27 Sept 2026, 18:01 UTC284 views1 reactionsread 29 September 2026 ለሁሉም ንግግር ቦታ ሲኖረው ለሁሉም ቦታም የሚመጥን ንግግር አለው።
አንድ ሰው ዑመር ቢን ዐብዲልዓዚዝ ታመው ሊጠይቅ ሄደና እንደት አረገወት ብሎ የበሽታውን ሁኔታ ጠየቀ እሳቸውም ነገሩት ሰውየውም በዛ በሽታ የሞቱ ሰዎችን መቁጠር ጀመረ ዑመር ትምህርት ቢሆነው ብለው የታመመ ስትጠይቅ ታማሚ ፊት እንድህ አይወራም አሁንም ከሄድክ መልሰህ አትምጣ ዚያራህ ቢቀር ይሻላል አሉት።
ሌላው የታመመ ልጠይቅ ብሎ ታማሚው ቤት ሲደርስ ለቤተሰቦቹ በሉ አላህ አጅሩን ያብዛላችሁ አላቸው የታማሚ ቤተሰቦችም በግርምት አልሞተም እኮ ቢሉት ያው ኢንሻ አላህ መሞቱ አይቀርም ብየ ነው አላቸው።
@rebizidniielma
👍1
Signed توفيق الحبشي
5 Sept 2026, 06:41 UTC188 views7 reactionsread 29 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤3👍3🥰1
Signed توفيق الحبشي
27 Aug 2026, 16:40 UTC218 viewsread 29 September 2026 ሱብሐነሏህ
አቡ ሙስሊም አል-ኸውላኒ ዱዓቸው የማይመለስ በለመኑ ጊዜ ወዳው አላህ የሚቀበላቸው ደግ ሰው ነበሩ። ህፃናቶች በጣም ሯጭ የሆነውን የሜዳ ፍየል ሲያዩ ዱዓ አረድርግና እንያዘው ብለዋቸው ዱዓ አድርገው ህፃናቶቹ በእጃቸው ይይዙት ነበር።
ታዲያ አንድ ሴት ጥሩ የነበረችውን ሚስታቸውን ባህሪ እንድትቀይር አረገችባቸውና አላህ አይኗን እንዲያጠፋው ዱዓ ቢያደርጉ ወዲያው እልም አለ። ሴትየዋም በአላህ ለመነቻቸውና አሳዘነቻቸው መልሰው አላህን ለመኑት በቅፅበት የዐይኗ ብርሀን ተመለሰ።
(ጃሚዕ አል-ኡሉም ወል-ሂከም፣ ገጽ፡ 771)
Signed توفيق الحبشي
21 Aug 2026, 18:47 UTC237 views4 reactionsread 29 September 2026 "ከዕውቀት ሁሉ ትልቁ ትልቁን ጌታ ማወቅ ነው ኢብኑ ተይሚያህ"
👍4
Signed توفيق الحبشي
22 Jul 2026, 18:14 UTC290 views6 reactionsread 29 September 2026 ከስስት በላይ የሚያስጠላው የሰጡትን መናገር ነው
❤6
Signed توفيق الحبشي
23 May 2026, 19:48 UTC341 views3 reactionsread 29 September 2026 ሱብሐነሏህ
የዕውቀት ባሕር የሰመጡት፡ መጽሐፍትን በመቶዎች ጊዜ የደጋገሙ ሊቃውንት
• ኢብኑ ሂሻም፦ «አልፊያህ ኢብኑ ማሊክን» 1,000 ጊዜ ደጋግሞታል።
• ጋሊብ ቢን ዓቲያህ፦ «ሶሒሕ አል-ቡኻሪን» 700 ጊዜ አንብቦታል።
• አቡበከር አል-አብሀሪ፦ «ሙኽታሰር ኢብኑ ዓብዱል ሐከምን» 500 ጊዜ ደጋግሞታል።
• ኢማም አን-ነወዊ፦ የገዛሊን «አል-ወሲጥ» 400 ጊዜ ደጋግመውታል።
