ አስፋልት ዳር የላስኪት ቤት ሰርተው ይኖራሉ፣ እዛው ይለምናሉ፣ እዛው ይኖራሉ።
ልጆች ሆነን ወደ ትምህርት ቤት ስንሄድ እናያቸዋለን፣ እኚህን የኔ ብጤ ሰላም እንላቸዋለን እሳቸውም "ልጆቼ" ይሉናል። አንድ ቀን ግን የሆነ ነገር ተከሰተ።
በጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ስንሄድ ፖሊስና ህዝቡ የአባባን የላስቲክ ቤት ከቦ ቆሟል፣ ስንጠጋ ለካ አባባ ሞተው ተገኝተው ነው። ማታ ሞተው አደሩ።
እሬሳቸውን አምፑላንስ መጥቶ ወሰደው። በኋላ አስገራሚ ነገር አየን፣ የአባባን ቤት የሞላው ቡትቶ ወጥቶ ወጥቶ ወጥቶ አላልቅ አለ። የሚያስገርመው ከዛ…
❤13🔥1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @wogse. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.