15 Sept 2026, 03:32 UTC184 views2 reactionsread 16 September 2026 ማክሰኞ 05/01/19
የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 61)
ስለ ምን ተጠራጠርህ
ማቴ14፡28-36
በማዕበል እየተናወጡ እጅግ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለነበሩ ደቀ መዛሙርት ጌታ ኢየሱስ በባህር ላይ እየተራመደ ከለሊቱ በአራተኛው ክፍል በመምጣት የሚያበረታቸውን ቃል ተናገረ “አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አለ፡፡ ይህንን የተናገረው ባዩት ጊዜ መንፈስ/ምትሐት ያዩ ስለመሰላቸውና እጅግ ታውከው ስለ ነበር ነው፡፡ ይህ ቃል የባህሩን ማዕበል ሳይሆን የተናወጠውን ልባቸውን ነው በሰላም የሞላው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ለገጠመን ችግር መፍትሄ ከመስጠቱ በፊት አስቀድሞ መፍትሄ የሚሰጠው ለውስጥ ሰውነታችን ነው፡፡ የትኛውንም ችግር ለማሸነፍ ቀዳሚው ነገር ልባችን መረ…
🔥2
Signed Mentesnot Kebede
14 Sept 2026, 03:54 UTC100 viewsread 16 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed Mentesnot Kebede
11 Sept 2026, 04:52 UTC459 views7 reactionsread 16 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤5👏2
Signed Mentesnot Kebede
10 Sept 2026, 04:37 UTC194 views3 reactionsread 16 September 2026 ኸሙሽ 0፶/13/18
የማቴዎስ ወንጌል መልዕት (ክፍል 60)
በዓላማ የተደረገ ጉዞ
ማቴ14፡22-27
ጌታ ኢየሱስ አንድ አገልግሎት ስለተሳካ፣ ሰዎች ደስ ስለተሰኙ አይሞቀውም፣ ልቡ ቀጣዩ የአባቱ አሳብ ላይ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ነገሮች መልካም የሆኑ ሲመስለን፣ የሰዎች ጭብጨባ ሲደራልን ወደ ፊት ከመሄድ ይልቅ ድንኳናችንን አስፍተን መጣል ነው የምንፈልገው፡፡ ጴጥሮስ ጌታን በክብሩ ሙላት ተገልጦ ሲያይ፣ የሙሴና የኤልያስ መከሰት የሆነበትን ያንን ክስተት በተመለከተ ጊዜ ተራራውን አንለቅም በሚል መንፈስ “… አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር” ሉቃ9፡33…
👏3
Signed Mentesnot Kebede
9 Sept 2026, 03:51 UTC441 views4 reactionsread 16 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤2👍2
Signed Mentesnot Kebede
8 Sept 2026, 03:52 UTC540 views1 reactionsread 16 September 2026 ማክሰኞ 03/13/18
የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 59)
እናንተው የሚበሉትን ስጡአቸው
ማቴ14:13-21
የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ ጌታ መጥተው የዮሐንስን መሠዋት ሲነግሩት ከነበረበት ስፍራ ወደ ምድረ በዳ ፈቀቅ አለ፡፡ ምክንያቱም ሄሮድስ በኢየሱስ እየተፈጸመ ያለውን ተዓምራት ሰምቶ ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው፤ እርሱ ከሙታን ተነሥቶአል፥ ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል በማለት ስጋት ላይ በመሆኑ ለጥንቃቄ ራሱን መሰወሩ ነው፡፡ ሰይጣን በምድራዊ ነገሥታት በኩል ስለሚሰራ አስፈላጊው ነገር ጥንቃቄ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ አንዳች አይሆንም ይላሉ ነገር ግን በምድር ላይ ብዙ አመጾች እየሆኑ ያሉት እኮ ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ መ…
❤1
Signed Mentesnot Kebede
7 Sept 2026, 03:48 UTC483 views5 reactionsread 16 September 2026 Photo
Photo, posted without a caption
🙏5
Signed Mentesnot Kebede
4 Sept 2026, 03:35 UTC199 viewsread 16 September 2026 "ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዘወር ብትል ጆሮህ ከኋላህ፣ “መንገዱ ይህ ነው፤ በእርሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል" ኢሳ30:21
