5 Dec 2022, 11:31 UTC≈19,100 views147 reactionsread 8 August 2026 የእግዚአብሔር ቃል
(ወንድም ሚናስ)
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈሳዊ ልጁ ለጢሞቴዎስ በሰደደው በኹለተኛው መልእክቱ ላይ የእግዚአብሔርን ቃል፣ θεόπνευστος “ቴኦፕኔውስቶስ” መኾኑን ይገልጽለታል (፪ጢሞ.፫፥፲፮)። θεόπνευστος “ቴኦፕኔውስቶስ” የሚለው ቃል θεό “ቴኦ” ማለትም “እግዚአብሔር” እና πνευστος “ፕኔውስቶስ” ማለትም “መንፈስ” ከሚሉ ኹለት የጽርእ ቃል የተገኘ ነው፤ ተገናኝቶ ሲነበብም “እስትንፋሰ እግዚአብሔር” ወይም “አፊዎተ መለኮት” የሚል ይኾናል። ቅዱስ ሳዊሮስ ዘእስሙናይን የተባለ የቤተክርስቲያን አባት በድርሳኑ ከላይ ያለውን ዐሳብ እንዲህ በማለት ያጠናክረዋል፣ “መጻሕፍት አምላካውያት እስትንፋሰ አፉሁ ለእግዚ…
👍88❤44👏11🔥2😱2
22 Jun 2022, 18:06 UTC≈18,300 views45 reactionsread 8 August 2026 የካህናት አለቃ ጌታችን እና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በምንችለውም በማንችለውም ያንተ ኀያል ክንድ ይዘርጋልን። የፈራናቸውን ቀኖች አሻግረን። ዐዘናችንን በፍሥሓ ቀይርልን። ለእናት አገራችን ፍጹም ትንሣኤ፣ ለሕዝቧም ፍቅር ሰላም እዘዝልን።
ሰአልናክ መሓሪ።
ሰአልናከ ከሃሊ።
@Who_is_jesus
👍35❤7👏3
31 May 2022, 13:49 UTC≈17,200 views32 reactionsread 8 August 2026 በእንተ ኢሳይያስ 53
ክፍል አራት
(በወንድም ሚናስ)
በስመ እግዚአብሔር መሓሪ ወመስተሣህል
ቊጥር ዐሥር
“መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፤ እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት ቢያደርገውም እንኳ፣ #ዘሩን ያያል፤ ዕድሜውም ይረዝማል፤ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”
וַיהוָה חָפֵץ דַּכְּאוֹ, הֶחֱלִי--אִם-תָּשִׂים אָשָׁם נַפְשׁוֹ, יִרְאֶה #זֶרַע יַאֲרִיךְ יָמִים; וְחֵפֶץ יְהוָה, בְּיָדוֹ יִצְלָח.
ይሁዲዎች ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ዓመታት ሥጋዊ ልጅ ስላልነበረው ኢሳይያስ 53:10ን “ዘሩን ያያል” የሚለውን ቃል፣ ሊመለከተው እንደማይችል ይ…
👍24❤5🤔2👏1
30 May 2022, 10:16 UTC≈12,000 views21 reactionsread 8 August 2026 በእንተ ኢሳይያስ 53
ክፍል ሦስት
(በወንድም ሚናስ)
በስመ እግዚአብሔር መሓሪ ወመስተሣህል
ቍጥር 9
“በአፉ ተንኰል ሳይገኝበት፣ ምንም ወንጀል ሳይሠራ፣ #አሟሟቱ ከክፉዎች፣ መቃብሩም ከባለጠጎች ጋር ኾነ።”
וַיִּתֵּן אֶת-רְשָׁעִים קִבְרוֹ, וְאֶת-עָשִׁיר #בְּמֹתָיו; עַל לֹא-חָמָס עָשָׂה, וְלֹא מִרְמָה בְּפִיו.
