9 Jul 2026, 05:59 UTC516 views7 reactionsread 8 August 2026 🧑🤝🧑 ጓደኝነት 👭
✅ አንዱ ለጓደኛው ስልክ ይደውልና እባክህ እናቴ በጣም ታማ ሆስፒታል ገብታለች እናም 3000 ሺ ብር ስለተባልኩኝ አሁኑኑ በፍጥነት እዚህ ሆስፒታል ድረስ ይዘህልኝ ና ይለዋል።
ጓደኛውም እሺ ግን 30 ደቂቃ ያህል ታገሰኝ አለው። እሺ ብሎ ሲጠብቅ 30 ደቂቃ ብሎም አንድ ሰአት አለፈው። ከዚያም ምነው ቆየ ብሎ ስልክ ሲደውልለት ስልኩ ጥሪ አይቀበልም ይላል። ደጋግሞ ቢሞክርም ስልኩ ዝግ ነው። በዚህም በጣም ይናደድና እንደውም በቃ ተወው ያንተን ገንዘብ አልፈልግም፣ ድሮም እኔ ጓደኛ አይወጣልኝም ብሎ ሚሴጅ ላከለት።
✅ ከጥቂት ደቂቃ በኃላ ጓደኛው ሆስፒታል መጣ፣ ገና እንዳየውም ስማ ባይኖርህ እንኳን በቃ የለኝም ወይ ደግሞ አላገኘሁም አ…
❤6🔥1
20 Jun 2025, 19:17 UTC≈1,550 views19 reactionsread 8 August 2026 Photo
😁አወዛጋቢው ሙጋቤ ስለትዳር ያስቃል😂
ሮበርት ሙጋቤ እና ሚስቱ ስድስት ልጆችን ከወለዱ በሗላ ከእለታት አንድ ቀን ይጣላሉ።
ከዛም ሚስቱ በጣም ተናዳ ልብሷን በሻንጣ መሰብሰብ ጀመረች። ሙጋቤ በድርጊቷ ተገርሞ ለምንድን ነው ልብስሽን እምትሰበስቢው ብሎ ይጠይቃታል። እሷም ከንግዲህ ከአንተ ጋር ኑሮ በቅቶኛል ወደ እናቴ እሄዳለሁ አለቺው። እሱም መኝታ ክፍል ገባና ልብሶቹን ሰበሰበ።
አየቺው አንተ ደሞ ወዴት ልትሄድ ነው ልብስህን እምትይዘው አለቺው። እኔም ወደ እናቴ እሄዳለሁ አላት። እሷም ልጆችን ለማን ጥለህ ነው እምትሄደው ስትለው? ሙጋቤ ቀበል አድርጎ እነሱም ወደ እናታቸው መሄድ ይችላሉ አላት፡፡
#ምርጥ_መጣጥፎች
https://t.me/mirt_metatf…
❤13👍6
1 Jun 2025, 12:54 UTC≈1,490 views22 reactionsread 8 August 2026 Photo
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። አንዱ አጠገቡ ላለው ጓደኛው እንዲህ አለው። "ቄሱ ቆንጆ ሚስት አለቻቸው። እንዋደዳለን። አሁን እሷ ጋ ልሄድ ነው። አንተ ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን በወሬ ያዝልኝ። ከመምጣትህ በፊት አስቀድመህ ደውልልኝ አደራ" አለው።
ጓደኛው ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን አስቁሞ የባጥ የቆጡን ያወራላቸው ጀመር። ቄሱም በሰውዬው የተዘበራረቀ ንግግር ግራ ገባቸውና ምን እንደፈለገ በቁጣ ጠየቁት።
ሰውዬም የሃጢአተኝነት ስሜት ተሰማውና ዕውነቱን ነገራቸው "ይቅር ይበሉኝ አባቴ! ጓደኛዬ ከእርስዎ ሚስት ጋር ሊተኛ ሄዶ እኔ እርስዎን በወሬ እንድይዝሎት ነግሮኝ ነው" ብሎ እግራቸው ላይ ወደቀ።
ቄሱም ፈጥነው አነሱትና እንዲህ አሉት "አንተ ሞኝ! አሁኑኑ ወደ ሚስትህ …
❤10😁5👍4🔥3
23 May 2025, 17:27 UTC≈1,390 views11 reactionsread 8 August 2026 ... የቀጠለ
