4 Aug 2026, 05:06 UTC86 views9 reactionsread 6 August 2026 ውድችዬ...ካስተዋልኩት ላካፍላችሁ...
ለምንድን ነው እልፍ ነውሮችን....እልፍ ልክ ያልሆኑ ተግባሮችን ያለ ሀፍረት እየከወንን ያለን ማህበረሰቦች ..መፈቃቀርን..ናፍቆትን...መተሳሰብን ሰው ፊት ለመከወን ወደ ኋላ የምንለው..የምንሸማቀቀው???
ይሄን ያልኩት ከአንድ ካየሁት ሁነት ተነስቼ ነው....አብረው ሱቅ የሚሰሩ ባለትዳሮችን አይቼ....በየቀኑ እየተጋገዙ ሱቃቸው ውስጥ የሚኖሩ ባለ ትዳሮችን....እና ሰሞኑን ሱቁን ሳስተውል ሰውዬው የለም ነበር...እና ዛሬ ሰፈር ቁጭ ብዬ ከመኪና ሲወርድ አስተዋልኩኝ ከለበሰው አለባበስ ከተማ ውስጥ እንዳልነበረ ተረዳሁኝ....እና ከመኪና እንደወረደ ወደ ሱቅ ገባ....እና የጠበቅኩት ከባለቤቱ ጋር የመተቃቀፍ ሰላምታን …
❤9
Signed 🥇
19 Jul 2026, 16:44 UTC277 views8 reactionsread 6 August 2026 "ለምንድነው ድንገት የተውከኝ አለቺኝ ?"
"እኔ'ንጃ ምን አልባት ፈርቼሽ ይሆናል"።
በአይኗ እየተቅለሰለሰች "ምኔ አስፈራህ ትባ'ላለች አሉህ ወይ "
ጥቁረቷ የዐይኗን ውበት ጨምሮታል ጥቁረቷ ጥርሷን ጥርሰ በረዶ ናት እንድትባል ያደረጋት ይመስለኛል።
ስታምር !
ትክ ብዬ እያየኋት
"የመወደድ ርኃብ ያለብሽ ይመስላል "አልኳት
ምን ማለት ነው ??
"የሚወደኝ አጥቼ ማለት ነው? " ሳቀች አሳሳቋ ፌዝ አዝሏል
አይምሰልሽ
የአንዳንድ ርሃብ ምንጭ እኮ የአቅርቦት እጥረት አይደለም የአስተዳደግ ጠባሳም ሊሆን ይችላል።
ቀጠሮ ኖርበት የክት ልብሱን አጥቦ ፀሃይን እንደሚጠብቅ ሰው ነው ቀልብሽ ቆሌሽ ሁሉ ነገርሽ መ…
👍6❤2
Signed 🥇
29 Jun 2026, 03:42 UTC371 views9 reactionsread 6 August 2026 ሰው እየሰጠመ እያያችሁት ፤ ዋና የማስተማሪያው ጊዜ እንዳልሆነ መቼም ትረዳላችሁ ።
አንዳንዴ ለመምከር ራሱ ተገቢ ጊዜ ነው ወይ ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ ።
የምትመክሩ ሰዎች ተመከሩ።
©ሶፊ
❤7💯2
Signed 🥇
22 Jun 2026, 05:55 UTC450 views12 reactionsread 6 August 2026 ህይወት በጣም ደስ ትላለች........
በዙሪያችሁ ያለ ምክንያት የሚወዷችሁ፣ምንም ሳታደርጉ መኖራችሁ ብቻ የሚያስደስታቸው ሰዎች ካላችሁ!
ብታጠፉ ፣ብትወድቁ፣ ብታዝኑ ከጎናችሁ የማይለዩ፣ ጥንካሬያችሁን ያለመታከት በየሰከንዱ የሚነግሯችሁ...ደከመኝ ስትሉ ማረፊያ የሚሆኑ....ወደኩኝ ስትሉ እጃቸውን የሚያቀብሏችሁ ድንቅ ሰዎች ካላችሁ.......
