11 Apr 2026, 05:37 UTC224 views7 reactionsread 6 August 2026 Photo
ከመጀመሪያው ሟች ከአቤል ጀምሮ የሰው ልጅ አስጨናቂ ወደ ነበረች ወደ መቃብር ሲጋዝ ኖሯል። ዛሬ ግን ሞትን በሞቱ የገደለ ክርስቶስ ወደ መቃብር በመውረዱ 'መቃብር' ታሪኳ ተቀየረ። በዚያ 'ፈርሶ በስብሶ' መቅረትን አስወግዷልና አስፈሪ የነበረችው መቃብር ወደ ክርስቶስ የምታሻግረን ተናፋቂ ድልድይ ሆነች። በመቃብር አድሮ የመቃብርን ታሪክ የቀየረ እርሱ አዳኛችን ክርስቶስ የተመሰገነ ነው።
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
❤7
Signed Amde Meskel
9 Apr 2026, 08:06 UTC195 views7 reactionsread 6 August 2026 Photo
ጌታዬ ሆይ! ልዑል አምላክ ስትሆን ዝቅ ብለህ የእኔን የባርያህን እግር ልታጥብ ፈቀድክን? እንግዲያውስ እጄንና ራሴን ጭምር እንጂ እግሬን ብቻ አትጠብ። አባቴ ሆይ የቆሸሸው ልቤን፥ ያደፈችው ነፍሴን መላ አካላቴን እጠበኝ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም።
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
❤7
Signed Amde Meskel
29 Mar 2026, 05:54 UTC231 views5 reactionsread 6 August 2026 Photo
ኒቆዲሞስ በትምህርት፥ በሹመትና በባለጸግነት የአይሁድ አለቃቸው የነበረ ሰው ነው። ከፈሪሳዊያን ወገን የእስራኤል መምህር የነበረው ይህ ሰው በሌሊት ለሰው ልጆች ሁሉ ወደሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መጣ። አይሁድን ፈርቶ በጨለማ የመጣው ይህ ሰው 'ጨለማ የማያሸንፈውን እውነተኛ ፀሓይ' ኢየሱስ ክርስቶስን ባገኘ ጊዜ ሕይወቱ ብርሃን ሆኖለት ተመለሰ።
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
❤5
Signed Amde Meskel
22 Mar 2026, 09:41 UTC252 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
የዐቢይ ጾም ስድስተኛው ሳምንት 'ገብርሔር' ይባላል። በአገልግሎት ስለመታመን፥ መክሊትንም ስለማትረፍ ይነገርበታል። የዕለቱ ወንጌል (ማቴ 25: 14 - 30) ሲሆን ስለ መታመንና መክሊትን አትርፎ በብዙ ስለመባረክ ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ እንዲህ ብለዋል፦
✢ 'እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንክ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል። በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልክ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል። ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል(ኤር. 12፥5)፥ የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነ…
❤4
Signed Amde Meskel
15 Feb 2026, 20:04 UTC257 views7 reactionsread 6 August 2026 Photo
የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ "የዓብይ ጾም" ጸሎት (The Lenten Prayer of St Ephraim the Syrian) ፦
"ጌታዬና እና የሕይወቴ አለቃ ሆይ! የስንፍናን፣ የተስፋ መቁረጥን፣ የሥልጣን ጥማትንና የከንቱ ንግግርን መንፈስ ከእኔ ውሰድ።
ነገር ግን ለባሪያህ የንጽህናን፣ የትህትናን፣ የትዕግስትንና የፍቅርን መንፈስ ስጥ።
አዎን ጌታዬ እና ንጉሤ ሆይ! የራሴን ኃጢያት እንዳይ እና በወንድሜ ላይ እንዳልፈርድ እርዳኝ። አንተ ለዘመናት የተባረክ ነህና። አሜን።
አቤቱ ኃጢአተኛውን አንጻኝ! አሜን።"
❤6🥰1
Signed Amde Meskel
18 Jan 2026, 05:43 UTC304 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
የእግዚአብሔር ልጅ በእውነት ተገለጠ!
"ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ በሰላም አስተርአየ ወልደ አምላክ ፍጹም፥ ወተወልደ በሀገረ ዳዊት፥ በዮርዳኖስ ተጠምቀ ከመ ይቤዝወነ፥ ወልደ አምላክ ፍጹም አስተርአየ።"
(ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፍጹም የአምላክ ልጅ በሰላም ተገለጠ፥ በዳዊት ሀገር ተወለደ፥ ይቤዠን ዘንድ በዮርዳኖስ ተጠመቀ፥ ፍጹም የአምላክ ልጅ ተገለጠ።)
ዋዜማ ዘጥምቀት!
