16 Dec 2025, 12:35 UTC830 views31 reactionsread 8 August 2026 ነጭ ልብስ "ከታላቁ መከራ የመጡ" ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ያነጹ የሰማዕታት መገለጫ ነው። [ራዕ 7፥14] በመከራ ውስጥ ነጭ መልበስ በጭቆና ፊት በፍጹም እምነት መቆም ነው።
“ይህ የምንዘምርበት ጊዜ አይደለም” የሚለው አባባል መንፈሳዊ ብልህነት የጎደለውና የሰማዕታትን ቅዱስ ታሪክ የዘነጋ ነው። በመከራ ፊት ዝማሬን ማቅረብ የክርስትና ዋና መገለጫው እንጂ ስህተቱ አይደለም!
ከመጀመሪያው የክርስትና ዘመን ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን ለስደትና ለጭቆና የምትሰጠው ምላሽ ሐዘንና ተስፋ መቁረጥ አልነበረም። መዝሙርን ማቆም ማለት “ከዓለም በመጣው በዚህ ትግል ተሸነፍኩ” ብሎ ለጠላት ፈቃድ ራስን አሳልፎ መስጠት ነው። የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን ይኽ…
❤28🔥3
13 Dec 2025, 15:59 UTC695 views14 reactionsread 8 August 2026 Photo
አማኒያንም ኤቲስቶችም ለዚህ ውይይት ተጠርታችኋል!
"እግዚአብሔር አለ ብሎ ማመን ሞኝነት ነው" ብለው የሚናገሩ athiests በሃልዎተ እግዚአብሔር ላይ ከሚያነሷቸው ሙግቶች ውስጥ ዋነኛው[ problem of evil] ወይም "እግዚአብሔር የእውነት ካለ የምናያቸው መጥፎ ነገሮች ለምን ኖሩ" የሚል ነው።
ለዚህ ጥያቄ ፍልስፍናዊ እና ክርስቲያናዊ መልሶች ከክርስቲያን አቃቢያነ እምነት ቀርበዋል። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ነገ ከ11:30 ጀምሮ ይኽ እና ተያያዥ ጥያቄዎች በጥልቀት ይመለሳሉ።
AAU የምትማሩም የማትማሩም አማኒያንም ኤቲስቶችም ተጋብዛችኋል።
❤10🔥3👍1
13 Dec 2025, 15:33 UTC486 views9 reactionsread 8 August 2026 Forwarded from @Theo_Sophia_apology
ተፈጥሯዊ ኢ-ነገረ መለኮት (NATURAL ATHEOLOGY ) ሲባል ሰምታቹ ከሆነ በእግዚአብሔር ማመን ኢ አመክንዮአዊ መሆኑን ምክንያትን ተጠቅሞ ለማሳየት የሚሞክር አንድ ዘርፍ ነው ። በዚህ ውስጥ ደግሞ በጣም በብዛት የሚነሳው ነገረ እኩይ(problem of evil) ነው። እግዚአብሔር ካለ ይህ ሁሉ የምናየው ክፋት እና ስቃይ ለምን ይኖራል የሚል ነው። ለዚህ ደግሞ ብዙ ፍልስፍናዊና ክርስቲያናዊ መልሶችን ከክርስቲያን ሊቃውንት እና ፈላስፎች ይሰጣል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ነገ ከ 11 30 ጀምሮ በጥልቀት ለማየት እንሞክራለን አትቅሩ። በተለይ AAU ያላቹ ልጆችህ ሁላቹም አማኒውም ኢ አማኒውም አትቅሩ(ለማስታወስ ያክል ነው።)
❤7👍2
9 Dec 2025, 12:11 UTC667 views12 reactionsread 8 August 2026 የሃይማኖት ምንጭ የእግዚአብሔር የራሱ መገለጥ (Revelation) እንጂ የሰው ልጅ አእምሯዊ ፍለጋ ወይም ልፋት አይደለም። ይሕ በምሥራቅ ንፍቀ ክበብ ለኖሩ ቅዱሣን አበው የነገረ እውቀት[epistomology] መሰረት ነው።
