6 Aug 2026, 19:41 UTC14 views1 reactionsread 6 August 2026 Photo
🌺በክርስቶስ ግንድ የተጣበኩ የማርያም ተክል ኹሉም የሚያርፍብኝ ጥላ የማይቆም ምንጭ ልኾን እመኛለኹ...
ተክል እንክብካቤን ይፈልጋል!
እንድለመልም፣ እንዳድግ፣ መልካም ፍሬ እንዳፈራ በጸሎት ኮትኩቱኝ፣ በጸሎት አጠጡኝ፣ በጸሎት ብርሃን ኹኑኝ።
ተክለ ማርያም ...ማርያም ኾይ ተክልሽን አደራ ብላችኹ አስቡኝ!
የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ የድንግል ማርያምን ምልጃ የምንመሰክርበት ሱባዔ ይኹንልን!
@tekile_mariyam
🙏1
5 Aug 2026, 19:59 UTC51 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
🌺የሚጾምን ሰውነት የምታጠራ ሕይወት
#ንስሓ
የምዕመናን ቤታቸው ናት። ያደፉትን የምታነጻ ባሕር ናት። በኃጢአት የዛገውን ኹሉ የምታጸራ ወናፍ ናት። ክርዳደ ኃጢአትን የምታቃጥል እሳት ናት። ዘር የምታበቅል መስኖ ናት።(ትሩፋትን የምታለማ ናት) ለወገኖቿ መዓዛ ጸጋን የምታስገኝ የተክል ቦታ ናት። ጠላቶቿ አጋንንትን ድል የምትነሳ ሠራዊት ናት።
ንስሓ የምዕመናን ሞግዚት ናት። በውስጧ ያለውን የምትጠብቅ ግንብ ናት። የተማረኩትን የምትመልስ ብርቱ አበጋዝ ናት። ንጹሕ ወገን የሚያመሰግንባት ቤተመቅደስ ናት። ክብር ሊኾናቸው ቅድስናን ሥጋውን ደሙን የሚያገኙባት ቤተመቅደስ ናት። ለተበደሉ ሰዎች መማጠኛ ናት። የሐብታት ምስጢራት መገኛ ናት። ደጅዋን የጸፋ የሚሻውን ክ…
👍3❤1
5 Aug 2026, 18:39 UTC56 viewsread 6 August 2026 🌺ጾም የተወደደ ምግባር ነው። ዋናው ነገር እንዴት እንጹም የሚለው ነው?
@tekile_mariyam
4 Aug 2026, 04:32 UTC72 views6 reactionsread 6 August 2026 ▯◈ ቸር ዐማኑኤል ◈▯
እልልልልል ....
እልል በሉ ምዕመናን አመስግኑ!
የእግዚአብሔር ቸርነት ያልተለያቸው ለምስክርነት የበቁ ምዕመናን እያመሰገኑ ነው።
ዓይኖቿ በዕንባ ተሞልተው፣ ልቧ ግን በሺህ ሐሳቦች ሲዋልል የሚታይ የአዕምሮ ጤና መታወክ እንዳለባት ኹኔታዋን የሚያሳብቅ አንዲት ወጣት ከቤተክርስቲያኑ ደጃፍ ኾና ትቅበዘበዛለች፤ እየገሰገሰች ወደ ውስጥ ለመግባት ምዕመኑን ታተረማምሳለች። ከቅጽሩ በር ሊያስወጧት ሲታገሉ የነበረውን ኹካታ የተመለኩት እኚህ በዕድሜ ጸና ያሉ መነኩሴ ቀረብ አሉና።...'ልጆቼ ተረጋጉ ተዉዋት ልቀቋት ብለው በእጃቸውም በያዙት መድኃኒተ መስቀል ባረኳት። ምን ዓይነት ካህን ናቸው? ማንን መባረክ እንዳለባቸው አያውቁምን? (የምዕመኑ…
❤6
4 Aug 2026, 04:31 UTC56 viewsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
2 Aug 2026, 05:03 UTC110 views5 reactionsread 6 August 2026 Photo
🌺ጌታን እሽኮኮ ብለህ ወደ ግብጽ በረሓ ይዘኸው የሔድህ ዮሴፍ ሆይ ንዑድ ክቡር ነህ።
የሚሸከሙትን የሚሸከም ጌታን መሸከም ክቡድ አይደለም። ወዳጄ አንተም እንደ ቅዱስ ዮሴፍ ኅሊናህ በጌታ ፍቅር ይቃጠል።
[አረጋዊ መንፈሳዊ]
የድንግል ማርያምን መከራ ስቃይ የተካፈለ ቅዱስ ዮሴፍ ዛሬ ሐምሌ 26 የዕረፍት በዓሉ ነው።
እንኳን አደረሳችኹ!