Signed Mentesnot Kebede
4 Sept 2026, 03:35 UTC255 views1 reactionsread 16 September 2026 ዓርብ 29/12/18
የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 58)
ስውሩ የጠላት እጅ
ማቴ14፡1-12
ይህ ስለ ክርስቶስ ዝና የሰማው ሄሮድስ አንቲጳስ ሲሆን የአራተኛው ክፍል ገዢ ተብሎ ይጠራ ነበር ምክንያቱም ታላቁ ሄሮድስ ሥልጣኑን ለአራት ልጆቹ አከፋፍሎት ስለ ነበረ ነው፡፡ ይህ ቤተሰብ እጅግ ክፉና በነፍሰ ገዳይነት መንፈስ የተያዙ፣ ሥልጣናቸውን አላግባብ የሚጠቀሙ ሰዎች ነበሩ፡፡ ማርቆስና ሉቃስ እንደተረኩት ማር6፡14-29፣ ሉቃ9፡7-9 ጌታ ኢየሱስ አስራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን በገሊላ ከተሞች እንዲያገለግሉ በላካቸው ጊዜ ያደርጉአቸው በነበሩ ተአምራቶች የጌታን ዝና ከፍ አድርጎት ነበር፡፡ ስለዚህ የሰሙት ነገር ያስደነገጣቸው እነዚህ ሰዎች ስራቸው ክፉ ነበ…
❤1
Signed Mentesnot Kebede
2 Sept 2026, 05:09 UTC711 views6 reactionsread 16 September 2026 ረብዕ 27/12/18
የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 57)
ይህንን ጥበብ ከወዴት አገኘው
ማቴ13:53-58
ጌታ ኢየሱስ መንግሥተ ሰማይ በምድር ምን እንደምትመስል በብዙ ምሳሌዎች ሲያስተምር ቆይቶ አሁን ደግሞ ወደ ገዛ አገሩ ወደ ናዝሬት ሄደ፡፡ ጸሐፊው ስለ ጉዞው የሚነግረን ጌታ ትምህርቶቹ ብቻ ሳይሆኑ እያንዳንዱ እንቅስቃሴው በሙሉ በመለኮታዊ ፈቃድና እቅድ መሆኑን ነው፡፡ ነገር ግን ለምን በዚህ ጊዜ ወደ ገዛ አገሩ ወደ ናዝሬት ለመሄድ አሰበ ብለን ብንጠይቅ ምንዓልባት በማቴ13፡12፡46,47 ላይ እናቱ ወንድሞቹ ሊፈልጉት መጥተው ስለ ነበር በእናቱ እንዲመጣ ተነግሮት ሊሆን እንደሚችል ማሰብ እንችላለን ምክንያቱም የአሁን ጉዞው እነርሱ ከፈለጉት በኋላ የ…
❤3🔥3
Signed Mentesnot Kebede
1 Sept 2026, 03:42 UTC634 views1 reactionsread 16 September 2026 ማክሰኞ 26/12/18
የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 56)
የመንግሥተ ሰማይ የምድር መልክ/02/
ማቴ13:45-52
4. እንቁ የሚሻ ነጋዴ
"ደግሞ መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤ ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት" ማቴ13:45,46
ይህ ምሳሌ ከላይ በእርሻ ውስጥ የተሰወረ መዝገብ አይቶ ከደስታው የተነሳ ያለውን ሽጦ እርሻውን ከገዛው ሰው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ከሁሉ አስቀድሞ ምንም እንኳን የሰው ልጅ በኃጢአት ቢወድቅም በሰው ልጆች መካከል ለእርሱ እንደ እንቁ የሆኑ ሰዎችን ስላየ አለኝ የሚለውን፣ እንደ እንቁ የሆነውን አንድያ ልጁን /ራሱን/ በመስጠት ያንን…
❤1
Signed Mentesnot Kebede
31 Aug 2026, 03:51 UTC562 views2 reactionsread 16 September 2026 ሰኞ 25/12/18
የማቴዎስ ወንጌል መልዕክት (ክፍል 55)
የመንግሥተ ሰማይ የምድር መልክ/01/
ማቴ13:31-33; 44-46
መንግሥተ ሰማይ ማለት የሰማይ መንግሥት ወይም እግዚአብሔር የሚያስተዳድርበት መንግሥት ማለት ነው፡፡ ይህች የእግዚአብሔር መንግሥት እግዚአብሔር በምድር ላይ ከኃጢአት ውድቀት በኋላ ከሰዎች ጋር ባደረገው ኪዳን መሰረት ሲሰራ ቆይቶአል እነርሱም የአዳም፣ የኖህ፣ የአብርሃም፣ የዳዊትና የክርስቶስ ኪዳን ሲባሉ የመጨረሻው የዘላለም ኪዳን ነው፡፡ እስራኤል በተሰጣት ኪዳን መሰረት ለመኖር ባለመቻልዋ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእነሱ ተወስደች ጌታ ሲናገር “ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰዳለች ፍሬዋንም ለሚያደርግ ሕ…
❤1🔥1
Signed Mentesnot Kebede
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @mentesnotkebede2020. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.