እምነት የሰውን አእምሮ የሚመጥን ንድፈ ሐሳብ ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ እና ከፍ ያለ ልምምድ ነው።
እግዚአብሔር ራሱን ለፍጥረቱ የገለጠበት መንገድ "ሃይማኖት" ነው። መዝሙረኛው "እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ እርሱም በላያችን ላይ አበራ" መዝ 118:27 በማለት እንደሚመሰክረው እምነት የሚጀምረው ሰው እግዚአብሔርን ከመፈለጉ ሳይሆን እግዚአብሔር ብርሃኑን በሰው ልጆች ላይ እንዲበራ ከመፍቀዱ ነው።
ይህ ብርሃን ድኅረ ውድቀት[p…
❤7🔥4👍1
8 Dec 2025, 11:31 UTC500 views28 reactionsread 8 August 2026 የዳቦ ጥያቄውን ላልመለሰ ሰው ስለ ሞራል ማሰብ ቅንጦት ነው። የራበው ሰው ዳቦ ስጠው እንጂ ተንከባለል ብትለው ይንከባለላል። ግራ የገባው ሰው ተስፋ ስጠው እንጂ አዲስ አምላክ ብታስተዋውቀው ይቀበለዋል።
ፕሮቴስታንቲዝም ከምስረታው ጀምሮ ስልት አልቀየረም። ማሕበራዊ ቀውስ ያለባቸው አከባቢዎች ላይ ኢየሱስን እና ዳቦን ይዞ ይቀርባል። ዳቦውን ሊቀበል የመጣ "ኢየሱስ"ን እንዲቀበል ይገደዳል። Tied selling ተብሎ የሚታወቀው ኢ-ሞራላዊ የmarketing concept በሐይማኖታዊ versionኡ ሲሆን protestantismን ይመስላል።
ለዚህ ድፍን የአፍሪካ ታሪክ ምስክር ነው።
እኔን ጎንደር!
❤18😢5💔3👍2
6 Dec 2025, 10:02 UTC558 views15 reactionsread 8 August 2026 Photo
ቅዱስ ኒኮላዎስ[የገና አባት] "patara" ተብላ በምትጠራው አከባቢ (አሁን የ turkey ግዛት ነች) በ 270 ዓ.ም ከ ጌታ ልደት በኋላ የተወለደ አባት ነው። Myra ተብላ በምትጠራው የ ቱርክ ግዛት ውስጥ ሊቀ ካህን ሆኖ እያስተማረ ኖሯል።
በኖረበት ዘመን እርዳታውን ለሚፈልጉ በሙሉ ያለ መታከት መልካምነትን ሲያደርግ ኖሯል። ብዙ ተዓምራትን እና ደግነቶችን ሲያደርግ የኖረ ሥለሆነ "ገባሬ መንክራት" ይባላል። የታመሙትን መፈወስ እና የተራቡትን ማብላት የሚታወቅባቸው ሥራዎቹ ነበሩ።
በተጨማሪም ሃይማኖትን ጠብቀው አርዮስን በኒቅያ ጉባኤ ካወገዙ 317ቱ ሊቃውንት አባቶች ጋር በጉባኤው የተሳተፈ አባት ነው።
December 6 ቀን በሶሪያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ…
❤15
23 Nov 2025, 04:24 UTC779 views17 reactionsread 8 August 2026 "መጽሐፍ ቅዱስ ነገረ ሃይማኖታዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ ባለ ሥልጣን አይደለም" የሚለው ሐሳብ ከላይ ሲታይ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተሰነዘረ ትችት ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ሐሳቡ የመጽሐፉን መለኮታዊ ሥልጣን የሚያሳንስ አይደለም። እየተባለ ያለውን በቅንነት መረዳት ከብዙ መወዛገቦች ያድናል።
ከታች ያሉትን ነጥቦች በጥንቃቄ ተከታትሎ የሚገጣጥማቸው ሰው ሙሉ ምስሉን ያያል!
