2 Nov 2022, 04:34 UTC≈6,080 views15 reactionsread 7 August 2026 Photo
#ተላላፊያልሆኑህመሞች አሉብዎ? እይታዎችዎን ያካፍሉ፣ እርምጃ ይውሰዱ እና ለውጡን ይምሩ። የ #ተላላፊያልሆኑህመሞችድምፆች @AfricaNCDsNet አካል ይሁኑ።
ስለእርስዎ ምንም ነገር የለም ያለርስዎ።
Do you have an #NCD? Share your views, take action & drive change. Be part of #NCDVoices @AfricaNCDsNet.
Nothing about you without you.
ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ይሳተፉ!
Get involved!
📌 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdDjjWYKAvBDlUHwFXFk_KrnvlcHl7aMO1CM1Mv1ptS4TBuMw/viewform
👍14❤1
27 Oct 2022, 16:42 UTC≈4,320 views47 reactionsread 7 August 2026 የክሮንስና ኮላይተስ ኢትዮጵያ መስራች ዶ/ር ፋሲካ ሽመልስ በዘ-ጋርዲያን አለምአቀፍ መፅሄት
የዶ/ር ፋሲካ ለብዙዎቻችን፣ በተለይም በክሮንስና ኮላይተስ ህመም ውስጥ ላለን ሁሉ ምሳሌ የሚሆን ታሪኳ የዘ-ጋርዲያን መፅሄት ላይ ሰፍሯል።
ዶ/ር ፋሲካ በድርጅታችን ዉስጥ ስላለሽ ቀዳሚ የመሪነት ሚናና እያደረግሽው ስላለው አስተዋፆ እናመሰግንሻለን።
ኮርተንብሻል!!!
https://www.theguardian.com/global-development/2022/oct/27/doctor-fasika-teferra-superpower-hope-crohns-ethiopia-acc
Crohn's and colitis Ethiopia 🇪🇹
ክሮንስና ኮላይተስ ኢትዮጵያ 🇪🇹
❤36👏7👍4
12 Oct 2022, 16:13 UTC≈2,930 views3 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @tikvahethmagazine
#ጤናረቡዕ
ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ-5
☑️የተለያዩ ስር የሰደዱ ህመሞች መድሃኒቶችና የስነ-ተዋልዶ ጤና
👉 ስር የሰደዱ ህመሞች አይነት እጅግ በርካታ እንደመሆኑ ለህመሞቹ የሚታዘዙ መድሃኒቶችም አይነት፣ ተግባር፣ የደም ውስጥ ስርጭትና የጎንዮሽ ጉዳትም በዛው ልክ እጅግ ሰፊና የተለያየ ነው፡፡
በዚህ ርዕስ ስር፤ ስር ለሰደዱ ህመሞች ከሚታዘዙ መድሃኒቶችና የስነ ተዋልዶ ጤና ተጽዕኖዎቻቸው ውስጥ የከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብና ከደም ጋር ለተያያዙ ችግሮች የሚታዘዙ፣የስኳር ህመም መድሃኒቶች፣ የሰውነት የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል ስርዓት መዛባት/ ስህተት ችግር መድሃኒቶች-( autoimmune disease)፣የካንሰር መድሃኒቶች ተጠቅሰዋል።
👉ከነዚ…
👍2❤1
5 Oct 2022, 15:44 UTC≈2,620 views2 reactionsread 7 August 2026 #ጤናረቡዕ
ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ-4
☑️ እርግዝናና ስር የሰደዱ ህመሞች
🔘 በእርግዝና ወቅት ሰውነት በተፈጥሮ አዲስ ለተፀነሰው ፅንስ ልዩ ጥበቃ ያደርጋል፡፡ ስር በሰደዱ ህመሞች ውስጥ ለሚያልፉ እናቶች ደግሞ ጤናማ በሆነ የቅድመና ድህረ እንዲሁም የእርግዝና ወቅት ውስጥ ለማለፍ ሰውነታችን ልዩ ክብካቤና ድጋፍ ሊያስፈልገው ይችላል።
🔘 ስር የሰደዱ ህመሞች ባህሪ በእጅጉ የተለያየና ሰፊ ቢሆንም በአጠቃላይ ግን በተለይም በህመሞቹ ንቁ ደረጃ ላይ የሚፈጠር እርግዝና የሰውነት መቆጣትና የመደበኛ ሆርሞን መዛባት ችግሮችን በማባባስ የማህፀን የፅንስ መሸከም ሂደትን ሊያደናቅፈው ይችላል፡፡ ከዚያ በተጨማሪ እርግዝናው በራሱ ለሰውነት፣ በተለይም በመጀ…
