29 Dec 2023, 08:29 UTC≈5,830 views70 reactionsread 7 August 2026 Photo
#ሊቀ_መላእክ_ቅዱስ_ገብርኤል
🥀ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ኢትዮጵያውያን እሳት ውስጥ ከገባን ቆይተናል:: የሠለስቱ ደቂቅ እምነት ግን የለንም::
እንዲያውም ከእኛስ ናቡከደነፆር ሳይሻል አይቀርም:: ከእሳት እንዳወጣ እርስ በእርሳችን እየተባላን ከእሳቱ በላይ ጥላቻ እያቃጠለን ነው:: አንዱ በሌላው ሞት እየዘበተ አንዱ የሌላው ለቅሶ እያሳቀው የኢትዮጵያ ሠለስቱ ደቂቆች ለፈጣሪም አልመች ብለን ተጨካክነናል::
🥀አንዴ አናንያና አዛርያ ሚሳኤል ላይ ሲወርዱበት አንዴ አዛርያ ከአናንያ ሲጣላ እየዋልን እርስ በእርሳችን ተራ በተራ እየተናከስን በእሳት ውስጥ ሆነን እንኳን መደማመጥ አልቻልንም:: ናቡከደነፆርና ወዳጆቹ በጥላቻ ዓይናቸው እያዩን እንኳን መስማማት አቅቶናል::
ቅ…
👍36❤19🥰9🤔6
Signed Abel
1 Dec 2023, 05:31 UTC≈4,890 views18 reactionsread 7 August 2026 Photo
🌹እንኳን ለጽዮን ማርያም ማሕደረ አምላክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
🌹ጽዮን ማለት ጸወን፣ አምባ ፣ መጠጊያ ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።
🌹አምላከ ቅዱሳን የአማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያምን ጣዕሟን ፍቅሯን ጸጋ በረከቷን ያሳድርብን አሜን
@ortodoxtewadochannal
@ortodoxtewadochannal
👏11❤7
Signed Abel
22 Nov 2023, 06:32 UTC≈4,160 views26 reactionsread 7 August 2026 ‹‹እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ›› (ኢያ.፭፥፲፫)
በቅድስና፣ በውዳሴ፣ በኅብረ ቀለም በመላእክት ዝማሬ በደመቀው በዓለመ መላእክት ውስጥ ቅዱሳን መላእክት በነገድ ተከፍለው ይኖራሉ፡፡ እነርሱም የዘወትር ምግባራቸው እንዲያውም ምግባቸው ፈጣሪን ማመስገን ነው፡፡ ስፍራ ቁጥር የሌላቸው መላእክቱም በሦስቱ የመላእክት ከተሞች ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር በአላቃቸው ስር ሆነው ዘወትር አምላክን ያገለግላሉ፡፡ ለዚህም ድንቅ ሥራው ክብረ ምስጋና ይድረሰውና፣ በኢዮር ከተማ የኃይላት አለቃ አድርጎ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ሾሞታል፤ ይህም የሆነበት ኅዳር ፲፪ ቀን የከበረ በዓል ነው፡፡ ስለዚህ የዚህን የከበረና የገናና መልአክ በዓሉን እንድናደረግ ቅዱሳን …
❤12👍10👏3💯1
Signed Abel
29 Oct 2023, 06:27 UTC≈2,810 views3 reactionsread 7 August 2026 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
.......ከክፍል አንድ የቀጠለ
➠ክፍል ሁለት
●●●●●●●●●●●●●●●●
አብዛኛው ሰው እራሱ በእጁ ጎትቶ ባመጣው ነገር ነው ነፍሱን እየገበረ የሚገኘው።
ወጣቶች በብዛት እራሳቸውን ሊያጠፉ የበቁት እድሜአቸው ሳይደርስ በልጅነታቸው የፍቅር ግንኙትተ ጀምረው ነው።
የፍቅር ግንኙነት ጀምረው ከሆነ ጊዜ በኋላ ግን የግንኙነታቸው ገመድ ሲበጠስ አንገታቸውን ለገመድ ይሰጣሉ።
በዚህ መሰረት ሌሎች ሌሎች ነገሮችንም እየጠቀስን መናገር ይቻላል።
በሌላ መንገድ ደሞ ወጣቱ ባልደረሰበት መከራውም ሆነ ችግሩ ተደራርቦ ይመጣል በዚህም ምክንያት እራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ።
ሰፊ ቦታዎችን የሚይዙት ደሞ መከራን ያልቀመሰ በችግር ያልተገረፈ ሰው ሁሉ …
👍2❤1
Signed Abel
29 Oct 2023, 06:27 UTC≈3,500 views6 reactionsread 7 August 2026 ☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
.....ከክፍል ሁለት የቀጠለ
ሌሎች መከራን በመጋፈጥ ላይ ያሉ ሰዎች እንደዚህ አይነት ዜናዎችን ሲሰሙ ውሳኔያቸው ምን ሊሆን ይችላል?
