12 May 2025, 18:56 UTC106 viewsread 7 August 2026 Photo
አንድ ወቅት ላይ አንድ አህያ ነበረ ታዲያ ይህ አህያ ዕድሜውን ሙሉ በፈረስ ሲቀና አሳልፏል።
እኔ እንደ ፈረሱ ብሆን ኖሮ… ህይወቴ የተሻለ ይሆን ነበር በማለት አሰበና "ከእንግዲህ አህያ አልሆንም ብሎ ወሰነ።"
ሸክሙን መሸከሙን አቆመ፣ በጨዋነት መራመድ፣ እንደ አህያ መጮህ ትቶ እንደ ፈረስ አስመስሎ ለመጮህ ሞከረ።
ነገርግን አህያው ባሰበው መንገድ አይደለም ባለቤቱ ያሰበው ባለቤቱ እሱን መጥራት አቆመ፤ እሱን መመገብ አቆመ።እሱን ችላ በማለት አህያው በህይወቱ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ምንም አይነት ተግባር አልነበረውም፡፡
አህያው"አደረኩት!" "አሁን እንደ ፈረሶች ነኝ!" ብሎ አሰበ
ቀናት እያለፉ ሲሄዱ ግን ረሃብ ገባ እግሮቹ ደከሙ፣ድርቆሽ ያመጣለት የለም።
…
Signed ♊️
10 May 2025, 17:53 UTC87 viewsread 7 August 2026 Photo
አንድ ጊዜ እናት ጠየቀች፡ ማንን የበለጠ ትወዳለህ? እኔን ወይስ ሚስትህን?
ልጂመለሰ፦ አላቅም ፍቅርሽ ግን ሚስቴን ያስረሳኛል የእሷ ፍቅሯ እና እንክብካቤዋ ደግሞ አንቺን ያስታውሰኛል!
ለማንኛውም
'መልካም የእናቶች ቀን!'
@kebranaw
Signed ♊️
19 Aug 2024, 11:42 UTC209 viewsread 7 August 2026 ስለአማርኛ ቋንቋ ይሄን ያውቁ ኖሯል?
——-
▪️አማርኛ አማራ ተብሎ ከሚጠራው የብሔረሰብ መጠሪያ የተገኘ ነው።
▪️አማርኛ የተፈጠረው ላስታ እና አካባቢው ነው።
▪️አማርኛ ከሴም የቋንቋ ዝርያዎች የተገኘ ነው።በሴም ውስጥ ግዕዝ፣ ትግሬ፣ ትግርኛ፣ አማርኛ፣ አደርኛ፣ ጉራግኛ፣ አርጎብኛ እና ጋፋትኛ ይገኛሉ።
▪️ለአማርኛ ቅርብ የሆነው ቋንቋ አርጎብኛ ነው።(እኔን ጨምሮ ብዙ ሰው ትግርኛ ይመስለዋል)
▪️አማርኛ ልሳነ-መንግስት ቋንቋ ነው።
▪️ ክልሎች አማርኛን የስራ ቋንቋቸው አድርገው ይጠቀሙታል።
▪️አማርኛ መነገር የጀመረው በ1000 ዓመተ ዓለም አካባቢ ነው።(ዓመተ ምህረት ሳይሆን ዓመተ ዓለም ነው)
▪️የአማርኛ ፊደል የተገኙት ከግዕዝ ቋንቋ ነው። 2…
Signed 🏹
29 Mar 2024, 20:33 UTC207 viewsread 7 August 2026 @KEBRANAW
Signed 🏹
11 Mar 2024, 08:58 UTC367 viewsread 7 August 2026 የአስቴር አወቀ አሳዛኝ የህይወት ታሪክ
ለምን ትዳር አልያዘችም
ለምን የምታፈቅረው ሰው ከዳት / ሸሻት /
የኖሩትን ህይወት ፡ ያሳለፉትን መልካም እና ጥሩ ያልነበሩ ጊዜያት ፡ ዜማ አድርገው ከሚሰሩ ድንቅ አርቲስቶች መሀል አስቴር አወቀ አንዷ ነች ።
አስቴር እውነተኛ ፍቅርን ፍለጋ ስትዋትት መኖሯን የሚገልፁ ብዙ ዜማዎች ፅፋለች ። ከነዚህም መሀከል ዛሬ ልናይ ያሰብነው ፡ ወይ ኑሮ የሚለውን ዘፈኗን ነው ።
አስቴር ስለዚህ ስለማናውቀው እና ለአመታት በልቧ ይዛው ስለምትኖረው ሰው በትዝታ ወደኋላ ሄዳ እያስታወሰች በብዙ ዜማዎቿ ስትዘፍን የሰማናት ቢሆንም ፡ ሀገሬ የሚለው አልበም ላይ ራሷ ፅፋ በዘፈነችው ወይ ኑሮ በሚለው ልብ የሚነካ ዘፈን ላይ ግን ቁጭ…
Signed 🏹
1 Mar 2024, 20:35 UTC417 viewsread 7 August 2026 Photo
