7 Jun 2026, 11:40 UTC118 views26 reactionsread 9 August 2026 Photo
እናትም፣ እህትም፣ አክስትም፣ አሳዳጊም፣ አስተማሪም፣ መካሪም፣ ተቆጭም፣ ተስፈኛም፣ ለጋስም፣ ሩህሩህም፣ ሁሉንም ሆና ራሷን ሰውታ ለዚህ ያደረሰችኝ እማዬ በሕይወተ ሥጋ ከተለየችኝ 30 ቀናት አለፉ። ማረፏን ለማመን አሁንም ይቸግረኛል። ህልም ህልም እንጂ እውነትነቱን ለመቀበል የሚያዳግት የሕይወት ዱብዕዳ። ጊዜው ሲደርስ የማያት፣ የማገኛት፣ የማወያያት ነው የሚመስለኝ። ራሳችሁን ለደስታ ለተስፋ ባዘጋጃችሁ ቁጥር ሃዘንም ተስፋ መቁረጥም ወደ እናንተ እየመጡ መሆኑን አስቡ። ይህ ከአንድም ሁለቴ ገጥሞኛልና። እግዚአብሔር በተቃራኒው ያስብልኝ ዘንድ እማጸነዋለሁ። ሃዘን ምን ያክል ከባድ ነው ግን? ይኽን ከገጠመው ሰው ውጭ ይረዳዋል ብዬ አላስብም።
እማዬ ነፍስሽን እ…
💔15😢11
7 Jan 2026, 06:36 UTC221 views8 reactionsread 9 August 2026 Photo
"ሰዎች ከሰማነው ነገር ይልቅ ያየነውን እናምናለንና ጥርጣሬያችንን ያስወግድ ዘንድ ራሱ በሚታይ ሥጋ መታየትን ወደደ"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ✍️
እንኳን ተወልዶ ወለደን😍
መልካም የልደት በዓል🙏
❤6👍2
2 Jan 2026, 12:15 UTC193 views6 reactionsread 9 August 2026 Video
#እንኳን_አደረሰን
#አቡነ_ተክለሃይማኖት
#ደብረሊባኖስ
❤4🔥2
12 Dec 2025, 08:54 UTC424 views9 reactionsread 9 August 2026 Photo
#ያልታተመ_ተዓምረ_ማርያም
#እንኳን_አደረሰን
ምስክርነት ከተባባሪ ፕሮፌሰር እና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም ዶ/ር ሰገነት ብዙነህ🙏
❤7🙏2
Signed Tesfaye Birhanu
9 Nov 2025, 01:10 UTC159 views5 reactionsread 9 August 2026 Photo
#ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ
#ሰቆቃወ_ድንግል
ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡
❤5
Signed Tesfaye Birhanu
6 Nov 2025, 21:08 UTC140 views2 reactionsread 9 August 2026 “እርሱ ደሙን አፍስሶልናል ስለዚህ ሌላ ደም መፍሰስ የለበትም!”
"በክርስትናችን በሃይማኖታችን መገደላችን የሚቆመው መቼ ነው? ነፃነት እንፈልጋለን። የሰው ልጆች ደም በከንቱ መፍሰስ መቆም አለበት። ይኼ ፖለቲካ አይደለም። ሰላም መሻት፣ ዕረፍት መፈለግ፣ አንሙት ማለት ፖለቲካ ሳይሆን ሰብአዊ መብት ነው። ሰው መሆን ነው። ደከመን። ብዙ ጊዜ ሰማን። እናንተም በእኛ ፈረዳችሁብን። እናንተም ወቀሳችሁን። እውነት አላችሁ።
ግን ለማን ነው የምንነግረው ይኼንን? ማን ነው የሚሰማን ይኼንን? ማን ነው የሚያቆመው ይኼንን?
