8 Jun 2020, 21:18 UTC≈80,600 viewsread 29 September 2026 3. (Security) ጥበቃ
ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው፣ የወንድ ልጅ ከለላ እና መጋ መሆን፣ አሁንም ድረስ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያለው እውነታ ነው፡፡ በዚህ በሰለጠነው እና የሴቶች እኩልነት በተረጋገጠበት 21ኛው ክፍለ ዘመን እንኳን፣ ሴት ልጅ በግሏ ገቢ በማስገኘት ሀብት ማካበት ብትጀምርም፣ የወንድ ልጅ ግብአት አቅራቢ እና ጠባቂ መሆን የሴትን ልጅ ስሜት ለማረጋጋት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህም በዘለለ ወንድ ልጅ ለሴት ከተለያየ አደጋ ጠባቂ ሆኖ መገኘቱ፣ እምነቷን የበለጠ ስለሚያጠነክረው ፍቅሯ እየጎለበተ ይሄዳል፡፡
4. Blind Loyalty (ፍፁም የሆነ ተአማኒነት)
በአብዛኛው አንዲት ሴት የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ስትሆን ወይም በወ…
Signed Bini Jemo
6 Jun 2020, 15:36 UTC≈54,200 viewsread 29 September 2026 ሴቶች በፍቅር ውስጥ አጥብቀው የሚፈልጉት ነገርሮች(ለወንዶች ብቻ)
👍
በጥንዶች መካከል ለሚኖር የተሳካ የፍቅር ግንኙነት የፍላጎት መጣጣም እጅግ አስፈላጊ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ በዚህ ረገድ የሰው ልጆች በአጠቃላይ፣ ተመሳሳይ የሚመስል መሰረታዊ ፍላጎቶች ቢኖራቸውም ወንዶችና ሴቶች በየግል ከፍተኛ ቦታ የሚሰጧቸው የተለያዩ የስሜት ፍላጎቶች ይኖሯቸዋል፡፡

በግንኙነት መስክ ውስጥ ከምንጠቀምባቸው ክህሎቶች ሁሉ የመጀመሪያውና ጠቃሚ ነገር፣ የተጓዳኛችንን ጥልቅ ፍላጎት እና ተግባራት አስቀድሞ መረዳት ሲሆን፣ ይህ ማስተዋል አብሮን ያለውን ሰው ጠንቅቀን እንድንረዳ ስለሚያግዘን ችግሮች ከመሰከታቸው በፊት እንድንታደጋቸው ብሎም ከተፈጠሩ በኋላ በንቃት እና በጥበ…
Signed Bini Jemo
5 Jun 2020, 20:31 UTC≈42,400 viewsread 29 September 2026 ከትናት የቀጠለ
2. መራራውንም ጣፋጩንም ፅዋ በጥንድነት መጎንጨት
ጥንድነት በሁለትዮሽ የተገመደ የፍቅር አሀድ እንደመሆን አንድነቱ ጠቅልሎ የሚያስራቸውን ትሩፉቶች ብቻ ሳይሆን በአንድነቱ ተበትነው የሚፈቱ የእርካታ ችግሮችንም ማስተናገዱ አይቀሬ ነው፡፡ በተለይ ከዚህ የጥንድነት ጉዞ ጣልቃ የሚገቡና ፈታኝ መሰናክሎችን የሚጋርጡ ችግሮችን ጥንዶች ለየብቻቸው መጋፈጣቸው የአንድነቱ መፈተሻ ሆኖ በማገልገል ከአንደኛው ወገን የተለየ እክልን ይፈጥራሉ፡፡ እንግዲህ ይህን ጊዜ ነው የብዙ የስነ ልቦና ሐኪሞችን ቀልብ በገዛው የአብርሃም ማስሎ መርሆ የመመራትና አለመመራት ጉዳይ ትውስ የሚለን፡፡ የዚሁ እውቅ የስነ ልቦና ሐኪም መርህና አገላለፅ መሰረት በእንግሊዝኛው “Self…
Signed Bini Jemo
4 Jun 2020, 18:31 UTC≈36,800 viewsread 29 September 2026 እውነተኛን ፍቅርን የምያጠናክሩ 5 ጠቃሚ ምክሮች
❤️
ከመነሻው በጥንድ እጆች ተጠምዶ የተነሳ የጥንዶች ፅዋ በመደፍረሱ (ከማጥራት ይልቅ) የሚገፉት ወይም ከጉንጭ በመምረሩ (ለማጣፈጥ ከመጣር) የሚተፉት፤ ውሎ ሲያድር ጣዕሙን በመቀየሩ የሚደፉትና ቀን ሲገፋ አንገሽግሸዋቸው የሚተዉት እስከመሆን መድረሱ የብዙ ፍቅረኛሞችና ባለትዳሮች የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ስለዚህ ወረት የለሽና እውነተኛን ፍቅር በእጃችን ለማስገባትና የበኩልን ድርሻ ለመወጣት መነሳትና ቢያቅት እንኳ በጋራ ለመካፈል እጅን መዘርጋት ከጥንዶች ይጠበቃል፡፡ ይህን ለማድረግ ከመነሳት አስቀድሞ ግን ከዚህ የአዳምና የሄዋን ምኞት ከሆነው ወረት የለሽና እውነተኛ ፍቅር መደራረሻ መንገድን ማወቅ ይጠይቃል፡፡…