🇪🇹እንኳን ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!🇪🇹
Signed 🏹
13 Oct 2023, 19:32 UTC696 viewsread 7 August 2026 #ዩኒቨርስቲ_ገነት_አይደለም‼️
በመምህር [ አበባየሁ ጌታ ] የዩኒቨርስቲ አስተማሪ
ከስር ያያዝኩት የ#Masters_Degreeዬ ውጤት ነው ፤ የዚህ ልጥፍ ዓለማ ራስን ማንቆለጳጰስ ምናምን ሳይሆን ልፋቴ እና የሚከፈለኝ አለመገናኘቱ ሲቀጥል ዩኒቨርስቲ መግባት እና ትምህርት መስቀል ትርጉም አልባነቱን እንዲሁም 12ኛ ክፍል ውጤት ላልመጣላቸው መጽናኛ እንዲሆናቸው ነው።
በአንድ የመንግስት ዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ፤ከህይወቴ 17 ዓመት ለመጀመሪያ ድግሪ ሁለት ዓመት ደግሞ ለMasters ድግሪ በአጠቃላይ 19 ዓመታትን ያጠፋሁበት በትምህርት ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም Highschool እና መሰናዶ ጓደኛቼ የነበሩ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላ…
Signed 🏹
6 Oct 2023, 19:29 UTC623 viewsread 7 August 2026 ወቀሳህ ነፃ አያወጣህም
፨፨፨፨፨///////////፨፨፨፨፨
በተበላሸ የአሰራር ስረዓት ውስጥ ልንኖር እንችላለን፣ የማይመቸን ስፍራ ልንገኝ እንችላለን፣ በማንወደው ሁኔታ ውስጥ እራሳችንን ልናገኝ እችላለን፣ በማይረዱን፣ በማያበረታቱን፣ በማይወዱንና በማያነቃቁን ሰዎች ልንከበብ እንችላለን፣ የመንግስትም ይሁን የመስሪያቤታችን አሰራር ላይመቻን ይችላል ነገር ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች እየደረደርን እያንዳንዱን አካል ብንወቀስ፣ በእነርሱ ብናሳብብ፣ በእነርሱ አለመመቸት ውድቀታችንን ብናመካኝ አንዳች የምናገኘው ነገር የለም። ላንተ ውድቀት ማንንም ብትወቅስ፣ ለእራስህ ስንፍና ምንም ምክንያት ብትደረድር፣ ህልምህን ላለመኖርህ የጓደኞችህን ተፅዕኖ እንደ ሰበብ ብትጠቅስ …
Signed 🏹
6 Sept 2023, 13:11 UTC359 viewsread 7 August 2026 Photo
ጳጉሜን
ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ሄፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ መሆኑን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ተነግሯል፡፡ “ኤፓጉሜኔ” ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ቋንቋችን ተውሳክ ማለት ነው፡፡ ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ (ምንጭ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ ፱፻፭)፡፡ ምዕራባዊያኑ ጳጉሜን ተጨማሪ ቀን አድርገዋታል፡፡ እኛ ግን የወር ተጨማሪ አድርገናታል፡፡ በጽርዕ ኤፓጉሜኔ ትባል እንጂ ሊቃውንት ግን ተረፍ ይሏታል፡፡ ጳጒሜን የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የአዲሱ ዓመት መንደርደሪያ ዕለት እንደሆነች የክርስቶስ ልደትም የዓመተ ፍዳ ማቆሚያ የዓመተ ምሕረት መጀመሪያ …