• አቡ ሰዒድ አል-በርደዒ፦ «አል-ጃሚዕ አል-ከቢርን» 400 ጊዜ ደጋግሞታል።
• ሱለይማን አል-ዐለዊ፦ «ሶሒሕ አል-ቡኻሪን» 280 ጊዜ አንብቦታል።
• ሸይኽ አቡ ኢስሐቅ አል-ሑወይኒ፦ «አል-ኢለል» የተሰኘውን መጽሐፍ 100 ጊዜ ደጋግመውታል። የሚገርመው ደግሞ የሻዝሊን …
❤3
Signed توفيق الحبشي
18 May 2026, 05:35 UTC284 views3 reactionsread 29 September 2026 ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ፡-
"የማንኛውም ሕዝብ (ኡመት) አስተዋይ ሰዎች በሙሉ በዚህ ነገር ላይ ተስማምተዋል፦ እውነተኛ ድሎት (ጸጋ) በድሎት አይገኝም፤ ምቾትን የመረጠ ሰው እውነተኛ እረፍት ያመልጠዋል። እንደየ መከራው መጋፈጥና እንደ ችግሮቹ ትዕግስት መጠን ደስታውና እርካታው ይጨምራል።
ዓላማ ለሌለው ሰው — እውነተኛ ደስታ የለውም፤
ትዕግስት ለሌለው ሰው — እርካታ የለውም፤
መከራን ላልቀመሰ — ድሎት የለውም፤
ድካምን ላላየም — እረፍት የለውም፤
ይልቁንም አንድ ባሪያ (ሰው) ለጥቂት ጊዜ ቢደክም ለረጅም ጊዜ ያርፋል። ለአንድ ሰዓት ያህል የትዕግስትን መራራነት ቢታገስ፣ ይህ ትዕግስቱ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት (ጀነት) ይመራዋል። በዘለዓለማዊው …
❤3
Signed توفيق الحبشي
17 Apr 2026, 06:47 UTC371 views3 reactionsread 29 September 2026 ድንቅ የህይወት መርህ
"ያለፈ አይወሳም"
መስዑድ አል-ሀመዛኒ ከምርጥ ሰዎች አንዱ ነበሩ። ሰዎችንም በብዛት ይቅር ይሉ ነበር፤ ይቅርታ ሲያደርጉም፦ «ያለፈው ነገር አይነሳም (አይወሳም)» ይሉ ነበር።
ከሞቱ በኋላ በህልም ታዩና እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦
«አላህ ምን አደረገህ? (ምን ገጠመህ?)»
እሳቸውም እንዲህ አሉ፦
«አላህ በፊቱ አቆመኝና፦ 'አንተ መስዑድ ሆይ! ያለፈው ነገር አይወሳም፤ ወደ ጀነት ውሰዱት' አለ።»
ታሪኩል ኢስላም/ኢማም አዝ-ዘሀቢ (42/327)
https://t.me/rebizidniielma
❤3
Signed توفيق الحبشي
2 Apr 2026, 08:37 UTC298 viewsread 29 September 2026 "ኢኽላስ ማለት በሥራህ ላይ ከአላህ ውጭ ሌላ ታዛቢ (ተመልካች)፣ ከእርሱም ሌላ ምንዳ ከፋይን ላትፈልግ ነው።"
— መዳሪጁ-ሳሊኪን (2/29)
https://t.me/rebizidniielma
Signed توفيق الحبشي
16 Mar 2026, 10:35 UTC345 views0 reactionsread 29 September 2026 ጉድኮ ነው ሱብሐነሏህ
የዑለማዎች መከባበርና ልግስና፡- አንድ ድንቅ ታሪክ
