15 Jan 2026, 21:23 UTC645 views45 reactionsread 7 August 2026 ከሰዎች መሃከል ተቀምጬ በመሃል "ራሴን አሞኛል" ስትለኝ " ውይ ምስኪን አይዞሽ እሺ እኔስ ራስ ምታት አይቼም አላውቅ" አልኩ በምን ፍጥነት እንደሆነ አላውቅም እራሴን የማይግሬን ታማሚ ሆኜ አገኘሁት።
"ለራስ ምታት ደግሞ የምን ፊት መስጠት ነው በሰው መሃል መርሳት ነው እንጂ" ስል ቆይቼ ራሴን ሳልወድ በግዴ ከሰው ስርቅ እና ከስብስቦች ስሸሽ አስተዋልኩ።
"መድሃኒት ምናምን ማስለመድ ጥሩ አይደለም"ብዬ የማምን እኔ ይሄ በሽታ ያለ መድሃኒት አላንቀሳቅስ ሲለኝ አየሁ።
ምን ያህል ኒዕማዎቻችንን በምላሳችን ሸኝተን ይሆን?
ማይግሬን ታማሚ አይመከርም።🤫🤫
@sumeyasu
❤34🥰8🔥3
Sumeya sultan pinned «አንዳንድ ሰዎች የተፈጠሩት ለሚሰሩት ወይም ለሚታወቁበት ስራ ብቻ አይደለም። ይህን ያየሁት በ ፉዓድ ነው። ፉዬ አብዛኛው ሰው እንደሚያውቀው ጸሃፊ ብቻ አይደለም የተፈጠረው ለዛ አይመስለኝም ሁላ። እንደው "የነካኸው ሁሉ ይመር" ተብሎ ስለተመረቀ ጽሁፉም ልብ የሚገባ ሆነለት እንጂ ፉዬ በጽሁፉ ዳዕዋ ሊያደርግ የተፈጠረ ነው። ጽሁፍ በ ፉዬ እና ለተፈጠረለት አላማ የተዘረጋ መተላለፊያ ድልድይ እንጂ እሱማ እንደው…»
4 Dec 2025, 13:39 UTC970 views16 reactionsread 7 August 2026 አንዳንድ ሰዎች የተፈጠሩት ለሚሰሩት ወይም ለሚታወቁበት ስራ ብቻ አይደለም። ይህን ያየሁት በ ፉዓድ ነው። ፉዬ አብዛኛው ሰው እንደሚያውቀው ጸሃፊ ብቻ አይደለም የተፈጠረው ለዛ አይመስለኝም ሁላ። እንደው "የነካኸው ሁሉ ይመር" ተብሎ ስለተመረቀ ጽሁፉም ልብ የሚገባ ሆነለት እንጂ ፉዬ በጽሁፉ ዳዕዋ ሊያደርግ የተፈጠረ ነው። ጽሁፍ በ ፉዬ እና ለተፈጠረለት አላማ የተዘረጋ መተላለፊያ ድልድይ እንጂ እሱማ እንደው በኢማናችን ደከምከም ያልነውን ሰብሰብ አድርጎ ጀነት ሊያስገባ የተላከ ዳዒይ ነው። በ ጽሁፎቹ ሁጥባ ከሃገር ውስጥ እና ሃገር ውጪ ያሉ ጀነት ፈላጊዎችን በ ኢማምነት ወደ አላህ የሚጣራ ዳዒ። ኢፋዳ መጽሃፍ ብቻ አይደለችም ኢፋዳ 44 የውሃ ጉድጓድ ናት፤ ኢፋ…
❤13😁3
3 Dec 2025, 15:56 UTC900 views35 reactionsread 7 August 2026 ስጦታዬን ስከፍተው የምታምር ቆንጆ ጥቁር ቦርሳ ናት
"ከለር ነበረው ጥቁር እና ኑድ" አለችና "ኑድ ከለር እንደምትወጂ እያወቅኩ ጥቁር ገዛሁልሽ" አለችኝ
"እንዴ ለምን?"