ተለማመድነው እኮ። ስንቶቻችን ስናልቅ ነው የሚቆመው? ይብቃ። ሕዝባችን ዕረፍት ይፈልጋል። ሞት ሰለቸን በቃን። ደም መፍሰስ ሰለቸን። ይበቃናል። …
❤2
Signed Tesfaye Birhanu
7 Sept 2025, 09:45 UTC176 views2 reactionsread 9 August 2026 "መኪና ሞልቷል፤ እግዚአብሔር ካለ መጣን።"
ውርጩ ፊታቸውን አጨፍግጎታል። ፎጣ ተከናንበው ሥራቸውን እያጧጧፉት ነው። ........"... ባባ አዲስ አበባ ነህ?" መነሃሪያ ውስጥ ዓይኑ የሚራወጠውን ተጓዥ በርቀት ይጣራሉ። ልንገባበት የነበረው መኪና ረዳት "ለአንድ ሰው ብቻ ስለሆነ ቦታ ያለኝ እናንተ ወደ ቀጣዩ ሂዱ" አለን። የተረኛው መኪና ረዳት ከጋቢናው ጀምሮ ቄጤማ እየጎዘጎዘ ደረስንበት። የያዘውን ቄጤማ ሳይሳሳ ለቤት እንደሚነሰነሰው እየነሰነሰ ሳለ ጠጋ ብዬ "በዓል በዓል እንዲሸተን ነው?" አልኩት እርሱም "አዎ በዓልም አይደል!" አለ። ቀጥሎም "የኛ በዓል መዋያ መኪናችን ነች። መኪናችን ማለት ለእኛ ሥራ ቦታችን ቢሯችን ነች። በዓል ማክበሪያ ቤታችን …
❤2
Signed Tesfaye Birhanu
7 Sept 2025, 09:44 UTC111 viewsread 9 August 2026 Photo
"መኪና ሞልቷል፤ እግዚአብሔር ካለ መጣን።"
ውርጩ ፊታቸውን አጨፍግጎታል። ፎጣ ተከናንበው ሥራቸውን እያጧጧፉት ነው። ........
፨ መጪው የተስፋ ዘመን አሽከርካሪዎቻችን፣ አሻጋሪዎቻችን በሰላም ገብተው የሚወጡበት እንዲሆን እመኛለዉ። ካህኑን ከደብሩ፣ ሼኹን ከመስጊዱ፣ ገበሬውን ከማሳው፣ ተማሪውን ከደብተሩ፣ ሹፌሩን ከመሪው፣ ሐኪሙን ከ... የማይለይብን ዓመት ይሁን። አሜን።
#ሰናይ_ዘመን_፳፻፲፰
#Happy_New_Year_2018
Signed Tesfaye Birhanu
10 Jul 2025, 17:55 UTC150 viewsread 9 August 2026 "ጌታ ሆይ የተጨነቀችውን ነፍስ አሳርፍ!"
Signed Tesfaye Birhanu
5 Jul 2025, 08:13 UTC156 views1 reactionsread 9 August 2026 Forwarded from @ThequorachannelFile
Unilateral global renal infarction in a patient with ischemic stroke and hypertensive heart disease in a resource limited setting: a case report
Tesfaye Birhanu Abebe, Getahun Jiru Bedada, Yakob Tadesse Fantu, Diriba Shiferaw Negese, Biniyam Bona Tasi, Henok Dessie Wubneh, Fraol Zeleke Desta & Solomon Kebede Adugna
Correspondence: Tesfaye Birhanu Abebe
* You can share your research publications here
➡️ Share
@T…
👍1
Signed Tesfaye Birhanu
10 Jun 2025, 20:10 UTC172 viewsread 9 August 2026 Forwarded from @tesfa_biranaye
https://youtu.be/VaG9QFdTQ7I
Signed Tesfaye Birhanu
10 Jun 2025, 20:10 UTC152 views1 reactionsread 9 August 2026 እስቲ ዛሬ ደግሞ መርሃግብር አብረን እንምራ🙂
#የሰርግ_መርሃግብር
ሰው እናቱንና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋ ይጣበቃል ይላል ቃሉ ይኼው እኔም አክላለሁ እናቱን አባቱን እህቱን ወንድሙን ብቻ አይደለም የሚተወው ራሱንም ጭምር እንጂ። ከዚህ በኋላ የገዛ ንብረቱ ላይ ብቻ ሳይሆን የገዛ ሰውነቱ ላይ የማዘዙንም ሥልጣን አሳልፎ ሰጥቷልና። ሙሽሮች ለዚህ ወግ ማዕረግ ላደረሷቸው ቤተሰቦቻቸው ምስጋናቸውን እየገለጹ ነው። ጉልበት ስመው እየገቡ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን። እግዚአብሔርን እናመስግን። እልልልል
(ሙሽሮች ወደ ተዘጋጀላቸው መድረክ እያቀኑ ነው)
ትውውቃቸው አሥር መስከረም ሊሞላው ወራት ነበር የቀሩት አሥረኛውን ያንተ ሆኜ ያንቺ ሆኜ ላክብረው ብለው ቀደሙ…
❤1
Signed Tesfaye Birhanu
Showing the 12 most recent of 13 posts we hold for @sutafeconena. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.