29 Jul 2026, 16:08 UTC87 views15 reactionsread 7 August 2026 መፅሀፍ ቅዱሳችን 1ነገስት 3፥3 ላይ እንዲህ ይላል
"ሰሎሞንም እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፥ በአባቱም በዳዊት ሥርዓት ይሄድ ነበር፤ ብቻ በኮረብታ መስገጃ ይሠዋና ያጥን ነበር።"
በዚህ ክፍል መሰረት ሰሎሞን ሁለት ትልልቅ በጎ ነገሮች ነበሩት።አንድ እግዚአብሔርን ይወዳል ሁለት ደግሞ በአባቱ በዳዊት ስርዓት ይሄዳል።ታድያ ምንም እንኳ እነዚህ ሁለቱ ባህርያቶቹ ደስ የሚያሰኙ ቢሆኑም ከእነርሱ እኩል ግን የተቀመጠ ደካማ ጎን ነበረው። እርሱም በኮረብታ ላይ ባለው መስገጃ ይሰዋና ያጥን ነበር።ይህ እንግዲህ እንደ ቀልድ እርሱ ችላ ያለው እግዚአብሔር የማይወደው ነገር በእድሜው ማምሻ ልቡ ለሚስቶቹ አማልክቶች እንዲኮበልል እንዳደረገው መፅሀፍ ቅዱሳችን ይነግረናል።
…
❤9🙏5👍1
Signed Sema yawit
28 Jul 2026, 09:54 UTC420 views13 reactionsread 7 August 2026 ትላንት ቤት ሁኜ መዝሙር ከፍቼ እየሰማው አንድ መች ያወረድኩት እንደሆነ በውል የማላስታወሰው "አስር ጊዜ ባይህ" የሚለው የዮሴፍ አስቻለው መዝሙር በስልኬ እንዲህ ሲል መንቆርቆር ጀመረ
ሁልጊዜ ባገኘህ ሁልግዜ ብርቅ ነህ
የየዕለት መናዬ የቶሎ ቶሎ ነህ
ደረትህ ስር ምውል ወዳጄ ብትሆን
ምንም ያህል ባውቅህ ብነግርህ
ሚስጥሬን
አስር ግዜ ባይህ አስሬ ፈራለው
ሁለግዜ ባገኝህ እደነግጣለው
እንደቤተኛ ቅርብ እንደ እንግዳ ብርቄ
ደጋግመህ ብትመጣ ሽርጉድ እላለው
ወገቤን ታጥቄ
እያለ ይቀጥላል ሰማውት አንዴ ሁለቴ እያልኩ ቁጥሩን እስካላስተውስ ድረስ ደጋግሜ አደመጥኩት።ወንድማችንን ጌታ ፀጋውን ያብ…
❤13
Signed Sema yawit
28 Jul 2026, 09:54 UTC111 views3 reactionsread 7 August 2026 File
File, posted without a caption
❤3
Signed Sema yawit
24 Jul 2026, 07:57 UTC181 views9 reactionsread 7 August 2026 ያኔ 2015 የሁለተኛ አመት ተማሪ እያለው ነበር አለማወቅን ያነበብኩት።ያኔ አለመኖር እጅግ ተወዳጅ ስለነበረ በእርግጠኝነት ይሄም ቆንጆ እንደሚሆን ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ አልነበረኝም።ሰሞኑን ደግሞ መፅሀፉን በድጋሚ እያነበብኩ ነው።እናም ምን ልላቹ ነው አንዳንድ መፅሀፎች ተደጋጎመው መነበብ አለባቸው።ከእነርሱም ውስጥ አንዱ አለመኖር ነው እንድታነቡ እያበረታታሁ ከእዛ ውስጥ እስከ አራተኛ ክፍል ቤት ተምራ ቆይታ ትምህርት ስትጀምር የመጀመርያ የፈተና ቀን የገጠማትን ገጠመኝ ጋብዣቹና ልሰናበት።
"አትሄጂም?" አለኝ
