29 Jul 2026, 19:18 UTC167 views6 reactionsread 7 August 2026 መከራ መክረው ፥ ችጋር አደቀቀው
የሀዘን ግርፋት ፥ እያፈራረቀው
ያኔ ሰው ሲነግረው ፥ አሻፈረኝ ብሎ
ይኸው ይማቅቃል ፥ ከሰው ተራ ጎድሎ
ምናለ ቢሰማ ^ ባያናንቅ ምክር
በድርቅናው አመል ^ ተኮፍሶ ባይውል
ሁሌም ባያስበልጥ ^ ብሎ እራሱን ብቻ
ቢቻቻል ከሌላው ^ ቢመርጥ አቻ ለአቻ
እኔ ብቻ ልክበር × ሁሌም ልቅደም ልብለጥ
ስሙኝ በቃ ላውራ × ምንድነው ማዳመጥ
ልክ ነኝ አልስትም × ከቶ አልሳሳትም
ተሳስተሀል የሚለኝ × ፍፁም አልፈልግም
እናንት ደካማ - እውቀት የሌላቹ
ወደ እኔ አትመጡም - ላስተምር ልምራቹ
ጊዜ የለኝም እኔ - ለማይረባ ወሬ
ከእናንተ የማብር -ነው እንዴ ሰክሬ????
እብድ ናችሁ እኮ ¡ እንዴት ልትመክሩኝ
ይልቅ ገንዘብ እንኩ …
❤6
Signed Biruk Tefera
29 Jul 2026, 17:33 UTC212 views8 reactionsread 7 August 2026 በዚህ ምድር ስትኖር
አስብ የሰው ድካም
ማንንም እስከ ጥግ
አትመነው በጣም
ቤተሰብ ጓደኛ
ፍቅረኛ ወዳጄ
አጋር መከታዬ
ብለህ ያልከው ቀኝ እጄ
ሁሉም በየጊዜው
ያልፋል ሆኖ ሽታ
አምላክህን ያዘው
አድርገህ አለኝታ
✍ብሩክ ተፈራ
🔥6❤2
Signed Biruk Tefera
29 Jul 2026, 17:25 UTC176 views4 reactionsread 7 August 2026 አለም ከንቱ
በኑሮ ዱብዱብ : እለት እለት ሩጫ
ለማግኘት በማሰብ :ከአሁኑ ብልጫ
ዝለትን መቋቋም: መዳከር በብርቱ
ለመኖር በደስታ: በዚህች አለም ከንቱ
ከመነሻው ማቀድ :ሲሳካም በሌላ
መሯሯጥ መዳከር :ፈልጎ ደልዳላ
በቃኝን በማያውቅ: ምኞት ባሰከረው
መውደቅ መነሳትን :ጎዳና ባረገው
የህይወት ኮሮኮንች :አንጥሮ የሚያነሳ
በእሽቅድድም ሁነት: ሁሉን የሚያስረሳ
ለሚያልቀው እድሜ :ስጋን አጨርጭሶ
እረፍት የሚያሳጣ :መንፈስ አኮስሶ
ለመጥፎ አሸርጋጅ : ለመልካም ጥላቻ
ፍትህ በሌለበት : መኖር ለየብቻ
ደጉን አሽቀንጥሮ : ጨካኝ የሚያንጠለጥል
እውነት እየገፋ :ለውሸት የሚውል
ነፍሰ በላ አውሬ ፨ ይሄ አለም ከንቱ
ስንቱን ደፈጠጠው ፨ ላይኖር በህይወቱ
🖋ብሩክ ተ…
🥰4
Signed Biruk Tefera
29 Jul 2026, 17:22 UTC175 views6 reactionsread 7 August 2026 አንዳንዴ ገጣሚም< ቃላት ይርቁታል
ደራሲም ሀሳቦች <ይተናነቁታል
ሰአሊም አልሰምር< ይሉታል እጆቹ
ተራኪም ይስታል < ላፍታ በድምፀቱ
ሀኪምም እውቀቱ <አልገለጥ ይላል
ሹፌርም መኪናው< አልሄድም ይለዋል
ተርጓሚም መተርጎም <ሲያቅተው ለአንዴ
ሯጩም ሲሸነፍ <ከአንዴም ሁለት ሶስቴ
አስታራቂም ሳይችል <ማስታረቅ ለሰዎች
ጥበብ ስትሸሸግ <ተቀብራ ከአንዳንዶች
አስተወል ወዳጄ‼️⁉️
ባለህ አትመካ =ሁሉም አላፊ ነው
ተጠጋ ከአምላክህ =ዘመን ከማይሽረው
✍ብሩክ ተፈራ
🔥6
Signed Biruk Tefera
29 Jul 2026, 17:17 UTC171 views6 reactionsread 7 August 2026 እናት ጎጆ ፥ እናት አምባ
እናት ወዲት ፥ እናት ግርማ
እናት ክብር ፥ እናት ልብስ
የዋህ እሩሩህ ፥ ሆዷ ልስልስ
•••••••••••••••••••••••••
የልጅ አሽሞንሟኝ ፥ ተንከባካቢ
ከውስጥ ከውጪ ፥ ሁሉን ሰብሳቢ
ጉድፉን አጥሪ ፥ የቤቱ ዋልታ
ውለታን የማታውቅ ፥ በፍቅር ሞልታ
እናት ናት አዛኝ ፥ አቅፎ አባባይ
ፈፅማ የማትፈቅድ ፥ የልጇን ዋይ ዋይ
•••••••••••••••••••••••••••••••
አይቀንስ ከቶ ፥ ጊዜ አይገድበው
የእርሷ ስጦታ ፥ ሁሌም አዲስ ነው
ነጋም እንስፍስፍ ፥ በቸር አዳሪ
ለራሷ የማትል ፥ ቅን አቀርቃሪ
•••••••••••••••••••••••••••••
ዘወትር ለልጇ ፥ መልካም አድራጊ
ከጉያ ቀብራ ፥ እልፉን ሸሻጊ
እናት እኮ ናት…
❤4🥰2
Signed Biruk Tefera
28 Jul 2026, 15:14 UTC269 views9 reactionsread 7 August 2026 Photo
አሜን!!!