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
❤4
Signed Amde Meskel
15 Jan 2026, 13:39 UTC264 views4 reactionsread 6 August 2026 Photo
Holy Trinity In our Liturgical Worship.
ቡሩክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኩሉ ዓለም አምላክነ - Blessed be the Lord, Almighty Father, our God. - ዓለምን የያዘ እግዚአብሔር አብ ቡሩክ ነው።
ወቡሩክ ወልድ ዋሕድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒነ - And blessed be the only Son, our Lord and Our savior Jesus Christ. - ጌታችንና መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ ዋሕድም ቡሩክ ነው።
ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ወመንጽሔ ኩልነ - And blessed be the Holy Spirit, the Paraclete, the comforter and cleanser of u…
❤4
Signed Amde Meskel
8 Jan 2026, 17:40 UTC258 views5 reactionsread 6 August 2026 Photo
"በሥጋ የተወለድክ ክርስቶስ አምላካችን ሆይ፥ በልባችንም ተወለድ። በጨለማ ውስጥ ብርሃን፥ በጉዟችን ውስጥ ሰላም፥ በድካም ውስጥ ተስፋ ሁንልን። ለአንተ ክብር ይሁን። አሁንም ለዘላለም። አሜን።"
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
❤5
Signed Amde Meskel
5 Jan 2026, 19:08 UTC266 viewsread 6 August 2026 Photo
ለእኛ ብሎ የተወለደው አዳኛችን!
"የእግዚአብሔር ቃል ወደዚህ ዓለም ይመጣ ዘንድ ከንጽሕት ድንግል ሥጋዋን ይዋሐድ ዘንድ ምን አተጋው? በጨርቅ ይጠቀለል ዘንድ በበረት ይጣል ዘንድ፥ ከድንግል ጡት ወተትን ይጠባ ዘንድ በዮርዳኖስም ይጠመቅ ዘንድ ምን አተጋው? ሕግ አፍራሽ ጲላጦስ ይዘብትበት ዘንድ፥ በመስቀል ይሰቀል ዘንድ በመቃብርም ይቀበር ዘንድ ምን አተጋው? በፍዳ ተይዘን የነበርን እኛን ያድነን ዘንድ ለእኛ ብሎ አይደለምን?''
(ሃይ. አበው ዘእለእስክንድሮስ ምዕ 16 ክፍል 1:1-3)።
እኛን ያድነን ዘንድ፥ ለእኛ ብሎ ሰው የሆነልን እርሱ የተመሰገነ ነው።
@OrthodoxConcepts
Signed Amde Meskel
4 Jan 2026, 04:22 UTC221 views5 reactionsread 6 August 2026 Photo
ቤተክርስቲያን ከልደት በፊት ያለውን የዛሬውን ሰንበት "ኖላዊ - እረኛ" ብላ ትጠራዋለች። በነቢያት የተሰበከ፥ በቤቴልሔም የተወለደ ክርስቶስ እውነተኛ እረኛ መሆኑ በስፋት የሚነገርበት ነው። ሐዋርያው "እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።" እንዳለን(1ጴጥ 2:25)። ከመቅበዝበዝ ወደ ዕረፍት የመለሰን እረኛችን እርሱ የተመሰገነ ነው።
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
@OrthodoxConcepts
❤5
Signed Amde Meskel
30 Dec 2025, 08:26 UTC236 views2 reactionsread 6 August 2026 ዓይናችን ነሽ ማርያም!
ነገሩ የከበረ የመንፈስ ቅዱስ በገና(Harp of Holy Sprit) ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ 'Hymn on the Church' በተባለ ውብ ኦርቶዶክሳዊ ድርሰቱ እመቤታችንን 'ብርሂት ዓይን' ይላታል። ሊቁ 'The world you see, has two eyes fixed in it; Eve was its left eye, blind. While the right eye, bright is Mary' በማለት የመጀመሪያዋ እናታችን ሔዋንን በግራ ዓይን፥ ዳግሚት ሔዋን እመቤታችንን ደግሞ በቀኝ ዓይን አንጻር ያስተምራል።
በእውነቱ ሔዋን 'ማየት ያልቻለች የግራ ዓይን' ናት፥ ለምን ቢሉ? በእርሷ ምክኒያት ልጆቿና የልጅ ልጆቿ ሁሉ በጨለማ ውስጥ ኖረዋልና፥ በጨለማ…
🙏2
Signed Amde Meskel
27 Dec 2025, 18:08 UTC202 views2 reactionsread 6 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤2
Signed Amde Meskel
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @OrthodoxConcepts. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.