11 Sept 2025, 06:18 UTC59 viewsread 10 August 2026 Photo
#መስከረም_1_ቀን 🌼
ርዕሰ አውደ ዓመት(ዕንቁጣጣሽ)
እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
ይህች ዕለት እጅግ ክብርትና ልዕልት ናት። አዲስ ዓመት፣ አዲስ ሕይወት፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ በረከት እናገኝ ዘንድ እርሱ በቸርነቱ ይህችን ዕለት በሰላም አድርሶናልና፤ ለእርሱ ምን ይከፈለዋል? "ተመስገን" ከማለት በቀር።
ይህች ዕለት ብዙ ስያሜዎች ቢኖሯትም፣ እነዚህን እንጠቅሳለን፡-
1. ቅዱስ ዮሐንስ [መጥምቁ ዮሐንስ ርእሰ ቅዱሳን ስለሆነ በእርሱ ተሰይማለች]
2. ቅዱስ ራጉኤል [የተሾመበት ዕለት]
3. ርእሰ ዓውደ ዓመት [የዓውደ ዓመቶች ራስ]
4. እንቁጣጣሽ [ንግሥተ ሳባንና ንጉሥ ሰሎሞንን አንድ ያደ…
Signed Kalab
17 Aug 2025, 11:38 UTC58 viewsread 10 August 2026 ✨✨✨🍂🌿✨🍂🌿
ይህ ቃል ያስደነግጠኛል ምን ያስደነግጣችኋል? ሞት ነውን? ይሄማ ከሞት በኋላ ሕይወት መኖሩን ለማያምኑት አይደለምን? ረሀብ ነውን? ይህስ ቢሆን “ስለ ጽድቅ የሚራቡ ብጹዓን ናቸው ይጠግባሉና” ማቴ. 5፥6 የሚለውን ቃል ኪዳን ለማያምኑት አይደለምን?
ስደት ያስፈራል እንዳትሉኝ ክርስቶስ እንደተሰደደ ለማያምኑት ነው።
እኔ ግን ሳስበውም ሆነ ሳነበው የሚያስደነግጠኝ
“የማይጠቅም ይህንን ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል” ማቴ. 25፥30 የሚለው ነው።
ከቀናት መካከል ይህ የፍርድ ቀን ያስፈራኛል፤ ከቃላት መካከልም ይህ ያስደነግጠኛል። የጌታ ቃል ነው ከማን ዘንድ ሂደው ይህንን ፍርድ ያስሽሩታል? ባሮቹን ሊቆጣ…
Signed Kalab
28 Aug 2021, 09:39 UTC601 viewsread 10 August 2026 +++ የነሐሴ 24 አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማኅሌት +++
መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ
ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤
ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤
ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤
ወተክለ ሃይማት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ፡፡
ዚቅ
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤
ዘኢይነውም ትጉህ በውስተ ቅዱሳን ስቡሕ፤
ከመ ቀስተ ደመና የዓውዶ ሱራሄ ሎቱ ለባሕቲቱ ይደሉ ስባሔ፡፡
መልክአ ሚካኤል
1
ሰላም ለሕጽንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤
ጸሎተ ቅዱሳን ዉኩፍ፤
ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤
ለረዲኦትየ ከመ ዘይሰርር ዖፍ፤
እንዘ ትሰርር ነዓ በከልኤ አክናፍ፡፡
ዚቅ
ርድአኒ ወአድኅነኒ፤ ወሥመር ብየ፤
በከመ ሠ…
Signed ኪዳንኪ ኮነ
11 Aug 2021, 04:41 UTC458 viewsread 10 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Andinet
9 Aug 2021, 13:38 UTC440 viewsread 10 August 2026 እንዲህ ካለ ልጅሽ... ቅድስት ሆይ ለምኝልን!
- 5500 ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነጻ ካደረገ ልጅሽ፥
- ይቅር ይለን ዘንድ ከወደደ ልጅሽ፥
- ሔዋንን ነጻ ካወጣ ልጅሽ፥
- ወልድ ዘበላዕሉ ሕጻን ዘበታሕቱ ከሚባል ልጅሽ፥
- እዱ መዝራእቱ ለአብ ከሚባል ልጅሽ፥
- ሰውም ቢሆን ከአብ ከባሕርይ አባቱ ከመንፈስ ቅዱስ ከባሕርይ ሕይወቱ ካልተለየ ልጅሽ፥
+ ዳግማይ አዳም ከሚባል ልጅሽ፥
+ እውነተኛ ብርሃን ከሚባል ልጅሽ፥
+ በማይመረመር ግብር ከወለድሺው ልጅሽ፥
+ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በአምሳለ ንጉሥ ካየው ልጅሽ፥
+ ሙሴ በአምሳለ ሐመልማል ወነበልባል ካየው ልጅሽ፥
+ ሃያውን ዓለም ከፈጠረ ልጅሽ፥
+ በቸርነቱና በይቅርታው ብዛት አዳምን ወደ …
Signed ምርሐኒ እግዚኦ ፍኖተከ
25 Jul 2021, 23:35 UTC369 viewsread 10 August 2026 'ጥቡዕ ልቡ ለሕጻን' (ቅዱስ ያሬድ)
የሕጻኑ ልብ ቆራጥ ነበር። አዎ የሦስት ዓመቱ ሕጻን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመመስከር ልቡ ቆራጥ ነበር። በጣኦት አምላኪው ንጉሥ ፊት 'እኔ የክርስቶስ ነኝ' ሲል ቅዱስ ቂርቆስ አላፈረምና። እናቱን 'ሁለተኛ ሞት አያገኘንምና እናቴ ሆይ ጨክኚ' ብሎ ለሰማዕትነት ያበረታታ ይህ ሕጻን ልቡ ቆራጥ ነበር! ሕጻኑ ቂርቆስ በአደባባይ ስለመሠከረለት ክርስቶስ እንመሰክር ዘንድ ልባችንን ቆራጥ ያድርግልን።
የቅዱስ ቂርቆስንና የቅድስት ኢየሉጣን በረከት ያሳድርብን።
@merafekidusan
@merafekidusan
@merafekidusan
Signed ምርሐኒ እግዚኦ ፍኖተከ
8 Jul 2021, 05:14 UTC479 viewsread 10 August 2026 የእግዚአብሔር እናት - Theotoks(Mother of God)
✔ በቅድስት ቤተክርስቲያን የነገረ ማርያም(Mariology) ትምህርት ትልቁ ነጥብ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት መሆኗ ነው። ድንግል ማርያም የ'አምላክ(የእግዚአብሔር) እናት' ናት ስንል አንዳንዶች እንደሚመስላቸው 'መለኮትን ወለደችው፥ አምላክ ከእርሷ ባሕርይ ተገኘ' ማለታችን አይደለም፥ ይልቅ ሁለት ነገረ ክርስቶሳዊ(Christological) ነጥቦችን በአጽንኦት ለመግለጥ ነው እንጂ። እነዚህም፦
👉 (1)- እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በምትሐት ሳይሆን በእውነት ሥጋንና ነፍስን ነስቶ ተወልዷል።
👉 (2)- ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው ኢየሱስ ክርስቶስ መጀ…
Signed ምርሐኒ እግዚኦ ፍኖተከ
18 Jun 2021, 13:42 UTC406 viewsread 10 August 2026 የሰኔ ሚካኤል ወረቦች - ከአማርኛ ትርጉማቸው ጋር
✔ በተወዳጁ መልአክ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በዓል ሌሊት በማኅሌት አገልግሎት የሚዘመሩ ወረቦችን ከአማርኛ ትርጉማቸው ጋር ይህን ይመስላሉ፦
(1)- ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ[፪]፥
ዘኢትነውም ትጉሕ 'ኖላዊነ ኄር'(፪)[፪]።
ትርጉም፦ ስምህን ስንጠራ ሰላምህን ስጠን
የማታንቀላፋ ትጉህ እረኛችን።
(2)- ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ[፪]፥
በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ[፪]።
ትርጉም፦ በስዕልህ ፊት ቆሜ ዘወትር ሳቀርብ ልመናን፥
እሺ በማለት ፈጥነህ አሰማኝ ቃልህን።
(3)- ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ፥
ርኢ…
Signed ምርሐኒ እግዚኦ ፍኖተከ
8 Jun 2021, 18:21 UTC335 viewsread 10 August 2026 'በሰማይ ያሉ መላእክትና ቅዱሳን ሰዎች በምድር የሚደረጉ ነገሮችን ያውቃሉን?'... ለሚለው ጥያቄ የአቡነ ሺኖዳ ምላሽ፦
✔ በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ መንበር 117ኛ ፓትሪያርክ የነበሩት ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ 'Comparative Theology' በሚለው መጽሐፋቸው 'Do angels and saints know our condition on earth?' የሚል ጥያቄ አንስተው መልስ ሰጥተዋል። ዋና ዋና ነጥቦቹን ለማስታወስ ያህል፦
(1)- ሰማያዊ ዕውቀት በምድር ካለው ዕውቀት እጅግ እንደሚበልጥ ጥርጥር የለውምና 'በሰማይ ያሉ ቅዱሳን በምድር የሚደረገውን የእኛን ጸሎት ጨምሮ ያውቃሉን?' የሚለው ጥያቄ አስገራሚ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ 'ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ …
Signed ምርሐኒ እግዚኦ ፍኖተከ
4 Jun 2021, 12:36 UTC341 viewsread 10 August 2026 ሮሜ 8:34 - በኦርቶዶክሳዊያን አበው ትርጓሜ
[በኢትዮጵያዊያን ሊቃውንትና በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ]
✔ 'የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።' (ሮሜ 8:34)
ምን ማለት ነው? በጥንቷ ቤተክርስቲያንስ እንዴት ይተረጎማል?
(1)- የኢትዮጵያ ሊቃውንት ትርጓሜ፦
✔ 'ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ፥ ወተንሥአ እሙታን፥ ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር፥ ወይትዋቀሥ በእንቲአነ።' የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ትርጓሜያችን 'ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ፥ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ፥ በእግዚአብሔር ዕሪና ይኖራል፥ ስለ እኛም ይከራከራል።' ብሎ ወደ አማረኛ ከመለሰው በኋላ 'መከራከርስ የለበትም፥ በዕለተ …
Signed ምርሐኒ እግዚኦ ፍኖተከ
31 May 2021, 06:28 UTC292 viewsread 10 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed ምርሐኒ እግዚኦ ፍኖተከ
31 May 2021, 06:28 UTC275 viewsread 10 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed ምርሐኒ እግዚኦ ፍኖተከ
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @merafekidusan. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.