ሁሉም ሰው ሽንፈት እና ተግዳሮቶች ያጋጥመዋል። ይሁን እንጂ በአሸናፊዎች እና ተሸናፊዎች ያለው ልዩነት አሸናፊዎች ዓለማቸውን ሳያሳኩ አያቆሙም።
4. በራስ መተማመን የመፍትሔ አንድ አካል ነው
Micheal አንድም ቀን በእቅዶቹ ጥርጣሬ አሳይቶ አያውቅም። እቅዱ ባይሳካ እንኳን ሌላ እቅድ በማውጣት ወደፊት ብቻ ነበር የሚያስበው ሁሌ እንደሚሳካ እምነት ነበረው።
በራስህ እምነት ይኑርህ ብዙዎች ከእቅድህ እና አላማህ አይቻልም እያሉ ሊያስቀሩህ ይሞክራሉ ነገር ግን አንተ በራስህ እምነት ይኑርህ።
አበቃሁ ከፊልሙ የሆነ ነገር እንደተማራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ከዚህ ጋር ምን ያገናኘዋል የሚል ካለ ስቃችሁ እለፉት ገና ህይወት አልገባውም እና ..
መ…
👍4🔥4❤3
23 May 2025, 17:25 UTC≈1,050 views6 reactionsread 8 August 2026 Photo
እስኪ ዛሬ ስለ #prison_break ፊልም የሆነ ነገር ልበላችሁ
መጀመሪያ ላይ ፕሪዘን ብሬክ ማየት ስትጀምሩ ከእስርቤት የማምለጥ ብቻ ታሪክ ያለው ፊልም ይመስላል። ነገር ግን ፊልሙን በጥልቀት እያያችሁ ስትመጡ ይህ ፊልም የህይወት ትምህርት መሆኑን እየተገነዘባችሁ ትመጣላችሁ። ስለ ስትራቴጂ ፣ ብቃት ፣ ፅናት ፣ አልሸነፍ ባይነት ፣ ራስ መተማመን እና መስዋዕትነት ምን እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያስተምር ተከታታይ ፊልም ነው። እስኪ ለዛሬ ከዚህ ቻናላችን የሚሄድ ከፊልሙ የተማርኩት ልንገራችሁ።
1. አእምሮ ከምንም ነገር በላይ ሀያል መሆኑ
Micheal Scofield በጉልበቱ ሀያል ሰው አልነበረም። ነገር ግን ለሁሉም ነገር አስቀድሞ በአእምሮው እቅድን ያወ…
👍2🥰2❤1🔥1
20 May 2025, 08:18 UTC≈1,110 views13 reactionsread 8 August 2026 [ ጥጋቧ አፍንጫዋ ጋር ከደረሰብህ ]
የወደድካት ሴት እየኮራችብህ ተቸግረሀል? ጥጋብ ደረቷን አሳብጦ አላስቀምጥ ብሎሀል? ቆንጆ ከእኔ ወዲያ ላሳር ብላ አብጣለች?
ና እናስተንፍሳት....
⭐️ ስለ ጓደኞቿ እየደጋገምክ ጠይቃት... ግን ሆን ብለህ እንደሆነ እንዳታስነቃ። የሆነ ጉጉት ወይም ፍላጎት ያለህ ብቻ እንዲመስላት። አንዷን ጓደኛዋን ይዘህም ሙጭጭ አትበል... ጠላቷ ነው የምታረጋት። ቁጥራቸውንም አታብዛው... እንደ ሴት አውል ቆጥራህ እንዳትርቅህ።
አላማችን እሷን ማብረድ ነው... በከተማው ያለችው ሴት እሷ ብቻ አለመሆኗን እንድትገነዘብ ነው።
ለምሳሌ እንዲህ ብለህ ጠይቃት
"ጓደኛሽ ሀና ደስ ትለኛለች.... ኢንስታግራም ወይም ቴሌግራም ትጠቀማለች…
😁5❤3🔥3👍2
2 May 2025, 20:19 UTC≈1,700 views20 reactionsread 8 August 2026 Photo
😁ፈገግ ለማለት😁
ወንዶች ለምን ከቤታቸው ውጭ ሄደው DSTV ቤት ወይም በካፌዎች ውስጥ እግር ኳስ ማየትን ይመርጣሉ?