"የት ልሂድ ?" አልኩት። መልሴ ግራ እንደተጋባው ጠቆመው መሰለኝ።
"ቆይ አንዴ"ብሎ ዘደ ውጭ በመውጣት በአያቴና በእናቴ ታጅቦ መጣ።
አያቴ "ጎ…
👍6❤3
Signed Sema yawit
21 Jul 2026, 09:25 UTC205 views17 reactionsread 7 August 2026 ልክ የዛሬ አመት በዚህ ሰዓት ነበር የተመረኩት።በዛ ሰሞን የሚያስጨንቀኝ ነገር ቢኖር ከግቢ ቶሎ ጨርሶ መውጣት ነበር።በጣም ሰልችቶኝ ስለነበር ቤት መጥቼ ማረፉ ነበር የሚታየኝ።ቤት መጣው ትንሽ አረፍኩ COC ተፈተንን አሁን ነገሮች ተቀየሩ።አሁን ላይ የሚያሳስበኝ የት ነው ምቀጠረው?እንዴት ነው ምሆነው ሆነ።ደግሞ በዚህ ጉዳይ GC ከነበርኩበት ጀምሮ ለአንድ አመት በጌታ ፊት እፀልይ ነበር።እግዚአብሔር ቀኑን ጠብቆ በሰው የሚቻል የማይመስል እራሱ የወሰነበት ቦታ ከዛንም እኔ ባልጠበኩት ሰዓት በታምራቱ አስደነገጠኝ።Apply ያደረኩበት ቦታ ነይ ብለው ሲጠሩኝ ምንም ሳልዘጋጅ እቃ ፓክ ለማድረግ እንኳ ግዜ እስካጣ ድረስ በችኮላ ወደዚህ መጣው።
እና ምን ልላቹ መሰ…
❤14🥰3
Signed Sema yawit
8 Jul 2026, 07:01 UTC272 views12 reactionsread 7 August 2026 ፀጉር ቤት ስሄድ ካክስ ውስጥ ከራሴ ጋር የማሳልፈው ግዜ እንዴት ደስ ይለኛል መሰላችሁ።ብዙ ግዜ ስልኬን አልነካካም ከነካሁም ለረጅም ግዜ "ግዜ ሳገኝ አነባችዋለው" ብዬ የሰበሰብኳቸውን ፅሁፎች በፅሞና አነባለሁ።አልያም ቦርሳዬ ውስጥ የማነበውን መፅሀፍ መርጬ ይዤ ሄዳለው አንዴ ካክስ ውስጥ ከገባሁ ቡኃላ ሰው ጮክ ብሎ ካላወራ የሚሉት ስለማይሰማኝ ድምፅ አይረብሸኝም።በተለይም ስራ ከጀመርኩ ቡኃላ መፅሀፍትን የማንበቡ ነገር ትንሽ እየተቀዛቀዘ ስለሆነ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልኛል።ወይም የሚመጡልኝን ሀሳቦች ሳወጣ ሳወርድ ቆንጆ ግዜ ከራሴ ጋር አሳልፋለው።እና ትላንት እዛ ሁኜ ምን እያሰብኩ ነበር መሰላቹ ሁላችንም በተለያየ የህይውት ሩጫ ተከበን ከራሳችን ጋር የምናሳል…
🙏10❤2
Signed Sema yawit
5 Jul 2026, 11:20 UTC266 views12 reactionsread 7 August 2026 ከቤት ወደዚህ እየተመለስኩ ነበር። መኪና ውስጥ ከነበሩ ሰዎች ውስጥ ህፃን ልጅ የያዘች ወጣት ሴት መታመም ጀመረች እና ከአቅሟ በላይ ስለነበር ልጇን እንኳ መያዝ ተሳናት። አበረዋት የተቀመጡት ሁለት ወጣት ወንዶች ያሳይዋት የነበረው ነገር እንዴት እንደገረመኝ።አንዱ ልክ መታመም ስትጀምር ልጇን ተቀበላት ሌላው ፌስታል ያዘላት እና even ሻርፗ ከአናቷ ሲወርድ እያሰተካከሉ ነበር ሲረዷት የነበሩት።ወጣት ናቸው የትም አያውቋትም ግን ለእርሷ ደግ ከመሆነ አልተቆጠቡም።ሰበዓዊነት አሁንም አለ ስንልኮ በምክንያት ነው☺️
እንዴት ናቹህ ግን?