1 መጽሐፍ ቅዱስ ከሰማይ የወደቀ ጥራዝ አይደለም።ይልቁኑም ፍጹም ባልሆነ ደግሞም ባልተቋረጠ advancement progress ውስጥ በሚያልፍ የሰዎች ቋንቋ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ነው። የጸሐፊዎቹ ሰብዓዊ ገደብ እንደ failure ሊታይ አይገባም።
2 መጽሐፍ ቅዱስ ሲጠና condescen…
❤11🔥6
22 Nov 2025, 17:24 UTC596 views14 reactionsread 8 August 2026 የመጽሐፍ ቅዱስን አለመሳሳት [inerrancy of bible]ን በተመለከተ የሚሰጠው ማብራሪያ የቅዱሳት መጻሕፍትን ሥልጣን ለአስተምህሯዊ ዓላማ [Didactic Purpose] በመገደብ ይጀመራል።
መጽሐፍ ቅዱስ በድኅነትና በሥነ-ምግባር (Soteriology and Ethics) ጉዳዮች ላይ ፍጹም እና ባለሥልጣን ሲሆን ነገረ ሃይማኖታዊ ባልሆኑ (Non-Theological) ጉዳዮች ላይ ግን በጸሐፊዎቹ ሰብአዊ ገደብ ምክንያት ስህተቶች ሊኖሩበት ይችላሉ።
መጽሐፍ ቅዱስ በመለኮታዊ አነሳሽነት [Divine Inspiration] የተጻፈ ቢሆንም ለጸሐፊዎቹ ነገረ ሃይማኖትን የገለጸ የእግዚአብሔር መንፈስ ጸሐፊዎቹን ከዘመናቸው አውጥቶ በኛ ዘመን ሳይንሳዊ ትክክለኛነት [Sci…
❤14
22 Nov 2025, 14:53 UTC563 views7 reactionsread 8 August 2026 ነገረ ሃይማኖትን የማይመለከቱ እውቀታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከመጽሐፍ ቅዱስ ልናገኝ የምንችለው የጸሐፊዎቹን የተገደበ መረዳት ብቻ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈበት ዘመን የተሻለ መልክዐምድራዊ እውቀት ፣ የሕክምና ጥበብ ፣ የአስትሮኖሚ ልኅቀት በኛ ዘመን አለ። ስለ ምድር ክብነት እና ጠፍጣፋነት ጥያቄ የተፈጠረበት ሰው ቢኖር ከዘፍጥረት መጽሐፍ የተሻለ ተጨባጭ እውቀትን ከ7ኛ ክፍል የgeography መጽሐፍ ማግኘት ይችላል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ ንባቦች ውስጥ አንድ ክርስቲያን እንዲቀበል የሚገደደው ነገረ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን ብቻ ነው። ከዚያ ውጪ ላሉት ጉዳዮች መጽሐፍ ቅዱስ ባለ ሥልጣን ምስክር ሆኖ መቅረብ አይችልም።
🔥5🤔2
21 Nov 2025, 06:17 UTC≈1,050 views15 reactionsread 8 August 2026 መላዕክትን የሚያጸናው መልዓክ
ነቢዩ ዳንኤል ለ ሶስት ሱባዔ በ ጾም እና በብዙ ጸሎት ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጥያቄውን አቀረበ ። ጸሎትን የሚመልስ እግዚአብሔርም የሱባዔውን መልስ በ መልዓኩ እጅ ወደ ባርያው ወደ ዳንኤል ላከ።
"ፊቱ እንደ መብረቅ አይኖቹም እንደ ነበልባል ፋና" የሚያበሩለትን የዛን መልዓክ ግርማ ባየ ጊዜ ዳንኤል ጸንቶ መቆምን አልቻለም ከመልዓኩ ግርማ የተነሳ ምንም ሃይል አልቀረለትም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፋ
ብርሃናዊው መልዓክ እጁን ልኮ በዳሰሰው ጊዜ ዳንኤል ሃይልን አጊኝቶ ቀጥ ብሎ ቆመ "በርታ ጽና" ብሎ መልዓኩ በስልጣን ተናግሮታልና ዳንዔል በረታ ጸናም።
ዳንኤልን ያበረታው ሌላ መልዓክ አለቃው ስለ ሚሆን ስለ ቅዱስ ሚካኤል…
❤15
17 Nov 2025, 05:38 UTC646 views11 reactionsread 8 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
❤10🥰1
16 Nov 2025, 08:14 UTC736 views18 reactionsread 8 August 2026 እግዚአብሔርን አናውቀውም...
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ያልጻፈው ምን አለ? በቅኔያዊ ውበታቸው ዛሬም ድረስ ተወዳዳሪ የሌላቸውን እነዚያን ድንቅ መጻሕፍት የጻፈው ቅዱስ የጌታን ክብር ባሰበ ጊዜ ግን "ገናንነቱን መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል።" ይላል።
ቅዱስ ኤፍሬምን ያኽል ባለቅኔ "ልናገረው አልችልም" ያለለት ክብር እንዴት ያለ ነው? ብዙ የውዳሴ ቃላት በፊቱ እንደ ዝምታ የሆኑለትን የእርሱን ክብር የሚመረምር ማነው?
“እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም።” የሚለው የኤሊሁ ምስክርነት የታመነ ነው።
❤18
Showing the 12 most recent of 14 posts we hold for @kale_amen. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.