14 Apr 2023, 13:53 UTC135 views1 reactionsread 10 August 2026 #ደም_መላሽ
ክፍል2⃣
......ከ ሁለት ወራት በኋላ
የዮናስ እናትም በሰው እጅ ተገድላ ነበር። ዮናስ በ12 ዓመቱ ስለ እናቱና ስለአባቱ ሲወራ ዐይኑ ደም ይለብሳል።
ከዕለታት አንድ ቀን ዮናስ መቃብርጋ ሄዶ እያለቀሰ ነበር። እያለቀሰ ድንገት የጨቅላ ህፃን ልጅ ለቅሶውን አቋረጠው። ድምፁን ወደሰማበት አቅጣጫ ሄደ። የ3 ወር ህፃን በፎጣ ተጠቅልሎ መቃብር መሀል አየ። አንስቶት ይዞት ወደቤቱ ሄደ። በለቅሶ መሀል ስላገኘው "ይስሐቅ" አለው።
. ........ከ 8 ዓመት በኋላ
ዮናስ የ20 ዓመት ወጣት ሆኗል። የተገኘው ይስሐቅ ደግሞ 8 ዓመት ሆኖታል። ቤት ውስጥ ሶፋ ላይ ተቀምጠዋል። ይስሐቅ ደብተር እና እስኪብሪቶ…
👍1
2 Apr 2023, 12:04 UTC124 viewsread 10 August 2026 #ደም_መላሽ
ምዕራፍ አንድ
ክፍል_አንድ
ዕድሜያቸው ከ 10-15 የሚሆኑ በርከት ያሉ ልጆች በአንድ ቤት ውስጥ ተሰብስበው የእግር ኳስ ጨዋታ እያዩ ነው።
ጨዋታውን የሚያዩት በቡድን ሆነው ብር አሲዘው ነው። በጣም ብዙ ብር አሲዘው ነው። ያሸነፉ ቡድኖች 10 10 ሺህ ብር ይደርሳቸዋል።
ህፃናት ናቸው ይህን ያክል ብር ምን ያረጉታል። ከአሸናፊዎች መካከል የ12 ዓመት ልጅ ነበር። ዮናስ ይባላል። ያስያዘው ከአባቱ ብር ሰርቆ ነው። ነገር ግን ወደ ቤት ሲመለስ በእጁ አስር ሺህ ብር ይዟል። ግን በመንገድ ሲሄድ ልቡ እየመታ ነበር።
ቤት እንደደረሰ የፈራው ነገር ደረሰ። አባቱ እየጮኸ እየተቆጣ ነበር። "እዚች ቤት ይደርሳታል። ቆይ አሳ…
10 Mar 2023, 16:01 UTC124 viewsread 10 August 2026 የዘንድሮ ፍቅር በጣሙን ተንዛዛ
ህፃን ሽማግሌው "i love you❤️" አበዛ🤧
@manbeblehiwot
28 Feb 2023, 14:12 UTC134 views0 reactionsread 10 August 2026 #ፖሊስ:- ሌባ እንድትሆን ይፈልጋል
#ዶክተር:-ታማሚ እንድትሆን ይፈልጋል
#ነጋዴ:-እቃ እንዲጎልህ ይፈልጋል
#ሌባ_ብቻ_ሀብታም_እንድትሆን_ይመኝልካል
😁🤣😆
26 Feb 2023, 11:28 UTC140 views2 reactionsread 10 August 2026 ሁ ለ ት ወ ን ድ
══•✦•══
✍ ዓለማየሁ ገላጋይ
'
"ፍቅረኛዬን ለምን አናገርካት"
ገጭ!
"ፍቅረኛዬ ላይ ምን ታፈጣለህ?"
ገጭ-ገጭ!!
ማንንም አይፈራም። እሷ ግን ትሸማቀቃለች። እሷን አቅፎ ዓይኑ የሚወሰልተውን ይፈልጋል። ገጭ! ገጭ!