እሁድ 28/10/18
@kebemnetmehader
@kebemnetmehader
❤12
Signed Sema yawit
5 Jun 2026, 12:52 UTC382 views15 reactionsread 7 August 2026 አንተ በምድር ላይ በኖርክበት ዘመን እንደሆነው ሁሉ ዛሬም ብዙዎች ከእጅህ የምትሰጣቸውን ነገር አስልተው በነቂስ ወጥተው ይከተሉሀል፤የሚያገኙት ነገር የጎደለ ከመሰላቸው አልያም በአይበቃኝም ጉርምርምታ ወደ ኃላ ለመመለሰ ሲወስኑ ቅንጣት ታህል ፀፀት አይምሮቸውን አይዳብሰውም።ወትሮም ወዳንተ ያንደረደራቸው ጥቅማቸው ነውና ያን ማያገኙ ከመሰላቸው ክህደት የመጨረሻ ሊያደርጉት የሚችሉት በጣም ቀላሉ ነገር ነው።
እየሱስ ሆይ🥺 ምናልባት እኔም እንደነዚህ ብኩን ሰዎች መጀመርያ ላይ ጥቅሜን አሳድጄ ምንም እንዳይጎድልብኝ ይሆናል የተከተልኩህ፤ምናልባትም ደግሞ በሰማዩም በምድሩም ስኬታማ ለመሆን ትክክለኛ ምርጫዬ ነህ ብዬም አስቤ ይሆን ይሆናል ከኃላህ አዘግም የነበረው።
ዛ…
🥰10❤5
Signed Sema yawit
26 May 2026, 18:16 UTC336 views11 reactionsread 7 August 2026 ቀኑን ሙሉ ሰራ ውላቹ ቤት ስትገቡ ያለው ስሜት😋በተለይ አልጋቹን ስታዩ😎
ማክሰኞ 18/9/18
@kebemnetmehader
@kebemnetmehader
😁8❤3
Signed Sema yawit
21 May 2026, 06:25 UTC388 views10 reactionsread 7 August 2026 ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።
1ቆሮንቶስ 10፥13
@kebemnetmehader
@kebemnetmehader
❤10
Signed Sema yawit
11 May 2026, 19:13 UTC458 views16 reactionsread 7 August 2026 ጠዋት ሁለት ሰዓት የወጣው ሴትዮ ቀኑን ሙሉ ስራ ውዬ ማታ ሁለት ሰዓት ቤት ስገባ የቤቴ መብራት አይሰራም።ብል ባደርግ ብፈጨረጨር ወፍ መፍትሔ።"ጌታ ሆይ በናትህ አብራልኝ" ብዬ ብለምንም እሱም ዝም።ጎረቤት ጠርቼ ባሳይም ወይ ፍንክች!በቃ ነገ አሰራለው ብዬ ልብስ ቀይሬ አልጋዬ ላይ ገደም ከማለቴ ሆዴ አናገረኝ ለካ እራት አልበላሁም።ውይ እራቴን ልብላ ብዬ ስነሳ ለካ እራት የለኝም🤧እራቴን በሻማ የሰራውበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው ጎበዝ!አንዳንዴኮ ሰኔና ሰኞ አይግጠምባቹ( ለካ አሁን ደግሞ ግንቦት ነው😏) ይህን ፅሁፍ እራሱ ፅፌ ጨርሼ copy ላድርገው ብዬ delete ያደረኩበት ሁኔታም ተፈጥሯል።ብቻ ነገሩ ውስብስብ ነው😌 ላጤነት ይለምልም ስላቹ ግን ይህንን ጎኑ…
😁15🫡1
Signed Sema yawit
5 May 2026, 17:44 UTC407 views17 reactionsread 7 August 2026 ዛሬ ጠዋት ክፍት ጫማ አድርጌ ሰበር ሰካ እያልኩ ስራ ገባውላቹ።እንደ ገባው አንድ ጓደኛዬ አተኩሮ አየኝና
"በምኒ በጌታ ይህን ጫማ ሁለተኛ አታርጊ!"
እኔ ደንግጬ
"ምነው ለምን?" አልኩት ምን ቢለኝ ጥሩ ነው
"ሴት ትመስያለሽ"😂
ለካ እስከዛሬ እንደ ወንድሙ ነበር ሲያየኝ የነበረው🤧ትንሽ ቆይቶ የሴት ቀሚሶችን እያሳየውት "ለምን ሱፍ አታሰፊም?ያምርብሻልኮ " አላለም😐
"ሴት የመምሰያ አምስት ነጥቦች" የሚል መፅሀፍ ተፅፎ እንደው ፈልጌ ማንበብ ይኖርብኛል።እንዲህ አይነት ትግል እኮ ነው የገጠመን ወገን😌
@kebemnetmehader
@kebemnetmehader
😁15❤2
Signed Sema yawit
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @kebemnetmehader. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.