4 Jul 2026, 18:11 UTC59 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
''አባቴዋ ግን የእውነት እንደምትለኝ የፀሎትክ ምላሽ ነኝ በኔስ የእውነት ደስተኛ ነክ?'' አለቺው
እሱም በስስት አይን እያያት እንደዚ አላት ''እናቴዋ አንቺ ከፀለይኩላትም በላይ በፀሎቴ ውስጥ የረሳሁትን ሁለ ፈጣሪ አሟልቶ የሰጠኝ ሙሉዋ ሚስቴ ነሽ;የኔ ሚስት ነፍሴ አንቺን ስታገኝ ነው ተደላድላ እርፍ ምትለው; ልቤ እንኳን በደስታ ለመዝለል አንቺን ማሰብ በቂው ሆኖል; አይኖቼ ሚያዩትን ውብ ነገር ሁሉ ባንቺ መልክ ነው ሚስሉት; ጆሮዬም ያማረ ዜማ በሰማ ቁጥር ድምፅሽን ይጣራል;አንቺን የሳሙ ከንፈሮቼ ሌላን ከሩቅ ይጠየፋሉ; አንቺን ያቀፉ እጆቼም በዘረጋዋቸው ቁጥር እንቺ የመጣሽ መስሏቸው በጉጉት ይጠብቃሉ።እና ምን ልልሽ መሰለሽ የኔ ሴት 👑 አንቺ የስጋ ሚስቴ…
🥰4❤1
Signed ናትዮጵያ✍️
29 May 2026, 18:51 UTC119 views6 reactionsread 7 August 2026 Photo
ራሴን እንድወደው ታደርገኛለህ ምትል ጓደኛ አለቸኝ🥰
ለነገሮች የምትሰጠው ትኩረት...ሰወች እና ስራዋን ምታከብርበት መንገድ...ባጠቃላይ ከእድሜዋ መብሰሏ ስለሚያስገርመኝ ያላትን ጥሩ ነገሮች ነግራታለሁ....አንተኮ ራሴን እንድወደው ታደርጊኛለህ ነው መልሷ🥰
ዙሪያችን ለይ ያሉ ሰወች መልካም ነገራቸውን ብንነግራቸው...አጥብቀው እንዲይዙት አረ እንደውም እንዳላቸው እንዲያውቁም እናግዛቸዋለን።
እሄ ባህሪ ጥሩ ነው ኢሄንን ብታሻሽለው ደሞ የበለጠ ጥሩ ይሆናል እየተባባልን መተራረማችን ለእርምጃዎቻችን አጋዥ ይሆናል።
ቀናት የሚቀጥሉት ያሉንን ልምዶች በማዳበርና እና አዳዲስ ነገሮችን በመማርና በመጨመር ውስጥ ነው ታዲያ ሁላችንም የመጣንበት መንገድ ለየቅል እንደመ…
❤3🥰3
Signed ናትዮጵያ✍️
28 May 2026, 20:22 UTC87 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
✨ሁሉ ነገሯ ከሰው የተሰራ ትመስላለች።ለልብ ትመቻለች ሳይሆን በእርሷ ሱስ አለመያዝ ከባድ ነገር ነው...አሰማሟ...ዓይኖቿ ውስጥ ያለው መረዳት....እንደቀልድ የምትወረውራቸው ነፍስን ሚጠግኑ ንግግሯቿ ...ሁሉ ነገሯ ያምራል...ምን ያህል ሰርታ...እንዴት ተሰርታ ይሆን እንደዚህ የተዋበችው ....?