Signed Bini Jemo
4 Jun 2020, 18:13 UTC≈34,200 viewsread 29 September 2026 የእውነተኛ ፍቅር መገለጫዎች…
1. ጥልቅ ስሜት (passion)
ፍቅረኛዬን ሳያት/ሳስባት የምወድላት፣ የማደንቅላት እና የምደነግጥላት ነገር ሊኖር ይገባል፡፡ ያ ነገር ለኔ ልዩ ስሜት የሚሰጠኝ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ወይ ዞማ ፀጉሯን…ወይ ብርሃን ፈገግታዋን…ወይ የጠቆሩ ብሌኖቿን…ወይ ውብ ተክለሰውነቷን…ወይም ሌላ፡፡ ይህ ጥልቅ ስሜት ከባህሪ/ስብዕና ይልቅ ወደ አካላዊ ገፅታ የሚያደላ ይመስላል፡፡ ከታች ያሉት የመሀሙድ አህመድ የዘፈን ስንኞች ይህን ስሜት ጥሩ አድርገው ይገልፁታል…
ቁንጅና ምንድነው፣ ሰዎች ንገሩኝ
እኔ እሷን በማየት ተብረከረኩኝ፡፡
2. ቅርበት/ቁርኝት (intimacy)
ፍቅረኛዬ የቅርብ ጓደኛዬ…
Signed Bini Jemo
4 Jun 2020, 02:50 UTC≈32,200 viewsread 29 September 2026 Video
Video, posted without a caption
Signed Bini Jemo
21 May 2020, 21:21 UTC≈32,600 viewsread 29 September 2026 Video
Video, posted without a caption
Signed Bini Jemo
28 Feb 2020, 17:38 UTC≈29,700 viewsread 29 September 2026 Forwarded from @sychologisttotelagram
ራስን እንዴት መቀየር ይቻላል
ሕይወት በድንገተኛ አጋጣሚዎች ታጅባ መጓዟ የተፈጥሮ ግዴታ በመሆኑ በድንገት ሁሉም ነገር ቦታውን ሊለቅ ይችላል። በአጋጣሚዎች ሕይወት የመመሳቀሏን ያህል ቀን ጠብቆ ነገሮች የሚለወጡበት አጋጣሚ ይፈጠራል።
ዘመኑን ሙሉ የተረጋጋና ሰላም የሰፈነበት ኑሮ ሲመራ የነበረ ሰው ድንገት ሕይወቱ ተዘበራርቆ የማያውቀው ዓለም ውስጥ ሊገባ ይችላል። ታዲያ ከገባበት የችግር አዘቅት ለመውጣት የሚፈልግ ሰው ችግሩ በተከሰተባ ቸው ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ ማሰብና መፍትሔ ማፈላለግ ሰላማዊው ኑሮውን ለመመለስ ይጣጣራል። ከገባበት ችግር ለመውጣት ቀዳዳውን ማግኘት የተሳነው ሰው ደግሞ በሚወስዳቸው የተሳሳቱ እርምጃዎች ከዕለት ዕለት ችግሩን እያወሳሰበው …
Signed የንስር አይን
25 Jan 2020, 20:41 UTC≈32,900 viewsread 29 September 2026 ፍቅር ለጠፋበት ትዳር ምክንያት የሚሆኑ ነገሮች
ጀማል አህመድ
• ገንዘብ:- “አንድ ሰው፣ ባልና ሚስት አብረው የጋራ ባጀት ማውጣታቸው ተባብረው እንዲሠሩ፣ ለኑሮ የሚያስፈልጉትን መሠረታዊ ነገሮች ለማግኘት ገቢያቸውን እንዲያብቃቁና በድካማቸው ፍሬ እንዲደሰቱ በማድረግ አንድ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ ይረዳቸዋል ብሎ ሊያስብ ይችላል። ይሁን እንጂ እዚህም ላይ ባልና ሚስቱን ለጋራ ዓላማ ሊያስተሳስራቸው ይገባ የነበረው ነገር አብዛኛውን ጊዜ ሲያለያያቸው ይታያል።”—ዶክተር አሮን ቲ ቤክ
• ወላጅነት:- “67 በመቶ የሚሆኑ ባልና ሚስቶች የመጀመሪያ ልጃቸው ከተወለደ በኋላ ከትዳራቸው ያገኙ የነበረው እርካታ በከፍተኛ ደረጃ እንደቀነሰ አስተውለናል። በመካከላቸው የሚነሳው…
Signed የንስር አይን