በዑለማዎች መካከል ከተከሰቱ እጅግ አስገራሚና ክብር የተሞላባቸው አጋጣሚዎች አንዱ እኔ ራሴ (ዓብዱልባሲጥ ዩሱፍ አል-ገሪብ) ከሸይኽ ዓብዱልቃድር አል-አርናኡጥ (አላህ ይዘንላቸውና) በጆሮዬ የሰማሁት ታሪክ ነው። ይህ የሆነው እሳቸው ከመሞታቸው ጥቂት ዓመታት በፊት ወደ ተዘዋወሩበትና እጅግ ሰፊና ውብ ወደሆነው አዲሱ ቤታቸው ከአንዳንድ ምርጥ ወንድሞች ጋር ሄደን በጎበኘናቸው ወቅት ነበር።
ሸይኽ ዓብዱልቃድር ይህን ቤት እንዴት ሊያገኙ እንደቻሉ እንዲህ ሲሉ አጫወቱን፦
ሸይኽ በክር አቡ ዘይድ (አላህ ይጠብቃቸውና — በወቅቱ በሕይወት ስለነበሩ) ሶሪያ በሚገኘውና ቤቶቹ አረጅተው በሚፈራርሱበት…
Signed توفيق الحبشي
13 Mar 2026, 16:42 UTC258 views3 reactionsread 29 September 2026 የስግብግቡ "ሐኪም" እና የየዋሁ ስጋ ሻጭ ታሪክ
አንድ ስጋ ሻጭ (ቄራ) ስጋ እየከተፈ ሳለ፣ አንዲት ትንሽ የዓጥንት ስባሪ ተፈናጥራ ዓይኑ ውስጥ ገባች። ዓይኑም ክፉኛ ያመው ጀመር። በዚያን ዘመን ሆስፒታሎች ስላልነበሩ፣ እንደ ሐኪምም ጭምር ያገለግል ወደነበረው ሰፈር ውስጥ ወደሚገኝ አንድ ምላጭ ሰላጭ ዘንድ ሄደ።
ምላጭ ሰላጩ ዓይኑን ካየው በኋላ እንዲህ አለው፦ "ይህ እኮ ቀላል ነው፤ ምንም አይከብድም፤ ትንሽ ማጽጃና ቅባት ብቻ ነው የሚያስፈልገው።" ከዚያም ዓይኑን አሰረለትና "በየቀኑ እየመጣህ ዓይንህን መጽዳት አለብህ" ብሎ አዘዘው።
በሁለተኛው ቀን ስጋ ሻጩ አንድ ኪሎ ስጋና አንድ ኪሎ ጉበት ይዞ መጣ። ምላጭ ሰላጩም ዓይኑን ያጸዳና ቅባት ይቀባለታል …
❤3
Signed توفيق الحبشي
12 Mar 2026, 10:49 UTC696 viewsread 29 September 2026 የጭንቅ መገላገያ ድንቅ ታሪክ
በኢራቅ ባግዳድ "ከርኽ" በሚባለው አካባቢ የሚኖር፣ በሱናው (በሃይማኖታዊ ትጋቱ) የሚታወቅ አንድ ዓጣር (ሽቶ ሻጭ) ነበር። ይህ ሰው 600 (ስድስት መቶ) ዲናር ዕዳ ይከማችበታል። ዕዳው ሲበዛበት ሱቁን ዘግቶ፣ ከስራው ተቋርጦ፣ ቤቱ ውስጥ ተቀመጠ። ለብዙ ሌሊቶችም ወደ አላህ በመጸለይ፣ በመንከባለልና በዱዓ (ልመና) አሳለፈ።
ከእለታት በአንዱ ሌሊት ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) በሕልሙ አያቸው። እርሳቸውም፦ "ወደ ወዚሩ ዓሊ ኢብን ዒሳ ሂድ፤ እሱ 400 (አራት መቶ) ዲናር እንዲሰጥህ አዝዤዋለሁ" አሉት።
ሰውየው ሲነጋ ወደ ወዚሩ ደጃፍ ሄደ። እዚያ ግን የሚያውቀው ሰው አልነበረም፤ እንዲያስገባው የሚጠይቅለት እስኪያገኝ ድረስ ለረጅም ሰዓት…
Signed توفيق الحبشي
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @rebizidniielma. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.