...ብቻ ታምራለች...💙🥰
ተቀላቀሉን👉👉👉@natopia_17
💚💛❤️
🥰3❤2
Signed ናትዮጵያ✍️
23 May 2026, 18:36 UTC109 views5 reactionsread 7 August 2026 Photo
አብረን ቁጭ ብለን ነበር በመሀል ድንገት '' አንድ ነገር ግን ታውቃለህ?'' አለቺኝ ፈገግ ብላ😊
ምንድን ነው እሱ ደግሞ የኔ አያልቅባት አልኳት በእጆቼ ጉንጫን እየዳበስኩ😊
ምን መሰለ ዓለሜ ፍቅር አንተ ጋር : ምትሃታዊ ኃይል ነው! ስታወራውም : ስትኖረውም : ልቤን ታቀልጣታለህ. . . ለዚህ ፍቅር እጄን ሰጥቻለሁ : ባንተ ፍቅር ተነድፊያለሁ : ባንተ ተይዤያለሁ : ለጨረቃ እንደማልነሳ ሆኜ ወድቂያለሁ : አፍቅሬሃለው : ናና ትከሻህ ላይ አሳርፈኝ : በሹክሹክታ ቃልህ : ወደ ጆሮዬ ጠጋ በጣም ጠጋ ብለህ : ፍቅርን አነብንብልኝ : ድምፅህ ከየትኛውም : የህይወት ድብርት : ከየትኛውም : የሀዘን ቋት. . . ነፃ ያወጣኛል።
ድምፅህን እወደዋለሁ! ❤'' አለቺ…
🥰4❤1
Signed ናትዮጵያ✍️
19 May 2026, 18:46 UTC99 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
አንዳንድ ሰዎች ፍቅራቸውን አልቀነሱ ይሆናል አገላለፃቸውን እንጂ... አንዳንድ ሰዎች ከነበሩበት ባህሪ ትንሽ ለወጥ ሲሉ ሁሌም መጥፎ ነገር ላይሆን ይችላል። ገለጥ ስናደርጋቸው ሌላ አዲስ.. የባሰውን ፍቅራቸውን ልናገኝ እንችላለን።
ተቀላቀሉን👉👉👉👉@natopia_17
💚💛❤️
🥰3
Signed ናትዮጵያ✍️
15 May 2026, 18:31 UTC105 views2 reactionsread 7 August 2026 Photo
ጥሩ ስፍራ ሄደህ ያገኘኸው ሰው ኹሉ "ጥሩ ሰው" አይደለም።
መጥፎ ስፍራ ተገኝተህ የተዋወቅኸው ሰው ሁሉ "መጥፎ ሰው" አይደለም።
©ሶፊ
ተቀላቀሉን👉👉👉@natopia_17
💚💛❤️
🥰2
Signed ናትዮጵያ✍️
14 May 2026, 18:57 UTC98 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
"አንተ ማነህ?" ስትባል ዝም!
"አንተ እንዲህ ነህ!" ሲሉህ ዝም!
"አንተ ለካ..." ዝም!
"አንተ ግን..." ዝም!
"አንተ..." ዝም! በቃ ዝም በል!
በየሄድክበት🗣️ እንዲህ ነኝ አትበል። ራስህን ለመግለጽ ቃል አትወራወር። እንዲያውቁህ በቃላት በኩል አትብራራ። በተግባር ተገለጥ። ይህንን የሰራው ሰው እሱ አይደል? ብለው ይግለፁህ። ዝም ብለህ ስራህን ቀጥቅጥ! ዝም ብለህ ህይወትን መርምር! ዝም ብለህ እወቅ! ዝም ብለህ ማዕበሉን ቀስቅስ!
ፅኑ ማንነትህ ተግባርህ ነው። አንተ ለሌሎች ሁለት አይነት ነህ። በአዕምሯቸው የተቀረፅከውና በዓይናቸው የምትታየው አንተነትህ መሀል ሰፊ ልዩነት ይኖራል። በዓይናቸው በኩል የተገለጥከው አንተ ትክክለኛው ማንነትህ ቢሆን…
🔥2❤1
Signed ናትዮጵያ✍️
13 May 2026, 18:46 UTC94 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
ከአጠገቧ እየተነሳ እንዲ አላት...
ዝምታ ያልቻለው ህመም
ትዝታ ያላቀፈው ናፍቆት የለም ምንም አለማለት እኮ ምንም ያለ መሆን ምክንያት አይደለም ምናልባት ከ ቃል ውርወራ አለመግባባት በዝምታ መተያየት ያከባብራል ብዬ ነው
ግና ያለፉትን የሳቅ እና የብዙ ፍቅር ጊዜ አስታውሶ ነበር ማለት ሲጨንቅ ሲከብድ ምናለ ወደ ቀድሞ ብንመለስ ማለት ሲደብር ደርሶ ተስፋ መቁረጥ አጠረኝ መሰለኝ ለነገሮች ሁሉ ማብራራትም ሆነ ማስረዳት ለ እንቆቅልሽ ሁሉ ፍቺ መስጠት አይኖርብኝም ብዬ አመንኩ ልክ ልሁን ወይም አጥፍቼ እንጃ ብቻ...
©️ፊላ
ተቀላቀሉን👉👉👉@natopia_17
💚💛❤️
❤1🔥1🥰1
Signed ናትዮጵያ✍️
10 May 2026, 17:44 UTC109 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
ያሻኝ ቦታ ሄጄ ያሻኝን ከመምረጥ
እኔን ሚያስደስተኝ
መንገድ ለመሻገር እናቴን መጨበጥ !
