4 Jul 2026, 23:19 UTC35 views1 reactionsread 9 August 2026 ጥበበኛ ሴት ማን ናት? ከብዙ በጥቂቱ ላብራራላችሁ፦
ጥበበኛ ሴት በትዳርም ሆነ በፍቅር ጉዞ ውስጥ የአጋሯ እኩል አጋዥ ናት። በመንፈስ፣ በዕውቀት፣ በጥበብ፣ በአካልና በሥነ-ምግባር እርስ በርስ ለመደጋገፍ ራሷን ያዘጋጀች የሕይወት ስጦታ ናት። ወንዶች የቤቱ ግንበኛና ደጋፊ ምሰሶዎች ሲሆኑ፣ ሴቶች ደግሞ ያንን ቤት በቅንነትና በብልሃት የሚያቆሙ መሃንዲሶች ናቸው።
ብልህ ሴት የቃላትን ኃይል ታውቃለች፤ መቼ መናገር፣ መቼ ማዳመጥና መቼ በዝምታ መረዳት እንዳለባት አርቃ ታስተውላለች። የአጋሯን ሕልምና ዕቅድ የምታጋራ፣ የስኬቱ ተካፋይ ናት። ባሏን በፍጹም ልቧ ትወዳለች፣ ታከብረዋለች፣ ትንከባከበዋለች፤ሰላምን ትሰጠዋለች። በጭንቀቱ ጊዜ ጭንቅላቱን በእጆቿ ደግፋ የም…
❤1
4 Jul 2026, 23:19 UTC33 viewsread 9 August 2026 Photo
ጥበበኛ ሴት ማናት
✍ጀማሪ ሀሳብ📝
30 Jun 2026, 12:36 UTC47 viewsread 9 August 2026 አዲስ የተከራየሁበት ቤት የመጀመርያው አዳሬ ጥሩ አልነበረም ቀኑን ቤቴን ሳስተካክል ደክሞኝ ገና ፍራሼ ላይ ጋደም እንዳልኩ አንዳች ድምፅ ወደ ጆሮዬ መጣ ፂጥ ፂጥ የሚል ድምፅ ያለ እረፍት ይሰማኛል ነገርየው ቶሎ ያቆማል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር ነገር ግን እየባሰ መጣ እንቅልፍ ዘበት ሆነ እንዳፈጠጥኩ ነጋና ጠዋት ወደ ስራዬ ልወጣ መሬን እየዘጋው ሌላኛዋ ተከራይ ጎረቤቴ የለሊት ልብሷን ለብሳ ጭኗን ገልጣ ብቅ አለች ዞር ስል እየተንጠራራች ነው መንጠራራቷ ግን የምር አይመስልም የለበጣ ነገር ነው ገና እንዳየችኝ....
እንዴት አደርክ እንግዳው ብላ የበሯ መቃን ላይ ደገፍ አለች
ደህና ነኝ ግን ለሊቱን አንድ ነገር ሲረብሸኝ አደረ የሆነ ፂጥ ፂጥ የሚል ነገር …
30 Jun 2026, 12:36 UTC30 viewsread 9 August 2026 Photo
እንደ ጎረቤት🙌
✍ጀማሪ ሀሳብ📝
23 Jun 2026, 19:16 UTC42 viewsread 9 August 2026 እኔን እንደልጅሽ አታዪኝም ልጆችሽ ማክቤልና ሮቤል ናቸው ብዬ ነብሷን ይማርና እናቴ እንዳስተማረቺኝ ኪዳነምህረትን ሄጄ ተነጫነጭኩባት.. መብቴ ነዋ እንደውም እያያ ከመሞቷ በፊት ቤተ ክርስትያን ሄጄ በሆነ ምክንያት ሳለቅስ ሰወች ይቆጡኛል እዚህ አይለቀስም ይሉኛል እያያ ግን አትቆጣኝም ነበር እንደውም መብትህ ነው አልቅስ እዚህ እናትህ ቤት ያላለቀስክ የት ሄደህ ልታለቅስ ነው??እነሱኮ ለቅሷቸውን ጨርሰው ነው ትለኝ ነበር...እውነቷን ነው ከኪዳነምህረት ውጪ የት ይለቀሳል??የትም!! ከዛ ወዲህ ኪዳነምህረት ስር መጥቶ ማልቀስን መነጫነጭን እንደመብቴ ነው ማየው . ለዚህ ነው ገና በሁለተኛው ፔሬድ ረሀብ ሲያንቆራጥጠኝ ትምህርቱን ጥዬ ወጥቼ ኪዳነምህረት ጋ ሄጄ የተ…
23 Jun 2026, 19:16 UTC30 viewsread 9 August 2026 Photo
ለካ አትወጂኝም🥺
3 Jun 2026, 08:19 UTC57 views2 reactionsread 9 August 2026 ፍቅሬ ሰሚራ የመጨረሻ ክፍል
ሰሚራ ያጋጠማትን ነገር ከሰማሁ በኋላ ለሊቱን ሙሉ ማልቀስ አቁሜ መተኛት አልቻልኩም ነበር። ቆይ ሰሚራዬን ምን ነካት?? ምን አገኛት?? ለምን?? እነዚህን ጥያቄዎች እራሴን እየጠየኩ ለሊቱ ነጋ። ካረፍኩበት ሆቴል በጠዋት ወጥቼ ትናንት ሰሚራን ወዳየሁባት አዲሰ አበባንም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደረገጥኩባት መናሀሪያ ተመልሼ ሄድኩኝ፣ እንደደረስኩ ያገኘሁትን ሰው በሙሉ ሰሚራን ያውቋት እንደሆን መጠየቅ ጀመርኩ...