" የምትፈልጊው ነው እንጂ ኑድ የሚያስፈልግሽ አይደለም። ከመውደድሽ ብዛት ብዙዎቹ እቃዎችሽ እሱን መሆናቸውን አውቃለሁ ጥቁር ነበር የሚያስፈልግሽ" አለችኝ
አላህም ለካ እንደዚህ ነው የሚያስፈልገንን ከምንፈልገው የሚያስቀድም ጌታ😍😍😍እንዴት ያለ ያማረ አምላክ ነው
❤29🔥6
19 Oct 2025, 15:47 UTC≈1,330 views24 reactionsread 7 August 2026 የ እናቷን መሞት ልናረዳት ወደ ጊቢዋ ስንገባ ከዲምፕሏ የሳቅ ኑር እየወጣ አይኗ ከመሳቅ ብዛት እያነባ ነበር።
ሳቋ ይጋባ ነበር እኮ። የጀመረችውን ጨዋታ ሳታበቃ፣ የሳቅ እምባዋን ሳትጠርግ ነበር ከበላይዋ የሃዘንን ካባ ያለበስናት።
ክፉ እኛ የሚጋባ ሳቅዋን የቀማናት እኛ🥹
ምስኪን እሷ የሚመጣባትን ሳታውቅ ሳቋን ያልጨረሰች
@sumeyasu
@sumeyaabot
😢18❤6
29 Sept 2025, 17:08 UTC≈1,460 views21 reactionsread 7 August 2026 እስከ ቅርብ ጊዜ ሰደቃ መስጠት ለሁሉም የገራ እና ሃብታም እንደ ሃብቱ ድሃም እንደ አቅሙ ለ ሰበቢያው የሚሰጥ ይመስለኝ ነበር። ለካ መስጠት መቻል አላህ ለሁሉም የማያድለው ኒዕማ ነው። በተለያየ ጊዜ የሰደቃ ጥሪዎች ላይ በማስተባበር ሲሰራ ሳይ ግን መስጠት ካለመቻል በላይ በምላሶቻቸው የ አላህን ፊት ፈልገው የሚለፉትን ሲያቆስሉ እና በ 100 ብር ለኛ ሃጃ ቆመው አላህ ለነሱ ሃጃ እንዲቆም የማይመርጡ ብዙዎችን ሳስተውል ወላሂ አግርቶላቸው በ ሰው እጅ ያነሰችውን አላህ ጋር ትልቅ ማበደርን የሆነውን 50ብር ሳይቀር የሚነይቱትን ሳይ "አላህ እንዴት ወደዳቸው?"
በኸይሩ የምታውቁት ኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት
22የውሃ ጉድጓድ አስቆፍራለሁ ብሎ 44ማሳካት የቻለው የኛ ኢ…
❤16🔥4👏1
4 Sept 2025, 16:06 UTC≈1,570 views57 reactionsread 7 August 2026 "ስትመርጪ ስትመርጪ ነዋ እስካሁን ያላገባሽው?"
እኔ: "ድብን አድርጌ እንደው መርጬም በሆነልኝ "
"ከሁሉም የሞላለት ማን አለና ነው እየታገልን እንጂ"
"አላህዬ ጋር አላህዬ ጋር አለ። ዱዓዬን ሰሚ ጌታዬ ጋር። ኒያዬን አዋቂው አንድ አላህ ጋር። የሚገባኝን የሚያውቅ የልቤ ጠጋኝ አንድ አላህ ጋር ያ ልኬ የሆነ ሰው አለ። ዱንያ ላይ ኖሮት እኔ ላይ ማጉደልን የሚያያፍረውን፣ ከአባቴ ቤት አውጥቶ የማይረግጠኝን፣ የማያጎሳቁለኝን አላህዬ ጋር አለ"
"ለሁሉም አላህ አይደል የሚሰጠው? እንደው ብዙ አትመኚ እስቲ"
"ስለሁሉም አላውቅም የኔ አላህ ግን ዱዓዬን መመለስ የሚያፍር ጌታ ነው። ትንሽ ላሰብኩት ብዙ ሚሰጠኝ።"
@sumeyasu
@sumeyaabot
❤32🔥20🥰5
24 Aug 2025, 05:52 UTC≈1,670 views42 reactionsread 7 August 2026 ኸሚስ ምሽት ነው። ጣፋጭ የኸሚስ ወጎችን ከወዳጆች ጋር እየተጨዋወትን ድንገት "ጓደኛሽ አርፋለች" የሚል ሜሴጅ ገባልኝ😭። ዱንያ ስትጠበኝ፣ መተንፈስ ስቸገር ራሴን አየሁት። እኩያዬ ናት ገና አንድ ፍሬ ወጣት። ልንሞሽራት ቀን ስንቆጥር የነበረች አንዲት የኛ ተወዳጅ በድንገት ወደ አኺራ ተሻገረች አሉ።