መቼም የዚህ ዘመን ሰው ሞት ክፉ ነው ብትሉት እስቲ ሞቼ ልየው የሚል ህዝብ ነው።
መርዝ ጥሩ አደምለ ብትሉት እስቲ ጠጥቼ ልየው የሚል ህዝብ ነው። /ጥሩ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማወቅ/
ሌላው ደሞ እራሳቸውን እያጠፉ ያሉ ሰዎችን መቆጣት ይሻላል ፤መርዳት ይሻላል፤ ወይስ እንደ እንቁላል መንከባከብ ይሻላል?
መቆጣት ፦እነዚህን ሰዎች መቆጣት እራሳቸውን እንዳያጠፉ ሊረዳቸው ይችላል አልያም ይባስ ለሞት ሊዳርጋቸው ይችላል።
መንከባከብ፦እነዚህን ሰዎች መንከባከብ እራሳቸውን እንዳያጠፉ ሊረዳቸው ይች…
👍6
Signed Abel
29 Oct 2023, 06:27 UTC≈2,640 views12 reactionsread 7 August 2026 ⚠️እራሳቸውን_የሚያጠፉ!⚠️
●●●●●●●●●●●●●●●●●●
/ሁላችሁም ብታነቡት ትጠቀሙበታላችሁ/
🔥🔥🔥🔥
➠ክፍል አንድ
ሰሞኑን እራሳቸውን እያጠፉ ያሉ ወጣቶች እየተበራከቱ ነው።
ለእራስ ማጥፋታቸው የሆነ ምክንያት እንዳላቸው ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያቸው እየገለፁ እንደሆነ አይተናል።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አንገታቸውን ለገመድ፣አፋቸውን ለመርዝ እየሰጡ እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ዜና ማበራከቱ ለሌሎቹ ሰዎች ተፅዕኖ የለውም?
ሌሎቹ ሰዎች እራሳቸውነሰ እንዲያጠፉ እንደመጠቆም አይሆንም? /አጢኑት/
እራሳቸውን ለማጥፋት ምክንያታቸው በጣም ከባድ እንደሆነ እና ሊወጡት የማይችሉት እንደሆነም ከፃፉት ፅሁፍ እንፃር መገመት ይቻላል።
በዕርግጥ የሁሉም ሰ…
👍11❤1
Signed Abel
10 Oct 2023, 11:31 UTC≈2,560 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ላይ ናቸው።
ከነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ በሰሜን አሜሪካን የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቀደም ሲል በተያዘው የጉዞ መርሐ ግብር መሠረት ጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመለሱ ይሆናል።
የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በረከት አይለየን
ምንጭ፡ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
@ortodoxtewadochannal
@ortodox…
👍4🤩1
Signed Abel
8 Oct 2023, 08:01 UTC≈2,610 views2 reactionsread 7 August 2026 Photo
በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙሪያ ውይይት የሚያደርግ ጉባኤ በፍራንክፈርት እየተካሄደ ይገኛል።
*
የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከነሐሴ ፳፮ - ፳፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ በተወሰነው መሠረት ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመንና አካባቢው እና የምሥራቅ ጎጃም አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ ጠቅላላ ካህናት፣ የሰበካ ጉባኤ አስተዳደር አባላትና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙሪያ ውይይት የሚያደርግ ጉባኤ ዛሬ ጠዋት መስከረም ፳፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም (October 7, 2023) በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ እየተከናወነ…
❤1👍1
Signed Abel
7 Oct 2023, 07:49 UTC≈2,510 views5 reactionsread 7 August 2026 ሰውም ሲኖርም ሲሞትም ፈጣሪውን ማስደሰት አለበት እንጅ ያለ ፍሬ ንስሓ መሞት የለበትም፤ "ግበሩኬ እንከ ፍሬ ሠናየ ዘይደልወክሙ ለንስሓ፤ እንግዲህስ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አድርጉ እንዲል፡፡ (ማቴ.፫፥፰)
