7 Aug 2026, 06:45 UTC28 viewsread 7 August 2026 💚 የነቢዩ ﷺ ሰላዋት ሚሊዮን ዘመቻ 💚
✨ 6️⃣ ከዓለም ሁሉ በላይ ወደሆኑት በረከተኛ ቀናት 6 ቀን ብቻ ቀርቷል!
#እንኳን_ወደ_ብርሃኑ_ረቢዕ_በደህና_መጣችሁ
አላህ ሆይ! ምስጢሩን ከአንተ በስተቀር ማንም የማያውቀውን፣ ሙሉ መብቱንም ከአንተ በስተቀር ማንም ሊፈጽመው የማይችለውን ሰላትና ሰላም በሰይዳችን ሙሐመድ ﷺ ላይ፣ በቤተሰቦቻቸውና በሶሓቦቻቸው ላይ አውርድ።
ጌታዬ! ይህን ልመናዬን በፊትህ አቅርቤያለሁ፤ ውዱን ነቢይህን ﷺ ወሲላ አድርጌ ወደ አንተ መጥቻለሁ። በቸርነትህና በምሕረትህ ጥያቄዬን ተቀበል፣ ፍላጎቴንም አሳካልኝ።
ጌታዬ! ወደ አንተ ከመመለሳችን በፊት ከአንተ ጋር ያለውን ቅርበት ስጠን፤ ነፍሳችን በምትወጣበት ጊዜ ውዳችን ነቢይ ሙሐመድ ﷺ…
Signed متيم
7 Aug 2026, 04:49 UTC37 views4 reactionsread 7 August 2026 Photo
ጌታዬ! ይህች ዓለም በራሷ ነገር አስጠምዳኝ፤ ዚክርህንም አስረሳችኝ። ዚክርህን በረሳሁ ጊዜ ልቤ ጠበበ።
ልቤ በዚክርህ የሚረጋጋው ጌታዬ ዚክርህን ለግሰኝ፤ ምላሴንም በዚክርህና በነቢይህ ﷺ ላይ በሰለዋት ሁልጊዜ እርጥብ አድርግልኝ።
አላህ ሆይ! በርኅራኄ ልብ፣ በጥበብ አእምሮ፣ በታጋሽ ነፍስ አስውበን።
ጌታችን! ፈገግታችንን ልማድ፣ ንግግራችንን ዒባዳ፣ ሕይወታችንን ደስታ፣ መጨረሻችንንም በሸሂድነት ውብ አድርግልን።
አላህ ሆይ! በመልካም ሥነ-ምግባር ከፍ ከፍ አድርገን፤ በሰዎች ልብ በእኛ ላይ ጥላቻ አታድርግ፤ በልባችንም በማንም ላይ ክፉ ነገር አታድርግ። በሕይወታችንም ከሞታችንም በኋላ መልካም ስምና መልካም ታሪክ አድርግልን።
🌷 መልካም የጁምዓ ቀን! …
❤4
Signed متيم
6 Aug 2026, 17:30 UTC59 views5 reactionsread 7 August 2026 የነብያችን ውልደት በሌሎች የላቁ(የተከበሩ) ወራቶች መሆኑ ቀርቶ በረቢዕ ወር የመሆኑ ምክንያት ፦እርሳቸው በዘመን አይልቁም
ዘመን ነው በእርሳቸው የሚልቀው ለዚያ ነው ይላሉ።
ኢማም ኢብን ሐጀር 💚
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله عدد كمال الله وكما يليق بكماله 💚
❤5
Signed متيم
6 Aug 2026, 14:47 UTC123 views6 reactionsread 7 August 2026 💚 የ10 ሚሊየን ሰለዋት ዘመቻ 💚
🌷 በነቢዩ ﷺ ፍቅር የሚገኝ የመንፈስ ስካር 🌷
በእያንዳንዱ ጊዜ ነቢዩን ﷺ በልቤ ውስጥ ይበልጥ ታላቅ ስፍራ ሲይዙ፣ ፍቅራቸውም ይበልጥ ጽኑ ይሆናል። ሁልጊዜም የእርሳቸው ምስል በልቤ ውስጥ እያንሾካሾከ እንዲህ ይለኛል፦ “አትድከም! የሙሐመድ ﷺ ልብ አሳደገህ አይደል?” ፍቅራቸው በልቤ ውስጥ ሥር ሰዶ ከትንፋሼ ጋር ተዋህዶ ሕይወት ሆኖኛል።
እውነት ነው፤ በዓይኔ አላየሆትም። ከእርስዎ ጋር አልተጓዝኩም፤ በፍርሃት ጊዜ ከጀርባዎ አልተጠጋሁም፤ በፈጅር ሰላት ውስጥ ድምፅዎን አልሰማሁም፤ በበይዓ ጊዜ እጅዎን አልነካሁም፤ የፊትዎን ግርማና ውበት አላየሁም። ምነው በክብርዎ ጥላ ስር ብሸሸግ፣ ከድምፅዎ ግርማ ብፈራ፣ ከእግር አካሄ…