የትምህርት ነገር ፥ ጅራፍ ለሆነብን
መድሀኒአለም ጌታ ፥ ምስራች ያርግልን
አሜን!!!
ክላሱ እንደ ገነት - ወንበሩ ትራስ
ፒፒቲው መናችን - መምህሩ ጳውሎስ
ፈተናው ከበሮ - ሀሴት የሚያጭር
ያርገው ደጉ ጌታ - ትምህርትን መዝሙር
አሜን!!!
ናላችን ለዞረው ፥ መማር ለቀፈፈን
የሰንበቴ ጠላ ፥ ትምህርቱን ያርግልን
ደግሞም በማስጨነቅ ፥ የኖሩት መምህሮች
እንደ ንስሀ አባት ፥ ይሁኑን ፈዋሾች
አሜን!!!
ፊዚክስ ላማረረን ^ ይሁን ቡራኬያችን
ኬሜስትሪን እንዲው ^ ያርገው ሎቶሪያችን
ማትስን ኢኮኖሚክስ ^ ያርጋቸው ፃዲቅ
በልትን በመጠጣት ^ እንሁን እስኪ ሊቅ
አሜን!!!!!
ያጣው ዜሮ አግኝቶ ~የተሸማቀቀው
መጨረሻው አምሮ ~የ…
🥰5😁2❤1🙏1
Signed Biruk Tefera
28 Jul 2026, 11:40 UTC182 views13 reactionsread 7 August 2026 Photo
ተው ስጠኝ
እኖራለው ፥ ያለ ፍሬ
እጓዛለው ፥ አቀርቅሬ
ሰዓት ቀናት ፥ ይነጉዳሉ
አመታትም ፥ ይሮጣሉ
ነግቶ መሽቶ ፥ እዚያው ከዚያው
የኔስ ህይወት ፥ ለውጥ የለው
መልፋት መስራት ፥ ላብ ማንጠፍጠፍ
መኖር ብቻ ፥ ከእጅ ወደ አፍ
አፈር ልሶ ፥ ዳገቱን
ለመሻገር ፥ ወሰኑን
ዳግም መውደቅ ፥ መንደባለል
ከወደ ታች ፥ መንከባለል
…
🔥7❤3🫡2👍1
Signed Biruk Tefera
28 Jul 2026, 05:36 UTC293 views6 reactionsread 7 August 2026 Photo
ብዕሬ ቅበረኝ
አንተ ባለ ቀለም ፥ አንተ ባለ ቅኔ
ትተኸኝ የማትሄድ ፥ የስጋ ወገኔ
እባክህ ቅበረኝ ፥ አብሬህ እንዳለቅስ
መከፋቴ በዝቶ ፥ እንዲህ ከምላወስ
ሰው•••••••••
አለው መሄድ ^ አለው መምጣት
ላንዴ መውደድ ^ላንዴም መጥላት
እልፍ አዕላፍ ^ ለገበረው
ባንድ ቅፅበት ^ ለሚያበነው
ማግኘት ማጣት ^ ነውና ህጉ
ና ገላግለኝ ^ አንተ ደጉ
እስኪ ጥራኝ ፥ ልምጣ ቤትህ
እዚያው ልቅር ፥ ከመቅደስህ
አሻግቶኛል ፥ የአለም ኑሮ
ላንዴ ስቆ ፥ ባንዴው ሮሮ
አንተ ምንም ፧ አትጨክንም
ቂም አርግዘህ ፧ አትመርግም
ጠጋም ሳትል ፧ በመጠኑ
ርቀህ ሳትሄድ ፧ ከወሰኑ
…
❤5👏1
Signed Biruk Tefera
27 Jul 2026, 07:29 UTC206 views4 reactionsread 7 August 2026 Voice message
የእለቱ ድንቅ ዝማሬ
የሴሎንዲስ ጥበብ
እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🌺🌸🌺🌸🌺🌸🌺🌸🌺🌸🌺🌸🌺
🥰4
Signed Biruk Tefera
25 Jul 2026, 15:54 UTC247 views8 reactionsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
🥰7🔥1
Signed Biruk Tefera
Posted without readable text
23 Jul 2026, 18:29 UTC≈3,890 views18 reactionsread 7 August 2026 Photo
እምነት አለኝ ብሎ ፥ ስራ ግን ለሌለው
ሊያድነው የሚችል ፥ ንገሩኝ ምንድነው???
ክርስትናን በህይወት ፥ መግለጥ ካልተቻለ
ቃሉ ብቻ ታውቆ ፥ ተግባር ላይ ካልዋለ
ለተራበው ምስኪን ¡ እርቃን ሆኖ ላለው
እሳት ና ሙቅ ብሎ ¡ ልክ እንደ መስጠት ነው
የ ያዕ ም 2፥ 14
(ወንድሞቼ ሆይ እምነት አለኝ የሚል ስራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል እምነቱ ሊያድነው ይችላልን???)
✍ብሩክ ተፈራ
❤18
Signed Biruk Tefera
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @menfesawtsihuf. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.