ሚስት፡ ወዴት እየሄድክ ነው?
ባል፡ ወዴ DSTV ቤት ኳስ ለማየት እየሄድኩ ነው
ሚስት፡ DSTV እዚህ አለ አይደል እንዴ? ለምን ከእኔ ጋር አብረን አናይም?
ባል፡ እሱማ ልክነሽ አለ ግን ከጓደኞቼ ጋር ማየት እፈልጋለሁ
ሚስት፡ አሃሃ ስለዚህ እኔ ለአንተ ምንም ማለት አይደለሁም ማለት ነው? ከእኔ ጓደኞችህን ታስበልጣለህ ማለት ነው?
ባል፡ እሺ እሺ ውዴ በቃ ይቅርታ !! ነይ አብረን እናያለን
ሚስት፡ እኔምልህ ውዴ ግብ ጠባቂው ለምን ጥቁር መለያ ለበሰ
ባል፡ አንድ የቅርብ ዘመዱ ሞታ ኃዘን ላይ ስለሆነ ነው
ሚስት፡ ስማኝማ ተንታኙ የሁሉንም ተጫ…
👍12😁5❤1🤔1🥰1
28 Apr 2025, 17:27 UTC≈1,200 views10 reactionsread 8 August 2026 Photo
"አርቲስት ሳያት ደምሴ"
ስኬት ማለት፦
"ለአንዳንድ ሰው ስኬት አግብቶ ልጅ መውለድ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንድ ሰው ደግሞ ተምሮ ዲግሪውን መያዝ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንዱ ደግሞ ደግሞ ሚሊዮን ብር ባንክ ማስቀመጥ ሊሆን ይችላል፣ ለእኔ ስኬቴ በየቀኑ ራሴን ማሸነፌ ነው፣ ወደ አልጋዬ ስሄድ ህሊናዬ ዛሬ ምን ሰርተሻል ብሎ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ መስጠት ነው። በዛ ረገድ ደስተኛ ነሽ ወይ ከተባልኩ አዎ ስኬት ግን መንገድ ነው ብትሄጂበት ጥግ የለውም፣ ደግሞ ደስ የሚለው መንገዱ ነው።"
#ምርጥ_መጣጥፎች
መልካም ምሽት 👍
https://t.me/mirt_metatfoch
https://t.me/mirt_metatfoch
❤5👍5
27 Apr 2025, 15:26 UTC≈1,130 views15 reactionsread 8 August 2026 Photo
👉አስተማሪ ታሪክ
አንድ ምሽት ላይ ልክ ባለሱቁ ሱቁን ከመዝጋቱ በፊት አንድ ውሻ ወደ ሱቁ ይገባል። ውሻው በአፉ ዘምቢል ይዟል። ዘምቢሉ ውስጥ የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር እና ገንዘብ ተቀምጧል። ባለሱቁ ገንዘቡን ወስዶ እቃዎቹን በዘምቢሉ ውስጥ ያኖረዋል። ወዲያውኑ ውሻው ዘምቢሉን ይዞ ይሄዳል። ባለሱቁ ስለገረመው የውሻው ባለቤት ማን እንደሆነ ለማወቅ ውሻውን ይከተለዋል።ውሻው ከአውቶብስ ፌርሜታ ቆሞ ይጠብቃል። ከትንሽ ጊዜ በኋላ አንድ አውቶብስ ሲመጣ ውሻው አውቶብሱ ውስጥ ይገባል። ትኬት ቆራጩ እነደመጣ ወደፊት ጠጋ አለ የአንገት ቀበቶው ላይ ያለውን ገንዘብና አድራሻ ለማሳየት። ትኬት ቆራጩም ገንዘቡን ወስዶ ትኬቱን በአንገት ቀበቶው ውስጥ ያኖርለታል። የሚወርድበት…
👍9❤4🔥2
24 Apr 2025, 13:05 UTC≈2,180 views14 reactionsread 8 August 2026 "እንጋባ" ሲል ጠየቃት፣
አሳምነዉ።
አልተቀበለችውም አስማሩ። "ወንድም እና እህትነቱ ይበልጣል" አለችው። ተስማሙ።