ልጅ እያለው ነፍስ በቅጡ ሳላውቅ እናቴ ነበረች ትምህርት ቤት ምታደርሰኝም ምትመልሰኝም ፣ ጠዋት ከቤት ስንወጣ ነፃነት እንዲሰማኝ ስለምትሻ የተወሰነ መንገድ አስባልቱ አቅራቢያ እስክንደርስ ትለቀኝና ዋና መንገዱን ልንደርስ አንድ ቅያስ ሲቀረን "ያዘኝ አለሜ" ብላ እጇን ወደኔ አቅጣጫ ሰዳ አጥብቃ ትይዘኝና ወደ ዜብራው አቅጣጫ ሄደን ሁለት ሶስት ግዜ ግራ ቀኝ ከቃኘች ብሃላ ይዛኝ ታልፋለች ። ነፍስ ካወኩ ብሃላ ሳሰላስለው እጅጉን ይገርመኛል እናቴ እንዳሻገረችኝ አስባልት መንገድ እጄኑ ይዛ ብዙ የህይወት ፈተናዎችን አልፋለች ፣ ማሻገር ማለት ማሳለፍ ብቻ አይደለም ማድረ…
🥰2❤1
Signed ናትዮጵያ✍️
9 May 2026, 19:30 UTC87 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
"አያስፈራም?" አለቺኝ በሚጣፍጥ የልጅ ለዛ ባለው ንግግሯ...
ምን እንዳስፈራት አልገባኝም ፊቴን በአሉታ ነቅንቄ ሐሳቧን እንድትቀጥል በጉጉት ተመለከትኳት።
ትኩር ብላ አይታኝ ንግግሯን ቀጠለች... " በቀን መሸነፉን ፤ በቀን መረታቱን ፤ መናቁን መገፋቱን ዋጥ አድርጎ ይዞ አብሮህ በቀልዶችህ የሚስቅ፣አብሮ እየበላ አብሮ እየጠጣ የእርሱን ቀን የሚጠብቅ ሰው እንዳለ ስታስብ አያስፈራም? አለች በጥያቄ እየተመለከተቺኝ።
አብረውኝ የሚስቁትን በእዝነ ልቦናዬ ማየት ዠመርኹ...
ተመልክታኝ ፈገግ አለችና..."ፈራህ እንዴ?" አለቺኝ። (መች እንዳስብ ፋታ ሰጠሺኝ 😁)
መልሴን ሳትጠብቅ
" አትፍራ !
በቀልን ሳይሆን ፈጣሪን ፈርተህ መልካም አድርግ። …
🔥3
Signed ናትዮጵያ✍️
8 May 2026, 17:44 UTC86 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
❤️🩹 አንዳንዶች 'ደህና ነኝ' የሚሉት ደህና ስለሆኑ ሳይሆን
ህመማቸውን የመደበቅ ጥበብ ስለተካኑበት ብቻ ነው።
ሰዎችን የምትይዙበትን መንገድ በጣም ጥንቃቄ አድርጉ! በሳቅ የታጀበ ወሬ ስለሚያወራላችሁ ብቻ "ሰላም ነው" ብላችሁ እንዳትደመድሙ። የምታወሩት ሰው ጥርሱ ቢስቅም ውስጡ ግን ላለመፈራረስ የመጨረሻውን ትግል እያደረገ ሊሆን ይችላል።
ደግነት ለእናንተ ቀላል ምርጫ ሊሆን ይችላል! ለሌላው ግን ለነገ የሚያደርሰው ብቸኛው ተስፋ ነው! ቃል አጥንት የለውም! ግን አጥንት የመስበርም ሆነ የቆሰለ ነፍስን የመጠገን ጉልበት አለው። ስታወሩ ስትጠነቀቁ ሰው 'ባትጠቅሙ' እንኳን አትጎዱም! 🤝
Be careful; you might be speaking to som…
❤1👍1🥰1
Signed ናትዮጵያ✍️
6 May 2026, 18:23 UTC89 views3 reactionsread 7 August 2026 Photo
ሐኑን ምን ማለት ነው?" አልኳት የተዋወቅን ሰሞን ...
"በሁለት ቋንቋ ሁለት ትርጉም ያለው ስም ነው ይላሉ" ብላ አብራራችልኝ። በሱማሌኛና በአረብኛ ... ደግሞ የሚገርመው የትርጉሙ መራራቅ። ሲላላ 'ሕመም'፣ ጠበቅ ተደርጎ ሲነበብ 'ጣፋጭ' ማለት ነው አሉ። እኔ ከራሴ ውጣ ውረድ ተነስቼ ሁለቱንም ትርጉም አቀላቀልኩት 'ጣፋጭ ሕመም!!' ሐኑን ጣፋጭ ሕመሜ ነበረች። ... የበደልኳት'ም እሷን ነው፣ እሷን ብቻ። አንድም ቀን በደሌን አንስታ ወቅሳኝ የማታውቀውም እሷ ብቻ ናት። እንደው በሰራሁት ሥራ ልክ "ይወገርም ይሰቀልም" ተብሎ ቢፈረድብኝ፣ አንደኛ መውገሪያ ድንጋይ አንስታ ከወጋሪው ሰልፍ ፊት መገኘት የነበረባት፣ እሷ አልነበረችም እንዴ? የመሰቀያ ገመዴን ሸ…
🥰3
Signed ናትዮጵያ✍️
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @natopia_17. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.