ከእንቅልፋችሁ ተቀስቅሳችሁ የእናታችሁን የሚጣፍጥ ቁርስ ደስስ ከሚል ጭቅጭቋ ጋር ከበላችሁ......
ከወንድማችሁ ጋር በውሀ ቀጠነ እየተጨቃጨቃችሁ ቤቱን በአንድ እግሩ ካቆማችሁ....
አይኖች ሁሉ በስስት ወደ እናንተ እየተመለከፈቱ ወፈረች፣ጠቆረች፣ከሳች ከተባለላችሁ.......
ካፋችሁ የሚወጣው ቃል በአፅኖት ከተ…
❤10🥰2
Signed 🥇
30 May 2026, 08:35 UTC506 views7 reactionsread 6 August 2026 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
⭐️⚡️⭐️⭐️⚡️⭐️⭐️⭐️✨⭐️
የሚቻል መስሎት አጉል ያለመ፣
ፀሀዩአን በጣት ሊጋርድ ቆመ።
ውበቷን አይሽር፣ጥቅሟን አይቆርሰው፣
ፀሀይ የለችም ቢልም እውር ሰው
እፍ ሲል ቢውል ሊያጠፋት ወዶ
የሻማ ልምዱን ፀሀይ ላይ ወስዶ
ትል ታይቶ አያውቅም ተራራን ንዶ
የማይሆን ላይሆን ትርፉ ነው ባዶ።
ማር የመረረው ነክቶ ሲቀምሰው፣
ከንብ ይጣላል እንኳንስ ከሰው።
❤6👏1
Signed 🥇
25 May 2026, 08:24 UTC≈1,940 views11 reactionsread 6 August 2026 እናት
ማስመሰል የማያውቃት፣ማጣት የማይበግራት፣ማግኘት የማይሸነግላት፣ችግር የማያጎብጣት፣መከራ የማያሸንፋት.........እውነተኛ ወዳጅ፣እየከፋት የምትስቅ ፣እየራባት የምትለግስ፣እየሞተች የምታኖር ....የዚች ምድር ውቧ ገፅታ ....የእውነተ ፍቅር የእውነት መውደድ ምሳሌ እናት ብቻ!!!!
በዚህ አለም ላይ ከተባረኳቸው እና ከማመሰግናቸው ነገሮች ውስጥ አንቺ ዋነኛዋ ነሽ!!!
እናትነት ምርጫ ቢሆን ኖሮ ደግሜ ሳላስብ አንቺን ብቻ ደጋግሜ እመርጥሻለሁ.......ዳግመኛ ብወለድ ያንቺ ልጅ ብቻ መሆንን እፈልጋለሁ
....
አንቺ መኩሪያዬ ነሽ፣የሷ ልጅ ናት ስባል የሚሰማኝ ውርር የሚያደርግ ደስታ ለኩራቴ ምስክር ነው!!!
ጠይቄሽ ያላደረግሽልኝ፣አማክሬሽ ያልፈፀም…
❤8🥰3
Signed 🥇
20 May 2026, 11:46 UTC509 views12 reactionsread 6 August 2026 Photo
This is a photo one of my friend sent me 😂
Honestly, I didn’t expect you guys to be this happy 😂.............
ብቻ we did it💪💪
እንኳን ደስ አለን!!!
❤11😁1
Signed 🥇
17 May 2026, 18:58 UTC≈2,040 views14 reactionsread 6 August 2026 አንዳንዴ የተከፈለላችሁ የተሆነላችሁ ተስፋ እንዳትቆርጡ ምክንያት ይሆናችኋል፣ደክሟችሁ ስትወላገዱ እጃችሁን ይዞ ይመራችኋል!!!..........