👍2
28 Sept 2022, 15:45 UTC≈2,030 views4 reactionsread 7 August 2026 #ጤናረቡዕ
ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ-3
የወር አበባ ዑደት፣ ጤናማ የሆድ እቃና ስር የሰደዱ ህመሞች ግንኙነት
✔️ የስነ- ተዋልዶ ጤና፤ ከተዋልዶ ጤና ጋር ተያይዞ የተሟላ የአካል፣ የስሜት፣የአዕምሮ፣ እንዲሁም የማህበራዊ ጤንነት ማለት እንደመሆኑና ከዚህም በተጨማሪ የበሽታ አለመኖር ወይም የመራቢያ አካላት ተገቢውን የተግባር ሂደት መተግበር መቻልን ያካተተ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ደግሞ የተስተካከለና ጤናማ የወር አበባ ዑደት አንዱ ነው።
👉የወር አበባ ዑደት የአንዲት ሴት ሰውነት በየወሩ ሊከሰት ለሚችል እርግዝና በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት የተነሳ የሚፈጠሩ የተለያዩ ለውጦች ውጤት ነው፡፡
👉ይህ የወር አበባ ዑደት ከሆድ እቃ ጤና ጋር በእጅጉ ይቆረኛ…
❤3👍1
21 Sept 2022, 15:09 UTC≈1,610 viewsread 7 August 2026 Forwarded from @tikvahethmagazine
#ጤናረቡዕ
ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ - 2
👉የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖችና የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን
- የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖች፤ በወንዶችና በሴቶች አጠቃላይ የስነ-ተዋልዶ ጤና፣የጉርምስና የሰውነት ለውጦች ላይ እንዲሁም በሰውነት እድገት፣ ፆታዊ ጠባይና መገለጫዎች ላይ ትልቅ ሚና አላቸው፡፡
- የስነ- ተዋልዶ ሆርሞኖች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ ዋነኞቹ፤ ኤስትሮጅን/ፕሮጀስትሮን እና ቴስተስትሮን ናቸው፡፡
👉የስነ-ተዋልዶ ሆርሞኖችና የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን ግንኙነት
- የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን በአንጀትና በሆድ እቃ መዋቅር ላይ ጉልህ ሚና አላቸው፡፡ እነዚህ ተህዋሲያን የሆድ እቃን ጤናማነት ከመጠበቅ ባሻገር በርከት ባሉ…
14 Sept 2022, 15:33 UTC≈1,750 views4 reactionsread 7 August 2026 #ጤናረቡዕ
ውድ የጤና ረቡዕ ተከታታዮቻችን በዚህኛው የጤና ረቡዕ የዝግጅት ምዕራፍ "ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ ስነ-ተዋልዶ" በሚል ርዕስ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለተከታታይ ሳምንታት እናቀብላችኋለን፡፡
ከምንዳስሳቸው ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ
👉 የጤናማ ስነ-ተዋልዶ ምንነትና የጤናማ ስነ-ተዋልዶና የሆድ እቃ ጤና ግንኙነት፤የስነ- ተዋልዶ ሆርሞኖችና የሆድ እቃ ጠቃሚ ረቂቅ ተህዋሲያን፤ ስር የሰደዱ ህመሞችና የስነ-ተዋልዶ ጤና (በወንዶችና በሴቶች ላይ)፤ የጤናማ የሆድ እቃና የወር አበባ ዑደት፣እርግዝና፣የእርግዝና መከላከያዎች፣ ጡት ማጥባትና ስር የሰደዱ ህመሞች ግንኙነት ይገኙበታል።
በመጨረሻው ሳምንትም ባለሞያ ጋብዘን በዚሁ ርዕስ ዙሪያ ከእናንተ የሚመጡልንን ጥ…
👍4
11 Sept 2022, 10:19 UTC≈1,580 views13 reactionsread 7 August 2026 Photo
መልካም አዲስ አመት የክሮንስ እና የኮላይተስ ኢትዮጵያ ቤተሰብ!