❤6
Signed متيم
6 Aug 2026, 14:46 UTC107 views1 reactionsread 7 August 2026 Photo
شمس الخميس إذا تغيب
فزد في الصلاة على الحبيب
"የሐሙስ ፀሐይ ስትጠልቅ ፤
በውዱ ነቢይ ﷺ ላይ ሶለዋትን አብዛ።
"
"أكثروا من الصلاة على النبي في هذه الليلة فإنها ليلة مباركة يا أحباب الله 💚"
"የአላህ ወዳጆች ሆይ! በዚህች የተባረከች ሌሊት በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ፤ እሷ በእርግጥም የተባረከች ሌሊት ናትና! 💚
"
በዚህ ውብ ሌሊት ያወረዱትን የሰለዋት ቁጥር በዚህ ይላኩልን
https://t.me/selualenebyi
❤1
Signed متيم
6 Aug 2026, 07:44 UTC39 views3 reactionsread 7 August 2026 Forwarded from @al_wird_al_mohammedi
✨ 📢 ታላቅ የላይቭ (LIVE) ፕሮግራም ጥሪ! 📢 ✨
🌹🌙 ለውድ የአል-ዊርድ አል-ሙሐመዲይ ቤተሰቦች በሙሉ 🌙🌹
🕊️ በአላህ ፈቃድ ዛሬ በጉጉት የሚጠበቅ እጅግ ልዩና መንፈስን የሚያድስ ታላቅ የደርስ ፕሮግራም ይዘንላችሁ ቀርበናል!
📚 የዛሬው የደርስ ርዕስ፦«ስለ አህሉ በይቲ ረሱሊላህ (የመልክተኛው ﷺ ቤተሰቦች)፦ ከነቢዩ ጋር ያላቸው ትስስር እና ከሰለዋት ጋር ስላላቸው ጥልቅ ግንኙነት» የምንመለከትበት እጅግ ውብ ማዕድ ይሆናል። 🌹📿━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
📌 የተሳትፎ ጥሪያችን፦
🫵 በመጀመሪያ ራሳችን በተሻለ ዝግጁነት በዚሁ ውድ ማዕድ ላይ ቀድመን በመገኘት በረከቱን እንሸምት!እንዲሁም...👨👩👧👦 በቅርባችን የምናውቃቸው የመልክተኛው ﷺ ዘ…
❤3
Signed متيم
5 Aug 2026, 12:16 UTC88 views12 reactionsread 7 August 2026 Photo
ልቤ የናፈቀውን ሰው ቢያገኝ ምኞቴ ነበር
❤🔥11❤1
Signed متيم
5 Aug 2026, 11:47 UTC88 views5 reactionsread 7 August 2026 ይህ ውዱ ነቢይ 💚
የተቀደሰው የነቢዩ ﷺ ታሪክ
"የአንብብ ምስጢር"
ጂብሪል (ዐለይሂስ ሰላም) በመጀመሪያ ጊዜ ከነቢዩ ﷺ ጋር ሲገናኙ፣
"አንብብ!" አሏቸው።
ነቢዩ ﷺ ግን ኡሚ (መማርና መጻፍ ያልተማሩ) ነበሩ።
በኖሩበት ማህበረሰብም ሰዎች በግጥምና በቃላት ብቃት የታወቁ ነበሩ፤ ነገር ግን ነቢዩ ﷺ በሕይወታቸው ሁሉ ግጥም አልተናገሩም።
አላህም እንዲህ ብሏል፦
"እኛ ግጥምን አላስተማርነውም፤ ለእርሱም አይገባውም።"
አላህ በወህይ አማካኝነት፦ "አንብብ!" ሲላቸው፣ ይህ ማለት እንደሚል ነው፦
"የእኔ ሙሐመድ ሆይ! አንተ ለዓለማት ሁሉ የተላክህ መልእክተኛ ነህ፤ ወደ አላህም የምትጠራ ሰው ነህ።
ወደ አላህ የሚጠራ ሰው በዕውቀትና በመረዳት መጥራት ይ…
❤5
Signed كريم kerim
5 Aug 2026, 11:46 UTC77 viewsread 7 August 2026 Photo
Photo, posted without a caption
Signed كريم kerim