አይ አላቃትም፣ ይቅርታ አባባ አላቃትም፣ እንደዛ ሚባል ሰው ብዙ አለ የትኛዋን እንደሆነ አላወኳትም..( የጠየኳቸው ሰዎች ሁሉ አላወቋትም ነበር) ተስፋ መቁረጥ ግን አልቻልኩም...ድንገት ትላንት ያደረሰኝን የታክሲ ረዳት አየሁ…
❤2
1 Jun 2026, 16:58 UTC42 views1 reactionsread 9 August 2026 ፍቅሬ ሰሚራ ክፍል 10
ዛሬ የእመቤታች ዋዜማ ስለሆነ የደብረ እንቁ በዋዜማው አሸብርቃለች።ጊዜ ይሮጣል...አመቱ እየገሰገሰ ያረጀሁ ያረጀሁ እየመሠለኝ ነው።አሸልቤ በነቃሁ ቁጥር ዘመን እያመለጠ ያህል ይሰማኛል።ደብረ እንቁ ከአመታት ወዲህ ብዙ ነገር ተቀይሯል፤አንዳንዴ የተማሪነት ትዝታዬን ዳገቱ አፋፍ ላይ እየኮመኮምኩ ከሩቅ አሻግሬ የየንታን እና
የእማሆይ ጨርቆሴን መቃብር ሳየው የጊዜው መሮጥ ይገርመኛል።እነሱን አረፍተ ዘመን ሲገታቸው እኛ ደሞ ወደማይቀረው ጎልማሳነት እየሄድን ነው...
አንቱ አሁንማ አረጁኮ..(ይለኛል ጦቢት ከዋዜማ እንደተመለስን የመለኩሴ ቆቡን አውልቆ ሉጫ ፀጉሩን እየደባበሰ
አሄሄ መልዐከ ፀሀይ እርሶስ ቢሆኑ ያ የልጅነት ጊዜ ቀርቶ....…
❤1
1 Jun 2026, 05:43 UTC32 views5 reactionsread 9 August 2026 Forwarded from @ayasekemPhoto
ፆም ገብቶ የለ??በጠዋት ተነስቼ ወደ ስራ ልሄድ በሬን እንደከፈትኩ ያበደ እንቁላል ሸተተኝና በሬ ላይ ቆሜ እያማተርኩ እማማ ታደሉ ከቤታቸው ብቅ አሉ ይኼኔ የእንቁላሉ ሽታ በደንብ ወደ አፊንጫዬ ሲመጣ ባነንኩኝና ወደ እማማ ታደሉ እያፈጠጥኩ...