🖋ተክለ ማርያም
https://t.me/tekile_mariyam
❤3🔥2
28 Jul 2026, 03:04 UTC190 views5 reactionsread 6 August 2026 ▯◈ ለኹሉ የተቸረ ውርስ ◈▯
በስሜ ለሚጠራው ልጄ የማኖረው ሊኖር ይገባል። በማለት ወላጅ በብዙ ይደክማል። በማምሻ ዕድሜያቸው በሞታቸው ዋዜማ ያላቸውን ውርስ ይናዘዛሉ። ከዚህ ውርስ የሚሳተፉት ግን ጥቂቶቹ ናቸው። የሚገርመው ግን ውርስ የተባለውም ወራሾቹም የማለፋቸው ነገር ነው።
በምልክት የማትታወቅ፣ በእዝነ ኅሊና የማትሰማ፣ በዚህ ዓለም ባለ ነገር በምንም የማትመሰል ይህች ውርስ በወርቅ የማትገዛ፣ በብር የማትለካ፣ በሥልጣን የማትጨበጥ ናት። ይህች ውርስ በእግዚአብሔር ምስጋና የምናገኛት የማታልፍ መንግሥተ ሰማያት ናት።
በምድር ያለ ውርስ ለውስን ቤተሰብ ይኾናል፤ የሰማይ ውርስ ግን ለኹሉም የተቸረ ሐብት ነው። የምድር ውርስ ዘርን ይፈልጋል፤ የሰማይ ውር…
🙏5
28 Jul 2026, 02:59 UTC99 viewsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
26 Jul 2026, 03:02 UTC117 views5 reactionsread 6 August 2026 Photo
🌺በዝምታ የማንቆረቁረውን የልቤን ዜማ ያ የነፍሴን ጩኸት ወደ ሰማይ የሚያሳርግ ሹም፤ በዚህ ባለ ግርማ ክንፍ ጥላ ሥር ልቤ አረፈ፤ ዕንባዬም እንደ ጥዋት ጤዛ በምሕረት ብርሃን ተዋጠች።
ቅዱስ ገብርኤል ሆይ፣ ፍቅርህ እንደ ዥረት ወንዝ በልቤ ፈሰሰ፤ የኩራቴን ድንጋይ አለሰለሰ፣ ያበጠውን ትዕቢቴን አጠፋው፣ መዓዛው የሚደንቅ የተስፋ አበባም በውስጤ አበበ።
የሰው ቃል ሲያቆስለኝ፣ የምስራች በሚናገር አንደበትህ የጌታን ምሕረት አስታወስከኝ፤ መንገዱ ሲረዝምብኝ ከቀቢጸ ተስፋ አንስተኸኝ ከብርሃኑ አደረስከኝ። እነኾ ኹሉም በጨለመብኝ ጊዜ አንተው ተስፋ ኾንከኝ።
እኔ የተናቅኹ ትቢያ ብኾንም፣ ፈጣሪዬ በፍቅሩ እንዳያልፈኝ ምልጃህን አጥብቄ እሻለሁ። የሚያልፍ ክብር…
❤5
21 Jul 2026, 04:31 UTC143 views5 reactionsread 6 August 2026 ▯◈ ማንም አያዝንላችኹም ◈▯
የሌሊቱ ጭለማ አልፏል። ሰዓቱ ገና ንጋትን እየጠበቀ ነው። ቀን ሙሉ በስራ የደከመ አንድ ወጣት ከአልጋው ላይ እንደ ተነጠፈ ድንጋይ ተዘርግቶ ተኝቷል። ሰውነቱ በእጅጉ ስለዛሉ ዕረፍትን ይፈልጋል፤ ዓይኖቹን ለተመለከተ ፅኑዕ እንቅልፍን ቋጥረዋል። በዚህ መጣጣር ውስጥ ሳለ የወዳጁ ጥሪ ያነቃዋል።
የማለዳ ድምፅ እስኪከፈት የቀረዘዘ ነው፤ የደወለችው ልጅትም ሙት የምታወራ መሰላት። 'ኧረ ተነስ ይበቃሃል። ስራህ ዘነጋኸው እንዴ' በማለት ለማንቃት ትጥራለች። ይህ ሰው ግን ድካሙንና ሕመሙን ይነግራት ጀመር። (ታዝንልኝ፣ ታስታምመኝ ይኾን በሚል ተስፋ) እርሷ ግን ቆፍጠን ያለ ምላሽ ሰጠችው።
'አይ እንግዲህ አትልፈልፈስ ወንድ አይደለህ …
❤5
21 Jul 2026, 04:31 UTC109 viewsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
14 Jul 2026, 03:01 UTC178 views7 reactionsread 6 August 2026 ▯◈ ፍቅረ ሥላሴ ◈▯
ቅዱስ ጳውሎስ ከሌሎች ትሩፋት ይልቅ ሃይማኖትን፣ ተስፋን፣ ፍቅርን ያከበረ፤ ከኹሉም ፍቅር ይበልጣል ያለ እንደምን ነው? (¹ቆሮ ፲፫÷፲፫) ለሚለው ጥያቄ መጽሐፍተ መነኮሳት (ፊልክስዩስ) ሲያብራራልን ትሩፋት ኹሉ ከሦስት ወገን ይሠራሉ። በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ፣ በንጽሐ ልቡና መዓርግ። እነዚህ ሦስቱ መዓርጋት ምሳሌ ኹነው ሃይማኖትን፣ ተስፋን፣ ፍቅርን ያስረዳሉ።
ሃይማኖት የተባለው በአካል ሦስት በባሕርይ አንድ ብሎ ማመን ነው። በአካላዊ ቃልነቱ፤ አንድም ለይኩን ባለው ቃሉ ማመን ነው።
ተስፋ ያለው ኹል ጊዜ በልቡና ጌታን መዘከር ነው። ተስፋ ኄራቲሁ ሲል ነው። በቸርነቱ የሚያወርሳት መንግስተ ሰማያትን ተስፋ ማድረግ ነው።
ፍቅር…
❤6🤗1
Showing the 12 most recent of 19 posts we hold for @tekile_mariyam. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.