መውደቅ ፣ተስፋ መቁረጥ እና መድከም ለእኛ አልተፈጠረም፣ሁሉም መንገድ አልጋበአልጋ አልነበረም.....የመጣነው በኩርንችች መንገድ ቢሆንም እስከአሁን እጅ አልሰጠንም ምክንያቱም በእሾህ መንገድ ተጉዘው ያደረሱን እግሮች እኛ ስለሚጠብቁን ነው!!!!
ዛሬ እነሱ በብዙ እሾህ ቁስሎች እና ደሞች ተሞልተው እየደከሙ እና እያቃታቸው ነው!ሳይወድቁ በፊት ልናሳርፋቸው ግድ ስለሚለን ሁሉንም ረስተን፣ሁሉንም በጫንቃችን ተሸክመን በጥንካሬ እንጓዛለን!!!
አዎ እኛ እንደዛ ነን....ህመምን ለማሽሞንሞን፣ማጣትን ለማቅበጥ አልታደልንም..…
❤10🥰4
Signed 🥇
17 May 2026, 17:57 UTC427 views5 reactionsread 6 August 2026 Photo
🥰አሁን ይሄ ምን ይባላል?🙊 ሶፊ
🤔4🥰1
Signed 🥇
14 May 2026, 13:07 UTC441 views8 reactionsread 6 August 2026 ለካ ሰውን እብድ የሚያሰኘው እብድ የሚያደርገውን ማድረግ አይደለም፣እብድ የሚያደርገውን ሲያደርጉ መታየቱ ነው!
ፍቅር እሰከ መቃብር
ቀን:06/09/2018
❤5😁3
Signed 🥇
10 May 2026, 13:11 UTC655 views18 reactionsread 6 August 2026 🎴ከብዙ ዓመታት በፊት ትንሹ ወንድሜ የክረምት ትምህርት ሲማር በዝናብ ተደብድቦ ከልብሱ ላይ ውኃው እየተንጠባጠበና እየተንቀጠቀጠ መጣ። እንደዚያ በስብሶ ቤት ሲገባ ሁላችንም አፍጥጠን አየነው።
እኔ ፣ "አንተ ደደብ! ዝናቡ እስኪያባራ ድረስ ጠብቀህ አትመጣም ነበር?" አልኩት።
🎴እህቴ ፣ "አንተ ጅላንፎ! ክረምት መሆኑን እያወቅህ ወፍራም ሹራብ ለብሰህ አትሄድም ነበር?" አለችው።
ሌላዋ እህቴ፣ "አንተ የማትረባ ትንሿን ጃንጥላ ይዘህ ሂድ ብዬህ አልነበር?"
🎴አባቴ ፣ "አንተ ልጅ! ሰው የሚልህን አትሰማም ማለት ነው? ሁልጊዜ መንገድ ላይ ዝናብ ሲይዝህ ዝናቡ እስኪያባራ ጓደኞችህ ቤት ቆይተህ እንድትመጣ ነግሬህ አልነበር?"
እማዬ ግን ቀስ ብላ ወደ ደረቷ …
❤12🥰6
Signed 🥇
5 May 2026, 12:24 UTC525 views8 reactionsread 6 August 2026 ✨✨
አዎ አናውቀውም እንጂ ሰው ማለት እኮ የትዝታው እና የትውስታው ድምር ነው.......ህይወት የመርሳትና የማስታወስ ሚዛን ናት.......መርሳት ያለብንን መርሳት ሲያቅተንም ህይወታችን ይመሳቀላል....እሱም ህመም ሊሆን ይችላል።
ደግሞ ማስታወስ ያለብንን የህይወት ልምዶች ጠቃሚ ሰዎችና ነገሮች ከረሳን፣የእኛነታችን መለያ የስብእናችን ድንበር ይጠፋና እንዳልሽው ሌላ ሰው እንሆናለን!!!
📚ሌላ ሰው📖
❤7👍1
Signed 🥇
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @ke_temir_gar. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.