እማማ ታደሉ እንቁላል እየሰሩ ነው እንዴ??አልኳቸው በመገረም እያየኋቸው ያው ልጆቻቸውን ሁሉ በማጣታቸው ምክንያት ወሰድ እንደሚያደርጋቸውኮ አውቃለሁ ደሞ ጨዋታ አዋቂ ናቸው ግን ዛሬ እፍርር ብለው "አዎ"አሉ
ምነው እማማ ታደሉ በፆሙ እንዴት እንዲህ ያደርጋሉ???አልኳቸው እንደገና ፈርጠም ብዬ እሳቸውም መለስ ብለው
ማታ ልበላው ገዝቼ መብራቱ ጠፍቶ አደረ በኋላ አሁን ስነሳ አሳዘነኝና ጠብሼ ልበላው ነው እንዳልከስር…
❤3🥰2
31 May 2026, 16:37 UTC29 views4 reactionsread 9 August 2026 ፍቅሬ ሰሚራ ክፍል 9
እንደውም እሰልማለሁ!!ከልጅነት የጣለኝን፤ እናት አባት የነፈገኝን፤ በጨቅላነቴ በረሀብ እና በብርድ የቀጣኝን
እግዜር ምበቀለው አሁን ነው!!ለሱ ብዬማ ሰሚራን አላጣትም!!እሷ ያመነችውን አላህ አምኜ ከሷ ጋ ኖራለሁ።የወደድኩትን ለመኖር ያፈቀርኩትን ለማግኘት.. (በውስጤ እየተንሾካሾኩ እያጠብኳት የነበረችው ሲኒ መሬት ላይ "ጧ" ስትል ከሀሳቤ ባነንኩ
ቀድሼ እንደወጣሁ ጨለምለም ሲል ነበር ደብረ እንቁን ለቅቄ የወጣሁት።ያደኩባት ገዳም፤ ያስተማሩኝ የኔታ፤ ጉባኤቤቱ፤ እነ ጦቢት ሳይቀሩ ከሰሚራ ጋ በልቤ ሊወዳደሩ አልቻሉም።አፈቅራታለሁ።ሀይማኖቷ እንደያዛት እንጂ እሷም እንደምታፈቅረኝ ነግራኛለች።ታድያ ሊቀጳጳሱን ተከትዬ አዲስ አበባ ብገባ ሰሚ…
💔2❤1😢1
29 May 2026, 14:32 UTC40 views1 reactionsread 9 August 2026 ፍቅሬ ሰሚራ ክፍል 8
ጦቢቴ ተሻለህ??(እማሆይ ጨርቆሴ ቤት ሹክክ ብዬ እየገባሁ
ውይ ስቡህ መጣህ ልጄ? ግባማ አረፍ በል.. አይዞህ አሁን በጎ ሆኗል።ወደ አገልግሎቱም ይመለሳል
እማሆይ ጨርቆሴ የቆጥ የባጡን ሲያወሩ ጦቢት ትንፍሽ አላለም።ቅሬታው ፊቱ ላይ ይነበባል ባያየኝ ደስ እንደሚለው ለማሳወቅ ነው መሰል ገና ፊቴን ሲያየው ነው ጀርባውን ሰጥቶኝ የተኛው።እርግጥ ትክክል ነው የማልችለው ነገር ሆኖ እንጂ ሰሚራ እንደማትሆነኝ እርግጥ ነው።በህግም በህሊናም ከሀይማኖት ውጪ መጋባት አይፈቀድም፡፡እሷም እያፈቀረቺኝ ይህንን መመለስ የማልችለውን ጥያቄ አሸክማ እንደላከቺኝ ማን በነገረው??
እማሆዬ ህመሙ ግና ምንድነው??(ጦቢት እስኪበርድለት ከእማሆይ ጋ ቀደዳዬን …
❤1
28 May 2026, 16:58 UTC33 views0 reactionsread 9 August 2026 ፍቅሬ ሰሚራ ክፍል 7
....ወዴት እየሄድኩ ነው??አንድ ቆሎ ትምህርት ቤት እግዚአብሔርን ከየኔታ አፍ ሲሸመድድ ያደገ፤ዳዊት የደገመ፤ቅዳሴ የቀደሰ፤ሰአታት ያዜመ፤ማህሌት የቆመ ዲያቆን እንዴት መስጂድ ይሄዳል??ልብሰ ተክህኖ ለብሼ ጧፍ እያበራሁ አሐዱ አብ ያልኩትን እግዚአብሔርን ክጄ ለአንዲት ሴት ስል መስጂድ ልገባ ነው??እግዜሩ ምን ይለኛል??የንታስ ቢሰሙ?ምድረ ኩታራ ተሜ ቢያቅብኝስ...??
ጭንቅላቴ ውስጥ አለም ዘጠና ዘጠኝ ሆናለች። ከኪዳን መልስ የጦቢትን ደህንነት አረጋግጩ የደብረ እንቁን ተራራ ቁልቁል እየወረድኩ እንደማልመለስባት ያህል ሆዴ እየተሸበረ መንፈሴ እየታወከ ነው።ፍቅር የምንፈልገውን ሳይሆን የማንፈልገውን፤የምንችለውን ብቻ ሳይሆን የማንችለ…
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @jemarihasab. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.