አንዳንዱ ጎረምሳ ዱቄት ተነፍቶበት ከወደ ሽንት ቤት ሲመጣ እንደታሸ ታውቃለች። አንዳንዱ የፊቱ ሚዛን ተዛብቶ ብቅ ይላል። የመጨረሻውን ወንድ እፊቷ ሲመታው እሷ ብሳ ቱግ አለች።
"አየሽ!"
"አላየኝም!"
"አይቶሻል እኮ!"
"ቢያየኝስ?"
ጭራሽ የተመታው ይገላግላቸው ጀመር።
"ካየሁም ይቅርታ" ብሎ ጉልበቱን ሊስም አጎበደደ። አንዳንዱ ወንድ ምኑ ታይቶ ነው ወንድ የሚባለው? አንድ ዓይኑ ተለስኗል። ይህን ስት…
👍2
26 Feb 2023, 11:26 UTC99 viewsread 10 August 2026 Forwarded from @ManbebNebsnYadsalPhoto
ወ/ ከ/ ሰ
ሆቴል ትገባና ጥብስ ታዛለህ።
ደም ግፊት ምናምን ካለብህ እንደው ምናልባት 'ጨው እንዳይገባበት' ትል ይሆናል!
' ቅባት አይብዛበት' ብትልም አሳማኝ ነው!
እንደሁኔታው ሽንኩርት የማይወድም ስለሚኖር ' ሽንኩርት እንዳይገባበት!' ብትል ሰዎች ይረዱሃል!
'እስቲ አንድ ጥብስ አምጡልኝ! ስጋ እንዳይገባበት!' ካልክ ግን ብራዘር ደም ግፊትህን ብቻ ሳይሆን የአእምሮ ጤና ምርመራም እንድታደርግ ነው የምመክርህ!
አንዳንድ ሰዎች ሚኒልክ የሌለበት የአድዋ ድል በዓል ለማክበር ሲፍጨረጨሩ ሳይ የሚመጣብኝ ሃሳብ ነው!
8 Feb 2023, 11:51 UTC113 viewsread 10 August 2026 የዓለማችን ውዱ ፈሳሽ እንባ ነው! 1% ውሃን እና 99% ስሜትን ይዟል አንድን ሰው ከመጉዳትህ በፊት ደጋግመህ አስብበት !
#share #share #share
8 Feb 2023, 11:51 UTC123 viewsread 10 August 2026 ታክሲ ውስጥ ከጎኔ ያለው ልጅ እምፅፈውን ቴክስት እያጮለቀ ሲያስቸረኝ #በቃ_ቦንቡን_ታክሲ_ውስጥ ትቼው ልወርድ ነው እሚል ስፅፍ አይቶኝ
ወራጅ ሳይል መኪናው እየሄደ በመስኮት ዘሎ ወጣ
😆😂
3 Feb 2023, 15:58 UTC131 viewsread 10 August 2026 አብረን አድረን ጠዋት ባሏ "የት ነበርሽ?" ብሎ ሲደዉልላት
"በቃ አንተ ራስህን ስለማታምነዉ ሰዉ ሁሉ እንዳንተ ይመስልሃል አይደል?" ብላ ተናዳ ስልኩን ዘጋችበት
ባሎች ግን ሚስቶቻችሁን እመኑ፤ አታበሳጯቸዉ 😁😂😁
@manbeblehiwot
21 Dec 2022, 14:31 UTC183 views0 reactionsread 10 August 2026 ወ ጥ
🥘 🥘
🥘
ወጥ ማን ያውቃል? ቀላዋጭ።
🥘
ወጥ ሲታጣ ይበላል በዱባ።
🥘
ወጥ ቢጣፍጥ፣ እጅ ያስመጥጥ።
🥘
አዲስ ወጠ ሰሪ፣ ዝንጅብል ታበዛለች።
🥘
ወጥ ያጣ ጎመን፣ አገር ያጣ ሰሜን።