25 Jan 2020, 13:25 UTC≈30,800 viewsread 29 September 2026 ቅር መፋረስ 100 በሚሆኑ የተለያዩ ህብረተሰቦች ላይ በተደረገው ጥናት ለትዳር መሰናክልና ለፍቅረኛሞች መለያየት ዋነኛ ምክንያት አንዳቸው ለሌላቸው ታማኝ አለመሆናቸው እንደሆነ ታውቋል፡፡ ተያይዞ በተደረገው ጥናት ሚስት ከባሏ በላይ የገቢ ምንጭ በምታገኝበት ትዳር ውስጥ ጥንዶቹ የመለያየት እድላቸው ከሌሎቹ ባለ ትዳሮች ጋር ሲነፃፀር 50 በመቶ ይጨምራል፡፡
በሰሜን አሜሪካና በሌሎቹ ሀገሮች በሚገኙ ባለትዳሮች ላይ በተደረገው ጥናት ብዙ ባለ ትዳሮች ፍቺን ቢፈልጉም ባላቸው ላይ ባላቸው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥገኝነት ምክንያት ፍቺን ለማከናወን የሚደፍሩት ጥቂቶች ናቸው፡፡ የሚደፍሩትም በራሳቸው መቆም የሚችሉና የኢኮኖሚ ጥገኝነት የሌለባቸው ሴቶች ናቸው፡፡ ሴቶችም ለፍቅረ…
Signed ዝምታም ያዎራል
25 Jan 2020, 13:25 UTC≈29,000 viewsread 29 September 2026 ትዳር የሚመሰርቱት ምን አይነት ፍቅረኞች ናቸው?
ጥንዶች በሶስት የተለያዩ መንገዶች ጥምረት በመፍጠር ወደ ትዳር እንደሚያመሩ ይታመናል፡፡ መጀመሪያው ጥንዶችን የሚያጣምራቸው በመሀላቸው የሚፈጠር ቅፅበታዊ ፍቅር ነው፡፡ በቅፅበታዊ ፍቅር የተለከፉ ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ማንነታቸውን ዘንግተው በአዕምሯቸው ሳሆን በስሜታቸው መንቀሳቀስ ይጀምራሉ፡፡ ማመዛዘን የሚባለው ነገር ጨርሶ ይጠፋባቸዋል፡፡ በእንዲህ አይነቱ ጊዜዊ ስሜት ውስጥ እያሉ የተጋቡ ጥንዶች ብዙ ጊዜ ትዳራቸው የሚቆየው ቅፅበታዊው ስሜታቸው አብሯቸው እስከሚቆይ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ጥንዶቹ በመጀመሪያ ወደ ትዳር ሲያመሩ ወደፊት ስለሚገጥማቸው ችግርም ሆነ ስለኑሯቸው ምንም አይነት ቅድመ ዝግጅት አያደርጉም፡፡ ትዳ…
Signed ዝምታም ያዎራል
20 Jan 2020, 15:21 UTC≈26,000 viewsread 29 September 2026 Love and loves relashinshep sayico
ጀማል አህመድ
ሁሉም ሰው የጋራ ፍቅር እና ደስተኛ ቤተሰብ እንዲኖረኝ ይፈልጋል. ነገር ግን በተግባር ግን አንዳንድ ሰዎች ይህንን ተገንዝበዋል. እውነተኛ እና የታመነ ግንኙነት እንዲኖርዎት, ከፍቅር ፍቅር ስሜታዊነት, ከጓደኝነት ስሜታዊነት እና ከጾታ ስሜታዊነት መካከል ያለውን ልዩነት ማየት አለብዎት, እንዲሁም በግንኙነትዎ ውስጥ ያሉትን ሶስቱን አካሎች በዘዴ ማመቻቸት ይችላሉ.
ከሳይኮሎጂ አንጻር, ፍቅር በጋራ የመተማመን እና የመደሰት ደስታ ላይ የተመሠረተ ክፍት ግንኙነትን ያመለክታል. በሳይኮሎጂ, የፍቅር ጽንሰ-ሀሳብ ሦስት ገጽታዎችን ይዟል-
ቃል ኪዳን. የፍቅር የሞራል ገጽታ. ችግሩን በጋራ ለመፍታ…
Signed Im Happey
Showing the 12 most recent of 20 posts we hold for @httptelegramme81biniyamin. View and reaction counts are the latest single reading for each post, not a live figure, and a recent post is still accumulating both. A view count marked ≈ was rounded by Telegram before we ever saw it — t.me prints views in full below 1,000 and to three significant figures above, so ≈1,200,000 means somewhere between 1,150,000 and 1,249,999. Unmarked counts are exact. Text is reproduced from the public post preview and truncated for length.