ይሁዲ ወገኖቻችን በዚህ ክፍል የሚያቀርቡት ሙግት בְּמֹתָיו “ቤሞታው” የሚለው ስም ብዜት ስለኾነ፣ ዕብራይስጡ የሚለን “አሟሟቱ” ሳይኾን “አሟሟታቸው” የሚል ነው፤ ስለዚህ ቊጥሩ ካንድ በላይ ለሚኾኑ አካላት የተነገረ እንጂ ነጠላ አካልን ይኸውም መሲሑን የሚመለከት አይደለም ይሉና…
👍16❤5
29 May 2022, 07:29 UTC≈9,560 views19 reactionsread 8 August 2026 በእንተ ኢሳይያስ 53
ክፍል ኹለት
(በወንድም ሚናስ)
በስመ እግዚአብሔር መሓሪ ወመስተሣህል
የክርስትናን አስተምህሮ የማይቀበሉና የማያምኑ ይሁዲ ወገኖቻችን፣ ምዕራፉ ስለ መሲሑ ሳይኾን ሕዝበ እሥራኤልን ይመለከታል፤ ለማለት ምርኵዝ ከሚያደርጐቸው ምንባባት መኻከል ደግሞ ፣ በዛሬው ጥናታችን አንዱን የምንመለከት ይኾናል።
ቊጥር ስምንት
“በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኀጢአት ተመቶ፣ ከሕያዋን ምድር #ርሱ እንደ ተወገደ፣ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?”
מֵעֹ֚צֶר וּמִמִּשְׁפָּט֙ לֻקָּ֔ח וְאֶת־דּוֹר֖וֹ מִ֣י יְשׂוֹחֵ֑חַ כִּ֚י נִגְזַר֙ מֵאֶ֣רֶץ חַיִּ֔ים מִפֶּ֥שַׁע עַמִּ֖י נֶ֥גַע #ל…
👍14❤5
28 May 2022, 11:54 UTC≈8,860 views14 reactionsread 8 August 2026 በእንተ ኢሳይያስ 53
ክፍል አንድ
(በወንድም ሚናስ)
በስመ እግዚአብሔር መሓሪ ወመስተሣህል
ኢሳይያስ 53 ስለ መሲሑ ሞት እና ቤዛነት የሚናገር ድንቅ ምንባብ ቢኾንም፣ በዘመነኞቹ የይሁዲ ቤተ እምነት አማኒያን ዘንድ፣ ምዕራፉ እየተናገረ ያለው ስለ መሲሑ ሳይኾን፣ ሕዝበ እሥራኤል በዓለም ስለሚደርስበት መከራ የሚመለከት ትንቢት ነው ብለው ይከራከራሉ፤ ኾኖም ግን የዚህን ትርጓሜ ትኽክለኝነት ለማጣራት ከምዕራፉ ዐውድ ውጪ ወጣ በማለት እንደ ሚሽና፣ ታልሙድ፣ ሚድራሺም...ወዘተ ያሉ ጥንታዊ የይሁዲ መዛግብቶችን ብንመለከት ትንቢቱ ስለ ሕዝበ እሥራኤል ሳይኾን፣ በተቃራኒው ስለ መሲሑ የሚናገር መኾኑን ከትበው አስቀምጠዋል። ይህ ብቻም አይደለም፣ ከመኻከለኛው ክ…
👍10❤4
20 Apr 2022, 14:23 UTC≈11,100 views35 reactionsread 8 August 2026 ✝ የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት 👈
I. ኢየሱስ ማን ነው? ፦
https://t.me/who_is_jesus/379
II. የክርስቶስ ህይወት ፦
➡ ከታሪክ መጻሕፍት፦
https://t.me/who_is_jesus/389
➡️ ከወንጌላት፦
https://t.me/who_is_jesus/401
➡️ ኢየሱስ የኖረበት መልክዓ ምድር
https://t.me/who_is_jesus/410
III. ስለ ኢየሱስ የመማር አስፈላጊነት
https://t.me/who_is_jesus/420
IV. የኢየሱስ መለኮታዊ ማንነት
4.1 ➡️ ኢየሱስ "የእግዚአብሔር ቃል"
[The word of God]