ይህ ዓመት ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ የበለፀገ ዓመት ይሁንልዎ።
@ibdeth
❤13
10 Sept 2022, 09:46 UTC≈1,550 views4 reactionsread 7 August 2026 ውድ ቤተሰቦቻችን
በዚህ ሳምንት #ጤናረቡዕ ፕሮግራም ላይ ስለ የሆድ እቃ ጤናና የአእምሮ ጤና የስነ-ልቦና ባለሙያ ከሆነውን ናትናኤል ሰይፉ ጋር የቀጥታ ስርጭት ቆይታ ነበረን።
የድምጽ ቅጂውን በዩትዩብ ገጻችን የለቀቅን ሲሆን ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጫን መከታተል ይችላሉ።
https://youtu.be/z6OK9ZCerfY
እናመሰግናለን!
@ibdeth
🙏4
7 Sept 2022, 08:49 UTC≈1,170 views8 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @tikvahethmagazinePhoto
#ጤናረቡዕ
🟣ማስታወሻ
ዛሬ በጤና ረቡዕ የውይይት ገፃችን ላይ ስለ የሆድ እቃ ጤናና የአእምሮ ጤና እንድንወያይበት እንዲሁም ጥያቄዎቻችሁ በባለሙያ እንዲመለሱ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ይዘን መጥተናል።
ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ የስነ-ልቦና ባለሙያ የሆነውን ናትናኤል ሰይፉን ይዘን እንቀርባለን።
ይከታተሉን!
በቲክቫህ ማጋዚን ላይ ብቻ!
@tikvahethmagazine @ibdeth
👍8
4 Sept 2022, 17:07 UTC≈1,490 views4 reactionsread 7 August 2026 Photo
#ቃለመጠይቅ #ጤናረቡዕ
ከስነ-አዕምሮ ባለሙያ ጋር
በጤና ረቡዑ ‹‹ ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አእምሮ›› በሚል ርዕስ ላለፉት ሳምንታት መረጃን ስናቀብላቹ ነበር፡፡
በቀጣይ ሳምንት በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከስነ-አዕምሮ ባለሙያ ጋር በቀጥታ ስርጭት ውይይት እናደርጋለን።
ከምንዳስሳቸው ርዕሶች ውስጥ:-
✔️ስር የሰደደ ህመም ከአእምሮ ጤና ጋር ያለውን ግንኙነት እንቃኛለን።
✔️የአንጀት ቁስለት ህመም እና ተመሳሳይ ህመሞች ያለበት ሰው እንዴት የስነ ልቦና ጤናውን መጠበቅ እንደሚችል እንወያያለን።
✔️የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ ቀን በቀን መተግበር ያለብንን የተለያዩ ተግባሪያዊ የስነልቦና የጤና ስልቶች በዝርዝር እናያለን።
በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንዲብራራ…
🙏4
31 Aug 2022, 14:56 UTC≈1,120 views7 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @tikvahethmagazine
#ጤናረቡዕ
ጤናማ የሆድ እቃ፣ ጤናማ አዕምሮ
- ስር የሰደዱ ህመሞችና የአእምሮ ጤና
✔️ የተለያዩ ስር የሰደዱ ህመሞች ጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴን በመፍጠር በአንድ ሰው ህይወት ላይ እክልን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
✔️በሌላ በኩል ፣ የአእምሮ ጭንቀት ሁኔታ ሲከሰት የተለያዩ የስር የሰደዱ ህመሞች ምልክቶች እና የህመሞቹን መልሶ መቀስቀስ ሊያስከትል ይችላል፡፡
👉ከሁለቱ የቱም ይቅደም የቱ፣ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴ በቀጥታ ስር የሰደዱ ህመሞችን ላያስከትሉ ቢችሉም ቀድሞ ለተፈጠረው ህመም አፀፋዊ ምላሽ ናቸው፡፡
👉ከጭንቀት፣ ስጋት እና ድባቴ በተጨማሪ ስር የሰደዱ ህመሞች ያለባቸው ሰዎች ሌሎች ተጨማሪ የስሜት ለውጦችን ሊያስተናግዱ …
👍6❤1
Showing the 12 most recent of 18 posts we hold for @ibdeth. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.