ቤቷ እየመጣ ይጠይቃታል።
ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፣ ካላት ታቀርባለች ይበላሉ።
አውግተው ይለያያሉ።
የትዳር ነገር ዳግም አልተነሳም።
አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ፀሐይ መጣ።
እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ ስለሙቀቱ ብዙ አውርተዉ ተለያዩ።
አስማሩ አሳምነው እረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት።
ዳግም ሲመጣ ደርቦ ደራርቦ ነበርና የምያወልቀው እንጂ የምደርበዉ ልብስ አላስፈለገውም።
ጃኬቱን አውልቆ ሄደ።
አስማሩ እሱንም አጥባ አኖረችው።
ሱሪውን ደርቦ መጣ "ወበቀኝ" አወለቀው።
አስማሩ አጥባ አኖረችው።
ካፖርቱን ጥሎ ሄደ ፣…
😁5👍3🤡3🙈3
21 Apr 2025, 07:19 UTC975 views16 reactionsread 8 August 2026 ቀጭኔ ልጇን ቆማ ስለምትወልደው ገና ከማህፀኗ አንደወጣ ቀጥታ መሬት ላይ ይፈጠፈጣል፤ ከወለደችውም በኋላ ከመንከባከብ ይልቅ ብዙ ጊዜ እንደ ኳስ እየጠለዘች ታፈርጠዋለች፤ እጣ ፈንታው ስለሆነ እየወደቀ ይነሳል።
ይሄን ድብደባ ለብዙ ጊዜ ታደርግና የሚደርስበትን ጫና ተቋቁሞ ቀጥ ብሎ መቆም ሲጀምር ልጇን መምታት ታቆማለች።
ይሄን እውነታ ዛሬ ገና የሚሰማ ሰው "ምን አይነት ጭካኔ ነው ግን?" ሊል ይችላል፤ ግን ህፃኑ ቀጭኔ እንደዚህ ሆኖ ካልጠነከረ ነገ ተልፈስፍሶ ከጠላት ማምለጥ አቅቶት በአውሬዎች ሊበላ እንደሚችል እናት ጠንቅቃ ታውቃለች፤ ስለዚህ በወለደ አንጀቷ ታንገላታዋለች።
ፈጣሪም ዛሬ የሚፈትነን ነገ ለሚመጣ ከባድ ችግር ራሳችንን እንድናዘጋጅ ነው። አ…
👍12🔥4
20 Apr 2025, 17:57 UTC980 views16 reactionsread 8 August 2026 ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ቀበሮ፣ በአንድ ገበሬ ግቢ እየመጣችና የሚያረባቸውን ዶሮዎች እየሰረቀች በጣም ታስቸግራለች፡፡
ገበሬው ለፍቶ ለፍቶ ለቀበሮ መቀለብ ሲሆንበት፣ ከሚስቱ ጋር ለመማከር ይወስንና፤
‹‹ሰማሽ ወይ ውዴ?››
‹‹አቤት ጌታዬ››
‹‹የዚችን የቀበሮ ነገር ምን ብናደርግ ይሻላል?››
‹እኔም ግራ- እየገባኝ ምን እናድርግ ልልህ ነበርኮ››
‹‹አንቺ ምን አሳብ አለሽ?››
‹‹እኔማ ሠፈሩን እንረብሻለን ብዬ ፈርቼ ነው እንጂ፤ መሳሪያ እያለህ አንድ ቀበሮ መግደል ምን ችግር ነበረው?››
‹‹አይ ያሉትን ይበሉ እንጂ ዕውነትም ጠመንጃዬን ወልውዬ አድፍጩ ብጠብቃት አታመልጠኝም›› አለ ፍርጥም ብሎ፡፡
‹‹ግን እንዲህ ብናረግስ?››
‹‹ምን?››
‹‹ለሰፈሩ …
👍6🥰6❤3😁1
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @mirt_metatfoch. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.