ምድር የመስፋቷን ያህል ስትጠብብኝ ዳግም ሰው ሆኜ የምቆም እስከማይመስለኝ ነበር። ዳግም እንባ ከ አይኔ የማይቆም እስኪመስለኝ ለሊት እና ቀኑን ሳለቅስ ቆይቼ ጀናዛዋን ልናጥብ ስንሄድ የተሰበሩ ልቦችን ማየቱ፣ የምትንሰፈሰፍ እናትን ማየት፣ጥጉን ይዞ የሚያለቅስ አባት...ብቻ ልብ ሰባሪ ትእይንቶች።
ከፍነናት ወዳጆቿ ግንባሯን ስንስመው ትኩስ እንባዬ የጀናዛዋ ፊት ላ…
😢40❤2
16 Aug 2025, 05:53 UTC≈1,450 views34 reactionsread 7 August 2026 ተማሪ ሆነን እኔና እህቴ በጣም የምንወደው ቆንጆ ቤት ነበር ። ያ ቤት ለ እድሜያችን ከምንወደው ፒዛቸው እና "ጁስ ያለዛ ቤት" የሚያስብለን መጠነኛ ካፌ ነበር። ከ አመታት በኋላ ከ እህቴ ጋር በ ስራ አጋጣሚ ወደዛ ሰፈር ስንሄድ ጎራ ብንል ቤቱ ግርማው ኮስምኖ፣ በፊት የነበረው ፒዛ እና ጁስም እንደዛው እንዳለ አገኘነው። አልጣፈጠንም። ቦታውም ምቾት ነሳን።
"የሆነ ነገር ተቀይሯል አይደል?" አልኳት
"አዎ ከዛ በኋላ ብዙ አየን " አለችኝ።
ማደጋችን መሰለኝ በፊት ያስቀይሙን የነበሩን ጉዳዮች አሁን ላይ ከተነጋገርናቸው በኋላ ትዝ አይሉንም። መብሰላችን መሰለኝ በፊት ያስቁን የነበሩ ጉዳዮች ላይ አሁን በ ቁም ነገር ቀይ መስመሮቻችን ሆነዋል። ከፍታን ለመድንና …
❤28👏5🔥1
11 Aug 2025, 18:18 UTC≈1,560 views38 reactionsread 7 August 2026 የቅርብ ወዳጄ ነው።ሲከፋኝ ውስጡ ይነግረዋል መሰለኝ ረጅም ወራት እንኳን ባናወራ የከፋኝ ቀን የሚጠራው ነገር አለ ደወለልኝ። ረጅም ሰዓት ብሶቴን አወራሁት ሲሰማኝ ቆየና
"እንደማያከፍር እና እንደማይገድል ያለ ፈተና ኒዕማ የለም" አለኝ። አንክፈር ብቻ። አንሙት ብቻ ሁሉም በኸይር ነው ክታቡ
❤33👍2🔥2🤔1
30 Jun 2025, 16:59 UTC≈1,890 views35 reactionsread 7 August 2026 የዱንያ ጥፍጥና በ አስታዋሽ ወዳጆች መታደል ሲጨመርበት ነው
"በ ዱአዬ እኮ አስታውሼሽ"
"ባለፈው እኮ ትዝ ብለሽኝ"
"ይሄን ለራሴ ስገዛ ትወጂዋለሽ ብዬ ላንቺም ገዛሁ"
እኚህን ቃላት ሲሉን ልባችን በ ደስታ የምትቦርቅ ነፍስ ያለችን እልፍ ነን። ስንወደድ የምንዘል፣ በመልካም ስንታወስ የምንቦርቅ ምስኪኖች😍😍
ብንራራቅም የማንረሳችሁ፣ ባንደዋወልም ናፍቆታችሁ በ ዱዓችን ውስጥ የምናስታውሳችሁ መልካሞች አላችሁ
ልቤ እስከ ጀነት የምትወዳችሁ ብዙ ናችሁ😍
@sumeyasu
@sumeyaabot
🥰20❤11👍3🔥1
16 Jun 2025, 17:34 UTC≈1,940 views12 reactionsread 7 August 2026 "መቼ ነው" ይሄንን ሰውማ አገባዋለሁ" ያልሽው"
"አባያ የመጀመሪያ ስጦታ ሲሰጠኝ"
ቲክቶክ ላይ @hanoonabaya2004 እስከማይ ድረስ እና የ አባያዎቹን ጥራት እና ስፋት ሳይ ነው በቃ እውነትም ምርጥ ጥሎሽ ያልኩት። በ ሱመያ ነው የመጣሁት ላላት ቅናሽ ታደርጋለች።
ለሱመያ ስጦታ ነው ላላት ደግሞ በደንብ ትቀንሳለች😂ለኔም ለናንተም እየሄዳችሁ ግዙ
በቴሌግራም ቀጥታ ለማግኘት @Kiyuye20
@sumeyasu
@sumeyaabot
❤8😁2🔥1🥰1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @sumeyasu. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.