https://t.me/who_is_jesus/435
…
👍22❤8👎2👏1🔥1🤔1
26 Mar 2022, 11:10 UTC≈8,930 viewsread 8 August 2026 "ኢየሱስ : የእግዚአብሔር : ልጅ : እንደሆነ : ከሚያምን : በቀር : ዓለምን : የሚያሸንፍ : ማነው?"
፩ኛ ዮሐ ፭፥፭
@who_is_jesus
16 Mar 2022, 08:25 UTC≈8,660 views6 reactionsread 8 August 2026 እውን ቅዱስ መላጥዮስ ዘሰርዴስ አርዮሳዊ ነበር?
( ሚናስ)
አውሳቢዮስ ዘቄሳሪያ በተባለው የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሓፊ ዘገባ መሠረት፣ ቅዱስ መላጥዮስ ከ ፻፳ እስከ ፻፹፭ ዓ.ም በምድር ላይ የኖረ፣ በዘመኑም የሰርዴስ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የነበረ አባት ነው[፩]፤ እናም በመላጥዮስ ዘሰርዴስ የእምነት አቋም መሰረት፣ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “በማንነቱ ፍጹም አምላክ እና ፍጹም ሰው(θεός ὡς φύσει καί ἄνθρωπος)” የሆነ [፪]፣ “አልፋና ኦሜጋ”፣ ደግሞም “በአብ ቀኝ የተቀመጠ”[፫]፣ ቅድመ-ሥጋዌ በሰማያት የነበረ፣ ስለ ሰዉ ልጆች ኃጢአት ሲል ከድንግል ሥጋን ለብሶ (σαρκόω) መከራን የተቀበለ [፬]፤ የዓለማት…
👍4❤2
13 Mar 2022, 08:28 UTC≈7,220 views2 reactionsread 8 August 2026 ወልድ ትንሹ ብርሃን ተብሏልን ?
(በወንድም ሚናስ )
“በሥላሴ ማመን ይገባሀልን?” በሚል ርዕስ ፣ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና የትራክት ማሕበር ያሳተመው አነስተኛ መጽሓፍ ላይ ፣ ከኒቂያ ጉባኤ በፊት የነበሩ ፣ ቀደምት የቤተክርስቲያን አባቶች ፣ የክርስቶስን አምላክነት የማይቀበሉ አርዮሳውያን መኾናቸውን ይገልጻል ። እናም ይኽ ድርጅት ፣ የክርስቶስ መለኮትነት አይቀበሉም ብሎ ከዘረዘራቸው የቤተክርስቲያን አበው መካከል ስመጥሩ የእስክንድርያው ሊቅ አርጌንስ ተጠቃሽ ነው፤ ድርጅቱ ሊቁን አስመልክቶ የሚከተለውን ጽሑፍ አስፍሯል፦
“ በ250 ዓ.ም የሞተው ኦሪገን ከአብ ጋር ሲወዳደር ወልድ በጣም ትንሹ ብርሃን ነው ሲል ገልጿል”[፩]
ይኽ Against…
❤1👍1
9 Mar 2022, 21:38 UTC≈5,750 views2 reactionsread 8 August 2026 የተቀደሰ ስም ያለህ እግዚአብሔር አብ ሆይ የብርሃንህ ጎርፍ፣ የፍቅርህ ጠል፣ የበረከትህ ዝናብ በእኔና የእኔ በሆኑት ላይ ይፍሰስ። አንተ እንዴት እንደምታስተዳድር ለአስተዳዳሪዎች ፣ እንዴት እንደምታኖር ለአባወራዎች ፣ እንዴት እንደምታሳድግ ለሞግዚቶች ፣ እንዴት እንደምትጠብቅ ለጠባቂዎች ፣ እንዴት እንደምታፈቅር ለአፍቃሪዎች ፣ እንዴት እንደምትሰጥ ለለጋሾች ግለጥላቸው ። በልጅህ በወዳጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ያለ ከሃሊነትና ክብር ላንተ ለመንፈስ ቅዱስም ይገባል ለዘላለሙ አሜን።
@who_is_jesus
❤2
9 Mar 2022, 10:45 UTC≈5,770 views1 reactionsread 8 August 2026 ይኽ መጣጥፍ ፣ የይሁዳ መልዕክት ምዕራፍ ፩ ላይ በመንተራስ ፣ የክርስቶስ አምላክነትን ፣ የሚያትት ዐዲስ ጽሑፍ ነው ። ሊንኩን በመጫን ሙሉ መጣጥፉን ያንብቡ ። http://ewnetlehulu.net/jude-christology/
@who_is_jesus
👍1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @who_is_jesus. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.