Signed 🏹
6 Sept 2023, 13:11 UTC482 viewsread 7 August 2026 የጳጉሜን ወር በጸሎት በንስሓ ተወስነን ወደ አዲሱ ዓመት የምንሸጋገርባት ድልድይ ናት፡፡ ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር የፈቀደላቸው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ጸሎት በመጸለይ ጸበል በመጠመቅ ያስቧታል፡፡ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው ሲሆን መሠረት የሚደረገውም ጾመ ዮዲት ነው፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ ይህን መሠረት አድርገው ሕዝቡ ሳይቀር “ጳጉሜን ዕድሜ ትሰጠናለች፤ በኋላም ታድነናለች” ብለው ጾም ይጾሙባታል፡፡ (ምንጭ-ቅዱስ መልከ ጸዴቅ ድርሳን)፤ በሀገራችንም ንግሥት ዘውዲቱ እና ምኒልክ የጾም ሥርዐት ይፈጽሙባት ነበር፡፡ ሌሎችም ሽ…
Signed 🏹
31 Aug 2023, 21:25 UTC653 viewsread 7 August 2026 አዲስ ዘመን ጋዜጣ ታህሣሥ 6 ቀን 1978 ዓ.ም የወጣ
አፄ ምኒልክን አንድ እንግሊዛዊ " ከጥቁርና ከነጭ ማን ይበልጣል ?" ሲል ይጠይቃቸዋል:: ምኒልክም " አስበህ እንደጠየቅከኝ አስቤ መልስ እሰጥሃለው " ብለው በቀጠሮ ይለያያሉ፡፡ ከዛም ሊቃውንቶቻቸውን ሰብስበው ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ እንዲሰጡ ይጋብዟቸዋል፡፡ ለጊዜው ምንም መልስ አልተገኘም፡፡ በኃላ አለቃ ድንቄ የተባሉ ብልህና አዋቂ ሰው " አይቸገሩ ጃንሆይ ! መልሱን እኔ እሰጥዎታለሁ " አሏቸው፡፡ ምኒልክም በፅሞና ይጠብቋቸው ጀመር፡፡
አለቃ ድንቄም " ፈረንጁ ከጥቁርና ከነጭ ማን ይበልጣል አይደል ያለው ? ፍላጎቱ ይገባናል፡፡ እርስዎም በፈንታዎ " ከአይንህ ነጩ ነው ጥቁሩ የሚያይልህ ? " ብለው ይ…
Signed 🏹
31 Aug 2023, 21:24 UTC375 viewsread 7 August 2026 'ኡቡንቱ"
አንድ የስነ ቅሪት ተመራማሪ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገጠራማ መንደር ለስራ ባቀናበት ወቅት በአካባቢው ከሚኖሩ ህጻናት ጋር ወዳጅነት ይመሠርታል። አንድ ቀን ሕጻናቱን ለማስደሰት ሽልማት ያለው ጨዋታ ያዘጋጃል።
በማንጎ የተሞላ አንድ ቅርጫት ከዛፍ ስር በማስቀመጥ ህጻናቶቹን ከዛፉ አንድ መቶ ሜትር እንዲርቁ አደረገ። ከዚያም እንዲህ አላቸው "እኔ ጀምሩ ስል ቀድሞ ከቅርጫቱ የደረሰ ሙሉውን ማንጎ ይበላል። "
ህጻናቶቹም ጨዋታው ሲጀመር ከጨዋታው ህግ ውጪ ያልተጠበቀ ነገር አደረጉ።
ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው እኩል ወደ ቅርጫቱ ሮጡ። ዚያም አንድ ላይ በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ማንጎ በአሸናፊነት መንፈስ ተካፍለው መብላት ጀመሩ።
የስነ ቅሪት ተመራማሪውም በ…
Signed 🏹
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @kebranaw. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.