ወርኃ ጽጌ የእናታችንን ስደት ከተወደደው ልጇ ጋር የምናስብበት ነው። በተለይም ማሕሌተ ጽጌ በተባለው ድርሰት ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል እርሷን በአበባ ጌታችንን በፍሬ፣ እርሷን በፍሬ ጌታን በአበባ እየመለሰ ብሉይን ከሐዲስ አጣጥሞ የተናገረው ምሥጢር ድንቅ ነው። ክርስቶስን በአበባ ሲመስለው ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ ቅዱስ ያሬድ በድጓው "ትወፅእ በትር እም ሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እም ጉንዱ" በማለት ድንግል ማርያምን በጉንድ ክርስቶስን በጽጌ መስሎ ይናገራል። …
❤2👍2👏1
Signed Abel
7 Oct 2023, 07:48 UTC≈1,480 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
ዘመነ ጽጌ
ዘመነ ጽጌ የሚባለው ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭ ያለው ነው። ይህ ወቅት ዐቢይ የምስጋና ቀናት ያለው ሊቃውንቱ በማሕሌት፣ ምእመናን በፍቅር ሆነው የእናታችን የድንግል ማርያምን ስደት ከተወዳጅ ልጇ ጋር የሚያዘክሩበት ወር ነው። ከማሕሌቱም በተጨማሪ ምንም እንኳን የዐዋጅ ጾም ባይሆንም የእመቤታችን ፍቅር የበዛላቸው በጾም ሆነው የሚያሳልፉት ዐቢይ የምስጋና ወቅት ነው።
ጽጌ ማለት ጸገየ አበበ ከሚል የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን አበባ፣ ውበት፣ ደም ግባት ማለት ነው። አበቦች ውብ፣ ማራኪና አስደሳች ከመሆናቸው የተነሣ የሰው ልጆች በሙሉ አበቦችን ይፈልጋሉ። ምድርም በአበቦች አጊጣ ተሸልማ ስትታይ ክረምት ከለበሰችው ልምላሜ ይበልጥ ታስደስታለች። …
👍2❤1
Signed Abel
6 Oct 2023, 09:14 UTC≈1,410 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
የሰማዕታቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይፈጸማል።
በአዳማ ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት በአርቱ መካነ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል፡፡
---------------------------------------------
መስከረም 24/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያንን በማገልገል ላይ የሚገኙ ታላቁ የጸሎት አባት አባ ተክለ አብ እና ቀሲስ መሠረት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን መሪጌታ ፍሰሐ እና መርጌታ ተቅዋም የተባሉ አገልጋዮችን ታፍነው ባልታወቁ ኃይሎች መወሰዳቸውን የሀገረስብከቱ ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘ…
😭1
Signed Abel
6 Oct 2023, 09:13 UTC≈1,290 viewsread 7 August 2026 Photo
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በታጠቁ ኃይሎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡
(ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት)
በኤልሳቤጥ ቤተ
+++++++++++++++++++++++++++++++++
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳማ ዙሪያ የመካነ ቅዱሳን አርቱ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች በጥይት መገደላቸው ተገለጸ፡፡
ድርጊቱ የተፈጸመው መስከረም 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ ሲሆን ከተገደሉት አንድ ካህን እና ዲያቆን በተጨማሪ ሁለት ካህናትና አንድ ምእመን በታጣቂ ኃይሎቹ መታገታቸውን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡
የታገቱት ካ…
Signed Abel
Showing the 12 most recent of 12 posts we hold for @ortodoxtewadochannal. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.