21 Nov 2022, 13:42 UTC310 viewsread 8 August 2026 "ራሱን አዋቂ ነኝ ሊል...!"
... ጸጉርህ አድጓል፤ ጺምህ ምንድነው ደግሞ ... ቢያንስ ሌላው ቢቀር ጺምህን አንሳው እንጂ ... ከብዙ የስሜት ውጥረት፣ ጊዜ ዕጥረት፣ ከአጥንት ውፍረት በኋላ ... ጫማ ለበስኩ። አወለቅኩ። ... ለካስ ሱሪ ሳልለብስ ነበር። ደግሞ ሌላ የጊዜ ብክነት። በሩጫ ሱሪ ፍለጋ፤ ከመኝታ ክፍል ሳሎኑጋ...።
ለሞት... ምን ያህል ጊዜ ቀረኝ? የጸጉር ማስከርከሚያ ያህል? ... የጺም ርዝመት ያህል? ... ከቤት እስከ ውበት ሳሎኑ ርዝመት ያህል? ወይስ የጊታር አውታር ርግብግቢት ያህል? ... ( Imagine your death if life is inversely proportional to frequency?)
... አንድ መጽሐፍ መረጥኩ…
Signed Sol Grace
17 Nov 2022, 09:29 UTC299 viewsread 8 August 2026 ትንሽ ስለ አገራችን ጉዳይ
“እናት ሀገር ፍቅር” ይለው የለ ደራሲው፤ በአንድ ቅርጫት ሲሠልሳቸው? እናቴን እወዳታለሁ (ፍቅር 1)፣ አገሬን እወዳታለሁ (ፍቅር 2)፣ ፍቅርን እወዳታለሁ (ፍቅር 3)። በእርግጥ “እናቴን ... ፍቅርን እወዳታለሁ” ብል የቦለቲካዊ ፈሪሳዊ ያደርገኛል። ፍቅርን መውደድ ግን ከቦለቲካም ከፈሪሳዊነትም ይርቃል፤ ተዓምር ነው ብለውታልም!
እስከ 24 ዓመት ማየት ተስኖት መንገድ ዳር ፍቅር እንዲመጸውቱለት ወዲያ ወዲህ የሚል፤ እርሱም ሆነ ቤተሰቦቹ ምንም እርም ሳይሰሩ ተፈጥሮ የበየነችበትን ከርታታ ድንገት ሲመለከት አንዲት ዛፍ እንደ ሰው ወዲያና ወዲህ ሽው ... ሽው ብትል ማንም ባይመሰክርለት እርሱ ለራሱ እማኝ አይሆንም ወይ? አሁንም …
Signed Sol Grace
14 Dec 2021, 11:08 UTC486 viewsread 8 August 2026 Photo
ለሙከራ ያህል የተሠራ...
Signed Sol Grace
15 Nov 2021, 20:25 UTC636 viewsread 8 August 2026 እንደምትወዳት ንገራት
==========
ሕይወት የአድባር በሬ፣ መቼ ሁሌ ይጠመዳል፣
ለጊዜው ብቻ የመጣ፣ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል፣
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፣ ደሞ ከአንተ ይወሰዳል።
ቀለበት፣ አምባር አይደሉም፣
እጅህ ላይ፣ ሁል ጊዜ የሉም፣
ቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራት፣
ዛሬውኑ፣ አሁኑኑ፣ እንደምትወዳት ንገራት።
አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ፣
ምዑዝ ሽታዎች ሳይጠፉ፣
ያፀጅ በሮች ሳይቆለፉ፣
በንቦች ጎዳና ላይ፣ ተርቦች ሳይሰለፉ፣
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ፣
ሕይወት --- የላምባ መብራት፣
አሁኑኑ ዛሬውኑ፣ እንደምትወዳት ንገራት።
ርቃ ሳትገሰግስ፣
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደ ጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደ እማትቀባው…
Signed Sol Grace
3 Nov 2021, 22:51 UTC496 viewsread 8 August 2026 Video
Enjoying @ ...