🥘
ወጥ ይሉሻል በርበሬ ነው።
🥘
ለወጡም እዘኑለት፣ ከደረቁም ብሉለት።
🥘
ቅመም የበዛበት ወጥ፣ አይፋጅ አይኮመጥጥ።
🥘
ለወጥ የሚሻል ቅልውጥ።
🥘
ወጥን የሚጨርስ መጎራረስ፣ ሴትን የሚያስመታት መመላለስ።
🥘
ወጥ ያጣ ዱባ፣ ልብስ ያጣ ዳባ።
🥘
ሃሳብ የለሽ ወጧ ይጣፍጣል።
🥘
ወጥና ወንድም ማስፈራሪያ ነው።
🥘
ወጡ ሳይወጠወጥ፣ ወስከንቢያው ቂጢጥ።
🥘
ደፋር ወጥ ያውቃል።
🥘
የኔን ወጥ በቀመስሽው፣ ያንቺን በደፋሽው።
🥘
ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍ…
17 Dec 2022, 13:38 UTC175 viewsread 10 August 2026 ሁለት መላጦች
═ 👨🦲👨🦲 ═
✍ ከበደ ሚካኤል
'
ሁለት በራ ሰዎች ሲያልፉ በጎዳና፣
ዕቃ መሬት ወድቆ ብልጭ ሲል አዩና፤
ተሽቀዳድመው ሄደው ከቦታው ሲደርሱ፣
ተፎካከሩበት ዕቃውን ሊያነሱ።
በኋላም ተማተው በጥፊ በጡጫ፣
አንደኛው ነጠቀ በጉልበቱ ብልጫ።
አገላበጠና ቢመለከት ፈጥኖ፣
ዕቃውን አገኘው ማበጠሪያ ሆኖ።
እስቲ ሁላችሁም በሉ ፍረዱት፣
እሱ ራሱ በራ ጠጉር የለበት።
ሮጦ ተማቶ ቀምቶ ቢያመጣ፣
ምን ያደርግለታል ሚዶ ለመላጣ?
ሰዎች ይፋጃሉ አስበው ሳይፈርዱ፣
የተጣሉበትን ጥቅሙን ሳይረዱ፤
ከመጣላት በፊት ከመቀያየም፣
የነገሩን ፍሬ መረዳት መልካም።
═══════
📓 የቅኔ ውበት
📖 📖 📖 📖 📖
@manbeblehiwot
@manbeblehiwot
17 Dec 2022, 13:36 UTC127 viewsread 10 August 2026 Photo
ድ ሃ
😔😔
😔
ድሃ ተበድሎ፣ ማሩኝ ይላል ቶሎ።
😔
ድሃ በጉልበቱ፣ ባለፀጋ በሀብቱ።
😔
ድሃና ጌታ ተሟግቶ፣ ድንጋይና ቅል ተማትቶ።
😔
የድሃ ብድር፣ አይውል አያድር።
😔
ድሃ ያመልክት፣ ዳኛ ያሟግት።
😔
ነጭ ድሃ፣ ነጭ ማር ይከፍላል።
😔
ድሃ ካልጋረ፣ ዶሮ ካልጫረ።
😔
ድሃ ለወዳጁ አይሰንፍ፣ ሀብታም ካለወዳጁ አይተርፍ።
😔
ድሃ የሚበላው እንጂ የሚከፍለው አያጣም።
😔
ለድሃ፣ ማን ሰጠው ውሃ።
😔
ድሃ ቢናገር አያደምቅ፣ ቢጭብጥ አያጠብቅ።
😔
ድሃና እመቤት፣ እልፍኝና ማድቤት።
😔
የድሃ ተዝካር፣ የጎባጣ ስካር።
😔
ድሃ ዶሮ ካረደ ከሁለት አንዳቸው ቢታመሙ ነው።
😔
ድሃ ካለቀሰ፣ ቀኑ መች አነሰ።
😔
በድህነት ላይ ስንፍና፣ በቂጥኝ ላይ …
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @manbeblehiwot. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.