4 Aug 2026, 14:54 UTC101 views7 reactionsread 7 August 2026 በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋትና ሰላም ማውረድ ታላቅ ኢባዳ ቢሆንም፣ በእውነት በእርሳቸው ﷺ ሰለዋት የሚያወርድ ሰው ሱናቸውን የሚከተልና ቢድዓን የሚርቅ ነው። እንዲህ ያለው ሰው ሰለዋቱን በምላሱ ባይጠራም በእውነት በእርሳቸው ﷺ ላይ ሰላት ያወርዳል።
ከቀጥተኛው መንገድ የሚወጣ ግን፣ ቀንና ሌሊት፣ በምቾትም ሆነ በችግር፣ በምላሱ ሰለዋትን ሳያቋርጥ ቢያወርድም፣ በሙሉ እውነታ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰላት ያወረደ ተብሎ አይቆጠርም።
ነገር ግን የዚህ ሰለዋት በረከት እንዲያገኝ ተስፋ ይደረጋል፤ ተውፊቅም ከአላህ ብቻ ነው።
(ከ«مطالع المسرات»)
እኔም እላለሁ፦ አንድ ሰው ጠዋትና ማታ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ ላይ ቢጸና፣ ምላሱም ከእርሱ ባይቆም፣ ከዚያም በት…
❤7
Signed متيم
4 Aug 2026, 11:30 UTC110 views3 reactionsread 7 August 2026 የነብያችን ሙሐመድ ﷺ ላይ ሰለዋትና ሰላም ማውረድ ምስጢሮች ከሚከተሉት መካከል ነው፦
ይህ አምልኮ ሪያዕ (ለሰው ማሳየት) የማይገባበት ብቸኛ አምልኮ ነው፤
ግብዝ (ሙናፊቅ) ወይም እድል የተነፈገ ሰውም በእርሱ ላይ አይጸናም።
ምክንያቱም የእውነተኛ ኢማን ፍጹምነት ማሳያ ረሱል ﷺ ከራስህ፣ ከቤተሰብህ እና ከሀብትህ በላይ እንድትወደው ነው።
የዚህ ፍቅር ምልክት ደግሞ ፍቅረኛው በተወዳጁ ውስጥ መጥፋት ነው፤ ሌላን ነገር ከእርሱ በላይ አያስታውስም።
ምክንያቱም ሰው የሚወደውን ነገር ብዙ ጊዜ ያስታውሳል።
አላህም ለዚህ አምልኮ ታላቅና ልዩ ምንዳ አዘጋጅቷል።
እርሱም፦ አላህ በረሱል ﷺ ላይ ሰለዋት ባወረደ ሰው ላይ ራሱ ሰለዋት ማውረዱ ነው።
ይህ ዋናው …
❤3
Signed كريم kerim
3 Aug 2026, 19:20 UTC117 views8 reactionsread 7 August 2026 1️⃣0️⃣ ቀን ቀረው 🌙✨
በአላህ ስም እጀምራለሁ።
የፈትህ በረከቶች ይመጣሉ፤ እርዳታም ይደርሳል፤ መልካም ነገር ይቀርባል፤ የተዘጉ ነገሮችም ይከፈታሉ።
ጨለማዎች ይከፈታሉ፤ ጨለማም ይጠፋል፤ መልካም ምልክቶች ይገለጣሉ፤ እውነተኛ ነገሮች ይገለጣሉ፤ ጭንቀት ይወገዳል፤ እፎይታም ይመጣል።
ይህ ሁሉ በተወዳጁ ታላቁ ሐቢብ፣ በነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ሐድራና በረከት ነው።
የረቢዑል አወል ወር መምጣት 10 ቀን ቀርቷል 🌿✨
የፍቅር ነፋሶች ይነፍሳሉ፤ የሙሐመዳዊ ብርሃን በልቦቻችን ይበራ።
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد ﷺ وعلى آله وصحبه وسلم. 💚
🥰5❤3
Signed متيم
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @hubuhabibillah. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.