@sgaltrature
Signed Sol Grace
22 Jul 2021, 19:40 UTC≈1,570 viewsread 8 August 2026 አንቺ ኮርቻ ሰሪ
አንቺ ኮርቻ ሰሪ
ሳንቃውን አቅልይ፣ ጠርዙን አለስልሺ፣
ያንዱ ፍጡር ወንበር፣
ለአንዱ ፍጡር ቀንበር፣
መሆኑን አትርሺ።
====================
በዕውቀቱ ስዩም፣ አዳምኤል፣ ገጽ 44
@sgaltrature
Signed Sol Grace
20 Jul 2021, 21:07 UTC≈1,120 viewsread 8 August 2026 ዘበት ሊሆን ነው ወይ?
ዘበት ሊሆን ነው ወይ፣
.............. ታሞ ጠበል መሄድ፣
..........................ተሰብሮ ወጌሻ፣
አልጋ 'ሚይዝ ጠፋ፣
.............እርሳስ እንደ ኪኒን፣
............................እየዋጠ አበሻ።
=================
በድሉ ዋቅጅራ፣ የራስ ምስል፣ ገጽ 67
@sgaltrature
Signed Sol Grace
19 Jul 2021, 13:33 UTC≈1,180 viewsread 8 August 2026 እወድሃለሁ ካልሺኝ....
እንዲህ ምሸልል፣
በውበት ቁንጅና፣ በቁዳ ልስላሴ፣
ድኩም ከጉንዳን፣ ጀግና ከሥላሴ፣
የሆንኩት እንዲሁ እንዳይመስልሽ፣
እሳት በላሰው፣
ማጭድ ይመስል፣ ምላጭ አልፌ፣
በኩሪንችት ውጋት፣
በፍትጊያ በእሽት፣
እሳት አዝሎኝ፣ ነበልባል ታቅፌ፣
ከጣት በማይሻል፣ ዱልዱም ወስፌ፣
ተሰፋፍቼ፣
ተበሳስቼ፣
ነው ያማረብኝ፣
እንጂ እንዳይመስልሽ፣
መንገዴ ጨርቅ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ፣
እወድሃለሁ ካልሺኝ፣ ከኋላዬ እለፊ!
=====================
ሐምሌ ፲፪~፳፻፲፫
©Sol Grace
@sgaltrature
Signed Sol Grace
13 Jul 2021, 03:58 UTC904 viewsread 8 August 2026 Video
መቻል ወጂ "የፍትህ ያለ" በሚል ቅኔ ስለ ፍትህ ጮዃል! ስሙት እስቲ!
Signed Sol Grace
12 Jul 2021, 17:58 UTC≈2,210 viewsread 8 August 2026 ግግምናዬ ነሽ!
=============
....
እንኳን የነበረው፣ ያለውም ቅሞ አይለየኝ፣
በገገሞች ቋንቋ፣ የኔ ነሽ ያንቺ ነኝ!!
እኔ ምልሽ ውዴ፣
አንቺም በኔ ፍቅር፣ ገግመሻል እንዴ?
እንግዲያስ....
በገገማ ጎንሽ፣ በገገማ ጎኔ፣
በፍቅር ዙፋንሽ፣ በፍቅር ዙፋኔ፣
እግዜር ያሰንብተን፣
እንጂ ብልጥ አልሆንም፣ ግግምናን ትተን!
================
አሌክስ አብርሃም፣ አንፈርስም አንታደስም፣ ገጽ ፻፩
@sgaltrature
Signed Sol Grace
11 Jul 2021, 19:47 UTC≈2,060 viewsread 8 August 2026 ያንድ ምሽት ናፍቆት
=============
ዛሬ ማታ ታምራለች ጨረቃ፣
ፊትሽን ፊቷ ላይ፣ እንደጭንብል አጥልቃ፣
እንሆ እኔም ቁሜያለሁ፣
የዛፉን መልክ መልኬ አድርጌ፣
በሩቅ ማየት ተፈቅዶልኝ፣
መንካቱን ግን ተነፍጌ።
====================
በዕውቀቱ ስዩም፣ የማለዳ ድባብ፣ ገጽ ፶
@sgaltrature
Signed Sol Grace
8 Jul 2021, 05:53 UTC≈1,570 viewsread 8 August 2026 መካሪና ነካሪ
=========
አባ በቤተ-መቅደሱ
"ልጄ አትጠጣ ይሉኛል፤
ምሽት ስንገናኝ፣
ሂሳቤን ይከፍሉኛል።
===========
ሰሎሞን ሞገስ፣ እውነትን ስቀሏት፣ ገጽ ፴፭
@sgaltrature
Signed Sol Grace
Showing the 12 most recent of 19 posts we hold for @sgaltrature. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.